TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
205 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#update ኢንጂነር ስመኘው⬇️

ኢንጅነር ስመኘው በቀለ ሐምሌ 19፣2010 መስቀል አደባይ ላይ በጥይት ተመተው መገኘታቸው ይታወቃል፡፡
ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ እና ፈደራል ፖሊስ ኮሚሽን የምርመራ ቡድኑን ውጤት ተመርኩዞ በሰጠው መግለጫ የተነሱ ነጥቦች፡
• ኢንጅነር ስመኘው በቀለ ሐምሌ19 ጠዋት 12 ፡45 ከቤታቸው ወጥተዋል
• 1 ሰዓት ላይ መስቀል አደባባይላይ መታያታቸውን
• 1፡05 -45 ቢሯቸው ድረስ ቆይተዋል፡፡
• በቆይታቸው ወደ መፀዳጃ ቤት ይመላለሱ ነበር
• ከሁለቱ ሹፌራቸው አንዱን የታሸገ ፖስታ ሰጥተውታል
• ሌላ የቢሯቸው አትክልተኛ ወደ መንግስት ኮሙኒኬሽን የታሻገ ፖስታ 2፡20 ላይ አሲዘው ልከውታል
• 2፡21 ላይ ወደ መኪናቸው ተመልስው መግባታቸውን የአይን እማኝ ገልጿል፡፡
• ፖሊስ 2፡30 ላይ አደጋው በደረሰበት ቦታ ደርሷል፡፡
• መኪናቸው አካባቢ ወድቀው የተገኙ ሶፍትና ጓንት እሳቸውን በህይወት መኖር አለመኖራቸውን ለማወቅ የተጠቀመባቸው ናቸው፡፡
• መኪና ውስጥ ሁለት ፖስታዎችና የራሳቸው ሽጉጥ መገኘቱ ተረጋግጧል፡፡
• የሞቱበት የሽጉጥ ጥይት እርሳስና ቀለሃ ተገኝቷል፡፡ ለማረጋገጥ በተደረገው ጥረት ከሽጉጣቸው የተተኮሰ መሆኑ ተረጋግጧል፡፡
• ስልካቸውም የምርመራው አካል ተደርጓል፡፡

©etv
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ኢንጂነር ስመኘው በቀለ⬇️

ኢንጅነር #ስመኘው_በቀለ ራሳቸውን ማጥፋታቸውን የፖሊስ የምርመራ ውጤት እንደሚያሳይ የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን አስታውቋል። ኢንጅነር ስመኘው ራሱን ካጠፋ በኃላ በወቅቱ ህይወቱ ሳትወጣ እያጣጣረ ፖሊሶች በቦታው መድረሳቸውንም ገልጸዋል፡፡

በፖስታው ውስጥ የተገኘው መልዕክት ስለ ቤተሰባቸው #አደራና ያለባቸውን #ጫና የሚገልፅ ፣ እንዲሁም ወደ ውጭ ለመውጣት ፍላጎት እንደነበራቸው ቢወጡም ለህዝቡ የሚሰጡት ምላሽ እንዳሳሰባቸው የሚገልጽ እንደነበረም ተናግረዋል፡፡

የሚሞቱበትን #ምክንያት ግን በፖስታው መልዕክት አሳማኝ ሆኖ #አለመጠቀሱን ፖሊስ ገልጿል፡፡

©etv
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ኢንጂነር ስመኘው⬇️

ኢንጂነር ስመኘው በቀለ በሰው በደረሰባቸው ጉዳት ህይወታቸው እንዳላለፈና ራሳቸውን እንዳጠፉ የምርመራ ውጤቱ እንደሚያመላክት ፖሊስ ገለፀ።

ፖሊስ የኢንጂነር ስመኘውን አሟሟት በተመለከተ በሰጠው መግለጫ፥ ኢንጅነር ስመኘው ራሳቸውን ማጥፋታቸውን የተደረገው የምርመራ ውጤት ያመላክታል ብሏል።

ፖሊስ በመግለጫው ሞተው የተገኙበት መኪና ውስጥ የተገኘው ሽጉጥም በእርሳቸው ስም ተመዝግቦ የሚገኝ መሆኑን ገልጿል።

በፎረንሲክ ምርመራ በተገኘው ውጤት መሰረትም የሽጉጡ ቀልሃና የተገኘው እርሳስም የዚሁ ሽጉጥ መሆኑን ፖሊስ እንዳረጋገጠ አስታውቋል።

ኢንጅነር ስመኘው ከመሞታቸው ቀደም ብሎ ባለው ቀን ከትልቁ ልጃቸው ጋር የስንብት የሚመስል መልዕክት መለዋወጣቸውንም ነው ፖሊስ በመግለጫው ያነሳው።

ኢንጅነሩ ባደረጉት የስልክ ልውውጥም በአብዛኛው የስንብት ይዘት ያለው መልዕክትን ከልጃቸውና ፀሃፊያቸው ጋር ተለዋውጠዋልም ነው ፖሊስ።

ከዚህ ጋር ተያይዞም ለፀሃፊያቸው ልጀን አደራ የሚል መልክዕክት ማስተላለፋቸውን የፌደራል ፖሊስ ጀኔራል ኮሚሽነር #ዘይኑ_ጀማል ተናግረዋል።

በሞቱበት ዕለት ማለዳ ላይም ለአንደኛው ሾፌራቸው ፖስታ በመስጠት ለማን እንደሚያደርስላቸው እነግርሃለው ማለታቸውን እና ለሌላኛው ሾፌር ደግሞ ፖስታ መንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት እንዲያደርስላቸው መስጠታቸውም በመግለጫው ተነስቷል።

©fbc
@tsegabwolde @tikvahethiopia
AUGUST 30⬆️

ከኢንጂነር #ስመኘው ሞት ጋር በተያያዘ ከሳምንት በፊት ስሙን በማልጠቅሰው የቻናላች ቤተሰብ አባል የተላከልኝ መልዕክት ኢንጂነሩ #እራሳቸውን ማጥፋታቸውን የሚያረጋግጥ ነው።

📌በወቅቱ ይህን መረጃ ይፋ ማድረግ ተገቢ መስሎ ስላልታየኝ ነው።
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update 10ኛ እና 12ኛ ክፍልን በተመለከተ ከኤጀንሲው ሰዎች ጋር #በስልክ ለመገናኘት ጥረት እይደረኩ ነው የደረስኩበትን አሳውቃችኋለሁ።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የ10ኛ ክፍል ውጤት #ዛሬ ይፋ ይደረጋል። የሀገር አቀፍ ትምህርት ምዘናና ፈተናዎች ኤጀንሲ ዛሬ 10 ሰዓት ውጤቱን በተመለከተ መግለጫ ይሰጣል።

©etv
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ከግንቦት 22-24/2010 ዓ.ም ለ1,200,676 ተማሪዎች የተሰጠው የኢትዮጵያ አጠቃላይ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ማጠናቀቂያ ሰርተፍኬት /የ10ኛ ክፍል ፈተና/ ክፍል ውጤት ይፋ መሆንን አስመልክቶ ዛሬ 2/13/2010 ዓ.ም ከቀኑ 10 ሰዓት ላይ ለተለያዩ ሚዲያዎች መግለጫ የምንሰጥ መሆኑን እየገለጽን ተማሪዎች ውጤታችሁን ከተጠቀሰው ሰዓት ጀምሮ በኤጀንሲው ድረ-ገጽ app.neaea.gov.et በመግባት ማየት የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን፡፡

የሀገር አቀፍ ትምህርት ምዘናና ፈተናዎች ኤጀንሲ!
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ከቂርቆስ ክፍለ ከተማ⬆️

"ፀግሽ በዶ/ር አበይ መሪነት የተጀመረውን የደካሞችን ቤት ማደስ #ከፓሊስ አባላት በመሆን ማደስ በወረዳ 4 የወ/ሮ ቡዝነሽን ቤ/ት በእድሳት ላይ ነን! እሸቱ ከቂርቆስ"

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ቸር ወሬ ከኢንጅነር ታከለ ኡማ⬆️

በቂርቆስ ክፍለ ከተማ በህገ ወጥ መንገድ ተይዘው የነበሩ የቀበሌ ቤቶች 50 ለሚሆኑ ለተቸገሩ ዜጎች ተሰጡ ምክትል ከንቲባ #ታከለ_ኡማ በህገ ወጥ መንገድ ተይዘው የነበሩ የቀበሌ ቤቶቸን #ለተቸገሩ የማስተላለፉ ተግባር በሁሉም ክፍለ ከተሞች #ይቀጥላል ብለዋል᎓᎓

የከተማው አስተዳደር የሰጠው ቤትና እያከናወነ ያለው ድሆችን የመርዳት ተግባር ለመደገፍ በላሀብቱ አቶ በላይነህ ክንዴ 500 ሺህ ብር እንዲሁም አትሌት ደራርቱ ቱሉ፣ ጌጤ ዋሚና ሌሎችም አስፈላጊውን ድጋፍ ለማድረግ ቃል ገብተዋል᎓᎓

©etv
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ትንሽ ታገሱ! ያለውን ነገር ለማጣራት እየሞከርኩ አሁን ባለኝ መረጃ ወጤት ይፋ አልተደረገም።

@tsegabwolde
ከ12 ሰዓት ጀምሮ ማየት ይቻላል!
የ10ኛ ክፍል ውጤት ይፋ ሆኗል⬇️

የሀገር አቅፍ ትምህርት ምዘናና ፈተናዎች ኤጀንሲ እንዳስታወቀው የ2010 የ10ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና ውጤት #ይፋ ሆኗል። በዘንድሮው የአስረኛ ክፍል ፈተና ከሰባት ሽ በላይ ተማሪዎች አራት ነጥብ አምጥተዋል። ከነዚህ ውስጥ 2375ቶቹ ሴቶች ናቸው።

📌ተማሪዎች ዛሬ ከ12:00 ሰዓት ጀምረው ውጤታቸውን ማየት እንደሚችሉ ተገልጿል፡፡

©ebc
@tsegabwolde @tikvahethiopia
12 ሰዓት ጀምሮ📌የ10ኛ ክፍል ተማሪዎች ውጤታችሁን ከተጠቀሰው ሰዓት ጀምሮ በኤጀንሲው ድረ-ገጽ app.neaea.gov.et በመግባት ማየት ትችላላችሁ፡፡

የሀገር አቀፍ ትምህርት ምዘናና ፈተናዎች ኤጀንሲ!
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የ2010 ዓ.ም የ10ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና ይፋ ሆኗል። የሀገር አቅፍ ትምህርት ምዘናና ፈተናዎች ኤጀንሲ እንደገለጸው በዘንድሮው የአስረኛ ክፍል ፈተና ከ7 ሺ በላይ ተማሪዎች አራት ነጥብ አምጥተዋል። ከነዚህ ውስጥ 2 ሺ 375ቶቹ ሴቶች ናቸው።

በዘንድሮው ሀገር አቀፍ የአስረኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና ከ1 ነጥብ 2 ሚሊየን በላይ ተማሪዎች ፈተናውን ወስደዋል፡፡

ከተፈታኞቹ 71.48 ከመቶ የሚሆኑት ማለፊያ ነጥቡን አሟልተው አልፈዋል። የማለፊያው ነጥብም ለወንዶች 2.71 ሲሆን ለሴቶች 2.57 ሆኗል።

ለታዳጊ ክልሎች ለወንድ 2.43፣ ለሴቶች 2.29 እንዲሁም ለአካል ጉዳተኞች ለወንድ 2.14 ለሴት ደግሞ 2.00 መሆኑ ተገልጿል።

ተፈታኖች ዛሬ ከ12 ሰአት በሃላ በ rtn 8181 እና በፈተናዎች ኤጄንሲ ድረገጽ https://app.neaea.gov.et/Home/Student ላይ ኮዳቸውን በማስገባት ውጤታቸውን ማየት እንደሚችሉም ሀገር አቀፉ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች ኤጄንሲ ገልጿል።

©ebc
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ውድ ተማሪዎች ተባበሩኝ📌ይህ ቻናል ስራው እውነተኛ መረጃ ማቅረብ ነው ብዙ ጉዳዮች የሚዳሰስበት በመሆኑ ከ10ኛ እና 12ኛ ክፍል ጋር የተያያዙ መረጃዎችን ሳገኝ አቀርባለሁ። በብዙ ሺ የሚቆጠሩ መልዕክቶችን ብቻዬን ለማስተናገድ አልችልም። በመሆኑም መልዕክቶችን እና ጥያቄዎችን ለጊዜው አቆዩልኝ።

📌የ10ኛ ክፍል ተማሪዎች ከ12 ሰዓት ጀምራችሁ ውጤታችሁን እዩ!
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የማለፊያ ነጥብ⬇️

📌የማለፊያ ነጥብ ለወንዶች 2.71 ሲሆን ለሴቶች 2.57 ሆኗል።

📌ለታዳጊ ክልሎች ለወንድ 2.43፣ ለሴቶች 2.29 እንዲሁም ለአካል ጉዳተኞች ለወንድ 2.14 ለሴት ደግሞ 2.00 መሆኑ ተገልጿል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ከቀናት በፊት ከኢንጅነር ስመኘው ልጅ #በእምነት_ስመኘው ጋር #የስልክ ቆይታ ነበረኝ በዚህም ስለ እናታቸው ሁኔታ ጠይቄው ነበር እናታቸው #ሰላም መሆኗን፤ እንደምትደውልላቸው እና በቀብር ስነስርዓቱ ላይ ለመገኘት ከፍተኛ ጥረት ብታደርግም ሊሳካላት እንዳልቻለ አጫውቶኛል።

@tsegabwolde
በሀላፊነት ይህን ድምፅ ስጡልኝ። ለቀጣይ ሀገራዊ መልካም ስራዎች ለመስራት በቻናላችን ቤተሰብ ውስጥ ምን ያህል #ሴቶች እንዳሉ ለማወቅ በማስፈለጉ በኃላፊነ ይህንምልክት በመጫን አብሮነታችሁን ግለፁ።

ሴቶች ብቻ በኃላፊነት ድምፅ ስጡ። በአዲሱ አመት ከሴቶች መብት ጋር በተያያዙ ጉዳዮች ላይ የሚሰሩ ስራዎች ስላሉ ቁጥሩን ማወቅ ማስፈለጉ ነው።

አመሰግናለሁ!
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ጥቆማ📌የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች ኤጀንሲ የ10ኛ ክፍል ውጤት ይፋ ተደጓል 12 ሰዓት ጀምሮ ተማሪዎች ማየት ይችላሉ ብሎ ቢያሳውቅም አሁንም ምንም አይነት ውጤት ማየት እንዳልተቻለ ለመጠቆም እንወዳለን።
@tsegabwolde @tikvahethiopia