TIKVAH-ETHIOPIA
ሻዕቢያ ? ➡️ " በፕሪቶሪያ ስምምነት አኩርፎ ከኢትዮጵያ መንግሥት ጋር የተጣላ ኃይል ጋር ተሰልፈህ የኢትዮጵያን መንግሥት ማስወገድ የሚቻልበት እድል ካለ ብለህ መንቀዥቀዥ በጣም አደገኛ ነው !! " - አቶ ጌታቸው ረዳ የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዝዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ ፦ " ትግራይ ውስጥ በሚፈጠር ትርምስ እናተርፋለን የሚሉ ብዙ ወገኖች አሉ። የኤርትራ መንግሥት አንዱ እንደሆነ አውቃለሁ። …
#Tigray
🔴 " ከኤርትራ መንግስት ግንኙት አላችሁ የሚል ወሬ በሬ ወለደ ውሸት ነው " - ጉባኤ ያካሄደው ህወሓት
➡ " የኤርትራ መንግስት የያዘው ትግራይ መሬት የለም " - የኤርትራ ከፍተኛ ባለስልጣን
ጉባኤ ያካሄደ ህወሓት ምክትል ሊቀ-መንበር ኣማኒኤል ኣሰፋ " ' በትግራይ መፈንቅለ መንግስት ተካሂደዋል ' የሚባለው ፍፁም ውሸት ነው ፤ ህወሓት በጊዚያዊ አስተዳደሩ ያለውን የስልጣን ድርሻ ከማስተካከል የዘለለ አንዳች የወሰደው እርምጃ የለም " አሉ።
" ህዝቡን በተዘባ ወሬ ወደ አላስፈላጊ ውዥንብር በማስገባት መሬት ላይ በሌለ ግጭት ውጥረት ውስጥ ማስገባት ሃላፊነት ከሚሰማው ፓለቲከኛ የሚጠበቅ አይደለም " ሲሉም ተናግረዋል።
" ህዝቡ የሚያሰጋ ነገር በሌለበት ሁኔታ ገንዘብ ከባንክ ለማወጣትና አስቤዛ ለመገዛት መሯሯጥ አይገባውም " ሲሉ ገልጸዋል።
በትግራይ ክልል ባለው ሁኔታ ነዋሪዎች ጦርነት ይቀሰቀሳል በሚል በስፋት ከባንክ ገንዘብ እያወጡ አስቤዛም በስፋት እየገዙ ይገኛሉ።
አቶ አማኒኤል ፤ " ህወሓት በፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነት መሰረት ለፌደራሉ መንግስት የሰጠው እውቅናን በማጠናከር በመመካከር መስራቱን ይቀጥላል " ያሉ ሲሆን " ፓርቲው ባነሳቸው የጊዚያዊ አስተዳደር ፕሬዜዳንት ምትክ ከፌደራል መንግስት በመተማመን አዲስ ፕሬዜዳንት ይመርጣል " ሲሉ ተናግረዋል።
" ህወሓት የትግራይ ሰራዊት በማያሳምን መንገድ ለመበታተን የሚደረግ ሴራ እንጂ DDR መተገበርን አይቃወምም " ያሉት ምክትል ሊቀ-መንበሩ ፤ " ፕሬዜዳንት ነበር " ሲሉ የጠሩዋቸው አቶ ጌታቸው ረዳ በከፍተኛ የሰራዊት አመራሮች የወሰዱት እርምጃ " በሌለ ስልጣን የተደረገና ተቀባይነት የሌለው " ሲሉ አጣጥለውታል።
አቶ አማኒኤል የተወሰኑ የህወሓት አንጃዎች ከሻዕቢያ ጋር ግንኙነት አላቸው በሚባለው ጉዳይ " ከኤርትራ መንግስት ጋር ግንኙት አላችሁ የሚል ወሬ በሬ ወለደ ውሸት ነው " ሲሉ መልሰዋል።
" ከኤርትራ መንግስት ከኢትዮጵያ መንግስት እውቅና ውጪ የሚካሄድ ግንኙነት የለም " ሲሉም አክለዋል።
በኤርትራ ወታደሮች ቁጥጥር ስር ስለሚገኙ የኢትዮጵያ የትግራይ ክልል ቦታዎች ምንም ያሉት ነገር የለም።
በተያያዘ " የኤርትራ መንግስት የያዘው የትግራይ መሬት የለም " ሲሉ አንድ የኤርትራ ከፍተኛ ባለስልጣን ፅፈዋል።
ባለስልጠኑ የማነ ገ/መስቀል " ይድረስ ለግጭት ጠማቂዎች " በሚል በX ገፃቸው ባሰፈሩት ፅሁፍ " የፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነት መተግበርና አለመተግበር የኢትዮጵያ የውስጥ ጉዳይ እንጂ ኤርትራ አይመለከትም " ብለዋል።
" የህወሓት መከፋፈል ኤርትራን አይመለከትም " ያሉት ባለስልጣኑ " የትግራይ ህዝብ የውስጥ ሰላም እንዲበጠበጥ ኤርትራ ምንም ዓይነት ፍላጎት የላትም " ብለዋል።
" የተለያየ የፓለቲካ እሳቤ ያላቸው የኢትዮጵያ ፓለቲከኞች የቀይ ባሀርን አጀንዳ እንደ አዲስ በማቀጣጠል የአፍሪካ ቀንድን ለሌላ ተጨማሪ ውጥረት ከማስገባት እንዲቆጠቡ " በማለትም ባለስልጣኑ በX ገፃቸው ባሰፈሩት ፅሁፍ አሳስበዋል።
ባለስልጣኑ ይህን ይበሉ እንጂ የኤርትራ ሰራዊት በኢትዮጵያ የትግራይ የደንበር አከባቢ በርካታ ቦታዎች ይዞ ይገኛል።
በርካታ በትግራይ ምስራቃዊ ፣ ማእከላዊ ሰሜን ምዕራብ ዞን የሚገኙ ቀበሌ ገበሬ ማህበራት በኤርትራ ወታደሮች ቁጥጥር ስር እንደሚገኙ ደጋግሞ የዘገበው ቲክቫህ ኢትዮጵያ የመቐለ ቤተሰብ አሁንም በመሬት ላይ የተለወጠ አዲስ ነገር እንደሌለ የአከባቢው ነዋሪዎች በመጠየቅ አረጋግጧል።
#TikvahEthiopiaFamilyMekelle
@tikvahethiopia

ዛሬ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በትግራይ ክልል ወቅታዊ ሁኔታ ዙሪያ በኢትዮጵያ ከሚገኙ የዲፕሎማቲክ ማህበረሰብ አባላት ጋር ውይይት አካሂዷል።
በመድረኩ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ጌዲዮን ጢሞቲዎስ እንዲሁም የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዜዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ ተገኝተው ነበር።
ለዲፕሎማቲክ ማህበረሰቡ በትግራይ ክልል ወቅታዊ ሁኔታ ዙሪያ ሰፋ ያለ ማብራሪያን መስጠታቸው ታውቋል።
ምን ተባለ?
የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዮን ጢሞቲዎስ (ዶ/ር) ፦
" ራሱን ነጥሎ የወጣው የህወሓት አንጃ የፕሪቶሪያው ስምምነት ሙሉ ለሙሉ እንዳይተገበር እንቅፋት ሆኗል።
በተጨማሪም ምርጫ ቦርድ ጠቅላላ ጉባኤ እንዲያካሄድ የሰጠውን መመሪያ አልተቀበለም።
የፌደራል መንግስት የፕሪቶሪያው ስምምነት ሙሉ ለሙሉ እንዲተገበር እየሰራ ሲሆን መንግስት የክልሉን ወቅታዊ ሁኔታ በጥሞና እየተከታተለ ነው።
ዓለም አቀፉ ማህበረሰብም በክልሉ የተፈጠረውን ችግር ለመፍታት አስፈላጊውን እገዛ ሊያደርግ ይገባል " ብለዋል።
የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዜዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ ፦
" ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ራሱን ነጥሎ የወጣው የህወሓት አንጃ የጊዜያዊ አስተዳደሩ የዕለት ተለት ተግባራት ላይ እክል እየፈጠረ መጥቷል።
ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ እና የፌደራል መንግሥት በክልሉ ዘላቂ ሰላም ግንባታ ያላቸውን ሚና አጠናክረው ሊቀጥሉ ይገባል " ብለዋል። #ኤፍኤምሲ

በትግራይ ያለው ሁኔታ ምን ይመስላል ? (ከቲክቫህ የመቐለ ቤተሰብ አባል) የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዜዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ በሦስት ከፍተኛ የሰራዊት አመራሮችና በክልሉ የሰላምና የፀጥታ ቢሮ ሃላፊ ላይ ያሳለፉትን ጊዚያዊና ዘላቂ እግድ ተከትሎ በትግራይ ብዙ ልክ ያልሆኑ ነገሮች በመታየት ላይ ይገኛሉ። የቲክቫህ አባል ከመጋቢት 1/2017 ዓ/ም በኃላ በትግራይ ያለውን ፓለቲካዊ ትኩሳትና…
" እስካሁን ማህተሙ በእጄ ነው ፤ የጊዜያዊ አስተዳደሩ ፕሬዚዳንት እኔው ነኝ " - አቶ ጌታቸው ረዳ
የትግራይ ጊዜያዊ አስታዳደር ፕሬዝዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ እስካሁን ድረስ በጊዜያዊ አስተዳደሩ ፕሬዝዳንት ላይ የተደረገ ለውጥ እንደሌለ ገለጹ።
ይህን የገለጹት ከአዲስ አበባ ሆነው ' ርዕዮት ' ከተሰኘ የማህበራዊ ሚዲያ ፕሮግራም ጋር ባደረጉት ቃለምልልስ ነው።
" ማህተምም አላስረከብኩም " ያሉት አቶ ጌታቸው " ምናልባት የሚደረግ ለውጥ ወይም የሚደረግ ሽግግር ካለ በይፋ እስካውቀው ድረስ የጊዜያዊ አስተዳደሩ ፕሬዝዳንት እንደሆንኩ ነው የማውቀው " ብለዋል።
" ጉዳዩ ይሄን ያህል ሊያጨቃጭቅ የሚገባው አልነበረም ፤ ግን እስካሁን ማህተሙ በእጄ ላይ ነው ያለው " ሲሉ ተናግረዋል።
ከሰሞኑን በማህበራዊ ሚዲያ ላይ " የፌዴራል መንግሥት አቶ ጌታቸው ረዳን አንስቶ ሌ/ጄነራል ታደሰ ወረደ ፕሬዝዳንት ለማድረግ ስምምነት ላይ ደርሷል " የሚል መረጃ ሲሰራጭ ነበር።
በዚህ ጉዳይ ላይ ቃላቸውን የሰጡት አቶ ጌታቸው " እኔ የማውቀው ምንም የተደረሰበት ስምምነት የለም " ብለዋል።
" ጊዜያዊ አስተዳደሩ 2 ዓመት ሞልቶታል ፤ እንዳለመታደል ሆኖ የተቋቋመበትን አላማ ፈጽሞ በምርጫ ለሚመረጥ መንግሥት የሚያስረክብበት ጊዜ ነበር " ያሉቱ ፕሬዝዳንቱ " በተቋቋመበት ደንብ መሰረት ሌላ ተጨማሪ 6 ወር በፌዴራል መንግሥት ካቢኔ መራዘም ይኖርበታል " ብለል።
ባለፈው ሳምንት ወደ አዲስ አበባ የመጡት አቶ ጌታቸው በቀጥታ ከዚህ ጉዳይ ጋር ባይሆንም አጠቃላይ ከጊዜያዊ አስተዳደሩ ስራዎች ጋር በተያያዘ ስለማራዘምም ጭምር ፤ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)ም ጥያቄዎች ስለነበራቸው ተገናኝተው አጭር ውይይት ማድረጋቸውን ጠቁመዋል።
" ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ጋር ውይይት ያደረኩት ብቻዬን ነው ፤ ባደረግነው ውይይት የሁለት ዓመት ፣ 6 ወርም እስከ ምርጫ ሊሆንም ይችላል አላውቅም የፌዴራል መንግሥት አዋጅ ላይ የሚመሰረት ነው የሚሆነው መራዘም እንደሚኖርበት ጊዜያዊ አስተዳደሩ ቀጣይነት እንዲኖረው ፍቃደኝነት እንዳለ ፣ የሁለት ዓመት ጉዞውን በዝርዝር አይቶ ቀጣይ አቅጣጫዎችን በሚመለከት ለውጥ ያስፈልግ እንደሆነ ለውጥ የሚደረግበት ፤ በአንድ ወይም በሌላ መንገድ የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ያልሰራቸውን ስራዎች ማጠናቀቅ የሚችልበት ተጨማሪ እድሜ በሚያገኝበት ጉዳይ ላይ እኔ ባለሁበት እንደሚመከር ነው የማውቀው " ሲሉ ተደምጠዋል።
" ከዛ በኃላ ጠቅላይ ሚኒስትሩ የTPLF ' ጉባኤ አድርጊያለሁ ' የሚለውን ወኪል / ወገን እንዳገኙ አውቃለሁ ባገኙበት ወቅትም ተመሳሳይ መልዕክት እንዳስተላለፉ ነው የሚገባኝ " ብለዋል።
" ከዚህ ውጭ እገሌ ይሁን እገሌ አይሁን በሚል ጉዳይ ላይ እስካሁን በበኩሌ የሰማሁት ነገር የለም። ይሄ ሂደት በድብቅ የሚደረግ ስላልሆነ እንደሚወራው እገሌ እግሌ የሚባል ነገር ካለ ያው በይፋ እስከምሰማው እጠብቃለሁ " ሲሉ ገልጸዋል።
" እንዲህ ያለው ነገር ርዕስ ሊሆንም የማይገባው ነበር እገሌ ሆኗ እገሌ ተሹሟል ከተባ ይሾማል ማለት ነው እኔ እስካሁን ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ጋር ያደረኩት አጭር ውይይት ከዚህ ጋር የተያያዘ ነው የማራዘም ጉዳይ የህግ ስርዓት ያስፈልገዋል እስከዛው የጊዜያዊ አስተዳደሩ ፕሬዝደንት እኔው ነኝ " ብለዋል።
#Tigray #AtoGetachewReda #TigrayInterimAdministration #Mekelle

" እስካሁን ማህተሙ በእጄ ነው ፤ የጊዜያዊ አስተዳደሩ ፕሬዚዳንት እኔው ነኝ " - አቶ ጌታቸው ረዳ የትግራይ ጊዜያዊ አስታዳደር ፕሬዝዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ እስካሁን ድረስ በጊዜያዊ አስተዳደሩ ፕሬዝዳንት ላይ የተደረገ ለውጥ እንደሌለ ገለጹ። ይህን የገለጹት ከአዲስ አበባ ሆነው ' ርዕዮት ' ከተሰኘ የማህበራዊ ሚዲያ ፕሮግራም ጋር ባደረጉት ቃለምልልስ ነው። " ማህተምም አላስረከብኩም " ያሉት አቶ…
አቶ ጌታቸው ረዳ ለህይወታቸው የሚያሰጋ ችግር ገጥሟቸው ነበር ?
🚨 " ከፍተኛ የሰራዊት ኃላፊ ' እንዴት ታሳልፉታላችሁ ' በሚል ደንፍቶ ፓትሮል ይዞ ኤርፖርት ድረስ እንደመጣ በኃላ ሰማን !! "
ካለፈው ሳምንት አንስቶ አዲስ አበባ የሚገኙት የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዚዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ ፤ ትግራይ በነበሩበት ሰዓት ደስ የማይሉ ነገሮች እንደነበሩ (ለአብነት የሰራዊት እንቅስቃሴ) ነገር ግን እሳቸው ለደህንነታቸው የሚያሰጋ ምልክት እንዳላዩ ተናገሩ።
ነገር ግን ወደ አዲስ አበባ ለመምጣት መቐለ አሉላ ኣባነጋ ኤርፖርት 10:30 በሚሄዱበት ወቅት እሳቸው የማያውቁት ኬላ በሰራዊት አባላት ተዘርግቶ መንገድም ተዘግቶባቸው እንዳስቆሟቸው ፤ አጃቢዎቻቸውንም ጥያቄዎችን መጠየቃቸውን ጠቁመዋል።
ይህን ቃል የሰጡት " ርዮት " ለተሰኘ የማህበራዊ ሚዲያ በሰጡት ቃለምልልስ ነው።
አቶ ጌታቸው ረዳ በዝርዝር ምን አሉ ?
" አዲስ አበባ የተጠራሁት በጠቅላይ ሚኒስትሩ ነው።
በአጋጣሚ function ውስጥ ባለሁበት ሰዓት ነው እሳቸው የሀገር ውስጥ ጉብኝት ላይ ነበሩ ' መገናኘት አለብን አንዳንድ ጉዳዮች በአካል ተገናኝተን መነጋገር አለብን ' አሉ።
ከዛ በፊት ማህተም መንጠቅ ዘመቻ እየተካሄደ ነበር። በብዙ መልኩ ይሄ ነገር እንዲቆም በተደጋጋሚ ጠይቄ ነበር። መተላለፍ ያለበትን ትዕዛዝ ህግን ተከትዬ ሰጥቼ ነበር ይሄ ሊሆን አልቻለም።
በዛ ሰዓት እኔ የአፄ ዮሐንስ ሙት ዓመት የሚከበርበት function ላይ ነበርኩኝ እዛ በነበርኩበት ሰዓት ቀደም ብለው ጠቅላይ ሚኒስትሩ ' ነገ መገናኘት አለብን ' ብለው ስለነበር ትኬት ቆርጠውልኝ ጉዞ ጀመርኩ።
ከዛ በፊት አንዳንድ ደስ የማይሉ ነገሮች ነበሩ። የሰራዊት እንቅስቃሴ መቆም አለበት ብለን ጠይቀን (ስርዓት እስኪይዝ ነው የሰራዊት እንቅስቃሴ መቆም ያለበት) ሰራዊቱ እንደ ሰራዊት ሌላ የታለመለት ግብ አለ ፤ መስራት ያለበት ስራ ይኖራል ከዛ ውጭ ማህተም የመንጠቅ እንቅስቃሴ ውስጥ መግባት የለበትም የሚል ተደጋጋሚ ትእዛዞች ተጥሰው የሚደረጉ ደስ የማይሉ እንቅስቃሴዎች ነበሩ።
በግሌ ለደህንነቴ የሚያሰጋ እዚህ ግባ የሚባል ምልክት አላየሁም።
በእርግጥ ከማገኛቸው መረጃዎች አንጻር በዚህ ሂደት የተሳተፉት የሰራዊት አመራሮች ቀጣይ የኔን እንቅስቃሴ የመገደብ ፍላጎት እንደነበራቸው እሰማ ነበር ከነሱ እስካልሰማሁት ድረስ ከቁም ነገር አልቆጠርኩትም።
የጀመሩት ማህተም መንጠቅ፣ ' እገሌ ትክክለኛ ከንቲባ ነው ' ፣ ህገመንግስት የመተርጎም ኃላፊነት የተወሰኑ የጦር አመራር ነን የሚሉ ሰዎች ከያዙት በኃላ ጊዜያዊ አስተዳደሩን በተግባር የመቀየር ስራ ተጀምሯል።
እንቅስቃሴ መገደቡ ምናልባት ቢሮ እንዳልገባ ይሁን፣ አላውቅም ብቻ። ግን በይፋ ይህ ነው የሚባል ነገር ሰምቼ አላውቅም።
ከምክትሌም ጋር መገናኘት ካቆምን ረጅም ጊዜ ሆኖናል። እሳቸው ብዙ ጊዜ ስታይላቸውም ነው የሆነ ችግር ሲፈጠር ብዙ ጊዜ ስልክ ማጥፋት ወይም መራቅ ነው።
እኔ በዚህ ደረጃ ለህይወቴ የሚያሰጋ እዚህ ግባ የሚባል ነገር አለ ብዬ አስቤ አላውቅም ነበር።
ለማንኛውም ያኔ ወደ አዲስ አበባ ጉዞ በምናደርግበት ሰዓት 10:30 መሰለኝ ኬላ እንደነበረ አላውቅም ኬላ ተደርጎ ነበር እንግዲህ እኔ በአጀብ ነው የምሄደው ኬላ ሲያስቆሙ የኔ ጠባቂዎች ' የምን ኬላ ነው ? ' የሚል ጥያቄ አቀረቡ።
አጃቢዎቼ ' የፕሬዜዳንቱ ነው መኪናው ' ሲላቸው ' አይ ማጣራት እንፈልጋለን እንደውላለን ' አሉ። ከዛ እኔ መስኮት ከፈትኩና ማን ጋር ነው የምትደውሉት የኔን ጉዞ በሚመለከት ስል እዛ አካባቢ ሲያስተባብር የነበረው ወጣት የሰራዊት ኃላፊ ይመስለኛል እኔን እንዳየ መከራከር አልፈለገም መንገዱን መንገዱን ከፍተውልን ሄድን።
ኤርፖርት ገባሁ። አውሮፕላን በምንሳፈርበት ሰዓት እዚህ ግባ የሚባል ምንም ነገር አልነበረም። አውሮፕላን ውስጥ ከገባን በኃላ የገባን ነገር ምንድነው የዛ አካባቢ ይሄን ኃላፊነት የወሰደ ከፍተኛ የሰራዊት ኃላፊ ' እንዴት ታሳልፉታላችሁ ' በሚል ደንፍቶ ፓትሮል ይዞ ኤርፖርት ድረስ እንደመጣ በኃላ ሰማን።
እኔ ምንም notice አላደረኩም ፓትሮል ይዞ መምጣት ብቻ ሳይሆን የፌዴራል ፖሊስ ለሚጠብቀው ኤርፖርት የፌዴራል ፖሊስን ጥሶ መግባት አይችልም ወይ ወደ ግጭት ይገባል። የኔም አጃቢዎች አሉ። ያኔ ወደ ግጭት ይገባል ወደ ግጭት ከተገባ የሚፈጠረውን ነገር እርግጠኛ መሆን አይቻልም። በቁጥር የኔ አጃቢዎች የሚበልጡ ይመስለኛል። የኔ ጠባቂዎች ደስ የማይል ነገር እየተፈጠረ እንደሆነ ገምተዋል ግን መመለስና መሟገት አንችልም።
አውሮፕላኑ ተነሳ ሄድን።
አዲስ አበባ እንደገባን የነበረውን ሁኔታ ስናጣራ ኬላው ዝም ብሎ ተራ ኬላ እንዳልነበር (በነገራችን ላይ ምንም አይነት ኬላ መንግሥት ሳያውቀው መቀመጥ አይችልም) እዛ አካባቢ ያሉ የጦር ኃላፊዎች ብቻቸውን ያደረጉትም አልነበረም ከበላይ በተሰጠ ትእዛዝ ነው ኬላ የተደረገው።
ያ ፓትሮል ይዞ የመጣው የሰራዊት ኃላፊ የአየር መንገድ / አቬዬሽን security አባል ጋር ስልክ ደውሎ ' እሱ ብቻ ነው ? ወይስ ሌሎችንም ይዞ ነው እየወጣ ያለው ? ' የሚል ጥያቄ ሁሉ እንደጠየቀው አውቃለሁ።
ከዛ በኃላ ያወኳቸውን መረጃዎች ግምት ውስጥ በማስገባት ምናልባት ጫን ያለ ስራ ለመስራት ፍላጎት እንደነበራቸው ፤ እንዲህ ያለው ኃላፊነት የጎደለው ተግባር ምንም ነገር ባይፈጣር ጭምር እጅግ እጅግ አደገኛና ተቀባይነት የሌለው ተግባር እንደሆነ ብቻ ነው የማውቀው።
ከዛ እስከወጣሁበት ፤ አውሮፕላን ላይ እስከ ተሳፈርን ሰዓት ድረስ ኬላውን ጭምር አይቼ ይሄን ያክል ህይወቴን አደጋ ላይ የሚጥል ነው ሳይሆን ምናልባት የተለዩ እንቅስቃሴዎች ይኖራሉ ከዛ ጋር የተያያዘ ነው የሚል እምነት ነበረኝ።
ከወጣሁ በኃላ የእነሱ ደጋፊዎች የሆኑ ስለማምለጤ በተደጋጋሚ ሲያወሩ ስሰማ ግን ምናልባትም አምልጬ መምጣቴ / ማምለጤ ነው የገባኝ ፤ ሀሳቤ የማምለጥ የነበር ባይሆንም። ደጋፊዎችቸው እና እነሱ የሚከፍሏቸው የሚዲያ ተቋማት ስለ ማምለጤ ሲያወሩ ምናልባትም ይዘውት የነበረ እቅድ መክሸፉን እራሳቸው ናቸው እያጋለጡ ያሉት እንጂ እስከዛ ድረስ የማውቀው አልነበረም። "
#AtoGetachewReda #Tigray #TgiraiInterimAdministration
@tikvahEthiopia

" ከቀበሌ የነዋሪ መታወቂያ ውጪ ሌላ መታወቅያ ይዞ መንቀሳቀስ ይከለከላል "- የትግራይ ክልል ሰላምና የፀጥታ ቢሮ
➡️ " መታወቂያው በሁሉም አከባቢዎች ተማልቶ ባልተዳረሰበት ሁኔታ ይህንን መሰል አስገዳጅ መግለጫ ማውጣት ተገቢ አይደለም " - የመቐለ ከተማ ነዋሪዎች
የትግራይ ክልል የሰላምና የፀጥታ ቢሮ ከቀበሌ ነዋሪ ማረጋገጫ መታወቂያ ውጪ በሌላ መንቀሰሳቀስ ይከለከላል ሲል ያወጣው መግለጫ አነጋጋሪ ሆኗል።
መግለጫውን በማስመልከት " ፋይዳ ፣ ፓስፓርት ፣ የባንክ ደብተርና የተለያዩ የመንግስትና የግል መስራቤቶች መታወቅያዎች ዋጋ የሚያሳጣ ልክ ያልሆነ መግለጫ ነው " በማለት አስተያየት የሰጡ አሉ።
" ከነዋሪዎች ገንዘብ ለመሰብሰብ ከማለም ውጪ የሚተገበር መግለጫ አይደለም " ያሉም አልጠፉም።
" በክልሉ ወጣት ያለውንና የሚታየውን ሰፊ የለውጥ ተነሳሽነትና ፍላጎት ለማዳካም እና ለማፈን ያለመ ነው " የሚል ጠንካራ አስተያየት ያንሸራሸሩ ወጣቶችም አሉ።
የክልሉ የሰላምና ፀጥታ ቢሮ ያወጣው መግለጫ የቀበሌ ነዋሪ ማረጋገጫ መታወቅያ ተዘጋጅቶ ለእደላ ዝግጁ መሆኑን እና ነዋሪው እየወሰደ እንደሆነ ያመላክታል።
" ከቅርብ ጊዜ በኋላም ያለ የቀበሌ የነዋሪ ማረጋገጫ መታወቅያ ሌላ መታወቅያ ይዞ መንቀሳቀስ ስለሚቆም ሁሉም ነዋሪ ተገቢውን ነገር አማልቶ ወደ ሚኖርበት የቀበሌ አስተዳደር በመሄድ መታወቅያ መያዝ ይኖርበታል " ይላል መግለጫው።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ የመቐለ ቤተሰብ አባል የክልሉ የሰላምና የፀጥታ ቢሮ መግለጫን ለማረጋገጥ ወደ ተወሰኑት የመቐለ የቀበሌ መስተዳደሮች ተዘዋውሮ እንደተመለከተው የተባለውን የነዋሪ መታወቂያ ተሟልቶ አልቀረበም።
የመቐለ ከተማ የአንድ ቀበሌ አስተዳደር ለቲክቫህ በሰጡት አስተያየት " ቢሮው የሚለው እና መሬት ላይ ያለውን አይገናኝም፤ ለምሳሌ የእኛ ቀበሌ ነዋሪዎች መታወቂያው እንዲዘጋጅ የሚጠየቀው ገንዘብ አሟልተው ባለመክፈላቸው ምክንያት የደረሰን የህትመት ውጤት ስለሌለ እደላ አልጀመርንም " ብለዋል።
ከጦርነቱ በፊት ለነዋሪዎች ሲሰጥ የነበረው የወረቀት የነዋሪ መታወቂያ ካርድ ወደ ዲጂታል ለማሳደግ ሲደረግ የነበረው እንቅስቃሴ በመቋረጡ ምክንያት ነዋሪዎች ከጦርነቱ በኋላ ለተለያዩ ስራዎቻቸው ማሳለጫ መታወቂያ አጥተው ሲጉላሉ ማየት የተለመደ ነው።
ከቀርብ ጊዜ በኋላ በክልሉ አገልግሎት መስጠት የጀመረው አገራዊው የፋይዳ ዲጂታል መታወቅያ እንዲሁም የአዲስ ፓስፓርት እደላና እድሳት ችግሮቻቸው በመጠኑ ሊያቃልላቸው ችሏል።

" እኔን እስካሁኗ ደቂቃ ድረስ ፕሬዜደንት አድርጎ የሾመኝ የለም " - ሌ/ጄነራል ታደሰ ወረደ በአሁኑ ባለው የትግራይ ቀውስ " አሸናፊም ሆኖ ተሸናፊ የለም " አሉ የትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር ምክትል ፕሬዜዳንት ሌተናል ጀነራል ታደሰ ወረደ። እስካሁኗ ሰዓት ድረስ የትግራይ ክልል ጊዚያዊ አስተዳደር ፕሬዜዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ ናቸው ያሉ ሲሆን " የሚጠበቅ ማስተካከያ ቢኖርም እኔን እስካሁኗ ደቂቃ ድረስ…
#Tigray
የትግራይ ህዝብ የጊዚያዊ አስተዳደሩን ፕሬዜዳንት እንዲጠቁም ጥሪ ቀረበ።
ጥሪውን ያቀረቡት የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚንስተር ዐብይ አሕመድ (ዶ/ር) ናቸው።
ጥቆማ የሚቀርብበት አድራሻ በኢሜል [email protected] መሆኑ የጠቀሱት ጠቅላይ ሚንስትሩ ጥቆማው መቼ ተጀምሮ እንደሚያልቅ እንዲሁም በህዝብ ጥቆማ የተመረጠው የጊዚያዊ አስተዳደሩ ፕሬዜዳንት እንዴትና መቼ ይፋ እንደሚሆን አስመልክተው በዝርዝር ያሉት የለም።
የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚንስተር ዐብይ አሕመድ (ዶ/ር) በትግርኛ ቋንቋ ምንድነው ያሉት ?
" ለትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር ፕሬዜዳንት ጥቆማ አስመልክቶ ለመላው የትግራይ ህዝብ የቀረበ ጥሪ !
በኢፌዴሪ ህገ-መንግስት አንቀፅ 62(9)፣ እንዲሁም በፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነት መሰረት የፌዴራል መንግስት በክልሎች ጣልቃ ለመግባት ለመደንገግ በወጣው አዋጅ ቁጥር 359/1995 መሰረት እንዲሁም በትግራይ አሳታፊ ጊዚያዊ አስተዳደር በሚመለከት የተደነገገው የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር 533/2015 መሰረት የቆመው ጊዚያዊ አስተዳደር ለሁለት ዓመታት መቆየቱ ይታወቃል።
በአዋጅ 359/1995 አንቀፅ 15(3) መሰረት ጊዚያዊ አስተዳደሩ ለሁለት ዓመት ብቻ እንደሚቆይ ይደነግጋል። ይሁን እንጂ በተጨባጭ ምክንያቶች የጊዚያዊ አስተዳደሩ ዕድሜ ማራዘም ይቻላል። ከላይ በተጠቀሱት ህጎችና በፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነት መሰረት የተቋቋመው ጊዚያዊ አስተዳደር የተቀመጡለት ተልእኮዎች አጠናቅቆ በህዝብ ለተመረጠ መንግስት ሃላፊነቱ ማስረከብ ይገባ ነበር።
ይሁን እንጂ የትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር የተሰጡት ዋና ተልእኮዎች በተወሰነለት ጊዜ ማጠናቀቅ አልቻለም።
ከተሰጡት ዋና ተልእኮዎች አንዱ ምርጫ ለማካሄድ የሚያስችል ምቹ መደላድል መፍጠር ነው። ጊዚያዊ አስተዳደሩ ይህንን ቁልፍ ተልእኮ ባለማሳካቱ ምክንያት ዕድሜውን ለአንድ ዓመት ለማራዘም አስገድዷል።
የፌደራል መንግስት መሬት ላይ ያለው ተጨባጭ ሁኔታ ከግምት በማስገባት የጊዚያዊ አስተዳደሩ ዕድሜ ለማራዘም ፣ ፓለቲካዊ ፣ አስተዳደራዊና የህግ ስራዎች በማከናወን ላይ የሚገኝ ሆኖ ከዚሁ ጎን ለጎን የጊዚያዊ አስተዳደሩ ፕሬዜዳንት መሾም አስፈላጊ ሆኖ ተገኝተዋል።
በደንብ ቁጥር 533/2015 አንቀጽ 3(2) መሰረት የጊዚያዊ አስተዳደሩ ፕረዜዳንት የመሾም ሃላፊነት የጠቅላይ ሚንስትሩ ስልጣን ቢሆንም ህዝብ በምርጫ መሪዎቹ እስኪመርጥ ድረስ የጊዚያዊ አስተዳደሩ ፕሬዜዳንት በመምረጥ በኩል ተሳትፎ እንዲኖረው አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ የጊዚያዊ አስተዳደሩ ተልእኮዎች በብቃት መፈፀም ይችላሉ ሰላምና ደህንነት ያረጋግጣሉ የምትሉዋቸው እጩዎች በ [email protected] የኢሜል አድራሻ ወደ ጠቅላይ ሚንስትር ቢሮ ከዛሬ ጀምራችሁ ጥቆማችሁን መላክ እንደምትችሉ እናሳውቃለን። "

" ህዝበ ሙስሊሙ ጾሙ የተሟላ እንዲሆን በየቀኑ ለአገርና ለህዝብ ከልብ የመነጨ ዱዓ ማድረግ አለበት " - ሀጂ መሐመድ ካሕሳይ
በትግራይ መቐለ ከተማ " ኢፍጣራችን ለሰላማችን " በሚል መሪ ቃል ኢስላማዊ የጎደና ላይ የኢፏጣር ስነ-ስርዓት ተካሂዷል።
በኢፍጧር ስነ-ስርዓቱ ላይ በርካታ የአስልምና እምነት ተከታዮች ተሳትፈውበታል።
የትግራይ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ዋና ፀሀፊ ሀጂ መሐመድ ካሕሳይ ፤ ረመዷን ማለት የመቻቻል፣ የመከባበርና ያለንን ለሌላ ማከፋል መግለጫ ነው ብለዋል።
" የኢፍጧር ስነ-ስርዓት በጋራ ከመብልና ከመጠጥ በዘለለ የአንድነታችን መግለጫ ነው " ያሉት ዋና ፀሀፊው " ህዝበ ሙስሊሙ ጾሙ የተሟላ እንዲሆን በየቀኑ ለአገርና ለህዝብ ከልብ የመነጨ ዱዓ ማድረግ አለበት " ብለዋል።
የኢፍጧር ስነ-ስርዓቱ ተፈናቃይ ወገኖች በማሰብና በማሰባሰብ መካሄዱንም ተናግረዋል።
#TikvahEthiopiaFamilyMekelle
Photo Credit - Destsi Woyane

#TPLF በደብረፅዮን ገ/ሚካኤል (ዶ/ር) የሚመራው ህወሓት የጠቅላይ ሚኒስትሩን ጥሪ ተቋወመ። ዛሬ ምሽት ባወጣው መግለጫ ፥ የኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚነንስትር ዐብይ አህመድ (ዶ/ር) የትግራይ ህዝብ ለቀጣይ አንድ ዓመት ስልጣኑ የሚራዘመውን የጊዚያዊ አስተዳደሩን የሚመራ ፕሬዜዳንት እንዲጠቁም አስመልክቶ ያወጡትን መልዕክት " የተናጠል ውሳኔና ተግባር " ሲል ተቃውሟል። " የፕሪቶሪያ ሥምምነት ከተፈረመ…
#Tigray
አቶ ጌታቸው ረዳ ምንድነው ያሉት ?
ከትግራይ ክልል " ለስራ " በሚል ምክንያት ከወጡ 20 ቀናት ያስቆጠሩት የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዝዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ ከሰሞኑን ለህክምና አንዴ ወደ ዱባይ ሌላ ጊዜ ወደ ባንኮክ ተጉዘዋል እየተባለ ሲነገርባቸው ነበር።
ትላንት እሁድ በሰዓታት ልዩነት ሁለት መልእክቶችን አጋርተዋል።
አንዱ ለህዝበ ሙስሊሙ የዒድ አልፈጥር በዓል የእንኳን አደረሳችሁ የሚል ሲሆን ፤ ሌላኛው ለተቀናቃኞቻቸው " ድሉ የህዝብ ነው " የሚል ጠንካራ ትችት አዘል መልእክት ነው።
" ላለፉት 20 ቀናት በትግራይ እየታየ ያለው ፓለቲካዊ ቀውስ ' ስልጣን ወይ ሞት ' የሚል ቡድን ላለፉት ሁለት ዓመታት የደሎተው ሴራ መጨረሻው ምዕራፍ ማሳያ ነው " ብለዋል።
ይህ ደሞ አንዳንድ የተሻለ ስምና ዝና ያላቸውን ግለሰቦችም ለስህተት የዳረገ ፍፃሜ ነው በማለት ተግባሩ አጣጥለውታል።
ፕሬዜዳንቱ " ኋላቀር ቡድን " ሲሉ የገለፁት አካል የጊዚያዊ መንግስቱ መዋቅር በመጣስ ማህተም ከተቆጣጠረ በኋላ በመጀመሪያ እርምጃው በትላለቅ ከተሞች ለደጋፊዎቹ በስፋት መሬት አከፋፍሏል ፤ ገቢ የሚያስገኙለትን የሽያጭ ስራዎች ፈፅሟል ብለዋል።
" መሬት ከመሸጥና ከማከፋፈል አልፎ ተፈናቃዮችን ወደ ቄያቸው መመለስና ግዛታዊ አንድነት ማረጋገጥ ከመፈክር በዘለለ ጣጣው አይደለም " ሲሉ ገልጸዋል።
" ኋላቀር ቡድን " ሲሉ የገለፁት አካል ሁለተኛ ትኩረቱ ወደ #ፌደራል እየተመላለሰ የፕሬዜዳንት ስልጣን እንዲሰጠው መለመን ሆኗል ሲሉ አብራርተዋል።
" ቡድኑና አሽከሮቹ በህልምና በቀልባቸው የማይለቁዋቸው ሁለት አጀንዳዎች መሬትና ስልጣን ናቸው " ሲሉ ገልጸዋል።
" ቡድኑ የሚያስተባብራቸው አካላት የተፈናቃዩ ተስፋና የወጣቱን ህልም በመቀማት ወደ ሁለተኛ ዙር ትርምስ ሊከቱን ታችና ላይ በማለት ስለሚገኙ ህዝቡ ሃይ ሊላቸው ይገባል " ሲሉ አክለዋል።
የትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር ፕሬዜዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ያጋሩትን ጠንከር ያለ ፅሁፍ " ድል የህዝባችን ነው " ሲሉ ቋጭተውታል።
#TikvahEthiopiaFamliyMekelle

" ታስረው ይቅረቡ " - ፍርድ ቤት ከሂጃብ ክልከላ ጋር ተያይዞ የቀረበውን ክስ ፍርድ ቤት ቀርበው መልስ እንዲሰጡ የተፃፈላቸውን ትእዛዝ " አንቀበልም " ያሉ አካላት ታስረው እንዲቀርቡ የአክሱም ከተማ ፍርድ ቤት አዘዘ። ፍርድ ቤቱ ጥር 19/2017 ዓ.ም በፃፈው ደብዳቤ ፤ ከሂጃብ ክልከላ ጋር ተያይዞ ክስ የቀረበባቸው 4 ርእሰ መምህራን የአክሱም ከተማ ፓሊስ አስሮ እንዲያቀርባቸው ፍርድ ቤቱ አዟል።…
#Tigray የትግራይ የእስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ፤ " በአክሱም ሙስሊም ሴት ተማሪዎች ላይ የተደረገው የሂጃብ መልበስ ክልከላ እስከ አሁን አልተነሳም " ሲል አሳውቋል።
ይህን ያሳወቀው ትላንት በመቐለ በተካሄደው የዒድ ሶላት ወቅት ነው።
ምክር ቤቱ ዋና ፀሓፊ ሀጂ መሀመድ ካሕሳይ " የሂጃብ መልበስ ክልከላ እስከ አሁን አልተነሳም " ያሉ ሲሆን " አሁንም ጥያቄያችን እንዲመለስ ጥሪ እናቀርባለን " ብለዋል።
የሃይማኖት መቻቻልና መከባበር የአንድ አገርና ህዝብ መልካም ጌጥና መለያ ናቸው ሲሉም ገልጸዋል።
ክልከላው " የሃይማኖት እኩልነትና የመማር መብት የሚፃረር ነው " ያሉ ሲሆን ምክር ቤቱ ጉዳዩ በህግ እየተከታተለው እንደሚገኝ አመልክተዋል።
የትግራይ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ከፌደራል የእስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት በመተባበር ታሪካዊውና ሃይማኖታዊውን የአልነጃሺ መስጂድ በማልማት የቱሪስቶች መዳረሻ ለማድረግ ያለመ " አልነጃሺ 00 " በማለት የተሰየመ ፕሮጀክት ግንባታ ለማካሄድ ጥናት ማጠናቀቃቸው ተነግሯል።
#TikvahEthiopiaFamilyMekelle
@tikvahethiopia
ይህን ያሳወቀው ትላንት በመቐለ በተካሄደው የዒድ ሶላት ወቅት ነው።
ምክር ቤቱ ዋና ፀሓፊ ሀጂ መሀመድ ካሕሳይ " የሂጃብ መልበስ ክልከላ እስከ አሁን አልተነሳም " ያሉ ሲሆን " አሁንም ጥያቄያችን እንዲመለስ ጥሪ እናቀርባለን " ብለዋል።
የሃይማኖት መቻቻልና መከባበር የአንድ አገርና ህዝብ መልካም ጌጥና መለያ ናቸው ሲሉም ገልጸዋል።
ክልከላው " የሃይማኖት እኩልነትና የመማር መብት የሚፃረር ነው " ያሉ ሲሆን ምክር ቤቱ ጉዳዩ በህግ እየተከታተለው እንደሚገኝ አመልክተዋል።
የትግራይ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ከፌደራል የእስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት በመተባበር ታሪካዊውና ሃይማኖታዊውን የአልነጃሺ መስጂድ በማልማት የቱሪስቶች መዳረሻ ለማድረግ ያለመ " አልነጃሺ 00 " በማለት የተሰየመ ፕሮጀክት ግንባታ ለማካሄድ ጥናት ማጠናቀቃቸው ተነግሯል።
#TikvahEthiopiaFamilyMekelle
@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#Tigray
" ትግራይ ከተደገሰላት የባሰ አዘቅትና አዙሪት የምናድንበት ጊዜ አሁንና አሁን ብቻ ነው " አለ በትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዜዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ የሚመራው የህወሓት ቡድን።
አቶ ጌታቸው የሚመሩት የህወሓት ቡድን ባወጣው መግለጫ "ልዩነቶቻችን በይደር በማቆየት ቂምና ቁርሾ ቀርፈን እኔነትንና ጠቅላይነት አስተሳሰብ ከውስጣችን በማስወገድ ትግራይ እናድናት " ብሏል።
ትግራይ ከገባችበት ቀውስና አጣብቂኝ " ያድናታል ብዬ አምኜበታለሁ " ያለውን የመፍትሄ ሃሳብ ለውይይት ማቅረቡ ያስታወቀው ቡድኑ ከቀረበው የተሻለ ክልሉን ማዳን የሚችል የመፍትሄ ሃሳብ ካለ ለማዳመጥ ዝግጁ መሆኑ ገልጿል።
ደብረፅዮን (ዶ/ር) የሚመሩትን ህወሓት በግልፅና ጠንካራ ቃላት የተቸም ሲሆን ጊዚያዊ አስተዳደሩ ለአንድ ዓመት መራዘሙ በመቀበል የሚከተሉት ሦስት የመፍትሄ ሃሳቦች አቅርበዋል :-
- ጊዚያዊ አስተዳደሩ ሁሉም አመለካከቶች በማቀፍ የፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነት ማእከል በማድረግ መዋቅሩ ተጠናክሮ በአስቸኳይ መቋቋም አለበት።
- ዕድሜውን የተራዘመው ጊዚያዊ አስተዳደር ማቋቋም የሚያስችል ሁሉም አመለካከቶችና የፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነት አፈራራሚዎች ያካተተ ፓለቲካዊ ውይይት ይቅደም።
- የትግራይ ሰራዊት ታጣቂዎች ወደ ማረፍያ ካምፓቸው ተመልሰው የሰላምና የፀጥታ ስራ ሙሉ በሙሉ በህዝባዊ ፓሊስ ይተካ ፤ የጊዚያዊ አስተዳደሩ መዋቅር እስከ ቀበሌ ድረስ ህዝብ ነፃ ሆኖ በመረጣቸው አስተዳዳሪዎች እንዲመራ ፣ ተግባሩ በአንድ ወር ውስጥ እንዲከናወን።
... ብሏል።
ፕሬዜዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ የሚመሩት የህወሓት ቡድን ከደብረፅዮን (ዶ/ር) ህወሓት ቡድን ጋር ለመወያየት ዝግጁ መሆኑ ባወጣው ወቅታዊ መግለጫ ይፋ አድርጓል።