#update አዲስ አበባ⬆️
የአዲስ አበባ ጤና ቢሮ በሰኔ 16 የድጋፍ ሰልፉ ላይ በደረሰው አደጋ ለተጎዱት ወገኖቻችን አስፈላጊውን የህክምና አገልግሎት ለሰጡ የጤና ተቋማት የማበረታቻ ሽልማት ሰጥቷል።
©የአዲስ አበባ ኮሚኒኬሽን
@tsegabwolde @tikvahethiopia

ከባህር ዳር⬆️
"ሰላም ፀግሽ እንዴት ነህ? ሰላም ለኢትዮጵያና ልጆቿ እናም ለሰውልጅ በሙሉ! እኔ አስራር አማን እባላለሁ ከባህርዳር ወሰን የለሽ የበጎ ፍቃደኛ ወጣች ቡድን "ደም ያስተሳስረናል" በሚል ደስ የሚል መፈክር መደመርን በተግባር ባረጋገጠመልኩ ደም እየለገስን ውለናል። ለአካባቢውም ሰዎች ትልቅ ምስጋና ይገባቸዋል በትልቅ ወኔ በመኪናቸው ጭምር በመምጣት ደም ለግሰዋል። "ደም ያስተሳስረናል" ደሜ ለወገኔ አሁንም ባንድነታችን ሰላማችን ይረጋገጣል። ትንሽ ብዥታ ያለባቸው ሰዎች ሊማሩበት ይገባል አጥፊውም እኛ ጠፊውም እኛ ከመሆን እነቆጠብ ለወጣቶች በሙሉ መልክቴ ነው።"

በአዲስ አበባ ጤና ቢሮ የተገዙ አምቡላንሶች ለጤና ጣቢያዎችና ለሆስፒታሎች የቁልፍ ርክክብ ሲደረግ የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ ኢንጂነር #ታከለ_ኡማ መልዕክት አስተላልፈዋል።

#update የመንግስት ማስተባበያ⬇️
ኢትዮጵያ ጦሯን ከኤርትራ ድንበር እያነሳች ነው ተብሎ የተሰራጨው መረጃ #ሐሰት ነው ሲል መንግሥት አስተባበለ፡፡
ባለፈው ሳምንት መጨረሻ አካባቢ በኢትዮጵያና በኤርትራ ድንበር በተለይም በሽራሮ ግንባር የሚገኘው ጦሯን ኢትዮጵያ እያነሳች እንደሆነ፣ በርካታ ቁጥር ያላቸው አውቶብሶችና ኦራል ወታደራዊ የጭነት ተሽከርካሪዎች ጦሩን ሲያጓጉዙ መታየታቸውን፣ በተለያዩ የማኅበራዊ ሚዲያዎች ሲሰራጭ ነበር፡፡
ጉዳዩን በተመለከተ የተጠየቁት የመከላከያ ሚኒስትሩ አቶ ሞቱማ መቃሳ መረጃው ሐሰት ነው ሲሉ አስተባብለዋል፡፡
‹‹እውነት ነው ሽራሮ ግንባር ላይ እንቅስቃሴዎች ነበሩ፡፡ ነገር ግን የተለመደ አሠራር ነው ሲሉ፤›› ለሪፖርተር ተናግረዋል፡፡
ኢትዮጵያና ኤርትራ ላለፉት 20 ዓመታት ከነበሩበት የጥላቻ መንፈስ ተላቀው ሰላም ካወረዱ ጥቂት ወራት እየተቆጠሩ ሲሆን፣ በመካከላቸው ያለውን የጠላትነት ስሜት አጥፍተው በሰላም ለመኖር መስማማታቸው ይታወሳል፡፡ ከዚህ ባለፈ የኢኮኖሚ ትስስር ለመፍጠር፣ በተለይም ኢትዮጵያ የኤርትራን ወደቦች መጠቀም የሚያስችላት ስምምነት መደረጉ አይዘነጋም፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (ዶ/ር) በኤርትራ ድንገተኛ ጉብኝት ካደረጉ በኋላ፣ ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂም በኢትዮጵያ ጉብኝት አድርገዋል፡፡
‹‹ሁለቱ አገሮች ድንበር ላይ ያሉ ወታደሮቻቸውን ለማንሳት እስካሁን የተፈራረሙት ስምምነት የለም ሲሉ፤›› አቶ ሞቱማ አክለዋል፡፡
ሁለቱ አገሮች እንደገና ወዳጅነት የጀመሩት የኢሕአዴግ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ የአልጀርስ ስምምነትን ሙሉ በሙሉ መቀበሉን ካስታወቀ በኋላ ነበር፡፡ እስካሁን ድረስ ይኼንን ስምምነት ተግባራዊ ለማድረግ የተጀመረ ሥራ ባለመኖሩ፣ ከድንበር ላይ ጦር የማንሳት እንቅስቃሴ ሊኖር አይችልም ሲሉ ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው ባለሙያዎች ያስረዳሉ፡፡
©ሪፖርተር

TIKVAH-ETHIOPIA via @like
ፈጣሪ ማስተዋል ይስጠን!
ዛሬ አንዳንዶች ባሉበት ሆነው ተዋልደው ተከባብረው የሚኖሩ #ብሄሮችን ለማጋጨት ይሞክራሉ፤ ሰዎችን ለጥል ያነሳሳሉ፤ እርስ በእርስ እንዲገዳደሉ ይቀሰቅሳሉ፤ በፍቅር የሚኖረውን ህዝብ ይከፋፍላሉ፤ ወጣቱ ሰብዓዊነቱን እንዲረሳና ብሄሩን እንዲያስቀድም በሙሉ አቅማቸውን ቀን ማታ ይቀሰቅሳሉ፤ ህግን ስርዓትን አክብሮ የሚኖረውን ወጣት ተነሳ ግደል፣ አጥፋ እያሉ ይመክራሉ፤ ብሄር መስደብ፣ ማንቋሸሽ ባህል እንዲሆን ይሰራሉ፤ ወጣቱን ሳያውቀው ከፈጣሪው ጋር ያጋጫሉ፤ የተወሰነ ሰው ባጠፋው ወንጀል ሚሊዮኖች መሰደብ፣ መገለል እንዳለባቸው ምንም ሳይፈሩ ይናገራሉ።
እንዲህ የሚያደርጉ ሰዎች ብዙዎቹ ከራሳቸው ጋር የተጣሉ፣ ሰውነታቸውን የረሱ፣ ፈጣሪን የካዱ፣ እውቀት የራቃቸው፣ ማስተዋል ያልፈጠረባቸው ናቸው።
ዛሬ በብሄሮች መካከል እሳት ለመለኮስ የሚጥሩ ሰዎች የለኮሱት እሳት እራሳቸውን እንደሚያነድ፤ እራሳቸውን እንደሚፈጅ ፍፁም አላስተዋሉም።
የዛሬዎቹ የጥላቻ ነጋዴዎች #ነገን አሻግረው አላዩም። ይህ ህዝብ በጣም የተዋሀደ፣ እርስ በእርሱ የተዋለደ ህዝብ ነው። ዛሬ ብሄር ለይተው በለው የሚሉት ተራ ግለሰቦች ነገ የራሳቸው ወንድም እና እህቶች ካሉበት አካባቢ ወጥተው እንደሚማሩ ረስተውታል፤ ከአንዱ ከተማ ወደ ሌላው ከተማ ሄደው የሚማሩትን #ምስኪን ልጆችን ረስተዋቸዋል።
የብሄር ተቆርቋሪዎች መስለው የራሳቸውን ወንድም እና እህቶች የሚያጋድሉት ሰይጣኖች ናቸው። ወንድም እና እህቶቻቸው በሄዱበት ቦታ ሁሉ በቋንቋቸውና በባህላቸው እንዲሸማቀቁ ሊያደርጓቸው ያሰቡ እነሱ እውነትም የዚህች ሀገር ጠላቶች ናቸው።
እናተ የጥላቻ ነጋዴዎች...
◾️ነገ ምስኪን እህት ወንድሞቻችሁ የት ተመድበው እንደሚማሩ አታውቁምና ከጥላቻ ይልቅ ፍቅርና አንድነትን አስተምሩ።
◾️ነገ ምንም የማያውቀው ሰራተኛ የዕለት ጉርሱን ፍለገ የትኛው ከተማ እንደሚሄድ አታውቁም ከጥላቻ ይልቅ ፍቅርና አንድነትን አስተምሩ።
ሁሉም ሰላምን የሚወድ፤ ሀገሩን የሚወድ ሰው በብሄር ማካከል ጥላቻ እንዲኖር የሚሰሩትን ያግልላቸው። የማዕበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚዎች የጥላቻ ገፆች እና ግለሰቦችን #Block አድርጓቸው።
ለወጣቱ ፍቅርን እናውርሰው። ፍቅር እንደሚያሸንፍ ደጋግመን እንገረው። #ሰውነት ከሀገር፣ ከብሄር፣ ከዘር እንደሚበልጥ እንገረው።
ፈጣሪ ማስተዋልን ይስጠን!
ፀጋአብ ወልዴ-ኢትዮጵያ

ከሰቆጣ⬆️
"ከነሐሴ 16 ጀምሮ የሚከበረውን የሻደይ ብአል ለመታደም የሰቆጣ ተወላጅ የሆነው የቀድሞው ጠ/ሚኒስትር ታምራት ላይኔ ዛሬ ገብቱዋል።"
©Meng & G

#update መቀለ⬇️
በትግራይ ክልል መቐለ ከተማ ‘‘ናትና ወጋገን’’ በሚል ስያሜ 16 ኪሎ የሚሸፍን የሩጫ ውድድር ለ2ኛ ጊዜ ተካሄደ።
ውድድሩ ባለፈው ዓመት ሚያዚያ ወር ላይ ለመጀመሪያ ጊዜ የተካሄደ ሲሆን፥ በክልሉ የሚገኙ ወጣት አትሌሎችን ለማስተዋወቅ ያስችላል ተብሏል።
በዚህም በሁለቱም ፆታዎች 16 ኪሎ ሜትር ርቀት የሚሸፍን የሩጫ ውድድር በዛሬው ዕለት በትግራይ ክልል መቐለ ከተማመካሄዱ ነው የተገለጸው።
በውድድሩም በወንዶች ሀጎስ ገብረ ህይወት ከመስፍን ኢንዱስትሪያል እንጅነሪግ 1ኛ፣ ሰለሞን በሪሁ ከትራንስ ኢትዮጵያ 2ኛ እና 3ኛ ሠጸጋየ ጊዳኔ ከመስፍን ኢንዱስትሪያል ኢንጂነረግ ከ1- 3ሻ ደረጃ ይዘው ውድድሩ መጠናቀቁ ነው የተገለጸው።
በተመሳሰይ ርቀት በሴቶች 1ኛ የሺ በላይ በግል፣ 2ኛ ፎቴን ተስፋየ ከመሶቦ ሲሚንቶ ፋብሪካና 3ኛ ጽገ ሃይለ ስላሴው በቅደም ተከተል ከ1ኛ- 3ኛ ደረጃዎችን ይዘው ማጠናቀቃቸው ታውቋል።
በውድድሩ በሁለቱም ጾታዎች ከ1ኛ – 3ኛ ደረጃ ለወጡ አትሌቶች በየደረጃው ከ50 ሺህ እስከ 20 ሺህ ብር የገንዘብ ሽልማት የተበረከተላቸው መሆኑም ነው የተገለጸው።
በተመሳሳይ መልኩ 2 ኪሎ ሜትር የሚሸፍን የህፃናት ውድድርም የተካሄደ መሆኑም ተገልጿል።
©FBC