TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.3K photos
1.51K videos
212 files
4.11K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#ጥብቅ ማሳሰቢያ⬇️

"...ከምንም በላይ የግልና የቡድን ጥቅሞቻችሁን #ሰላማዊ በሆነ መንገድ ማስጠበቅ እየቻላችሁ በተለያዩ ወንጀሎችና ሰላምን የማደፍረስ #እኩይ ተግባራት ላይ ለመሰማራት #የምታስቡ አካላት ከድርጊታችሁ እንድትቆጠቡ እያሳሰብኩ በማንኛውም የህዝብን ፀጥታ #በሚያደፈርሱና ህዝብን ከህዝብ #በሚያጋጩ ህገወጥ ተግባራት ላይ ተሰማርቶ የተገኘ እንዲሁም ለእንደዚህ አይነት ህገወጥ ተግባራት በምንም መልኩ ትብብር ያደረገ አካል ላይ ህግን ተከትሎ አስፈላጊውን #እርምጃ ለመውሰድ መንግስት #ቁርጠኛ እንደሆነ በጥብቅ ለማሳወቅ እወዳለሁ፡፡"

◾️◾️ጠ/ሚ ዶክተር አብይ አህመድ◾️◾️

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ከሀዋሳ⬆️

"በሀዋሳ ከተማ አረብ ሰፈር(ፈለቀች) በህዝብ ጥቆማ በፌደራል ፖሊስ እና ደቡብ ፖሊስ ትብብር ቁጥሩን ያላወቅነው ህገወጥ መሳሪያ አልያም ደግሞ የህገ ወጥ ኮንትሮባንድ እቃዎች ተይዘዋል። የበለጠ ለማጣራት ጥረት እያደረግን እንገኛለን። የደረስንበትን እናሳውቅሀለን።"

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ከአርባ ምንጭ⬇️

"ጤና ይስጥልኝ ፀግሽ A. K ነኝ ከአርባ ምንጭ አስካሁን የክረምት በጎ ፍቃድ አልጀመርንም ለምን እንዳልተጀመረ ለመጠየቅ ከተማ አስተዳደር ብንሄድም ከከተማዋ ከንቲባ በተላለፈ ትዛዝ የቁም ከመባሉ በስተቀር ምናቀው ምንም ነገር የለም ነው ሚሉን የከተማውን ከንቲባን ለማናገር በተደጋጋሚ ወደ ከተማዋ ማዘጋጃ ቤት ብንሄድም በስብሰባ ላይ ናቸዉ እያሉ ለሁለት ሳምንት ከማመላለስ በስተቀር ትክክለኛ ምላሽ ሚሰጠን አካል አላገኘንም ከተማዋ በምትገኝበት ጋሞ ጎፋ ዛን የሚገኙ ወረዳዎች ስራው እየተሰራ በዛኑ ዋና ከተማ የማይሰራበት ምክኒያት ግልፅ አልሆነልንም ወጣቱ ባለዉ አቅም ከተማዋን ለማገልገል ዝግጁ ቢሆንም የሚያሰራው አካል ባለማግኘቱ በጣም ነው ያዘንነው እኛ ከተማዋን ና ህብረተሰቡን በማገልገል ከምናገኘው እርካታ ባሻገር ክቡር ጠቅላይ ሚኒስተራችን ዶ/ር አብይ አሕመድ እንደተናገሩት ከአገልግሎት በሁዋላ የሚሰጠን የምስክር ወረቀት ስራ በምንቀጠር ወቅት እንደ ስራልምድ እንደሚቆጠረ ሰምተናል። ይህን የበጎ አድራጎት ስራ መስራት ካልቻልን ወደ ስራ ፍለጋ በምንሰማራበት ወቅት እኛ የአርባምንጭ ከተማ ወጣቶች ከሌላው የኢትዮጵያ ወጣቶች ቀርቶ ከዛኑ ወጣቶች ጋር መፎካከር አያስችለንም ይህንን ጉዳይ የሚመለከተው አካል አይቶ መፍትሔ እንድሰጠን እንጠይቃለን አመሰግናለሁ።"

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update አዲስ አበባ⬆️

በህብረተሰቡ ሲነሳ የነበረውን የአቅርቦት ችግር ለመፍታት እየሰራ መሆኑን የአዲስ አበባ ጤና ቢሮ አስታወቀ። ቢሮው በ49 ሚሊዮን ብር የተገዙ 47 ዘመናዊ አምቡላንሶችን ለጤና ጣቢያዎችና ለሆስፒታሎች የማከፋፈል ሥነ ሥርዓት እያካሄደ ይገኛል። በሥነሥርዓቱ የተለያዩ የከፍተኛ ተቁዋማት አመራሮች መልዕክት አስተላልፈዋል።

©የአዲስ አበባ ኮሚኒኬሽን
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update አግ 7⬇️

የ“አርበኞች ግንቦት 7 ንቅናቄ” ሊቀመንበር ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ፤ 100 ያህል አመራሮችና አባላትን ይዘው በመጪው ሳምንት ወደ ሃገር ቤት እንደሚገቡ የታወቀ ሲሆን ንቅናቄው በሃገር ውስጥ በአዲስ አደረጃጀትና ቅርፅ እንደሚዋቀር ተገልጿል፡፡

ላለፉት 10 ዓመታት ያህል የትጥቅ እንቅስቃሴን ጨምሮ ዋና መቀመጫውን ኤርትራ በማድረግ ሁለገብ ትግል ሲያከናውን የቆየው “አርበኞች ግንቦት 7”፤ በቅርቡ በሃገር ውስጥ በተፈጠረው ምቹ ሁኔታና መንግሥት ባደረገው ጥሪ መሰረት፣ ወደ ሀገር ቤት ተመልሶ፣ ፖለቲካዊ እንቅስቃሴ ለማድረግ መወሰኑ ይታወቃል፡፡

የንቅናቄው ሊቀ መንበርና ከፍተኛ አመራሮች በመጀመሪያው ዙር ከሰሞኑ ወደ ሃገር ቤት እንደሚመለሱ አቀባበል ለማድረግ የተዋቀረው ኮሚቴ የገለፀ ሲሆን በቀጣይም በኤርትራ ያሉ የሰራዊት አባላትና ሌሎች አመራሮች በተመሳሳይ ወደ ሃገር ውስጥ የሚመለሱበት ሁኔታ ይመቻቻል ብሏል፡፡

አመራሮቹ ወደ ሃገር ቤት በሚመጡበት ወቅትም ደጋፊዎቻቸው ከቦሌ አውሮፕላን ማረፊያ ጀምሮ ደማቅ አቀባበል እንደሚያደርጉላቸው የጠቆመው ኮሚቴው፤ ወደፊት አመራሮቹ ከህዝቡ ጋር በሰፊው የሚገናኙባቸው መድረኮች ይፋ ይደረጋሉ ብሏል፡፡

በሀገር ውስጥ በህቡዕ፣ በውጪ ሃገራት፣ በይፋ ሁለገብ የትግል እንቅስቃሴ ሲያደርግ ቆይቷል የተባለው “አርበኞች ግንቦት 7” በቀጣይ ራሱን ከንቅናቄ ወደ ፖለቲካ ፓርቲነት ቀይሮና በህጋዊነት ተመዝግቦ በዜግነት ላይ የተመሰረተ የፖለቲካ ስልት በመከተል ለምርጫ ውድድር እንደሚቀርብ ተገልጿል፡፡

ከሊቀመንበሩ ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ ጋር ከሚመለሱት አመራሮች መካከል አቶ አንዳርጋቸው ፅጌ፣ ዶ/ር ታደሰ ብሩ፣ አቶ ኤፍሬም ማዴቦ፣ ዶ/ር አዚዝ መሐመድ እና አቶ ነአምን ዘለቀ ይገኙበታል፡፡

በሀገሪቱ የጠቅላይ ሚኒስትር ለውጥ ከተደረገ በኋላ ከተወሰዱ የፖለቲካ ማሻሻያዎች አንዱ በሽብርተኝነት የተፈረጁ ድርጅቶችን ፍረጃ በማንሳት ወደ ሃገር ውስጥ እንዲገቡ የተደረገው ጥሪ ሲሆን በዚህ መሰረት እስካሁን ከ10 ያላነሱ ተፅዕኖ ፈጣሪ የፖለቲካ ድርጅቶች ወደ ሃገር ውስጥ ተመልሰዋል፤ 25 ያህሉም ለመመለስ በዝግጅት ላይ መሆናቸውን አስታውቀዋል፡፡

ወደ ሃገር ውስጥ ከተመለሱት መካከል የአፋር ብሔራዊ ንቅናቄ፣ የትግራይ ዲሞክራሲያዊ ትብብር፣ የትግራይ ህዝብ
ዲሞክራሲያዊ ንቅናቄ፣ የአማራ ህዝብ ዲሞክራሲያዊ ንቅናቄ፣ የኦሮሞ ነፃነት ግንባር (ኦነግ)፣ የኦሮሞ አቦ ነፃነት ግንባር፣ የኦሮሞ ነፃነት ግንባር ህብረት፣ የኦሮሞ ዲሞክራሲዊ ግንባር (ኦዴግ) እንዲሁም የኦጋኤን ብሔራዊ ነፃነት ግንባር (ኦብነግ) ይገኙበታል፡፡

ምንጭ፦ አዲስ አድማስ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update እየሩሳሌም ሆቴል⬆️

የአርበኞች ግንቦት 7 አባላት እና ደጋፊዎች በአዲስ አበባ ከተማ እየሩስሌም ሆቴል በዛሬው ዕለት ተወያይተዋል።

ተጨማሪ መረጃ እየተላከ ይገኛል እንደደረሰኝ አቀርባለሁ!

ፎቶ፦ ቢንያም
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ቴዲ አፍሮ⬇️

የድምፃዊ ቴዲ አፍሮ የአዲስ አመት ዋዜማ ኮንሰርት #መሰረዙ ተሰምቷል። ኢትዮፒካሊንክ የተባለው የራድዮ ዝግጅት ከአዘጋጆቹ የቅርብ ሰዎች ሰምቻለሁ ብሎ ይፋ ባደረገው መረጃ የቴዲ አፍሮ የሚሊንየም አዳራሽ ኮንሰርት በዋዜማው አይደረግም። ኮንሰርቱ የማይደረግበት ምክንያት በግልፅ አልታወቀም።

*በመስከረም አጋማሽ የቴዲ ኮንሰርት በሚሊኒየም አዳራሽ እንደሚካሄድ ከአዘጋጆቹ ተሰምቷል።
@tsegabwolde @tikvahethiopia