TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.3K photos
1.51K videos
212 files
4.11K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#update አዲስ አበባ⬆️

በዛሬው ዕለት በሺዎች የሚቆጠሩ ቄሮና ቀሬዎች የተሳተፉበት ስብሰባ በቦሌ ክፍለከተማ ፅ/ቤት አዳራሽ ውስጥ ተካሂዷል። በስብሰባውም በርካታ ጉዳዮች ተነተዋል።

ፎቶ፦ OMN
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update አሳዛኝ ዜና⬆️

በምንሼ ፊልም እንዲሁም በሌሎች በርካታ ፊልሞች ላይ እና በሬድዮ እና በቴሌቪዥን ተከታታይ ድራማዎች ላይ በመስራት የምትታወቀው አርቲስት መስከረም ወንድማገኝ በ28 ዓመቷ ከዚህ አለም በሞት ተለይታለች። ስርዓተ ቀብሯ ነገ ነሀሴ 14 በገርጂ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን በ8 ሰዓት ይፈፀማል።

©ጋዜጠኛ ጌጡ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የደብረ ታቦር በዓል⬇️

"ሰሎሞን ነኝ! ዛሬ የደብረ ታቦርን በዓል አዳማ(ናዝሬት) ከተማ በሚገኘው ምስራቀ ፀሐይ ደብረ ታቦር ቅዱስ እግዚአብሔር አብ ቤተ ክርስቲያን እጅግ በደመቀ ሁኔታ ነበር ያሳለፍነው።

በክብረ በዓሉ ላይ የሀገረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ የሆኑት ብፁዕ አቡነ ጎርጎርዮስ ተገኝተው እጅግ ጠቃሚና ወቅታዊ የሆነ መልእክት እጅግ ልብን በሚነካ ሁኔታ ለህዝቡ አስተላልፈዋል።

ብፁዕነታቸው ካነሷቸው ነጥቦች መካከል፦

- በሶማሌ ክልል አብያተ ክርስቲያናት ቢቃጠሉም, አንዳንዶች የተሰዉ ቢሆንም ብዙዎች ለስደት እና ለመሰዋት የበቁ መሆኑ ይታወቃል። ነገር ግን በቀልን በበቀል አንመልስም; በቀል የእግዚአብሔር ስለሆነ እኛ ሁሉንም እንወዳለን።

- በየአካባቢው ብዙ ስርዓት አልበኞች አሉ እነሱን ስርዓት ማስያዝ የሁሉም ሰው ሀላፊነት ነው, ቤተሰብ ልጆቹን መቆጣጠር አለበት, ስለልጆቹ አያገባኝም የሚል ቤተሰብ መኖር የለበትም።

- እኛ የሀይማኖት አባቶች የጥሉን ግድግዳ አፍርሰን አንድ ሆነናልና ሁላችሁም ይህንን የእኛን ፈለግ በመከተል አንድ ሁኑ።

- አንድነትና መቻቻል ድሮም ቢሆን ቀድሞ ከአባቶቻችን የወሰድነው የኖረ ትውፊት ነው; አሁን አዲስ ነገር አይደለም የምናደርገው። እሱን ነው የምንተገብረው።

- ለሰላም ዋጋ ከፍለን ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ አቡነ መርቆርዮስ ለሀገራቸው በቅተዋል; በዚህም ቤተክርስቲያን ደስታዋ እጥፍ ድርብ ነውና እንኳን ደስ አላችሁ።

- ጠቅላይ ሚኒስትሩ (ዶ/ር አቢይ አህመድ) "ፍቅር" እያሉ ሲናገሩ መጽሐፍ ቅዱስ ነው የተናገሩት። ልንሰማቸው ሀሳባቸውን ልንከተል ይገባል።

- እንደመር እያሉ ባለበት በዚህ ወቅት የመቀነስ ሀሳብ ይዘው የተነሱ አሉ። እነዚህ ፍፁም ከስነምግባር ውጭ የሆኑ ስርዓት አልበኞችን አብረን "እረፉ) ልንላቸው ይገባል።

- ክርስቲያን ሁል ጊዜ ሰዎችን ሳይለይ በፍጹም ልቡ ሁሉንም የሚወድ መሆን አለበት; እርስ በርሳችን እንዋደድ። እና የመሳሰሉትን መልእክቶች በማስተላለፍና ቃለ ምዕዳን በመስጠት የዕለቱ ክብረ በዓል በሰላም ተጠናቋል።"

©ሰለሞን
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ኤርትራዊ አርቲስት ካሕሳይ በርሀ የአሸንዳንና አዲስ አመት በዓልን ምክንያት በማድረግ የሁለቱም ህዝቦች ግኑኝነት እንዲጠናከር ዛሬ መቐለ ገብቷዋል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
በድጋሚ...#ጥብቅ ማሳሰቢያ⬇️

"...ከምንም በላይ የግልና የቡድን ጥቅሞቻችሁን #ሰላማዊ በሆነ መንገድ ማስጠበቅ እየቻላችሁ በተለያዩ ወንጀሎችና ሰላምን የማደፍረስ #እኩይ ተግባራት ላይ ለመሰማራት #የምታስቡ አካላት ከድርጊታችሁ እንድትቆጠቡ እያሳሰብኩ በማንኛውም የህዝብን ፀጥታ #በሚያደፈርሱና ህዝብን ከህዝብ #በሚያጋጩ ህገወጥ ተግባራት ላይ ተሰማርቶ የተገኘ እንዲሁም ለእንደዚህ አይነት ህገወጥ ተግባራት በምንም መልኩ ትብብር ያደረገ አካል ላይ ህግን ተከትሎ አስፈላጊውን #እርምጃ ለመውሰድ መንግስት #ቁርጠኛ እንደሆነ በጥብቅ ለማሳወቅ እወዳለሁ፡፡"

◾️◾️ጠ/ሚ ዶክተር አብይ አህመድ◾️◾️

@tsegabwolde @tikvahethiopia
አፋልጉኝ⬆️ቴዎድሮስ አለነ ብዙነህ የእናት ስም መረሳ የትውልድ ቦታ ሁመራ ሢሆን አሁን ያለበት ቦታ አክሱም ነው ተብሎ ይታሠባል ያለበትን የሚያቅ 0939978326 በዚ ስልክ ይደውልልኝ ፈላጊ ወንድሙ እና አባቱ።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
Audio
"አብረን ከፍ እንበል"

ከዝቅታው እንነጠል
ከሀኬቱ ከቶማታው እንገለል
ከክፋቱ ካሉባልታው እንከለል
አብረን ሆነን አብረን ከፍ እንበል
ከመቀናናት
ከመቆራቆስ
ከመተናናቅ
እንጠንቀቅ!
ከመጠላላት
ከመኮናነን
ከመጠቋቆም
እንቁም!
ከመዛዛት
ከመካሰስ
ከመጠበቅ
እንራቅ!
ከስሜታዊነት
ከጭፍንነት
ጥራዝ ከመንጠቅ
እንወቅ!
ከመበታተን
ከመለያየት
ከመገንጠል
እንነጠል!
አንድ ሆነን
አንድ እንሁን
ሁላችን የኢትዮጵያ ልጆች
የታላቅ አካል ብልቶች
ልዩ የሆንን ህብሮች
አንዳችን ለአንዱ ህይወቶች
የማንዘረዝ እውነቶች
የማንደበዝዝ ውበቶች
አንድ አካል ስንሆን ብዙዎች
ብዙዎች ስንባል አሀዶች
ካነሰው ሀሳብ እንነጠል
ከወረት ግንድ እንገንጠል
በፍቅር ላይ እንጠልጠል
በአብሮነት ካዝማ እንቸከል
እንደ ሰንደቅ እንተከል
ኑ! ከፍ ብለን አብረን ከፍ እንበል
ከዝቅታው እንነጠል
ከሀኬቱ ከቶማታው እንገለል
ከክፋቱ ከአሉባልታው እንከለል
በፍቅር ሆነን አብረን ከፍ እንበል
ከመናናቅ
ከመበላለጥ
ተመተናነስ
እንፈወስ!
ከመነጣጠቅ
ከመበላላት
ከመዘራረፍ
እንግዘፍ!
ከመከዳዳት
ከመዛዛት
ከመገዳደል
እንጉደል
ከመደባባት
ጥላ ከመውጋት
ከመጠራጠር
እንጠር!
ካለመከበር
ካለመታወቅ
ካለመታመን
እንዳን!
ከማደግደግ
እንደግ
ከመዘራጠጥ
እንለወጥ
ከመልመጥመጥ
እንብለጥ
ከማስመሰል
እንብሰል
ከመዋሸት
እንሟገት
ከማማረር
እንምረር
ሁላችን የኢትዮጵያ ልጆች
የታላቅ ሰውነት ብልቶች
የሺ ዘመናት እውነቶች
በአንድ አካል ያለን ህዋሶች
የአንደኛው ህመም ስሜቶች
እንዳፍንጫ እንደ ዓይን ቅርቦች
ለሌላው ስቃይ አልቃሾች
እንደ ምላስ እንደ ጥርስ ፍቅረኞች
የልስላሴና የጥንካሬ ውህዶች
ከልስላሴው ጣእምን
ከጥንካሬው ሀይልን
በመተጋገዝ ሰጭዎች
በአንድ አፍ ለዘላለሙ
እሰከ መቃብር ነዋሪዎች
ሁላቸችን የኢትዮጵያ ልጆች
ልዩ የሆንን ህብሮች
አንዳችን ለሌላው ህይወትች
የማንሰረዝ እውነቶች
የማንደበዝዝ ውበቶች
አንድ አካል ስንሆን ብዙዎች
ብዙዎች ስንባል አሀዶች
ኑ! ከፅንፈኝነት እንነጠል
በሀይል ከማመን እንከለል
ከፀብ ርስት እንገለል
ከፍ ብለን አብረን ከፍ እንበል
ከዝቅታው ከሲኦሉ ከመቀመቅ በርባሮሱ
ሀከጂኒ ኤላው ከገደሉ ከገሀናም ከእጦረጦሱ
ከትውልድ በካይ ጦሱ
ከቂም ከበቀል ጉርሱ
ከመጠፋፋት ሱሱ
ከመጎደል ብቻ ምሱ
ሀገር ከሚያወድም መንፈሱ
ኑ በፅናት ሆነን ከፍ እንበል
ከግለኝነት እንገንጠል
በፍቅር ላይ እንጠልጠል
ከፍ ብለን አብረን ከፍ እንበል
በመሞላላት
በመተጋገዝ
በመደጋገፍ
እንረፍ
በመከባበር
በመተሳሰብ
በመመካከር
እንክበር!
በመወያየት
በመነጋገር
በመደማመጥ
እንብለጥ!
ከመካረር
እንማከር
ብረት ከማንሳት
አንሳሳት
ከመሰናዘር
እንነጋገር
ከመቆራቆዝ
እንፈወስ
ዘር ከመቁጠር
እንጠር
ጎሳን ከማሰብ
እንሰብሰብ
ነገን ከመርሳት
አንሳት
ኑ የኢትዮጵያ ልጆች
አንዳችን ለአንዳችን ህይወቶች!
ኑ!

#አበባው_መላኩ

#ሼር
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የድምፃዊ ቴዎድሮስ ካሳሁን የአዲስ አመት ዋዜማ ኮንሰርት ለሌላ ጊዜ የተሸጋገረው በዕለቱ መንግስት አዳራሹን ለዝግጅት በመፈለጉ ነው። የኢትዮጵያ መንግስት የቴዎድሮስን ኮንሰርት አልሰረዘም አዘጋጆቹ በትህትና ተጠይቀው ነው ለቀጣይ ግዜ የተሸጋገረው።

#ብዙ ሰዎች በማህበራዊ ሚዲያ በመንግስት ላይ እንዲሁም የአመራሮችን ስም በመጥቀስ ዘለፋ እና የስም ማጥፋት ላይ ስላሉ ጥንቃቄ ይደረግ።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ጅግጅጋ ዩኒቨርሲቲ⬆️

የጅግጅጋ ዩኒቨርሲቲ በክልሉ በተፈጠረዉ የፀጥታ መደፍረስ ለተጎዱ የጅግጅጋ ከተማ ነዋሪዎች የመኝታ፣ ፍራሽና የታሸጉ ምግቦች እርዳታ ሰጥቷል፡፡ የዩኒቨርሲቲዉ አመራር ይህንን የወሰነዉ ነዋሪዎቹ በከፍተኛ ሁኔታ መጎዳታቸዉን ከግንዛቤ በማስገባት ነዉ፡፡ የዩኒቨርሲቲዉ ፕሬዝዳንት ዶ/ር #አብዱላዚዝ_ኢብራሂም "ህብረተሰቡ መልሶ እንዲቋቋምና ከተማዋ ወደ ቀደመ ሰላሟ እንድትመለስ የሚቻለንን ሁሉ ከማድረግ ወደኋላ አንልም" ብለዋል።

©ጅግጅጋ ዩኒቨርሲቲ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#Update ከስድስት ወራት በኋላ የሁሉም የስኳር ፕሮጀክቶች ግንባታ እንደሚጠናቀቅ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐብይ አህመድ ተናግረዋል። ግንባታቸው በተለያዩ ምክንያቶች ተጓቶ የነበሩ የስኳር ፕሮጀክቶች አሁን ላይ የማጠናቀቂያ ስራ እየተሰራ መሆኑ ነው የተገልፀው፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ይህንን ያሉት በባህርዳር ከተማ ከብአዴን አመራሮች ጋር ባደረጉት ምክክር ላይ ነው፡፡

©አብመድ
@tsegabwolde @tikvahethiopia