THIQAH
13.3K subscribers
2.61K photos
29 videos
1 file
23 links
ይህ ቲቃህ (ታማኝ) ኢትዮጵያ በቲክቫህ ኢትዮጵያ ሥር የሚተዳደር የኢትዮጵያን ጨምሮ ወቅታዊ ዓለም አቀፋዊ መረጃዎች የሚቀርቡበት ገጽ ነው።
Download Telegram
አሜሪካ ኢራን ለምታደርሰው ጥቃት መዘጋጀቷን አስታወቀች፡፡

አሜሪካ ኢራን ከአጋሮቿ ጋር ተባብራ በእስራዔል ላይ ታደርሰዋለች ተብሎ ለሚጠበቀው ጥቃት የአጸፋ ምላሽ ለመስጠት ዝግጁ መሆኗን አስታውቃለች፡፡

የብሔራዊ ደህንነት ቃል አቀባይ ጆን ኬርቢ፣ በጉዳዩ ላይ በሰጡት ሀሳብ እስራዔል የአሜሪካን ሙሉ ድጋፍ ታገኛለች ሲሉ ተደምጠዋል፡፡

ኢራን፣ የሃማስ መሪ እስማዔል ሀኒዬህን ግድያ ተከትሎ በእስራዔል ላይ እርምጃ እንደምትወስድ አስታውቃ ነበር፡፡ #trt #associatedpress

@thiqaheth
👍39😡12😱4😁32🔥2