Crohn's & Colitis Ethiopia
648 subscribers
52 photos
1 video
7 files
44 links
Crohn's & Colitis Ethiopia aims to serve as a hub for patients and families with IBD to learn, share and support eachother. Disclaimer: all information is for educational purposes only.
Questions? Talk to us at @IBDETHIOPIA
Download Telegram
የክሮንስ ወይም የአልሰሬቲቭ ኮላይተስ ህመም ክትትል ላይ ኖት?

ከሆኑ በዚህ አጭር ቃለመጠይቅ የክሮንስ & ኮላይተስ ኢትዮጲያ ማህበረሰባችን ከግል ወይም ከመንግስት ሀኪም ቤቶች የትኛው ላይ በብዛት እንደሚከታተሉ ማወቅ እንሻለን። እርሶ የሚከታተሉት የት እንደሆነ እዚህ ላይ ባለው ምርጫ ያሳውቁን። እናመሰግናለን!
Final Results
29%
Public Hospitals የመንግስት የህክምና ማዕከላት
74%
Private Hospitals/Clinics የግል የህክምና ማዕከላት
Forwarded from TIKVAH-MAGAZINE
#ጤናረቡዕ #እርድ

ክፍል-2 ( የመጀመሪያውን ክፍል ማንበብ ለምትፈልጉ ከላይ ተያይዟል)

ተጨማሪ የእርድ ጠቀሜታዎች

- እርድ በውስጡ የፀረ-ብግነት ባህሪ'ን ስላተላበሰ የተለያዩ ህመሞችን ለማስታገስ ይረዳል።

- በሰውነታችን ያሉ መርዛማ ንጥረ ነገሮች በጉበታችን ውስጥ በማለፍ ይመክናሉ፤ እርድ ይህንን መርዛማነትን ከሰውነታችን የማስወገድ ሥራን እጅጉን ያግዛል

- እርድን በቀን ሁለት ጊዜ መጠቀም በደማችን ውስጥ የሚገኘውን የኮሌስትሮል መጠንን ይቀንሳል።

- በእርድ ውስጥ የሚገኘው Curcumin የተሰኘው ንጥረ ነገር የደም ስሮቻችንን የውስጠኛውን ግድግዳ የሚሸፍነውን የመጀመሪያውን ንብር በማገዝ፤ የሰውነት ግፊትን እንዲሁም የደም መርጋትን ይከላከላል።

ለምን እርድ ውስጥ ቁንዶ በርበሬ እንጨምራለን?

ጥናቶች እንደሚያሳዩት ፣ በቁንዶ በርበሬ ውስጥ የሚገኘውን Piperine የተሰኘ ንጥረ ነገር እርድ ውስጥ ከሚገኘው Curcumin ጋር እብሮ መጠቀም የCurcumin'ን ወደ ሰውነታችን የመሰረፅ እድሉን በ2000% ያህል ያሳድገዋል።

እርድ ለማን አይመከርም?

፨ የጨጓራ አሲድ የሚቀንሱ መድሐኒት በምንወስድበት ጊዜ።
፨ የስኳር ህመም መድሐኒት በሚወሰድበት ጊዜ።
፨ የሀሞት ጠጠር ላለባቸው ሰዎች ላይ።
፨ የደም ማቅጠኛ መድሐኒትን የሚጠቀሙ ሰዎች።

ተጨማሪ ጠቃሚ መረጃዎችን በተከታዩ ሊንክ በቀላሉ ማግኘት ይችላሉ https://telegra.ph/Turmeric-Continued-07-26

በቲክቫህ ማጋዚን ላይ ብቻ!

@tikvahethmagazine @ibdeth
Forwarded from TIKVAH-MAGAZINE
#እንግዳችን

በቀጣይ ሳምንት የምግብና የአመጋገብ ስርዓት ባለሙያ በቀጥታ ስርጭት ይዘን የምንቀርብ ሲሆን ያሎትን ጥያቄዎች በቀጥታ ስርጭቱ ላይ ወይንም በዚህ ሳምንት በግል በ @IBDETHIOPIA ማስተላለፍ ይችላሉ።

እንግዳችንን ለማወቅ የተያያዘውን ምስል ይመልከቱ!

@tikvahethmagazine @ibdeth
የአካል ብቃት እንቅስቃሴና የአንጀት ቁስለት #quickfacts #ibd_sport

በዚህ አጋጣሚ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ልዑካን ቡድን በ18ኛው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና በአሜሪካ ኦሪገን አስደናቂ የውድድር ጊዜ አሳልፎ ከፍተኛ ድል አስመዝግቧል። በዚህም ድርጅታችን ክሮንስና ኮላይተስ ኢትዮጵያ የተሰማውን ኩራት ይገልፃል!

ከዚህ በታች ስለ የአካል ብቃትና የአንጀት ቁስለት መረጃን ይዘንላቹ መጥተናል። ሊንኩን በመጫን ያንብቡ!

https://telegra.ph/IBD--Sports-07-30
Forwarded from TIKVAH-MAGAZINE
#ቃለመጠይቅ #ጤናረቡዕ

ከስነ-ምግብ የህክምና ባለሙያ ጋር

በጤና ረቡዑ ‹‹ጤናማ አመጋገብ ፣ ጤናማ የሆድ እቃ›› በሚል ርዕስ ላለፉት አምስት ሳምንታት መረጃን ስናቀብላቹ ነበር፡፡

ነገ ዕሮብ ከምሽቱ አንድ ሰዓት ላይ ከስነ-ምግብ የህክምና ባለሙያ ትርሲት ደምሰው ጋር በቀጥታ ስርጭት ውይይት እናደርጋለን፡፡

ከምንዳስሳቸው ጉዳዮች በከፊል ...

- አጠቃላይ የምግብ እቅድ ግምገማ ሂደትና ጠቀሜታ

- የአመጋገብ ለውጥ በማድረግ የሆድ እቃን ጤና እንዴት መጠበቅ ይቻላል?

- የባለፉት ሳምንታት ርዕሶች ጠቅለል ያለ ማብራሪያ

በዚህ ርዕሰ ጉዳይ ላይ እንዲብራራሎት የሚፈልጉት ጥያቄ አሎት? በ @IBDETHIOPIA መልዕክቶን ይላኩልን፡፡ በቀጥታ ስርጭቱ ላይ ተገቢውን ማብራሪያ እና ምላሽ በባለሙያ እንዲሰጦ እናደርጋለን፡፡

@tikvahethmagazine @ibdeth
Forwarded from TIKVAH-MAGAZINE
ማስታወሻ!

ዛሬ አንድ ሰዐት ላይ ስለ አመጋገብ እና የአንጀት ጤና ትርሲት ደምሰው ዳይቲሽያን ይዘን የምን ቅርብ ሲሆን ጥያቄዎቻችሁን መልስ ለመመለስ እና ማብራሪያ ለመስጠት ተዘጋጅተናል።

በቀጥታ ስርጭት ላይ ለመጠየቅ እንዲሁም ስለአመጋገብ እና ጤናችን ላይ ስላለው ሚና ተጨማሪ ግንዛቤ ለማግኘት አንድ ሰዐት ላይ ይጠብቁን!

እናመሰግናለን!

@tikvahethmagazine @ibdeth
ቃለመጠይቁ እንደጠቀምዎት እንዲሁም ጥያቄዎን እንደመለስን ተስፋ እናደርጋለን። አብራችሁን ለለነበራችሁ እንዲሁም እንግዳችንን ዳይተሺያን ትርሲት ደምሰውን ከልብ እናመሰግናለን!

የድምጽ ቅጂውን በመጪው እሁድ የምንለቅ ይሆናል።

በፕሮግራሙ ላይ ስለተጠቀሰው የምግብ ማስታወሻ መች ተመርቆ ለእናንተ እንደሚደርስ በቅርቡ የምንገልጽ ይሆናል።

ይከታተሉን!

መልካም ምሽት!
#ጤናረቡዕ

ዛሬ በጤና ረቡዕ የውይይት ገፃችን ላይ ስለ የአንጀት ቁስለት ህመምና የአመጋገብ ስርዓት እንድንወያይበት እንዲሁም ጥያቄዎቻችሁ በባለሙያዎች እንዲመለሱ የቀጥታ ስርጭት ፕሮግራም ይዘን መጥተናል።

እንደተለመደው ከምሽቱ አንድ ሰዓት ላይ የአንጀት ስፔሻሊስት የሆኑትን ዶ\ር ኃይለሚካኤል ደሳለኝ እንዲሁም የስነ ምግብ ህክምና ስፔሻሊስት የሆኑትን ዶ\ር ዘላለም ደበበን ይዘን ቀርበናል።

ስለባለሙያዎቹ በዝርዝር ከላይ በፎቶ አያይዘናል።

ከምሽቱ አንድ ሰዓት ላይ በቲክቫህ ማጋዚን ላይ ብቻ!

@tikvahethmagazine @ibdeth
ውድ ቤተሰቦቻችን
#ጤናረቡዕ ፕሮግራም ላይ ስለ አንጀት ቁስለት እና አመጋገብ ስርዐት ከ ዶ\ር ዘላለም ደበበ እንዲሁም ዶ\ር ሀይለሚካኤል ደሳለኝ ጋር የቀጥታ ስርጭት ቆይታ ነበረን።

የድምጽ ቅጂውን በዩትዩብ ገጻችን የለቀቅን ሲሆን ይህንን ማስፈንጠሪያ በመጫን መከታተል ይችላሉ።

እናመሰግናለን!

https://youtu.be/TXT4DFTlcoU
Forwarded from TIKVAH-MAGAZINE
#ጤናረቡዕ

ውድ የጤና ረቡዕ ተከታታዮቻችን በዚህኛው የጤና ረቡዕ የዝግጅት ምዕራፍ "ጤናማ የሆድ እቃ፣ ጤናማ አዕምሮ" በሚል ርዕስ ሳይንሳዊ መረጃዎችን ለተከታታይ ሳምንታት እናቀብላችኋለን፡፡

እንደሚታወቀው በአሁኑ የክረምት ወቅት በሀገራችን በተማሪዎችም ሆነ በሰራተኞች ዘንድ የተወሰነ የስራ መቀዛቀዝ የሚስተዋልበት ጊዜ እንደመሆኑ የአዕምሮ ጭንቀትና ድባቴ በርከት ያሉ ሰዎችን ያጠቃል፡፡ ይህ ደግሞ በተለያየ ስር የሰደደ ህመም ባጋጠማቸው ሰዎች ላይ በተወሰነ መልኩ ተባብሶ ይታያል፡፡

ለዚህም ለተከታታይ ሶስት ሳምንታት ስለ የአዕምሮ ጤናና የሆድ እቃ፣ እንደ የአንጀት ቁስለት ያሉ ስር የሰደዱ ህመሞችና የመድሃኒቶቻችው የጎንዮሽ ጉዳት በአዕምሮ ጤና ላይና የእነዚህ ስሜቶች ተግባሪያዊ ማሳያዎችና መፍትሄዎችን እንዳስሳለን፡፡

በአራተኛውና በመጨረሻው ሳምንትም ባለሞያ ጋብዘን በዚሁ ርዕስ ዙሪያ ከእናንተ የሚመጡልንን ጥያቄዎች በቀጥታ ስርጭት የምንመልስ ይሆናል።

በዚህ ሳምንትም፦

✔️ የአዕምሮ ጤናና የሆድ እቃ ጤና እንዴት ይገናኛሉ?

✔️ የሆድ እቃ ጠቃሚ ረቂቅ ተህዋሲያን ተፅዕኖ በአዕምሮ ጤና ላይ

✔️ ከአካባቢያዊ ሁናቴዎችና የአኗኗር ዘይቤ ተፅዕኖ በአዕምሮና በሆድ ዕቃ ጤና ላይ በሚሉት ርዕሶች ላይ ሳይንሳዊ ማብራሪያ ይዘን ቀርበናል፡፡

የበለጠ ለማንበብ ማስፈንጠሪያውን ይጫኑ https://telegra.ph/Healthy-Gut-Healthy-Mind-08-17

@tikvahethmagazine @ibdeth
እንኳን ለደብረ ታቦር (ቡሄ) በዓል አደረሳችሁ

ክሮንስ ና ኮላይተስ ኢትዮጵያ 🇪🇹
Crohn's and colitis Ethiopia 🇪🇹
Forwarded from TIKVAH-MAGAZINE
#ጤናረቡዕ ለህክምና ተማሪዎች!

የአንጀት ቁስለት ህክምና ተማሪ ስኮላር ፕሮግራም

ይህ የአንጀት ቁስለት ህክምና ተማሪ ስኮላር ፕሮግራም በአይነቱ ለየት ያለ ለህክምና ተማሪዎች የቀረበ ሲሆን፤ የውስጥ ደዌ እንዲሁም የአንጀት ጤና ስፔሻሊስት መሆን ለሚሹ ከአንደኛ እስከ አራተኛ አመት ህክምና ትምህርት ላይ ላሉ የተዘጋጀ ነው።

ይህ እድል በአለማችን ላይ ስላሉት ከአንጀት ቁስለት ህመም ህክምና ጋር የተያያዙ ጉድለቶች እንዲሁም ከዚህ ህመም ጋር ያሉ ወጣት እና ጎልማሳ ሰዎች ምን አይነት የህክምና ትኩረት ይፈልጋሉ የሚለውን ይዳስሳል።

መስፈርት

-ማንኛውም አመት ላይ ያለ የህክምና ተማሪ
-የአንጀት ጤና ስፔሻሊቲ የመማር ፍላጎት
-ከየትኛውም የአለማችን ክፍል

ፕሮግራም

- 90 በመቶ የወርሀዊ ውይይት ዝግጅት መሳተፍ
- በየወሩ ከሚደረገው ስብሰባ በኃላ ስለ ስብሰባው የሚጻፍ ጽሁፍ መሳተፍ\ማገዝ
- ከአንጀት ቁስለት ህመም ጋር የሚኖሩ ወጣቶች ጋር በቅርበት ስለሚያስፈልገው ልዩ ትኩረት መረዳት
- ከድርጅቱ የህክምና አማካሪ ቦርድ እና አመራር ጋር በቅርብ መገናኘት
- በአመት አንድ ጊዜ ለሚካሄደው የአንጀት ቁስለት ህመም ኮንፈረንስ በፈረንጆች አቆጣጠር 2023 አመተ ምህረት ላይ ወደ አሜሪካ የመጓዝ እድል (የጉዞ ድጋፍ እስከ 1000 የአሜሪካ ዶላር)

ስለፕሮግራሙ ዝርዝር ከላይ ተያይዟል።

ለማመልከት ይህንን ማስፈንጠሪያ ይጫኑ

https://docs.google.com/forms/d/e/1FAIpQLSfflOypTySxTtFYjoGKvbojfO2EV7-vKSMoyz2Kaf9OZv3srA/viewform

#ጤናረቡዕ ላይ ስትሳተፉ የነበራችሁ የህክምና ተማሪዎች @IBDETHIOPIA ላይ በመጻፍ የምስክር ደብዳቤ ማግኘት ትችላላችሁ።

@tikvahethmagazine @ibdeth
#quickfact

በዚህ ሳምንት ስለ አንጀት ቁስለት እና የወር አበባ ዑደት እንወያያለን። ከምንዳስሳቸው ነጥቦች ውስጥ:-

✔️የወር አበባ ምንድን ነው?
✔️የወር አበባ ዑደት እና የአንጀት ቁስለት ግንኙነት
✔️የወር አበባ የህመም ስሜት ለምን በአንጀት ቁስለት ህመም ታካሚ ሴቶች ላይ ሊብስ እንደሚችል

በቀጣይ ሳምንት ምን አይነት መፍትሄ እና አማራጮች እንዳሉት እንወያያለን።

ማስፈንጠሪያውን በመጫን በሰፊው ያንብቡ ።

https://telegra.ph/IBD--Menses-08-20
Forwarded from TIKVAH-MAGAZINE
#ጤናረቡዕ

የአመጋገብ ስርዓት እና የአይምሮ ጤና

[ በ @ibdeth የቀረበ ]

- አካላዊ ጤና እና የአመጋገብ ስርዓት ዘርፈ ብዙ ተዛምዶ አላቸው።

- ደካማ የአመጋገብ ሥርዓት ለወረደ ስሜት አንደኛው ምክንያት ሊሆን ይችላል፤ በሌላ ጎኑ ተገቢ የአመጋገብ ሥርዓት ጉልህ በሚባል ደረጃ የአዕምሮን ጤና ያሻሽላል።

- የአመጋገብ ስርዓታችን በሆድ እቃችን ውስጥ በሚገኙ ረቂቅ ተህዋሳት ላይ በሚያመጣው ተፅዕኖ የአዕምሮን ጤና ላይ በተላያየ መንገድ ተፅዕኖ እንደሚያሳድር የተለያዩ ጥናቶች አረጋግጠዋል።

- የዘወትር የማዕዳችን ሥርዓት፥ እንደ ትኩራት ማጣት እና በስሜት ግፊት ነገሮችን በማድረግ የሚገለጠውን Attention Deficit Hyperactivity Disorder/ADHD/ ያሉ የአዕምሮ ጤና ችግሮች ጋር ተያያዥነት አለው።

- ኦሜጋ-3 ፋቲ አሲድ በተላዩ ምግቦች ውስጥ የሚገኝ ንጥረ ነገር ሲሆን የተለያዩ የአዕምሮ ህመም ተጠቂዎች ላይ እራሱን ችሎ ወይም እንደ አባሪ መድኃኒት መጠቀም ስኬታማ ውጤትን አሳይቷል።

- የአመጋገብ ሥርዓታችን በተለያየ መንገድ የአዕምሮ ጤና ላይ ተፅዕኖ ያደርጋል። በአዕምሮ ምግቦች የበለጠጉ ምግቦችን መጠቀም ስኬታማ እና በእንፃራዊ መልኩ ደግሞ ቀላል በሆነ መንገድ የአይምሮ ጤናን ለማሻሻል እንዲሁም ከአይምሮ ህመም ለማገገም አይነተኛ መንገዶች ናቸው።

🔗 ተጨማሪ በ 👉 INSTANTVIEW ያንብቡ

@tikvahethmagazine @WriteforTikvahbot
Crohn's & Colitis Ethiopia
#quickfact በዚህ ሳምንት ስለ አንጀት ቁስለት እና የወር አበባ ዑደት እንወያያለን። ከምንዳስሳቸው ነጥቦች ውስጥ:- ✔️የወር አበባ ምንድን ነው? ✔️የወር አበባ ዑደት እና የአንጀት ቁስለት ግንኙነት ✔️የወር አበባ የህመም ስሜት ለምን በአንጀት ቁስለት ህመም ታካሚ ሴቶች ላይ ሊብስ እንደሚችል በቀጣይ ሳምንት ምን አይነት መፍትሄ እና አማራጮች እንዳሉት እንወያያለን። ማስፈንጠሪያውን በመጫን…
#quickfact

የወር አበባ ዑደትና የአንጀት ቁስለት               

ክፍል 2                  

ለማንበብ ማስፈንጠሪያውን ይጫኑ

https://telegra.ph/IBD--Menses-08-27
Our very own Dr. Armoniam Mulatu Teshome has graduated from medical school! He works in supporting our health awareness campaigns and is the mastermind behind most of our Amharic content. Happy graduation Dr!