Crohn's & Colitis Ethiopia
648 subscribers
52 photos
1 video
7 files
44 links
Crohn's & Colitis Ethiopia aims to serve as a hub for patients and families with IBD to learn, share and support eachother. Disclaimer: all information is for educational purposes only.
Questions? Talk to us at @IBDETHIOPIA
Download Telegram
Forwarded from TIKVAH-MAGAZINE
ጤናማ አንጀት፣ ጤናማ ኩላሊት ክፍል ፪

ኤሌክትሮላይቶች ምንድን ናቸው?

ኤሌክትሮላይት በሰውነታችን ፈሳሽ ውስጥ በተፈጥሮ የሚገኙ ኬሚካሎች ናቸው፡፡እነዚህም ክሎራይድ፣ ሶድየም እና ካልሺየምን ያካትታሉ፡፡

ኤሌክትሮላይቶች ለጤነኛ እና ለተመጣጠነ የሰውነት ተግባር አስፈላጊ ሲሆኑ በተመጣጠነ እና ለሰውነት በሚያስፈልገው ልክ መገኘት አለባቸው፡፡

ብዙ ሰዎች ለሰውነት አስፈላጊ የሆኑትን ኤሌክትሮላይቶች ከምግባቸው ውስጥ ያገኛሉ፤ሆኖም በሰውነት ውስጥ በሚካሄዱ አንዳንድ ሂደቶች ምክንያት በእነዚህ ኤሌክትሮላይቶች መጠን ላይ መዛባት ይከሰታል፡፡

መንስኤው ምንድን ነው?

የኤሌክትሮላይቶች አለመመጣጠን ከሚከሰትባቸው ምክንያቶች አንዱ ብዙ የሰውነት ፈሳሽን በአንድ ጊዜ ስናጣ ነው፡፡ ለምሳሌ ብዙ የሰውነት ላብ እና ማስመለስ ሲኖረን በሰውነታችን ውስጥ ያለ የኤሌክትሮላይቶች መጠን እንዲቀንስ ያደርጋል፡፡

በሰውነታችን ውስጥ ያሉ የኤሌክትሮላይቶች መጠን መዛባት ምልክቶች ምንድን ናቸው?

ከኤሌክትሮላይቶች መጠን መዛባት ምልክቶች ውስጥ የተወሰኑት፡-

· ቁርጠት

· የማዞር ስሜት

· ከመደበኛው የተለየ የልብ ምት

· ድካም

በአንጀት ቁስለት ህመም ምክንያት የሚከሰት የሰውነት ፈሳሽና ኤሌክትሮላይት መጠን መዛባትና የኩላሊት ህመም
በርከት ያሉ ጥናቶች እንደሚያሳዩት በአልሰሬቲቭ ኮላይተስና በክሮንስ ህመም ታካሚዎች ላይ የሚከሰት የኤሌክትሮላይቶች እጥረት አነስ ያለ ጉዳትን ከማስከተል ጀምሮ ለህይወት እስከሚያሰጋ ደረጃ ድረስ ሊደርስ እንደሚችል ነው፡፡ ይህም የሚሆንበት ምክንያት በተለይም በአንጀት ቁስለት ህመም ንቁ የህመሙ ደረጃ ላይ በአንጀት ግድግዳ ንጣፍ ቁስለት ምክንያት የሚከሰት የአንጀት መዋቅር ለውጥ የሰውነታችን ኤሌክትሮላይቶች በአስፈላጊው መጠን እንዳይመረቱና ወደ ሰውነታችንም እንዳይመጠጡ በማድረግ የኤሌክትሮላይቶችን መጠን መዛባት ያስከትላል፡፡

የኤሌክትሮላይቶች መጠን መዛባት እንዳይከሰት ምን ማድረግ እንችላለን?

1. ዉሃን መጠጣት ፡- ዉሃን መጠጣት ቀላሉና ወሳኙ በኤሌክትሮላይቶች መጠን መዛባት ምክንያት የሚከሰቱ ውስብስብ ችግሮች ከመከሰታቸው በፊት ልንከላከልበት የምንችለው መንገድ ነው፡፡

2. በኤሌክትሮላይት የበለፀጉ ምግቦችን መመገብ ፡- እንደ ካሮት፣አቮካዶ፣ብርቱካን፣ሙዝ፣እንጆሪና ሰላጣ ያሉ ምግቦችን መመገብ

በሰፊው ለማንበብ ከታች ያለውን ማስፈንጠሪያ ይጫኑ ⬇️⬇️

https://telegra.ph/Healthy-Gut-Healthy-Kidney-06-14

በቀጣይ ሳምንት የኩላሊት ስፔሻሊስት በቀጥታ ስርጭት ይዘን የምን ቅርብ ሲሆን ያሎትን ጥያቄዎች በቀጥታ ስርጭቱ ላይ ወይንም በግል በ @IBDETHIOPIA ማስተላለፍ ይችላሉ።

በቲክቫህ ማጋዚን ላይ ብቻ

Tikvah Magazine

Crohn’s & Colitis Ethiopia
Forwarded from TIKVAH-MAGAZINE
ቃለመጠይቅ ከኩላሊት ህክምና ባለሙያዎች ጋር

በጤና ረቡዑ ‹‹ጤናማ አንጀት፣ ጤናማ ኩላሊት›› በሚል ርዕስ ላለፉት ሶስት ሳምንታት መረጃን ስናቀብላቹ ነበር፡፡ በሚቀጥለው ሳምንት እሮብ ከምሽቱ አንድ ሰዓት ላይም፣ በኩላሊት ህክምና ባለሙያዎች በዶ/ር ሐመልማል ገበየሁና በዶ/ር እሴተ ጌታቸው የኩላሊታችንን ጤና እንዴት መጠበቅ እንደምንችልና የኩላሊታችን ጤና ከአንጀታችን ጤና ጋር በምን መልኩ እንደሚገናኝ በቀጥታ ስርጭት ውይይት እናደርጋለን፡፡

ከምንዳስሳቸው ጉዳዮች በከፊል...

✔️የኩላሊት ጤናዬን እንዴት መጠበቅ እችላለሁ?
✔️ምን አይነት ምርመራ ባደርግ የኩላሊቴን ጤና ሁኔታ ማወቅ እችላለሁ?
✔️አንጀት ጤና እና ኩላሊት ምን ያገናኛቸዋል?
✔️የአንጀት ህመም ስሜቶች እንደ ማስመለስ እና ማስቀመጥ ኩላሊት ላይ የሚያመጣው አደጋ


በዚህ ርዕሰ ጉዳይ ላይ እንዲብራራሎት የሚፈልጉት ጥያቄ አሎት? በ @IBDETHIOPIA መልዕክቶን ይላኩልን፡፡ በቀጥታ ስርጭቱ ላይ ተገቢውን ማብራሪያ እና ምላሽ በባለሙያዎች እንዲሰጦ እናደርጋለን፡፡

@tikvahethmagazine @ibdeth
Quick Facts: ESR & CRP

ለማንበብ ማስፈንጠሪያውን ይጫኑ
⬇️⬇️⬇️

https://telegra.ph/ESR--CRP-06-18

@ibdeth
Forwarded from TIKVAH-MAGAZINE
#ጤናረቡዕ

በዛሬው መርኃግብራችን ''ጤናማ አንጀት፣ ጤናማ ኩላሊት'' በሚል ርዕስ የኩላሊት ህክምና ባለሙያዎቹ ዶ/ር ሐመልማል ገበየሁና ዶ/ር እሴተ ጌታቸው በ #TikvahMagazine ማታ #1ሰዓት ላይ ማብራሪያ ይሰጣሉ።

ይጠብቁን!

#ጤናረቡዕ ክሮንስ እና ኮላይተስ ኢትዮጵያ ከቲክቫህ ኢትዮጵያ ጋር በመተባበር ስር ስለሰደዱ ህመሞች መረጃ የሚያቀርብበት ዝግጅት ነው።

@tikvahethmagazine @ibdeth
#quickfact ስለ እርድ በጥቂቱ

ይህንን ማስፈንጠሪያ በመጫን እርድን በመጠጥ መልክ የማዘጋጃ ሁለት አይነት መንገድን ያንብቡ።

https://telegra.ph/Turmeric-06-25

ከሚቀጥለው ረቡዕ ጀምሮ ለተከታታይ ሳምንታት ስለ ምግብ እና መጠጦች በሳይንሳዊ ጥናት የተደገፈ መረጃ ይዘን እንቀርባለን።
Crohn's & Colitis Ethiopia
Photo
የጤናረቡዕ የቀጥታ ስርጭት ቅጂ ዛሬ ከሰዐት 11 ሰዐት ላይ በYouTube ቻናላችን ይለቀቃል። ሲለቀቅ መልዕክት እንዲደርስዎ የYouTube ቻናላችንን ይቀላቀሉ!

https://youtube.com/channel/UCmgJ-F6CJzzaaOAj7ztTVFw

እናመሰግናለን!
ፍራፍሬ እና አትክልቶች ለጤናማ አመጋገብ ወሳኝ እንደሆኑ ሁል ግዜ ይነገራል። ለዚህም እንደ ምክንያት የሚጠቀሰው ፋይበርን፣ ቫይታሚኖችንና ሌሎች ጠቃሚ ንጥረ ነገሮችን በውስጣቸው ስለያዙ ነው።


ነገ በ #ጤናረቡዕ ላይ ስለ ጤናማ አመጋገብ እና ፍራፍሬ እና አትክልት ውስጥ ያለውን የጤና ጥቅም እንዳስሳለን።

@tikvahethmagazine @ibdeth
Forwarded from TIKVAH-MAGAZINE
#ጤናረቡዕ

አመጋገብና የሆድ እቃ ጤና ምግብ በምግብ ልመት ስርዓት ውስጥ ያለውን ሚና ለማወቅና ለመረዳት፤ የምግብ ልመት ስርዓት በራሱ ምን እንደሆነ መረዳትና ማወቅ እጅግ አስፈላጊ ነው፡፡

በዛሬው የ #ጤናረቡዕ ፕሮግራማችን ላይ የምግብ ልመት ስርዓት፣ጤናማ የሆድ እቃን ምንነትና ስለ ፍራፍሬ እና አትክልት ይዘት እንዲሁም ከጥቅሞቻቸው የተወሰኑትን አንስተን እናያለን።

በተጨማሪም ብዙ የተነገረለት polyphenol ምን እንደሆነ በጥቂቱ የምንዳስስ ሲሆን በቀጣይ ሳምንት የpolyphenol የምግብ ምንጮችንና የጤና ጥቅሞችን በዝርዝርና የምንገልፅ ይሆናል፡፡

በቀጣይ አራት ሳምንታት በሚኖረን የጤናማ አመጋገብ፣ ጤናማ አንጀት ርዕሰ ጉዳይና በምናነሳቸው ሃሳቦች ላይ ያሎትን ማንኛውም ጥያቄ በ @IBDETHIOPIA ያድርሱን።

በአምስተኛው ሳምንት ላይ ከስነ ምግብ ባለሙያ ጋር በሚኖረን ቃለመጠይቅ ከናንተ የሚነሳውን ጥያቄ እንመልሳለን። ይከታተሉን!

ማስፈንጠሪያውን በመጫን በሰፊው ያንብቡ! ⬇️⬇️
https://telegra.ph/Healthy-Diet-Healthy-Gut-06-27

@tikvahethmagazine @ibdeth
Forwarded from TIKVAH-MAGAZINE
#ጤናረቡዕ #ጤናማአመጋገብ

polyphenols በተለያዩ ምግቦች ውስጥ የሚገኙ ዘርፈ ብዙ ጥቅም ያላቸው ንጥረ ነገሮች ናቸው፡፡ ከነዚህ ጠቀሜታዎች ውስጥ፡-

✔️የሰውነትን ክብደት ማስተካከል

✔️በሰውነታችን ውስጥ ያለውን ግሉኮስ ( ስኳር ) የመፈጨትና ለሰውነት ጥቅም የማዋል ሂደት ማስተካከልና መቆጣጠር

✔️የሰውነት መቆጣትንና ቁስለትን መቀነስ፣

✔️እንዲሁም የልብ ህመም፣ የአጥንት መሳሳት ና ካንሰር ያሉ ስር የሰደዱ ህመሞችን ለመከላከል ትልቅ አስተዋፆ እንዳላቸው ይታወቃል።

polyphenolsን ከተለያዩ ከእፅዋት ከሚገኙ ምግቦች ውስጥ እናገኛቸዋለን፡፡ በ polyphenols የበለፀጉ ምግቦችን ዝርዝር ለማንበብ ማስፈንጠሪያውን ይጫኑ!
⬇️⬇️⬇️

https://telegra.ph/What-are-Polyphenols-07-05

በሚቀጥለው ሳምንት በሻይና በpolyphenols ዙሪያ ሰፊ ማብራሪያን ይዘን እንቀርባለን፡፡ ይከታተሉን!

@tikvahethmagazine @ibdeth
እንኳን ለዒድ አል-አድሐ ዐረፋ በዓል በሰላም አደረሰን!


ክሮንስ & ኮላይተስ ኢትዮጵያ
#ጤናረቡዕ

በሰፊው ሲጠየቅ ስለነበረው አረንጓዴ ሻይ ወይም Green Tea በዛሬው ጤና ረቡዕ ፕሮግራም ላይ የምንወያይ ይሆናል።

አረንጓዴ ሻይ ለአነጀት ጤና እና የአንጀት ቁስለት ጋር ያለውን ግንኙነት፣ በቀን ምን ይህል መጠጣት ይመከራል፣ አረንጓዴ ሻይ መጠጣት የሌለባቸው ሰዎች እና ማን ናቸው እና ሌሎችንም ጥያቄዎቻችሁን በሳይንስ የተደገፈ መረጃ የምናቀርብ ስለሚሆን ይከታተሉን!
Forwarded from TIKVAH-MAGAZINE
#ጤናረቡዕ #አረንጓዴሻይ

አረንጓዴ ሻይ በየሱቁ እና ሱፐር ማርኬት የሚገኝ የሻይ አይነት ሲሆን ሻይ ቅጠሉ በተለያየ መልኩ ታሽጎ ለተጠቃሚ ይቀርባል።

ይህ ሻይ በቻይና፣ ጃፓን የመሳሰሉት አገራት ላይ ለብዙ ሺህ አመታት ሲጠቀሙበት ኖረዋል። የዚህ ሻይ ጥቅም በብዙ ሳይንሳዊ ምርምር የተደገፈ ማስረጃ ሲኖር ለልብ፣ ለአንጀት ጤና እንዲሁም ኮሌስትሮል የመቀነስ ሀይሉ፣ ካንሰር የመከላከል እንዲሁም የአንጀት ቁስለት ላይ ያለውን ጠቀሜታ በዝርዝር ቀርቧል።

አረንጓዴ ሻይን በቀን ስንት ግዜ ልጠቀም፣ ለኔ ይሆናል ወይ እንዲሁም ሻዩን ከመውሰድ በእንክብል መልክ ተዘጋጅቶ የቀረበው የአረንጓዴ ሻይ ከ ሻይ ቅጠሉ የሚለየውን ነገር ከታች ያለውን ማስፈንጠሪያ በመጫን ማንበብ ይችላሉ።

የአረንጓዴ ሻይ ጣዕም ለማይወዱ እንዲሁም ለየት ባለ መልኩ መጠቀም ለሚሹ ከ ክሮንስ እና ኮላይተስ ግሩፕ የተወጣጣ ለየት ያሉ የሻይ፣ የጁስ የመሳሰሉትን አማራጮችን በቅዳሜ ለት @ibdeth ላይ ይዘን እንቀርባለን።

ተጨማሪ ለማንበብ https://telegra.ph/Green-Tea--Our-Gut-07-13

@tikvahethmagazine @ibdeth
#quickfact #አረንጓዴሻይ

አረንጓዴ ሻይ ስንጠጣ ከምንጠቀማቸው አማራጭ አሰራር መካከል የተወሰኑትን ዛሬ ወደናንተ ይዘን ቀርበናል።

እርሶ ከሚወዱት ቅመም ወይም ፍራፍሬ ጋር በመቀላቀል የአረንጓዴ ሻይን ጥቅም በተለያየ የአሰራር መንገድ ያግኙ።

የአረንጓዴ ሻይን ጣዕም ለማይወደው ወይም አልፎ አልፎ ለውጥ ባለ መልኩ ለመጠቀም አማራጮች ሲኖሩ ስኳር መጨመር ግን አይመከርም። ከስኳር ይልቅ ማር መጠቀም ይመከራል ሻዩ ለጤና ያለውንም ጥቅም ከፍ ያደርገዋል።

ስለአማራጮቹ የሚገልጹ ምስሎቹን ለማየት ይህንን ማስፈንጠሪያ ይጫኑ ⬇️⬇️⬇️

https://telegra.ph/Green-Tea-Variations-07-15
Forwarded from TIKVAH-MAGAZINE
#ጤናረቡዕ #እርድ

ሰሞኑን በጤና ረቡዕ ፕሮግራም ላይ ስለተለያዩ የሰውነት መቆጣትን የሚከላከሉ በማዕድ ቤት ውስጥ ስለሚገኙ ቅመማት እና ሻይ ስንወያይ ቆይተናል።

ይህንን የpolyphenol ተከታታይ ፕሮግራም የምንቋጨው በእርድ እና የእርድ ጥቅሞች ሲሆን ለተከታታይ ሁለት ሳምንታት ስለ እርድ እና የተለያዩ ህመሞች ጋር ስላላለው ግንኙነት እንወያያለን። እንደተለመደው ለቀረበው መረጃ ሳይንሳዊ መረጃ በማጣቀሻ ላይ በዝርዝር ስለቀረበ በጥልቅ ማንበብ ካሻዎ ማስፈንጠሪያውን ይጫኑ።

https://telegra.ph/Turmeric--Inflammation-07-19

በቀጣይ ሳምንት የእርድን ተጨማሪ የጤና ጥቅሞች፣ እርድን መጠቀም ለማን አይመከርም? የሚለውን፣ እንዲሁም ስለ ቁንዶ በርበሬ መረጃን እናቀርብላችሗለን።
በተጨማሪም የስነ ምግብ ባለሙያ እንግዳችንን በቀጣይ ሳምንት የምናስተዋውቅ ይሆናል።

በፊታችን ቅዳሜ በተደጋጋሚ ስለተጠየቅነው ስለ ማር በ @ibdeth እናቀርባለን።

ይከታተሉን!

@tikvahethmagazine @ibdeth
የአንጀት ህክምና ስፔሻሊስት ባለሙያ የሆነውን ዶ/ር ሃይለሚካኤል ደሳለኝ እናስተዋውቆ!

ስለአንጀት ቁስለት ህክምና እና ተያያዥ ጥያቄዎች ካሎት በመወያያ ገጻችን ላይ #GI ብለው በማያያዝ ይጻፉልን።

ሁሌም እዚህ ገጽ ላይ የሚፃፈው የሀኪምዎን ምክር እና ውሳኔ ሳይተካ እውቀት በማስገንዘብ ስለ ጤንነትዎ ሙሉ መረጃ እንዲኖርዎ ማድረግ ነው።
የማር የጤና ጥቅሞች በጥቂቱ


✔️ማር በውስጡ የተለያዩ ንጥረ ምግቦችን ይዟል።

✔️በፀረ-ኦክሲደንት/Anti-oxidant/ የበለጠገ ነው።
✔️በደማችን ውስጥ ለሚገኘው መጠነኛ የስኳር መጠን፣ ከመደበኛ ስኳር ፤ማር የተሻለ ነው።
✔️ማር የላቀ የምግብ ይዘትነት እንዲሁም ለጤና ጠቀሜታ አለው።

✔️በተጨማሪም ከማር የሚገኘውን የፀረ-ኦክሲዳንት ጥቅም ትንሽ መጨመር ለማግኘት መደበኛ ስኳር'ን በምንጠቀምበት መንገድ መጠቀም እንችላለን። ሻይ፣ ቡና እንዲሁም እርጎን ለማጣፈጥ ተመራጭ ነው።

የበለጠ ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ

⬇️⬇️⬇️

https://telegra.ph/Honey-07-23