Crohn's & Colitis Ethiopia
647 subscribers
52 photos
1 video
7 files
44 links
Crohn's & Colitis Ethiopia aims to serve as a hub for patients and families with IBD to learn, share and support eachother. Disclaimer: all information is for educational purposes only.
Questions? Talk to us at @IBDETHIOPIA
Download Telegram
እንኳን ለደብረ ታቦር (ቡሄ) በዓል አደረሳችሁ

ክሮንስ ና ኮላይተስ ኢትዮጵያ 🇪🇹
Crohn's and colitis Ethiopia 🇪🇹
Forwarded from TIKVAH-MAGAZINE
#ጤናረቡዕ ለህክምና ተማሪዎች!

የአንጀት ቁስለት ህክምና ተማሪ ስኮላር ፕሮግራም

ይህ የአንጀት ቁስለት ህክምና ተማሪ ስኮላር ፕሮግራም በአይነቱ ለየት ያለ ለህክምና ተማሪዎች የቀረበ ሲሆን፤ የውስጥ ደዌ እንዲሁም የአንጀት ጤና ስፔሻሊስት መሆን ለሚሹ ከአንደኛ እስከ አራተኛ አመት ህክምና ትምህርት ላይ ላሉ የተዘጋጀ ነው።

ይህ እድል በአለማችን ላይ ስላሉት ከአንጀት ቁስለት ህመም ህክምና ጋር የተያያዙ ጉድለቶች እንዲሁም ከዚህ ህመም ጋር ያሉ ወጣት እና ጎልማሳ ሰዎች ምን አይነት የህክምና ትኩረት ይፈልጋሉ የሚለውን ይዳስሳል።

መስፈርት

-ማንኛውም አመት ላይ ያለ የህክምና ተማሪ
-የአንጀት ጤና ስፔሻሊቲ የመማር ፍላጎት
-ከየትኛውም የአለማችን ክፍል

ፕሮግራም

- 90 በመቶ የወርሀዊ ውይይት ዝግጅት መሳተፍ
- በየወሩ ከሚደረገው ስብሰባ በኃላ ስለ ስብሰባው የሚጻፍ ጽሁፍ መሳተፍ\ማገዝ
- ከአንጀት ቁስለት ህመም ጋር የሚኖሩ ወጣቶች ጋር በቅርበት ስለሚያስፈልገው ልዩ ትኩረት መረዳት
- ከድርጅቱ የህክምና አማካሪ ቦርድ እና አመራር ጋር በቅርብ መገናኘት
- በአመት አንድ ጊዜ ለሚካሄደው የአንጀት ቁስለት ህመም ኮንፈረንስ በፈረንጆች አቆጣጠር 2023 አመተ ምህረት ላይ ወደ አሜሪካ የመጓዝ እድል (የጉዞ ድጋፍ እስከ 1000 የአሜሪካ ዶላር)

ስለፕሮግራሙ ዝርዝር ከላይ ተያይዟል።

ለማመልከት ይህንን ማስፈንጠሪያ ይጫኑ

https://docs.google.com/forms/d/e/1FAIpQLSfflOypTySxTtFYjoGKvbojfO2EV7-vKSMoyz2Kaf9OZv3srA/viewform

#ጤናረቡዕ ላይ ስትሳተፉ የነበራችሁ የህክምና ተማሪዎች @IBDETHIOPIA ላይ በመጻፍ የምስክር ደብዳቤ ማግኘት ትችላላችሁ።

@tikvahethmagazine @ibdeth
#quickfact

በዚህ ሳምንት ስለ አንጀት ቁስለት እና የወር አበባ ዑደት እንወያያለን። ከምንዳስሳቸው ነጥቦች ውስጥ:-

✔️የወር አበባ ምንድን ነው?
✔️የወር አበባ ዑደት እና የአንጀት ቁስለት ግንኙነት
✔️የወር አበባ የህመም ስሜት ለምን በአንጀት ቁስለት ህመም ታካሚ ሴቶች ላይ ሊብስ እንደሚችል

በቀጣይ ሳምንት ምን አይነት መፍትሄ እና አማራጮች እንዳሉት እንወያያለን።

ማስፈንጠሪያውን በመጫን በሰፊው ያንብቡ ።

https://telegra.ph/IBD--Menses-08-20
Forwarded from TIKVAH-MAGAZINE
#ጤናረቡዕ

የአመጋገብ ስርዓት እና የአይምሮ ጤና

[ በ @ibdeth የቀረበ ]

- አካላዊ ጤና እና የአመጋገብ ስርዓት ዘርፈ ብዙ ተዛምዶ አላቸው።

- ደካማ የአመጋገብ ሥርዓት ለወረደ ስሜት አንደኛው ምክንያት ሊሆን ይችላል፤ በሌላ ጎኑ ተገቢ የአመጋገብ ሥርዓት ጉልህ በሚባል ደረጃ የአዕምሮን ጤና ያሻሽላል።

- የአመጋገብ ስርዓታችን በሆድ እቃችን ውስጥ በሚገኙ ረቂቅ ተህዋሳት ላይ በሚያመጣው ተፅዕኖ የአዕምሮን ጤና ላይ በተላያየ መንገድ ተፅዕኖ እንደሚያሳድር የተለያዩ ጥናቶች አረጋግጠዋል።

- የዘወትር የማዕዳችን ሥርዓት፥ እንደ ትኩራት ማጣት እና በስሜት ግፊት ነገሮችን በማድረግ የሚገለጠውን Attention Deficit Hyperactivity Disorder/ADHD/ ያሉ የአዕምሮ ጤና ችግሮች ጋር ተያያዥነት አለው።

- ኦሜጋ-3 ፋቲ አሲድ በተላዩ ምግቦች ውስጥ የሚገኝ ንጥረ ነገር ሲሆን የተለያዩ የአዕምሮ ህመም ተጠቂዎች ላይ እራሱን ችሎ ወይም እንደ አባሪ መድኃኒት መጠቀም ስኬታማ ውጤትን አሳይቷል።

- የአመጋገብ ሥርዓታችን በተለያየ መንገድ የአዕምሮ ጤና ላይ ተፅዕኖ ያደርጋል። በአዕምሮ ምግቦች የበለጠጉ ምግቦችን መጠቀም ስኬታማ እና በእንፃራዊ መልኩ ደግሞ ቀላል በሆነ መንገድ የአይምሮ ጤናን ለማሻሻል እንዲሁም ከአይምሮ ህመም ለማገገም አይነተኛ መንገዶች ናቸው።

🔗 ተጨማሪ በ 👉 INSTANTVIEW ያንብቡ

@tikvahethmagazine @WriteforTikvahbot
Crohn's & Colitis Ethiopia
#quickfact በዚህ ሳምንት ስለ አንጀት ቁስለት እና የወር አበባ ዑደት እንወያያለን። ከምንዳስሳቸው ነጥቦች ውስጥ:- ✔️የወር አበባ ምንድን ነው? ✔️የወር አበባ ዑደት እና የአንጀት ቁስለት ግንኙነት ✔️የወር አበባ የህመም ስሜት ለምን በአንጀት ቁስለት ህመም ታካሚ ሴቶች ላይ ሊብስ እንደሚችል በቀጣይ ሳምንት ምን አይነት መፍትሄ እና አማራጮች እንዳሉት እንወያያለን። ማስፈንጠሪያውን በመጫን…
#quickfact

የወር አበባ ዑደትና የአንጀት ቁስለት               

ክፍል 2                  

ለማንበብ ማስፈንጠሪያውን ይጫኑ

https://telegra.ph/IBD--Menses-08-27
Our very own Dr. Armoniam Mulatu Teshome has graduated from medical school! He works in supporting our health awareness campaigns and is the mastermind behind most of our Amharic content. Happy graduation Dr!
Forwarded from TIKVAH-MAGAZINE
#ጤናረቡዕ

ጤናማ የሆድ እቃ፣ ጤናማ አዕምሮ

- ስር የሰደዱ ህመሞችና የአእምሮ ጤና

✔️ የተለያዩ ስር የሰደዱ ህመሞች ጭንቀት፣ ስጋት እና ድባቴን በመፍጠር በአንድ ሰው ህይወት ላይ እክልን ሊያስከትሉ ይችላሉ፡፡

✔️በሌላ በኩል ፣ የአእምሮ ጭንቀት ሁኔታ ሲከሰት የተለያዩ የስር የሰደዱ ህመሞች ምልክቶች እና የህመሞቹን መልሶ መቀስቀስ ሊያስከትል ይችላል፡፡

👉ከሁለቱ የቱም ይቅደም የቱ፣ ጥናቶች እንደሚያሳዩት ጭንቀት፣ ስጋት እና ድባቴ በቀጥታ ስር የሰደዱ ህመሞችን ላያስከትሉ ቢችሉም ቀድሞ ለተፈጠረው ህመም አፀፋዊ ምላሽ ናቸው፡፡

👉ከጭንቀት፣ ስጋት እና ድባቴ በተጨማሪ ስር የሰደዱ ህመሞች ያለባቸው ሰዎች ሌሎች ተጨማሪ የስሜት ለውጦችን ሊያስተናግዱ ይችላሉ፡፡

ሆኖም ያጋጠመንን ህመም መቀበል የለት ተዕለት ኑሯችንን በተገቢው ሁኔታ ለማስኬድ፣ የሀኪማችንን ምክር በአግባቡ ተቀብሎ ለመፈፀም እና ጤናማ ህይወት ለመኖር ይረዳናል፡፡

🔗 ተጨማሪ ያንብቡ 👉 https://telegra.ph/NCDs--Mental-Health-08-31

#በቀጣይሳምንት

በቀጣይ ሳምንት እስካሁን ስንወያይበት በቆየንበት ጤናማ የሆድ እቃ፣ ጤናማ አዕምሮ በሚለው ዙሪያ ባለሙያ ጋብዘን፤ ከእናንተ የሚደርሱንንም ጥያቄዎች አካተን ሰፊ ማብራሪያን በቀጥታ ስርጭት ይዘን እንቀርባለን፡፡
በዚህ ርዕሰ ጉዳይ ላይ ያሎትን ጥያቄ በ @IBDETHIOPIA ያድርሱን!

@tikvahethmagazine @ibdeth
#ቃለመጠይቅ #ጤናረቡዕ

ከስነ-አዕምሮ ባለሙያ ጋር

በጤና ረቡዑ ‹‹ ጤናማ የሆድ እቃ፣ ጤናማ አእምሮ›› በሚል ርዕስ ላለፉት ሳምንታት መረጃን ስናቀብላቹ ነበር፡፡
በቀጣይ ሳምንት በዚሁ ርዕሰ ጉዳይ ላይ ከስነ-አዕምሮ ባለሙያ ጋር በቀጥታ ስርጭት ውይይት እናደርጋለን።

ከምንዳስሳቸው ርዕሶች ውስጥ:-
✔️ስር የሰደደ ህመም ከአእምሮ ጤና ጋር ያለውን ግንኙነት እንቃኛለን።
✔️የአንጀት ቁስለት ህመም እና ተመሳሳይ ህመሞች ያለበት ሰው እንዴት የስነ ልቦና ጤናውን መጠበቅ እንደሚችል እንወያያለን።
✔️የአእምሮ ጤናን ለመጠበቅ ቀን በቀን መተግበር ያለብንን የተለያዩ ተግባሪያዊ የስነልቦና የጤና ስልቶች በዝርዝር እናያለን።

በዚህ ርዕሰ ጉዳይ ላይ እንዲብራራሎት የሚፈልጉት ጥያቄ አሎት?
@IBDETHIOPIA መልዕክቶን ይላኩልን፡፡ በቀጥታ ስርጭቱ ላይ ተገቢውን ማብራሪያ እና ምላሽ በባለሙያ እንዲሰጦ እናደርጋለን፡፡

👉 ከዚህ በተጨማሪም ከእንግዳችን ከስነ-አዕምሮ ባለሙያው ናትናኤል ጋር የአንድ ለአንድ የስነ-ልቦና ድጋፍና ምክክር ለሚፈልጉ የትና እንዴት ማግኘት እንደሚችሉ ከቀጥታ ስርጭቱ በሗላ የምናሳውቅ ይሆናል።

ይከታተሉን!

@tikvahethmagazine @ibdeth
Forwarded from TIKVAH-MAGAZINE
#ጤናረቡዕ

🟣ማስታወሻ

ዛሬ በጤና ረቡዕ የውይይት ገፃችን ላይ ስለ የሆድ እቃ ጤናና የአእምሮ ጤና እንድንወያይበት እንዲሁም ጥያቄዎቻችሁ በባለሙያ እንዲመለሱ የቀጥታ ስርጭት ፕሮግራም ይዘን መጥተናል።

ከቀኑ ሰባት ሰዓት ላይ የስነ-ልቦና ባለሙያ የሆነውን ናትናኤል ሰይፉን ይዘን እንቀርባለን።
ይከታተሉን!

በቲክቫህ ማጋዚን ላይ ብቻ!

@tikvahethmagazine @ibdeth
መልካም አዲስ አመት የክሮንስ እና የኮላይተስ ኢትዮጵያ ቤተሰብ!

ይህ ዓመት ለእርስዎ እና ለቤተሰብዎ የበለፀገ ዓመት ይሁንልዎ።

@ibdeth
#ጤናረቡዕ

ውድ የጤና ረቡዕ ተከታታዮቻችን በዚህኛው የጤና ረቡዕ የዝግጅት ምዕራፍ "ጤናማ የሆድ እቃ፣ ጤናማ ስነ-ተዋልዶ" በሚል ርዕስ ሳይንሳዊ መረጃዎችን ለተከታታይ ሳምንታት እናቀብላችኋለን፡፡

ከምንዳስሳቸው ርዕሰ ጉዳዮች ውስጥ
👉 የጤናማ ስነ-ተዋልዶ ምንነትና የጤናማ ስነ-ተዋልዶና የሆድ እቃ ጤና ግንኙነት፤የስነ- ተዋልዶ ሆርሞኖችና የሆድ እቃ ጠቃሚ ረቂቅ ተህዋሲያን፤ ስር የሰደዱ ህመሞችና የስነ-ተዋልዶ ጤና (በወንዶችና በሴቶች ላይ)፤ የጤናማ የሆድ እቃና የወር አበባ ዑደት፣እርግዝና፣የእርግዝና መከላከያዎች፣ ጡት ማጥባትና ስር የሰደዱ ህመሞች ግንኙነት ይገኙበታል።

በመጨረሻው ሳምንትም ባለሞያ ጋብዘን በዚሁ ርዕስ ዙሪያ ከእናንተ የሚመጡልንን ጥያቄዎች በቀጥታ ስርጭት የምንመልስ ይሆናል።

በዚህ ሳምንት፦
👉ጤናማ ስነ-ተዋልዶ ምን ማለት ነው?

☑️ የስነ- ተዋልዶ ጤና
የስነ- ተዋልዶ ጤና ማለት ከተዋልዶ ጤና ጋር ተያይዞ የተሟላ የአካል፣ የስሜት፣የአዕምሮ፣ እንዲሁም የማህበራዊ ጤንነት ማለት ነው፡፡ ከዚህም በተጨማሪ የበሽታ አለመኖር ወይም የመራቢያ አካላት ተገቢውን የተግባር ሂደት መተግበር መቻልን ያካትታል፡፡ ከዚህ በተቃራኒ ሁኔታ የሚገኙ ነገሮች የስነ-ተዋልዶ ጤና ችግሮች ናቸው፡፡

☑️ የጤናማ ስነ-ተዋልዶና የሆድ እቃ ጤና ግንኙነት

🔘ጤናማ የሆድ እቃ ፤ ጠቃሚ ረቂቅ ተህዋሲያንና በሽታ ተከላካይ ጥቃቅን ህዋሳትን ስለሚይዝ ሰውነታችንን እንደ ባክቴሪያ ፣ቫይረስና ፈንገስ ካሉ በሽታን ከሚያስከትሉብን ነገሮች ይከላከልልናል።

🔘ከዚያ በተጨማሪም ጤናማ የሆድ እቃ በነርቭና ሆርሞኖች አማካኝነት ከጭንቅላት ጋር ስለሚገናኝ አጠቃላይ የሰውነት ጤናችንን ለመጠበቅም ትልቅ አስተዋፆ አለው፡፡ ከዚህም ውስጥ የሰውነት ሆርሞኖች የማመንጨት፣ ማዋሃድና ማሰራጨት ሂደት ላይ ያለው አስተዋጾ ይጠቀሳል፡፡ በዚህም ምክንያት የሆድ እቃ ጤናችን ከስነ- ተዋልዶና መራባት ሂደትን ጋር በቀጥታ ይገናኛል ማለት ይቻላል፡፡

የበለጠ ለማንበብ ማስፈንጠሪያውን ይጫኑ።

https://telegra.ph/Gut-Health--Reproductive-Health-09-14

@tikvahethmagazine @ibdeth
Forwarded from TIKVAH-MAGAZINE
#ጤናረቡዕ

ጤናማ የሆድ እቃ፣ ጤናማ ስነ-ተዋልዶ - 2

👉የስነ-ተዋልዶ ሆርሞኖችና የሆድ እቃ ጠቃሚ ረቂቅ ተህዋሲያን 

- የስነ-ተዋልዶ ሆርሞኖች፤ በወንዶችና በሴቶች አጠቃላይ የስነ-ተዋልዶ ጤና፣የጉርምስና የሰውነት ለውጦች ላይ እንዲሁም በሰውነት እድገት፣ ፆታዊ ጠባይና መገለጫዎች ላይ ትልቅ ሚና አላቸው፡፡
- የስነ- ተዋልዶ ሆርሞኖች ተብለው ከሚጠቀሱት ውስጥ ዋነኞቹ፤ ኤስትሮጅን/ፕሮጀስትሮን እና ቴስተስትሮን ናቸው፡፡

👉የስነ-ተዋልዶ ሆርሞኖችና የሆድ እቃ ጠቃሚ ረቂቅ ተህዋሲያን ግንኙነት

- የሆድ እቃ ጠቃሚ ረቂቅ ተህዋሲያን በአንጀትና በሆድ እቃ መዋቅር ላይ ጉልህ ሚና አላቸው፡፡ እነዚህ ተህዋሲያን የሆድ እቃን ጤናማነት ከመጠበቅ ባሻገር በርከት ባሉ የሰውነታችን ሂደቶች ውስጥም ይሳተፋሉ፡፡

- የሆድ እቃ ጠቃሚ ረቂቅ ተህዋሲያን መጠን መዛባት ሲከሰትና እነዚህ ረቂቅ ተህዋሲያን ከምንመገበው ምግብ ውስጥ አስፈላጊ ንጥረ ነገሮች ወደ ሰውነት እንዲመጠጥ ማድረግ ሳይችሉ ሲቀሩ የሚከሰተው የአልሚ ምግቦች እጥረትም ለሆርሞኖች መጠን መዛባት እንደምክንያት ይጠቀሳል፡፡ የሆርሞኖች መዛባቱ ደግሞ በስነ-ተዋልዶ ሆርሞኖችም ላይ ይታያል፡፡

👉ስር የሰደዱ ህመሞችና የስነ-ተዋልዶ ጤና 

- ስር የሰደዱ ህመሞች የሚባሉት ለረጅም ጊዜ የቆዩ ህመሞች ሆነው የእለት ተዕለት ኑሮዋችንን በአግባቡ ለመምራት እንቅፋት የሚሆኑብንና ቀጣይነት ያለው የህክምና ክትትል የሚፈልጉ ናቸው፡፡

- ስር በሰደዱ ህመሞች በተጠቁ ታካሚዎች ዘንድ የስነ-ተዋልዶ ጤናቸው ከህመሞቹ ባህሪ፣ሰውነታችን ለህመሞቹ ከሚሰጠው ምላሽና ህመሞቹን ለመቆጣጠር ከሚታዘዙ መድሃኒቶች የጎንዮሽ ጉዳት የተነሳ በተለያየ መንገድ ይጠቃል፡፡

የበለጠ ለማንበብ ሊንኩ ይጫኑ።
https://telegra.ph/Gut-Health-Reproductive-Health-09-21

@tikvahethmagazine    @ibdeth
#ጤናረቡዕ

ጤናማ የሆድ እቃ፣ ጤናማ ስነ-ተዋልዶ-3

የወር አበባ ዑደት፣ ጤናማ የሆድ እቃና ስር የሰደዱ ህመሞች ግንኙነት

✔️ የስነ- ተዋልዶ ጤና፤ ከተዋልዶ ጤና ጋር ተያይዞ የተሟላ የአካል፣ የስሜት፣የአዕምሮ፣ እንዲሁም የማህበራዊ ጤንነት ማለት እንደመሆኑና ከዚህም በተጨማሪ የበሽታ አለመኖር ወይም የመራቢያ አካላት ተገቢውን የተግባር ሂደት መተግበር መቻልን ያካተተ ሲሆን ከዚህ ዉስጥ ደግሞ የተስተካከለና ጤናማ የወር አበባ ዑደት አንዱ ነው።

👉የወር አበባ ዑደት የአንዲት ሴት ሰውነት በየወሩ ሊከሰት ለሚችል እርግዝና በሚያደርገው ቅድመ ዝግጅት የተነሳ የሚፈጠሩ የተለያዩ ለውጦች ውጤት ነው፡፡
👉ይህ የወር አበባ ዑደት ከሆድ እቃ ጤና ጋር በእጅጉ ይቆረኛል።ጤናማ የሆድ እቃ በነርቭና ሆርሞኖች አማካኝነት ከጭንቅላት ጋር ስለሚገናኝ አጠቃላይ የሰውነት ጤናችንን ለመጠበቅም ትልቅ አስተዋፆ አለው፡፡ከዚህም ውስጥ የሰውነት ሆርሞኖች የማመንጨት፣ ማዋሃድና ማሰራጨት ሂደት ላይ ያለው አስተዋጾ ይጠቀሳል፡፡ የወር አበባ ዑደት ደግሞ የተለያዩ የሆርሞን ለውጦች ዉጤት እንደመሆኑ በሆድ እቃና በሆድ እቃ ጠቃሚ ረቂቅ ተህዋሲያኖች ጤና መዛባት ምክንያት የሚከሰት የሆርሞኖች መዛባት ጤናማ የወር አበባ ዑደትን ሊያዛባው ይችላል።
👉 ስር በሰደዱ ህመሞች፣ ማለትም፤ ለረጅም ጊዜ የቆዩና ቀጣይነት ያለው የህክምና ክትትል በሚፈልጉ ህመሞች ውስጥ የሚያልፉ ሴቶች የወር አበባ ዑደት እንደህመሙ ደረጃና እንደ ሰው የሰውነት ሁኔታ ይለያያል፡፡ ለዚህም እንደምክንያት ከሚጠቀሱት ውስጥ፤ ስር በሰደዱት ህመሞች ንቁ ደረጃ ላይ የሚከሰተው የሰውነት መቆጣት ፤የሰውነታችን መደበኛ የሆርሞን ስራ እንዲዛባ ምክንያት ስለሚሆን የወር አበባ ዑደትም በዚሁ ምክንያት ሊዛባ ይችላል፡፡ በተጨማሪም ቀደም ሲል የተደረጉ ቀዶ ህክምናዎች፣ የመድሃኒቶች የጎንዮሽ ጉዳቶችና ሲጋራን ማጨስም እንደምክንያት ይጠቀሳሉ፡፡

ተጨማሪ ለማንበብ ማስፈንጠሪያውን ይጫኑ።
https://telegra.ph/Gut-Health-Reproductive-Health-09-28-2

@tikvahethmagazine @ibdeth
#ጤናረቡዕ

ጤናማ የሆድ እቃ፣ ጤናማ ስነ-ተዋልዶ-4

☑️ እርግዝናና ስር የሰደዱ ህመሞች

🔘 በእርግዝና ወቅት ሰውነት በተፈጥሮ አዲስ ለተፀነሰው ፅንስ ልዩ ጥበቃ ያደርጋል፡፡ ስር በሰደዱ ህመሞች ውስጥ ለሚያልፉ እናቶች ደግሞ ጤናማ በሆነ የቅድመና ድህረ እንዲሁም የእርግዝና ወቅት ውስጥ ለማለፍ ሰውነታችን ልዩ ክብካቤና ድጋፍ ሊያስፈልገው ይችላል።

🔘 ስር የሰደዱ ህመሞች ባህሪ በእጅጉ የተለያየና ሰፊ ቢሆንም በአጠቃላይ ግን በተለይም በህመሞቹ ንቁ ደረጃ ላይ የሚፈጠር እርግዝና የሰውነት መቆጣትና የመደበኛ ሆርሞን መዛባት ችግሮችን በማባባስ የማህፀን የፅንስ መሸከም ሂደትን ሊያደናቅፈው ይችላል፡፡ ከዚያ በተጨማሪ እርግዝናው በራሱ ለሰውነት፣ በተለይም በመጀመሪያዎቹና በመጨረሻዎቹ ሳምንታት፣የሰውነትመቆጣት(inflammatory state) አይነት ምላሽን ይሰጣል፡፡ ይህ ደግሞ ቀደም ሲል ስር በሰደዱ ህመሞች ምክንያት የተፈጠረን የሰውነት መቆጣት ሊያባብሰው ይችላል፡፡

🔘 ሆኖም እነዚህ ችግሮች እንዳይከሰቱ መከታተልና መቆጣጠር ብሎም ጤናማ በሆነ የእርግዝና ሂደት ጤናማ ልጅን መውለድ ይቻላል፡፡ በተለይም እርግዝናን በማቀድ በቅድመ እርግዝና ወቅት ከሃኪም ጋር በመመካከር ሰውነት ተገቢውን ዝግጅት ለሚመጣው ፅንስ እንዲያደርግ ማገዝ ይቻላል፡፡

☑️ የእርግዝና መከላከያዎችና ስር የሰደዱ ህመሞች 

🔘የእርግዝና መካላከያ ዘዴዎች ያልተፈለገን እርግዝና ለመከላከል የሚውሉ ናቸው፡፡በሁለቱም ፆታዎች ስር በሰደዱ ህመሞች ለተጠቁ ታካሚዎች በደም ዝውውራቸው ጤናማነት ሁናቴ፣ ከችግሮቹ ጋር የተያያዘ ከተፈጥሮ ውጪ የሆነ የደም መርጋት፣ የህመሞቹ በንቁ የህመም ደረጃ መሆንና ባለመሆን፣የእርግዝና መከላከያዎቹ የህመሞቹ መጠን ላይ ያላቸው ተጽዕኖና ስር ለሰደዱ ህመሞቹ ከሚወሰዱ መድሃኒቶች ጋር ያላቸው መስተጋብርና ተፅዕኖ ምን አይነት የእርግዝና መከላከያ አማራጮችን መውሰድ እንዳለባቸው የሚወስኑ ነገሮች ናቸው፡፡

☑️ ጡት ማጥባት፣ ስር የሰደዱ ህመሞችና ጤናማ የሆድ እቃ

🔘የእናት ጡት ማጥባት ለአንድ ህፃን ሁለንተናዊ የጤና ጥቅሞች አሉት።የእናት የጡት ወተትን በተገቢው መንገድ ያገኙ ህፃናት የሆድ እቃ ጤናም በእጅጉ የተሻሻለ ነው፡፡ ይህ የሚሆንበት ምክንያት የእናት ወተት ለጤናማ የሆድ እቃ መሰረታዊ የሆኑትን የሆድ እቃ ጠቃሚ ረቂቅ ተህዋሲያን እድገትና ተግባርን ስለሚያግዝ ነው፡፡

🔘ከዚህ በተጨማሪም ለእናቲቱም በርካታ ጥቅሞች አሉት።ስር በሰደዱ ህመሞች ውስጥ ላሉ እናቶች የጡት ማጥባት ጥቅሞች እንዳሉ ሆነው ለአንዳንድ ስር ለሰደዱ ህመሞች በሚወሰዱ መድሃኒቶች ምክንያት የጡት ወተቱ ለህፃኑ ጤና እክልን በሚያመጣበት ጊዜ ሌሎች አማራጮችን መጠቀም ይመከራል፡፡በመሆኑም ከጡት ማጥባት እጅግ የጎላ ጠቀሜታ አንፃር ከሃኪም ጋር በመመካከር ተገቢውን ውሳኔ መወሰን አስፈላጊ ነው፡፡ 

የበለጠ ለማንበብ ማስፈንጠሪያውን ይጫኑ።
https://telegra.ph/Gut-Health-Reproductive-Health-10-05

@tikvahethmagazine @ibdeth
Forwarded from TIKVAH-MAGAZINE
#ጤናረቡዕ

ጤናማ የሆድ እቃ፣ ጤናማ ስነ-ተዋልዶ-5

☑️የተለያዩ ስር የሰደዱ ህመሞች መድሃኒቶችና የስነ-ተዋልዶ ጤና

👉 ስር የሰደዱ ህመሞች አይነት እጅግ በርካታ እንደመሆኑ ለህመሞቹ የሚታዘዙ መድሃኒቶችም አይነት፣ ተግባር፣ የደም ውስጥ ስርጭትና የጎንዮሽ ጉዳትም በዛው ልክ እጅግ ሰፊና የተለያየ ነው፡፡ 
በዚህ ርዕስ ስር፤ ስር ለሰደዱ ህመሞች ከሚታዘዙ መድሃኒቶችና የስነ ተዋልዶ ጤና ተጽዕኖዎቻቸው ውስጥ የከፍተኛ የደም ግፊት፣ የልብና ከደም ጋር ለተያያዙ ችግሮች የሚታዘዙ፣የስኳር ህመም መድሃኒቶች፣ የሰውነት የተፈጥሮ በሽታን የመከላከል ስርዓት መዛባት/ ስህተት ችግር መድሃኒቶች-( autoimmune disease)፣የካንሰር መድሃኒቶች ተጠቅሰዋል።

👉ከነዚህ ህመሞችና መድሃኒቶቻቸው ውስጥ የተወሰኑት የስነ ተዋልዶ፣ በተለይም የመራቢያ አካላት ላይና የተራክቦ ፍላጎትና ጤናማነት ላይ የተወሰነ ተጽዕኖ እንዳላቸው ቢገለፅም መድሃኒቶቹ የሚታዘዙት ለህመሞቹ መፍትሄን ለማግኘት እጅግ ወሳኝ በመሆናቸው በመሆኑ እነዚህን  መድሃኒቶችም ያለ ሃኪም ትዕዛዝ ማቋረጥ የማይቻል ሲሆን ሌሎች አማራጭ ዘዴዎችን በመጠቀም የጎንዮሽ ጉዳታቸውን ለመቀነስ እንዲሁም በተራክቦ ሂደትም ከፆታ አጋሮች ጋር በመሆን መወያየትና መደጋገፍ እጅግ ወሳኝ ነው፡፡

☑️የስነ-ተዋልዶ ጤናዬን እንዴት ማሻሻል እችላለሁ?

👉የስነ-ተዋልዶ ጤና ከአጠቃላይ የሰውነት ጤና መገለጫ አንዱ እንደመሆኑና  ትውልድ በማስቀጠል ሚና ውስጥ ትኩረት የሚሻ ስለሆነ፣ በተለይም የአኗኗር ዘይቤን በማስተካከል፣የሰውነት ክብደትን መቆጣጠር፣የስነ-ተዋልዶን ጤናን ለማረጋገጥ በየጊዜው ምርመራን ማድረግ፣አስፈላጊ የሆኑ የእርግዝናና የአባላዘር ህመም መከላከያዎችን በአግባቡ መጠቀምና ከፆታና ከትዳር አጋር ጋር በግልፅ በመመካከርና በመተጋገዝ የዚህን የስነ-ተዋልዶ ጤና ማሻሻልና ማስተካከል ይቻላል፡፡

የበለጠ ለማንበብ ማስፈንጠሪያውን ይጫኑ።

https://telegra.ph/Gut-Health-Reproductive-Health-10-12

በቀጣይ ሳምንት እስካሁን ስንወያይበት በቆየነው ጤናማ የሆድ እቃ፣ጤናማ ስነ-ተዋልዶ ርዕስ ዙሪያ ባለሙያ ጋብዘን፣ ከእናንተ የሚደርሱንን ጥያቄዎች አካተን በቀጥታ ስርጭት ሰፊ ማብራሪያን ይዘን እንቀርባለን፡፡
ጥያቄዎቻችሁን በ @IBDETHIOPIA ያድርሱን።

@tikvahethmagazine    @ibdeth
የክሮንስና ኮላይተስ ኢትዮጵያ መስራች ዶ/ር ፋሲካ ሽመልስ በዘ-ጋርዲያን አለምአቀፍ መፅሄት

የዶ/ር ፋሲካ ለብዙዎቻችን፣ በተለይም በክሮንስና ኮላይተስ ህመም ውስጥ ላለን ሁሉ ምሳሌ የሚሆን ታሪኳ የዘ-ጋርዲያን መፅሄት ላይ ሰፍሯል።

ዶ/ር ፋሲካ በድርጅታችን ዉስጥ ስላለሽ ቀዳሚ የመሪነት ሚናና እያደረግሽው ስላለው አስተዋፆ እናመሰግንሻለን።
ኮርተንብሻል!!!

https://www.theguardian.com/global-development/2022/oct/27/doctor-fasika-teferra-superpower-hope-crohns-ethiopia-acc

Crohn's and colitis Ethiopia 🇪🇹
ክሮንስና ኮላይተስ ኢትዮጵያ 🇪🇹
#ተላላፊያልሆኑህመሞች አሉብዎ? እይታዎችዎን ያካፍሉ፣ እርምጃ ይውሰዱ እና ለውጡን ይምሩ። የ #ተላላፊያልሆኑህመሞችድምፆች @AfricaNCDsNet አካል ይሁኑ።
ስለእርስዎ ምንም ነገር የለም ያለርስዎ።

Do you have an #NCD? Share your views, take action & drive change. Be part of #NCDVoices @AfricaNCDsNet.
Nothing about you without you.

ከታች ያለውን ሊንክ በመጠቀም ይሳተፉ!
Get involved!
📌 https://docs.google.com/forms/d/e/1FAIpQLSdDjjWYKAvBDlUHwFXFk_KrnvlcHl7aMO1CM1Mv1ptS4TBuMw/viewform