Forwarded from TIKVAH-MAGAZINE
#ጤናረቡዕ #እርድ
ሰሞኑን በጤና ረቡዕ ፕሮግራም ላይ ስለተለያዩ የሰውነት መቆጣትን የሚከላከሉ በማዕድ ቤት ውስጥ ስለሚገኙ ቅመማት እና ሻይ ስንወያይ ቆይተናል።
ይህንን የpolyphenol ተከታታይ ፕሮግራም የምንቋጨው በእርድ እና የእርድ ጥቅሞች ሲሆን ለተከታታይ ሁለት ሳምንታት ስለ እርድ እና የተለያዩ ህመሞች ጋር ስላላለው ግንኙነት እንወያያለን። እንደተለመደው ለቀረበው መረጃ ሳይንሳዊ መረጃ በማጣቀሻ ላይ በዝርዝር ስለቀረበ በጥልቅ ማንበብ ካሻዎ ማስፈንጠሪያውን ይጫኑ።
https://telegra.ph/Turmeric--Inflammation-07-19
በቀጣይ ሳምንት የእርድን ተጨማሪ የጤና ጥቅሞች፣ እርድን መጠቀም ለማን አይመከርም? የሚለውን፣ እንዲሁም ስለ ቁንዶ በርበሬ መረጃን እናቀርብላችሗለን።
በተጨማሪም የስነ ምግብ ባለሙያ እንግዳችንን በቀጣይ ሳምንት የምናስተዋውቅ ይሆናል።
በፊታችን ቅዳሜ በተደጋጋሚ ስለተጠየቅነው ስለ ማር በ @ibdeth እናቀርባለን።
ይከታተሉን!
@tikvahethmagazine @ibdeth

Telegraph
Turmeric & Inflammation
የእርድ የጤና ጥቅሞች በደፈናው የአንጀታችንን ጤና ለማማሻሻል ስናስብ፣ የጠቃሚ ረቂቅ ነፍሳት አዘል ምግቦች/Probiotics/ እና የተብላሉ ምግቦች/Fermented foods/ ወደ አዕምሮአችን በቀዳሚ ደረጃ ይመጣሉ፤ ሆኖም ግን ማዕዳችን ላይ እርድን/Turmeric/ መጨመር የአንጀታችንን ጤና ከመደገፍ በተጨማሪ ሌሎች የጠኑ የአንጀት ህመሞችን በመከላከል የበኩሉን አስተዋጽኦ ያደርጋል። አንጀት…
Forwarded from TIKVAH-MAGAZINE
#ጤናረቡዕ #እርድ
ክፍል-2 ( የመጀመሪያውን ክፍል ማንበብ ለምትፈልጉ ከላይ ተያይዟል)
ተጨማሪ የእርድ ጠቀሜታዎች
- እርድ በውስጡ የፀረ-ብግነት ባህሪ'ን ስላተላበሰ የተለያዩ ህመሞችን ለማስታገስ ይረዳል።
- በሰውነታችን ያሉ መርዛማ ንጥረ ነገሮች በጉበታችን ውስጥ በማለፍ ይመክናሉ፤ እርድ ይህንን መርዛማነትን ከሰውነታችን የማስወገድ ሥራን እጅጉን ያግዛል
- እርድን በቀን ሁለት ጊዜ መጠቀም በደማችን ውስጥ የሚገኘውን የኮሌስትሮል መጠንን ይቀንሳል።
- በእርድ ውስጥ የሚገኘው Curcumin የተሰኘው ንጥረ ነገር የደም ስሮቻችንን የውስጠኛውን ግድግዳ የሚሸፍነውን የመጀመሪያውን ንብር በማገዝ፤ የሰውነት ግፊትን እንዲሁም የደም መርጋትን ይከላከላል።
ለምን እርድ ውስጥ ቁንዶ በርበሬ እንጨምራለን?
ጥናቶች እንደሚያሳዩት ፣ በቁንዶ በርበሬ ውስጥ የሚገኘውን Piperine የተሰኘ ንጥረ ነገር እርድ ውስጥ ከሚገኘው Curcumin ጋር እብሮ መጠቀም የCurcumin'ን ወደ ሰውነታችን የመሰረፅ እድሉን በ2000% ያህል ያሳድገዋል።
እርድ ለማን አይመከርም?
፨ የጨጓራ አሲድ የሚቀንሱ መድሐኒት በምንወስድበት ጊዜ።
፨ የስኳር ህመም መድሐኒት በሚወሰድበት ጊዜ።
፨ የሀሞት ጠጠር ላለባቸው ሰዎች ላይ።
፨ የደም ማቅጠኛ መድሐኒትን የሚጠቀሙ ሰዎች።
ተጨማሪ ጠቃሚ መረጃዎችን በተከታዩ ሊንክ በቀላሉ ማግኘት ይችላሉ https://telegra.ph/Turmeric-Continued-07-26
በቲክቫህ ማጋዚን ላይ ብቻ!

Turmeric Continued
ተጨማሪ የእርድ ጠቀሜታዎች ♦️እርድ በውስጡ የፀረ-ብግነት ባህሪ'ን ስላተላበሰ እንደ ሪህ ያሉ በሽታዎች እንዲሁም የጡንቻ እና መገጣጠሚያ ህመሞችን ለማስታገስ ይረዳል። ♦️በሰውነታችን ያሉ መርዛማ ንጥረ ነገሮች በጉበታችን ውስጥ በማለፍ ይመክናሉ፤ እርድ ይህንን መርዛማነትን ከሰውነታችን የማስወገድ ሥራን እጅጉን ያግዛል ፤ በሰውነታችንም ያነሰ የመርዛማነት መጠን እንዲሁም የተነቃቃ ስርዓት-ፍርንት/Lymphatic…