Ashewa Technologies
7.72K subscribers
2K photos
160 videos
33 files
1K links
We Revolutionize African commerce/business by providing innovative, e-commerce, software development, o,r rmeirslogistics, e-learning, payment, and entertainment to do business easily, affordably, and reliably at any time, and any place through cutting-ed
Download Telegram
🌟 Exciting Partnership Announcement! 🌟

We are thrilled to announce a new Memorandum of Understanding (MoU) between Ashewa Technology Solution (ATS) S.C. and the Equal Trade Alliance (ETA)! 🤝

As a leading digital solutions provider, ATS is committed to enhancing ETA's digital presence and supporting its mission to promote fair trade practices. Together, we aim to leverage our expertise in software development and digital solutions to empower both local and international professional associations.

This
partnership marks a significant step forward in fostering growth and innovation in the fair trade sector. Stay tuned for updates on our collaborative projects! 🚀

#Partnership #DigitalSolutions #FairTrade #Innovation #AshewaTechnology #EqualTradeAlliance
❤3👍3
አሸዋ ቴክኖሎጂ ከኢፌድሪ ቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኢንስቲትዩት በጋር ለመስራት ተፈራረመ።

አሸዋ ቴክኖሎጂ ሶሉሽን አክሲዎን ማህበር በተለያዩ ጉዳዮች ላይ አብሮ ለመስራት የሚያስችለውን ስምምነት ከኢፌዲሪ ቴክኒክ እና ሙያ ስልጠና ኢንስቲትዩት ጋር በዛሬው እለት ተፈራርሟል። በዋናነትም ስምምነቱ የተደረገው የቴክኖሎጂ ውጤቶች ላይ፣ ጥናትና ምርምር ፣ ችግር ፈቺ ሃሳቦች ተደራሽ ማድረግ ፣ ስልጠና መስጠት ፣ ማርኬቲንግ፣ የስራ እድል መፍጠርና ለወጣቶች ስልጠና መስጠት ላይ ነው

በስምምነቱም ወቅት የኢትዮጵያ ቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኢንስቲትዩት ጀነራል ዳይሬክተር ዶ/ር ብሩክ ከድር "አሸዋ ቴክኖሎጂ ተጽዕኖ መፍጠር የቻለ፣ ለብዙ ሰዎች የሥራ እድል የፈጠረ፣ ከዚህ በፊት ሲደረግ ከነበረው ወጣ ባለ መንገድ እያመጣ ያለው ለውጥ የሚበረታታ ነው" በማለት ተናግረዋል። " ከእናተ ጋር መስራታችን እንፈልገዋለን። የሁለታችንን ግንኙነት እንዲዳብር ሃላፊነት ወስዳችሁ የሰራችሁ በሙሉ ምስጋና ይገባችኋል፤ ከአሸዋ ጋር ብዙ የምንሰራቸው ስራዎች አሉ " በማለት ገልጸዋል።

የአሸዋ ቴክኖሎጂ ሶሉሽን ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ዳንኤል በቀለ በበኩላቸው " አሸዋ ቴክኖሎጂ ለመንግስትና እና ለግል ተቋማት እየሰራቸው እና እያቀረባቸው ያለው የዌብሳይት ማበልጸጊያ (ነሃቢ)፣ ስማርት ኢአርፒ ፣ ሃይብሪድ ለርኒንግ፣ አስተማማኝ ክላውድ እና ሌሎች በርካታ ዌብ እና ሞባይል አፕ መፍትሄዎች አሰራርን ከዝልማዳዊ አካሄድ ወደ ዘመናዊ የቀየሩ ናቸው" ብለዋል።

የበለጠ ለማንበብ https://bit.ly/3YRQFiw

#Ashewatechnology #Partnership #SmartERP #WebsiteBuilder #CloudComputing #Softwaredevelopment
👍9❤1
አሸዋ ቴክኖሎጂ ከኢትዮጵያ ፋርማሲ ማህበር ጋር አብሮ ለመስራት ተፈራረመ።

አሸዋ ቴክኖሎጂ ከኢትዮጵያ ፋርማሲ ማህበር ጋር አብሮ መስራት በሚያስችላቸዉ ጉዳይ የመግባቢያ ሰነድ የፊርማ ስነ- ስርዓት አካሂዷል። የፊርማ ስነ-ስርአቱ የሁለቱም ተቋማት ከፍተኛ አመራሮች በተገኙበት አራት ኪሎ በሚገኘው የኢትዮጵያ ፋርማሲ ማህበር ዋና መስሪያ ቤት ተከናዉኗል። ተቋማቱ በዋናነትም የተፈራረሙት የቴክኖሎጂ ውጤቶችን ለማበልጸግ፣ የገበያ ትሥሥር ለመፍጠር እና በጋራ በመመካከር ስራዎችን ተደጋግፎ ለመስራት ነው።

ሙሉ መረጃውን ለማግኘት 👉 https://bit.ly/3VeZh0e

#ashewatechnology #Partnership #Erp #newthings #Ethiopia
👏8❤4👍3