TIKVAH-SPORT
246K subscribers
46.9K photos
1.48K videos
5 files
2.98K links
Download Telegram
ሪያል ማድሪድ እና ናፖሊ ድል ቀንቷቸዋል !

በአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ የጥሎ ማለፍ ጨዋታ ሪያል ማድሪድ ሊቨርፑልን 5ለ2 በሆነ ውጤት ሲያሸንፍ ናፖሊ በበኩሉ ፍራንክፈርትን 2ለ0 በሆነ ውጤት ማሸነፍ ችሏል።

- የሪያል ማድሪድን የማሸነፊያ ግቦች ቪንሰስ ጁንየር 2x ፣ ካሪም ቤንዜማ 2x እና ሚሊታኦ ሲያስቆጥሩ ለሊቨርፑል ግቦችን ሞሀመድ ሳላህ እና ኑኔዝ ከመረብ አሳርፈዋል።

- የናፖሊን የማሸነፊያ ግቦች ቪክተር ኦስሜን እና ሎሬንዞ ከመረብ ማሳረፍ ችለዋል።
 
- ሪያል ማድሪድ ከሊቨርፑል ጋር ያደረጋቸውን ያለፉት ሰባት ጨዋታዎች አልተሸነፈም #ስድስቱን ጨዋታዎች በአሸናፊነት ማጠናቀቅ ችሏል።

- የሊቨርፑል የፊት መስመር ተጨዋች ሞሀመድ ሳላህ በውድድር ዓመቱ #ስምንተኛ የአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ ግቡን ማስቆጠር ችሏል።

- ብራዚላዊው የሎስ ብላንኮዎቹ የፊት መስመር ተጨዋች ቪንሰስ ጁንየር ከሊቨርፑል ጋር ባደረጋቸው አራት ጨዋታዎች ላይ #አምስት ግቦች ከመረብ አሳርፏል።

- ሪያል ማድሪድ ሊቨርፑል ላይ በአውሮፓ ውድድሮች በሜዳው #ከአራት በላይ ግቦችን ማስቆጠር የቻለ የመጀመሪያው ክለብ መሆን ችሏል።

- የናፖሊው የፊት መስመር ተጨዋች ቪክቶር ኦስሜን በውድድር ዓመቱ ለናፖሊ ባደረጋቸው ሀያ አራት ጨዋታዎች ላይ #ሀያኛ ግቡን ከመረብ ማሳረፍ ችሏል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe