TIKVAH-SPORT
246K subscribers
46.8K photos
1.48K videos
5 files
2.97K links
Download Telegram
ሊቨርፑል ድል ቀንቶታል !

በእንግሊዝ ፕርሚየር ሊግ ሀያ ሶስተኛ ሳምንት መርሐ ግብር ሊቨርፑል ከ ኤቨርተን ጋር ያደረገውን የመርሲሳይድ ደርቢ ጨዋታ 2ለ0 በሆነ ውጤት ማሸነፍ ችሏል።

- የሊቨርፑልን የማሸነፊያ ግቦች ሞሀመድ ሳላህ እና ኮዲ ጋክፖ ከመረብ ማሳረፍ ችለዋል።

- ኮዲ ጋክፖ ለመርሲሳይዱ ክለብ ሊቨርፑል የመጀመሪያ ግቡን ከመረብ ማሳረፍ ችሏል።

- ሞሀመድ ሳላህ በውድድር ዓመቱ በሀያ ጨዋታዎች #ስምንተኛ የሊግ ግቡን ማስቆጠር ችሏል።

- ሊቨርፑል ማሸነፉን ተከትሎ ነጥቡን ሰላሳ ሁለት በማድረስ #ዘጠነኛ ደረጃ ላይ ሲቀመጥ ኤቨርተን በበኩሉ በአስራ ስምንት ነጥቦች አስራ ስምንተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል።

- በቀጣይ የሊጉ መርሐ ግብር ሊቨርፑል ከ #ኒውካስል_ዩናይትድ እንዲሁም ኤቨርተን ከ ሊድስ ዩናይትድ የሚገናኙ ይሆናል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
#PremierLeague 🇬🇬

ተወዳጁ የእንግሊዝ ፕርሚየር ሊግ በሳምንቱ መጨረሻ በተደረጉ ተጠባቂ ጨዋታዎች ተካሂደው ሲገባደዱ ያልተጠበቁ ውጤቶችን ተመዝገበው ተጠናቀዋል።

- ቼልሲ ከበርካታ ጨዋታዎች በኋላ በማሸነፍ ከ " TOP 4 " ደረጃ #በአስራ አንድ ነጥቦች ብቻ ርቀው አስረኛ ደረጃ ላይ መቀመጥ ችለዋል።

- አራተኛ ደረጃን ይዞ ለማጠናቀቅ #ቶተንሀም#ሊቨርፑል እና #ኒውካስል በቀጣይ የሊጉ መርሐ ግብር ብርቱ ፉክክር እንደሚያደርጉ ይጠበቃል።

- ላለመውረድ በሚደረገው ትንቅንቅ ከሀያ እስከ አስራ አምስተኛ ደረጃ ያሉ ክለቦች #በሶስት ነጥብ ብቻ ተራርቀው ይገኛሉ።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe