TIKVAH-SPORT
246K subscribers
46.8K photos
1.48K videos
5 files
2.97K links
Download Telegram
የእንግሊዝ ፕርሚየር ሊግ !

አሁን በወጣው መረጃ ባለፉት ሰባት ቀናት ለፕርሚየር ሊጉ ክለቦች በተደረገ የ ኮሮና ቫይረስ ምርመራ #ሰላሳ_ስድስት የቡድን አባላት በቫይረሱ መያዛቸው ይፋ ሆኗል ።

በሀገረ እንግሊዝ ዳግም እየተስፋፋ የመጣውን የኮቪድ ወረርሽኝ ተከትሎ ለሊጉ ክለቦች በሳምንት ሁለት ጊዜ ምርመራ እየተደረገላቸው እንደሆነ ተገልጿል ።

@tikvahethsport @kidusyoftahe
#አሳዛኝ_ዜና

ዛሬም በአትሌቶች ላይ የመኪና አደጋ ደርሶ ሆስፒታል ገብተዋል ።

ባለፈው እሁድ በመኪና አደጋ ህይወታቸው ያለፈውን አትሌቶች የቀብር ስነ-ስርዓት ላይ ለመገኘት በጉዞ ላይ የነበሩ #ሰላሳ አትሌቶች የተሳፈሩበት ቅጥቅጥ መኪና ጎማ ወልቆ በመብረሩ ምክንያት መኪና ተገልብጦ አደጋው መድረሱ ተገልጿል ።

➥ በአትሌቶቹ ላይ #ቀላል ጉዳት ነው የደረሰው

➥በአደጋው ጉዳት የደረሰባቸው አትሌቶች በአምቦ ሆስፒታል እየተረዱ ይገኛሉ።

[ በ @EthioRunner የቀረበ ]

@tikvahethsport @kidusyoftahe
ዩናይትዶች በ ሀትሪክ ታጅበው ድል ቀንቷቸዋል !

የ ራፋኤል ቫራንን ዝውወር ይፋ በማድረግ ጨዋታቸውን የጀመሩት ማንችስተር ዩናይትዶች የ ማርሴሎ ቤይልሳውን ሊድስ 5 ለ 1 በሆነ ውጤት በ መርታት ጅማሯቸውን የ ሰመረ አድርገዋል ።

• ፖርቹጋላዊው ቁልፍ ተጫዋች ብሩኖ ፈርናንዴዝ ለ ማንችስተር ዩናይትድ የ መጀመሪያ ሀትሪኩን መስራት ችሏል ።

• ፈረንሳዊው የ መሐል ሜዳ ተጫዋች ፖል ፖግባ አራት ለ ግብ የሚሆኑ ኳሶችን አመቻችቶ በ ማቀበል ሀትሪክ ሰርቷል ።

• ሜሰን ግሪንውድ ለ ማንችስተር ዩናይትድ ያስቆጠረውን ግብ ወደ #ሰላሳ ከፍ አድርጓል ።

• ፖል ፖግባ ለ ግብ የሚሆን ኳስ አመቻችቶ በ ማቀበል በ ሊጉ ሀትሪክ ሲሰራ የ መጀመሪያው ነው ።

• የ ሊድስ ዩናይትድን ብቸኛ ግብ ያስቆጠረው ሉክ ኤይሊንግ የ መጀመሪያ የ ፕርሚየር ሊግ ጎሉ ሆኗል ።

• ፖል ፖግባ ባለፉት ሁለት የ ውድድር ዓመት ካስመዘገበው ለ ግብ የሚሆኑ ኳሶች የበለጠ በ ዘንድሮው የውድድር ዓመት ከወዲሁ ማስመዝገብ ችሏል ።

• ብሩኖ ፈርናንዴዝ በ #ሊጉ የመጀመሪያ ሳምንት ጨዋታ ሀትሪክ መስራት የቻለ #አስረኛው ተጫዋች ሆኗል ።

• ብሩኖ ፈርናንዴዝ በ ሊጉ የመጀመሪያ ሳምንት ጨዋታ ሀትሪክ መስራት የቻለ የ መጀመሪያው የ #ክለቡ ተጫዋች ለመሆን በቅቷል ።

• አዲሱ የ ክለቡ ፈራሚ ጀዳን ሳንቾ ተቀይሮ በመግባት የ መጀመሪያ ጨዋታውን አድርጓል ።

• ማንችስተር ዩናይትድ በ #ወቅታዊ ውጤት የ ሊጉን የ ደረጃ ሰንጠረዥ ለመምራት ችለዋል ።

@tikvahethsport @kidusyoftahe
ተስፈኛው የ ኤሲ ሚላን ኮከብ !

የ አስራ ሶስት አመቱ የ ኤሲ ሚላን ታዳጊ የ ፊት መስመር አጥቂ ፍራንሲስኮ ካማራዳ በ ሚላን የ ወጣቶች ቡድን ላይ ድንቅ ብቃቱን እያሳየ ይገኛል ።

ተስፈኛ ታዳጊው ፍራንሲስኮ ካማራዳ 87 #ጨዋታዎችን ብቻ ሲያደርግ ያስቆጠረው ጎል ደግሞ 483 መሆኑ ከወዲሁ በርካቶች እይታ ውስጥ እንዲገባ አድርጎታል ።

➡️ 2017 / 18 :- በ #አርባ ጨዋታዎች 247 ጎሎች

➡️ 2018 /19 :- በ #ሰላሳ_አንድ ጨዋታዎች 172 ጎሎች

➡️ 2019 / 20 :- በ #አስራ_ስድስት ጨዋታዎች 64 ጎሎችን ሲያስቆጥር በ አማካይ በ አንድ ጨዋታ #አምስት ጎሎችን እንደሚያስቆጥር ተነግሯል ።

@tikvahethsport @kidusyoftahe
#Ballon_d'Or

የ ዘንድሮው የውድድር ዓመት የ ባሎን ዶር እጩ #ሰላሳ ተጫዋቾች ዝርዝር በዛሬው ዕለት ይፋ ይደረጋሉ ።

የዘንድሮውን የ ባሎን ዶር ማን የሚያሸነፍ ይመስልዎታል ?

@tikvahethsport @kidusyoftahe
#QatarWorldCup 🇶🇦

የሞሮኮ ግዙፉ የአየር መንገድ ተቋም ሮያል ኤር ማሮክ ብሔራዊ ቡድኑ በግማሽ ፍፃሜው ከፈረንሳይ አቻቸው ጋር ለሚያደርጉት ጨዋታ #ሰላሳ በረራዎችን ማዘጋጀታቸው ተገልጿል።

ለዕሮቡ ጨዋታ ከ #ካሳብላንካ ወደ #ዶሀ ሰላሳ በረራዎች ሲደረጉ በአንድ በራራ 200 ተሳፋሪዎች እንደሚጓጓዙ ተዘግቧል።

የሞሮኮ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ከሀገር በቀሉ የአየር መንገድ ሮያል ኤር ማሮክ ጋር በቅርበት ሲሰራ ለጨዋታው የሚጓጓዝ አንድ ደጋፊ ለደርሶ መልስ 475 የአሜሪካ ዶላር የሚከፍል ይሆናል።

@tikvahethsport @kidusyoftahe
ኢትዮጵያ መድን የሊጉን መሪነት ተረክቧል !

በቤት ኪንግ የኢትዮጵያ ፕርሚየር ሊግ አስራ አምስተኛ ሳምንት መርሐ ግብር ኢትዮጵያ መድን ከ ሀድያ ሆሳዕና ጋር ያደረገውን ጨዋታ 1ለ0 በሆነ ውጤት አሸንፏል።

- ኢትዮጵያ መድን የማሸነፊያ ግብ ያሬድ ደርዛ በመጨዋታው መጠናቀቂያ 90+5 ደቂቃ ላይ ማስቆጠር ችሏል።

- ኢትዮጵያ መድን ማሸነፉን ተከትሎ የሊጉን መሪነት ከቅዱስ ጊዮርጊስ መረከብ ችሏል።

- በጨዋታው የሀድያ ሆሳዕናው ተጨዋች ፍሬዘር ካሳ በቀይ ካርድ ከሜዳ ተሰናብቷል።

- ሀድያ ሆሳዕናዎች ባለፉት ተከታታይ ስምንት የሊግ ጨዋታዎች ላይ ግብ ማስቆጠር ሳይችሉ ቀርተዋል።

- በውድድር ዓመቱ ሀድያ ሆሳዕና ያለፉትን ስድስት ተከታታይ የሊግ ጨዋታዎች ማሸነፍ አልቻሉም።

- ኢትዮጵያ መድን በሊጉ ደረጃ ሰንጠረዥ #ሰላሳ ነጥቦችን በመሰብሰብ #አንደኛ ደረጃ ላይ ሲቀመጥ ሀድያ ሆሳዕና በሀያ አንድ ነጥቦች አራተኛ ደረጃን ይዟል።

- በቀጣይ የሊጉ መርሐ ግብር ኢትዮጵያ መድን ከቅዱስ ጊዮርጊስ እንዲሁም ሀድያ ሆሳዕና ከ መቻል የሚገናኙ ይሆናል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
#ETHIOPIA 🇪🇹

በላቲቪያ ሪጋ በተካሄደው የአለም የጎዳና ላይ ሻምፒዮና የግማሽ ማራቶን ውድድር በሁለቱም ፆታዎች የተሳተፉት ኢትዮጵያዊያን አትሌቶች የሜዳልያ ደረጃ ውስጥ ሳይገቡ ቀርተዋል።

በሴቶች ውድድር ከኬንያውያን አትሌቶች ጋር ብርቱ ፉክክር ያደረገችው አትሌት ጽጌ ገ/ሰላማ አራተኛ ደረጃን ይዛ ስታጠናቅቅ ያለምጌጥ ያረጋል ስድስተኛ እንዲሁም ፍታው ዘርዬ ሀያ ስምንተኛ ደረጃን ይዘው አጠናቀዋል።

በወንዶች የግማሽ ማራቶን ውድድር አትሌት ጀማል ይመር አራተኛ ፣ አትሌት ንብረት መላክ ሰባተኛ እንዲሁም አትሌት ፀጋዬ ኪዳኑ አስረኛ ደረጃን በመያዝ ማጠናቀቅ ችለዋል።

የግማሽ ማራቶን ውድድሩን በሁለቱም ፆታዎች ኬንያውያን አትሌቶች ከአንድ እስከ ሶስት ያለውን ደረጃ በመያዝ በበላይነት ማጠናቀቅ ችለዋል።

በዚህ ውድድር አሸናፊዎች ምን ያህል ያገኛሉ ?

1️⃣ኛ. #ሰላሳ ሺህ ዶላር

2️⃣ኛ. አስራ አምስት ሺህ ዶላር

3️⃣ኛ. አስራ ሁለት ሺህ ዶላር

4️⃣ኛ. ዘጠኝ ሺህ ዶላር

5️⃣ኛ. ስምንት ሺህ ዶላር

6️⃣ኛ. ሰባት ሺህ ዶላር

7️⃣ኛ. ስድስት ሺህ ዶላር

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
የማድሪድ ተጨዋቾች ስንት ትኬቶች ያገኛሉ ?

የሪያል ማድሪድ ተጨዋቾች ለምሽቱ የአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ ፍፃሜ ጨዋታ ሁለት ነፃ የስታዲየም መግቢያ ትኬቶች እንደሚሰጣቸው ተገልጿል።

በተጨማሪም #ሰላሳ በገንዘብ የሚቀርቡ የስታዲየም መግቢያ ትኬቶች አጠቃላይ ሰላሳ ሁለት ትኬቶች ለተጨዋቾቹ እንደሚቀርብላቸው ተነግሯል።

እያንዳንዱ የሪያል ማድሪድ ተጨዋች ለስታዲየም መግቢያ ትኬቶች 12,300 ዩሮ ወጪ ማድረጋቸው ሲገለፅ ሁሉንም ትኬቶች ለቤተሰባቸው እና ጓደኞቻቸው መስጠታቸው ተገልጿል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe