TIKVAH-SPORT
246K subscribers
46.9K photos
1.48K videos
5 files
2.98K links
Download Telegram
#Budapest 🇪🇹

በሀንጋሪ ቡዳፔስት ከተማ በሚደረገው በዘንድሮው የ2023 የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ላይ የሚሳተፈው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ልኡካን ቡድን የሽኝት መርሐ ግብር እንደተዘጋጀለት ተገልጿል።

ይህንንም ተከትሎ የፊታችን እሁድ ነሀሴ 7/2015 ዓ.ም በሀይሌ ግራንድ ሆቴል የሽኝት መርሐ ግብሩ እንደሚካሄድ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን አስታውቋል።

የ2023ቱ የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና በሀንጋሪ ቡዳፔስት ከተማ ከነሀሴ 13/2015 ዓ.ም እስከ ከነሀሴ 21/2015 ዓ.ም ይካሄዳል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
#Budapest 🇪🇹

ሀገራችን ኢትዮጵያ ደማቅ ታሪክ ከምትፅፍባቸው ውድድር አንዱ የሆነው የአለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና በቡዳፔሽት ሀንጋሪ ሊጀምር የአራት ቀናት እድሜ ብቻ ቀርተውታል።

የውድድሩ አዘጋጅ ሀገር ሀንጋሪ በአለም ሻምፒዮናው ስልሳ ሶስት አትሌቶችን በማሰለፍ ቀዳሚው ሀገር ትሆናለች። በተጨማሪም ከአርባ ዘጠኝ ውድድሮች ውስጥ በአርባ አራቱ የሀንጋሪ አትሌቶች እንደሚካፉሉ የአለም አትሌቲክስ አሳውቋል።

🥇 ውድድሩ ቅዳሜ ሲጀምር በመጀመሪያ ቀን #የፍፃሜ ውድድር ሀገራችን ከምሽቱ 3:55 ተጠባቂ የ 10,000ሜትር ሴቶች ፉክክር አትሌቶቻችን ይጠበቃሉ።

የ 10,000ሜትር ሴቶች የአለም ሪከርድ ( 29:01.03 ) በኢትዮጵያዊቷ አትሌታችን ለተሰንበት ግደይ ስር ይገኛል።

10,000ሜትር ሴቶች ሀገራችን በማን ትወከላለች ?

1. ለተሰንበት ግደይ :- 29:01.03 ( የግል ምርጥ ሰዓት )

2. ጉዳፍ ፀጋይ :- 29:29.73 ( የግል ምርጥ ሰዓት )

3. እጅጋየሁ ታዬ :- 29:57.45 ( የግል ምርጥ ሰዓት

4. ለምለም ሀይሉ :- 29:59.15 ( የግል ምርጥ ሰዓት )

5. ሚዛን አለም ( ተጠባባቂ ) :- 29:59.03 ( የግል ምርጥ ሰዓት )

ተጠባቂ ተፎካካሪ አትሌት ማነው ?

- በሶስት ርቀቶች በዘንድሮው የአለም ሻምፒዮና የምትካፈለው ሲፋን ሀሰን በ 10,000ሜትር ውድድር ላይ ዳግም ተጠባቂዋ አትሌት ነች።

- ሲፋን ሀሰን በመክፈቻው ዕለት በቅድሚያ በ 1500ሜትር ማጣርያ በመቀጠልም 10,000ሜትር ፍፃሜ የምትወዳደር ይሆናል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
#Budapest 🇪🇹

ከጥቂት ሰዓታት በኋላ በሚጀምረው 19ኛው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ላይ አዳዲስ ነገሮች ተግባራዊ እንደሚሆኑ ተገልጿል።

ከእነዚህም መካከል :-

- ከ 800 ሜትር በላይ ባሉ የማጣሪያ ውድድሮች ቀጣዩን ዙር የሚቀላቀሉ አትሌቶች የሚለዩት ከሁሉም የውድድር ምድቦች በሚያስመዘግቡት ደረጃ #ብቻ ሆኗል።

- የውድድሩ አሸናፊ አትሌት አሰልጣኞች በተመሳሳይ የሜዳሊያ ሽልማት የሚበረከትላቸው ይሆናል።

- የ1,500ሜትር ፣ 3,000መሰናክል እና 5,000 ሜትር ማጣሪያ ተወዳዳሪዎች ቀጣዩን ዙር የሚቀላቀሉት በሚያስመዘግቡት #ደረጃ ብቻ ይሆናል።

- ይህም ከዚህ ቀደም በነበሩ የዓለም ሻምፒዮናዎች ላይ የተሻለ ሰዓት ያላቸው አትሌቶች ወደ ቀጣዩ ዙር የሚያሳልፈውን አሰራር #ያስቀረ ሆኗል።

የአዲሱ ህግ ሙሉ መረጃ ከላይ በምስሉ ላይ ተያይዟል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
TIKVAH-SPORT
ኢትዮጵያ ዛሬ በማን ትወከላለች ? 1⃣ - 3000ሜትር መሰናክል ወንዶች ማጣርያ  👉 ጌትነህ ዋለ ( ምድብ አንድ ) ፣ አብርሀም ስሜ ( ምድብ ሁለት ) እና ለሜቻ ግርማ ( ምድብ አራት ) 🇪🇹 አትሌት ለሜቻ ግርማ የወቅቱ የአለም እና የኦሎምፒክ ( ቶኪዮ ) የብር ሜዳሊያ አሸናፊ ሲሆን በዚህ ርቀት አዲስ ታሪክ ይፅፋል ተብሎ ይጠበቃል። በዚህ የማጣርያ ውድድር ከምድቡ ቀዳሚውን #አምስት ደረጃዎች…
#Budapest 🇪🇹

የ 19ኛው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ከጠዋቱ 2:00 ሰዓት ጀምሮ ሊካሄድ የነበረ ቢሆንም በዝናብ ምክንያት የጠዋት ውድድሮች የሰዓት ሽግሽግ እንደተደረገባቸው ተገልጿል።

ይህንንም ተከትሎ የጠዋት ውድድሮች ከሰዓታት በኋላ 4:50 ላይ ጅማሮውን አድርጎ 9:45 ላይ እንደሚጠናቀቅ አወዳዳሪው አካል ይፋ አድርጓል።

የምሽት ውድድሮች አስቀድሞ በተያዘለት የሰዓት መርሐ ግብር የሚከናወን ይሆናል።

የተሻሻለው የኢትዮጵያ 🇪🇹 መርሐ ግብር ሰዓት :-

- ከሰዓት 7:35 :- የ3000 ሜትር ወንዶች መሰናክል ማጣርያ

- ከሰዓት 9:15 :- የ1500 ሜትር ሴቶች ማጣርያ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
#Budapest 🇪🇹

በዛሬው ዕለት ጅማሮውን ባደረገው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ኢትዮጵያዊያን አትሌቶች የ 3,000 ሜትር መሰናክል ወንዶች ማጣሪያ ውድድራቸውን ማድረግ ችለዋል።

በውድድሩ የመጀመሪያ ምድብ የተካፈለው ኢትዮጵያዊ አትሌት ጌትነት ዋለ ውድድሩን 8:19.99 በሆነ ሰዓት በመግባት በአንደኝነት አጠናቆ ለፍፃሜ ማለፍ ችሏል።

በምድብ ሁለት የተካፈለው ኢትዮጵያዊ አትሌት አብርሃም ስሜ ውድድሩን ስምንተኛ ደረጃን በመያዝ ማጠናቀቁን ተከትሎ ለፍፃሜ ማለፍ ሳይችል ቀርቷል።

በመጨረሻው ምድብ የተወዳደረው ኢትዮጵያዊ አትሌት ለሜቻ ግርማ ውድድሩን በበላይነት በማጠናቀቅ ለፍፃሜ ማለፉን ማረጋገጥ ችሏል።

የ3,000 ሜትር መሰናክል ወንዶች የፍፃሜ ውድድር የፊታችን ማክሰኞ ምሽት 4:42 የሚደረግ ይሆናል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
#Budapest 🇪🇹

19ኛው የአለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና በዛሬው ዕለት በሀንጋሪ ቡዳፔሽት መካሄዱን በይፋ የጀመረ ሲሆን ሀገራችን ኢትዮጵያ ታሪካዊውን 100ኛ ሜዳሊያዋን በዚህ መድረክ ታሳካለች ተብሎ ይጠበቃል።

የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ቡድን ባለፉት አስራ ስምንት የአለም ሻምፒዮናዎች ተሳታፊ የነበረ ሲሆን  ከአንዱ #በስተቀር በሁሉም ሻምፒዮናዎች ላይ በሜዳልያ ሰንጠረዥ ውስጥ ገብታለች፡፡

ሀገራችን ምን ያህል ሜዳሊያዎችን አግኝታለች ?

🥇ወርቅ  :- ሀገራችን በድምሩ በአለም ሻምፒዮናው 33 የወርቅ ሜዳልያዎችን በአስራ ዘጠኝ አትሌቶቿ አሳክታለች።

ከነዚህም መካከል :-

1. ቀነኒሳ በቀለ እና ጥሩነሽ ዲባባ አምስት ወርቆችን ( በድምሩ አስር )

2. ሀይሌ ገብረሥላሴ :- አራት ወርቅ

3. መሰረት ደፋር ፣ ሙክታር እድሪስ እና አልማዝ አያና እያንዳንዳቸው ሁለት ወርቆችን ለሀገራቸው አስገኝተዋል።

🥈ብር :- ሰላሳ አራት የብር ሜዳልያዎች በሀያ ስምንት አትሌቶች ተገኝተዋል።

🥉ነሐስ :- ሀያ ስምንት የነሐስ ሜዳልያዎችን በሀያ አምስት አትሌቶቻችን መገኘት ችሏል፡፡

በ19ኛው የአለም ሻምፒዮና 100ኛውን ታሪካዊ ሜዳሊያ የሚያሳካው አትሌት ማን ይሆናል ብለው ያስባሉ ❓

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
#Budapest 🇪🇹

19ኛው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና መደረጉን ሲቀጥል ኢትዮጵያዊያን አትሌቶች የ 1,500 ሜትር ሴቶች ማጣሪያ ውድድራቸውን አድርገው ሁሉም ግማሽ ፍፃሜውን ተቀላቅለዋል።

በውድድሩ ሁለተኛ ምድብ የተካፈለችው ኢትዮጵያዊት አትሌት ድርቤ ወልተጂ ውድድሯን በሁለተኝነት በማጠናቀቅ ግማሽ ፍፃሜውን መቀላቀል ችላለች።

በሶስተኛው ምድብ የተወዳደረችው ኢትዮጵያዊት አትሌት ብርቄ ኃየሎም ውድድሯን በሶስተኛነት በማጠናቀቅ ግማሽ ፍፃሜውን ተቀላቅላለች።

በመጨረሻው ምድብ የተወዳደረችው ኢትዮጵያዊት አትሌት ሂሩት መሸሻ በበኩሏ ውድድሯን በበላይነት በማጠናቀቅ ግማሽ ፍፃሜውን የተቀላቀለች ሶስተኛ ኢትዮጵያዊት አትሌት ሆናለች።

የ1500 ሜትር ሴቶችች የግማሽ ፍፃሜ ውድድር በነገው ዕለት አመሻሽ 12:05 የሚደረግ ይሆናል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
#Budapest 🇪🇹 እንኳን ደስ አለን 🇪🇹

በ2023ቱ የአለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና የ10,000 ሜትር ሴቶች ፍፃሜ ውድድር ኢትዮጵያዊያን አትሌቶች ለሀገራችን የመጀመሪያ ሜዳልያ ተከታትለው በመግባት ማስመዝገብ ችለዋል።

ኢትዮጵያዊቷ አትሌት ጉዳፍ ፀጋዬ ውድድሩን በበላይነት ስታጠናቅቅ ለተሰንበት ግደይ ሁለተኛ እጅጋየሁ ታዬ ሶስተኛ ደረጃን ይዘው ማጠናቀቅ ችለዋል።

🥇ጉዳፍ ፀጋዬ 🇪🇹🇪🇹
🥈ለተሰንበት ግደይ 🇪🇹🇪🇹
🥉እጅጋየሁ ታዬ 🇪🇹🇪🇹

🇪🇹🇪🇹 እንኳን ደስ አለን 🇪🇹🇪🇹

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
#Budapest 🇪🇹

19ኛው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና በሁለተኛ ቀን ውሎ አትሌቶቻችን ከቀትር በኋላ ተጠባቂ ውድድራቸውን በቡዳፔሽት የአትሌቲክ ሴንተር ያደርጋሉ።

👉 ምሽት 12:05 :-  የ 1500ሜ ሴቶች ግማሽ ፍፃሜ ( ሂሩት መሸም ፣ ድርቤ ወልተጂ እና ብርቄ ሀየሎም )

👉 ምሽት 1:25 :- የ 10,000ሜ ወንዶች ፍፃሜ

ተወዳዳሪዎቻችን እነማን ናቸው ?

- በሪሁ አረጋዊ ፣ ሰለሞን ባረጋ ፣ ይስማው ድሉ እና ታደሰ ወርቁ ( ተጠባባቂ )

በወንዶች 10,000ሜ ሀገራችን ወርቅ ያመጣችው በ 2011 በዴጉ የዓለም ሻምፒዮና በኢብራሂም ጄይላን አማካኝነት ነበር።

🇪🇹🇪🇹🇪🇹 የዕለቱ የምሽት ውድድሮች ከመጀመሩ አስቀድሞ አረንጓዴውን ጓርፍ ያሳኩት አትሌቶቻችን እና አሰልጣኞች ሜዳሊያዎቻቸው ይረከባሉ።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
#Budapest 🇪🇹 እንኳን ደስ አለን 🇪🇹

በ2023ቱ የአለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና የ10,000 ሜትር ወንዶች ፍፃሜ ውድድር ኢትዮጵያዊው አትሌት ሰለሞን ባረጋ ለሀገራችን የነሀስ ሜዳልያ ማስመዝገብ ችሏል።

አትሌት ሰለሞን ባረጋ ለሀገራችን ኢትዮጵያ ሁለተኛውን የነሀስ ሜዳልያ ማስመዝገብ ችሏል።

በርቀቱ የተሳተፈው ሌላኛው ኢትዮጵያዊ አትሌት በረሁ አረጋዊ ውድድሩን አራተኛ ደረጃን በመያዝ ማጠናቀቅ ችሏል።

ውድድሩን ኡጋንዳዊ አትሌት ጆሹዋ ቺፕቴጌ በበላይነት ሲያጠናቅቅ ኬንያዊው ሁለተኛ ደረጃን ይዞ አጠናቋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
#Budapest 🇪🇹

በሀንጋሪ ቡዳፔሽት መደረጉን በቀጠለው 19ኛው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና አራተኛ ቀን ውሎ አትሌቶቻችን ምሽት ላይ ተጠባቂ የፍፃሜ ውድድራቸውን በቡዳፔሽት የአትሌቲክ ማዕከል ያደርጋሉ።

የዛሬ ተጠባቂ ውድድሮች :-

👉 ምሽት 4:30 :-  የ 1500ሜ ሴቶች ፍፃሜ

👉 ምሽት 4:42 :- የ 3000ሜ መሰናክል ወንዶች ፍፃሜ

ተወዳዳሪዎቻችን እነማን ናቸው ?

- በ1500ሜ ሴቶች ፍፃሜ ( አትሌት ድርቤ ወልተጂ እና ብርቄ ሀየሎም )

- በ1500ሜ ሴቶች ውድድር ኢትዮጵያዊያን አትሌቶች ለኔዘርላንድ ከምትሮጠው ትውልደ ኢትዮጵያዊት አትሌት ሲፋን ሀሰን ጋር ብርቱ ፉክክር ያደርጋሉ ተብሎ ይጠበቃል።

- የ 3000ሜ መሰናክል ወንዶች ፍፃሜ ( አትሌት ጌትነት ዋለ እና ለሜቻ ግርማ )

በርቀቱ ከዚህ በፊት ለሀገራችን አራት የብር ሜዳልያዎችን ማስመዝገብ የቻለው አትሌት ለሜቻ ግርማ ዛሬ የሚያሸንፍ ከሆን በዓለም ሻምፒዮና ታሪክ ለሀገራችን የመጀመሪያው ወርቅ ሆኖ ይመዘገባል።

ለሜቻ በርቀቱ ያለው ውጤት ምን ይመስላል ?

2019 :- የዶሀው የዓለም ሻምፒዮና 🥈

2021 :- ቶኪዮ ኦሎምፒክ 🥈

2022 :- የቤልጋሬድ የቤት ውስጥ ሻምፒዮና 🥈

2022 :- ኦሬጎን የዓለም ሻምፒዮና 🥈

መልካም ዕድል ለአትሌቶቻችን 🇪🇹🇪🇹🇪🇹

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
#Budapest 🇪🇹 እንኳን ደስ አለን 🇪🇹

በ2023ቱ የአለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና የ 3000ሜ መሰናክል ወንዶች ፍፃሜ ውድድር ኢትዮጵያዊው አትሌት ለሜቻ ግርማ ለሀገራችን የብር ሜዳልያ ማስመዝገብ ችሏል።

ሀገራችን ኢትዮጵያ በአለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ውድድር ታሪክ በአትሌት ለሜቻ ግርማ አማካኝነት 101ኛ ሜዳልያዋን ማስመዝገብ ችላለች።

ውድድሩን ሞሯኳዊው አትሌት ኤል ባካሊ በአንደኝነት ሲያጠናቅቅ ኬንያዊው ሶስተኛ ደረጃን ይዟል።

ሀገራችን ኢትዮጵያ በዛሬው ዕለት ሁለት የብር ሜዳልያዎች ማስመዝገቧን ተከትሎ በውድድሩ ያላትን የሜዳልያ ቁጥር ወደ ስድስት ከፍ ማድረግ ችላለች።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
#Budapest 🇪🇹

አምስተኛ ቀኑ ላይ የደረሰው 19ኛው የዓለም ሻምፒዮና በዛሬው ዕለት ሀገራችን በሶስት ማጣርያ ውድድሮች ላይ የሚካፈሉ ይሆናል።

በዚህም መሰረት :-

ከቀኑ 5:05 800ሜ ሴቶች ማጣርያ ( ሀብታሙ አለሙ ፣ ወርቅነሽ መለሰ እና ትዕግስት ግርማ

ከምሽቱ 2:02 5000ሜ ሴቶች ማጣርያ ( ጉዳፍ ፀጋይ ፣ እጅጋየሁ ታዬ ፣ መዲና ኢሳ እና ፍሬወይኒ ሀይሉ

ከምሽቱ 2:45 3000ሜ ሴቶች መሰናክል ማጣርያ ( ሲምቦ አለማየው፣ ዘርፌ ወንድማገኝ ፣ሎሚ ሙለታ እና መቅደስ አበበ )

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#Budapest 🇪🇹

የቶኪዮ ኦሎምፒክ ሻምፒዮናው አትሌት ሰለሞን ባረጋ በአለም ሻምፒዮናው የነሐስ ሜዳሊያ ማግኘቱን ተከትሎ ከውድድሩ በኋላ በከፍተኛ ሀዘን ውስጥ እና በእምባ ታጅቦ ታይቷል።

በተለይም ከውድድሩ መጠናቀቅ በኋላ የቡድኑ አመራሮች አትሌቶቹን ሲያፅናኑ ታይተዋል። ሰለሞን ባረጋ ሀሳቡ ለሀገሩ ወርቅ ማምጣት እንደነበረ በዕለቱ መናገሩ የሚታወስ ነው።

📽 ሀይሌእግዚአብሔር አድሀኖም

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
#Budapest 🇪🇹

ስድስተኛ ቀኑ ላይ የደረሰው አስራ ዘጠነኛው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና በዛሬው ዕለትም በሀንጋሪ ቡዳፔሽት ቀጥሎ ሲደረግ ሀገራችን በአንድ የማጣርያ ውድድር ላይ የምትካፈል ይሆናል።

በዚህም መሰረት :-

👉 ከምሽቱ 2:00 :- 5000ሜ ወንዶች ማጣርያ ውድድር

ሀገራችንን እነማን ይወክሏታል ?

- አትሌት ዮሚፍ ቀጀልቻ
- አትሌት በሪሁ አረጋዊ
- አትሌት ሀጎስ ገብረህይወት

ሀገራችን ኢትዮጵያ በአለም ሻምፒዮናው እስካሁን ባደረገቻቸው የፍፃሜ ውድድሮች አንድ የወርቅ ፣ ሶስት የብር እና ሁለት የነሀስ ሜዳልያዎች ማሳካት ችላለች።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
#Budapest 🇪🇹

በሀንጋሪ ቡዳፔሽት ከተማ እየተካሄደ የሚገኘው 19ኛው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ውድድር ሰባተኛ ቀኑን ሲይዝ ዛሬ ምሽትም ኢትዮጵያ የምትወከልበት የሴቶች 800ሜ ግማሽ ፍፃሜ ውድድር ይደረጋል።

የዛሬ ተጠባቂ ውድድር :-

👉 ምሽት 3:25 :- የሴቶች 800ሜ ግማሽ ፍፃሜ ውድድር

ኢትዮጵያ በማን ትወከላለች ?

- አትሌት ወርቅነሽ መለሰ

- አትሌት ሀብታም አለሙ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
#Budapest 🇪🇹

በ2023ቱ የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና የሴቶች 5000ሜ ፍፃሜ ውድድር ሲካሄድ ኢትዮጵያዊያን አትሌቶች ድል ሳይቀናቸው ቀርቷል።

ውድድሩን ኬንያዊቷ አትሌት ኪፕዬጎን በበላይነት ስታጠናቅቀው ትውልደ ኢትዮጵያዊቷ ሲፋን ሀሰን ሁለተኛ ደረጃን ኬንያዊቷ ቼቤት ሶስተኛ ደረጃን ይዘው አጠናቀዋል።

ኢትዮጵያዊያን አትሌቶች እጅጋየሁ ታዬ ፣ መዲና ኢሳ እና ፍሬወይኒ ሀይሉ አምስት ፣ ስድስት እና ሰባት ደረጃዎችን በመያዝ ማጠናቀቅ ችለዋል።

የ10,000ሜ የወርቅ ሜዳልያ አሸናፊዋ አትሌት ጉዳፍ ፀጋዬ አስራ ሶስተኛ ደረጃን ይዛ ማጠናቀቅ ችላለች።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
#Budapest 🇪🇹

በ2023ቱ የአለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና የወንዶች ማራቶን ውድድር ኢትዮጵያዊው አትሌት ልዑል ገብረ ስላሴ ሶስተኛ ደረጃን ይዞ በማጠናቀቅ ለሀገራችን ሶስተኛውን የነሀስ ሜዳልያ ማስመዝገብ ችሏል።

ውድድሩን ዩጋንዳዊው አትሌት ኪፕላንጋት በበላይነት ሲያጠናቅቀው እስራኤላዊው ማሩ ተፈሪ ሁለተኛ ደረጃን በመያዝ ማጠናቀቅ ችሏል።

በውድድሩ የተሳተፉት ሌሎች ኢትዮጵያዊያን አትሌቶች ሚልኬሳ መንገሻ 6ኛ ፣ ፀጋዬ ጌታቸው 17ኛ ደረጃን ይዘው ማጠናቀቅ ችለዋል።

የባለፈው አመት የአለም ሻምፒዮን ኢትዮጵያዊ አትሌት ታምራት ቶላ ውድድሩን ለማቋረጥ ተገዷል።

ሀገራችን ኢትዮጵያ በዛሬው ዕለት አንድ ሜዳልያ ማስመዝገቧን ተከትሎ በውድድሩ ያላትን የሜዳልያ ቁጥር ወደ #ዘጠኝ ከፍ ማድረግ ችላለች።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
#Budapest 🇪🇹

በ2023ቱ የአለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ውድድር የወንዶች የ5000ሜ ውድድር ሲካሄድ በውድድሩ የተካፈሉት ኢትዮጵያዊያን አትሌቶች ድል ሳይቀናቸው ቀርቷል።

በውድድሩ የተካፈሉት ኢትዮጵያዊያን አትሌቶች ዮሚፍ ቀጀልቻ 5ኛ ፣ ሀጎስ ገብረህይወት 6ኛ እንዲሁም በሪሁ አረጋዊ 8ኛ ደረጃን ይዘው አጠናቀዋል።

ውድድሩን ኔርዌያዊው አትሌት ጃቆብ ኢንገብሪግሴን በበላይነት ሲያጠናቅቀው ስፔናዊው መሐመድ ሁለተኛ ኬንያዊው ክሮፕ ሶስተኛ ደረጃን ይዘው ማጠናቀቅ ችለዋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
#Budapest 🇪🇹

በ2023ቱ የአለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ውድድር የሴቶች 3000ሜ መሰናክል ውድድር ሲካሄድ በውድድሩ የተካፈሉት ኢትዮጵያዊያን አትሌቶች ድል ሳይቀናቸው ቀርቷል።

በውድድሩ የተካፈሉት ኢትዮጵያዊያን አትሌቶች ዘርፌ ወንድማገኝ 4ኛ ፣ ሎሚ ሙለታ 12ኛ እንዲሁም ሲምቦ አለማየሁ 13ኛ ደረጃን ይዛ ማጠናቀቅ ችላለች።

ውድድሩን ባህሬናዊቷ አትሌት ጃቆብ በበላይነት ስታጠናቅቀው ኬንያዊያኑ አትሌቶች ሁለተኛ እና ሶስተኛ ደረጃን ይዘው ማጠናቀቅ ችለዋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe