ኢትዮጵያ በዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ታሪኳ 100ኛውን ሜዳሊያ ማግኘት ችላለች።
ኢትዮጵያ በተሳተፈችባቸው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና በታሪኳ 100ኛ የሆነውን ሜዳሊያ አትሌት ድርቤ ወልተጂ አማካኝነት ማግኘት ችላለች።
አትሌት ድርቤ ወልተጂ ዛሬ ምሽት በተካሄደው የ1500 ሜትር የሴቶች ፍጻሜ ውድድር በሁለተኛ ደረጃ በማጠናቀቅ ለሀገሯ የብር ሜዳሊያ አስገኝታለች።
ከዚህ ቀደም በነበሩት የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ኢትዮጵያ 95 ሜዳሊያዎችን በአትሌቶቿ አማካኝነት ማግኘት ችላ ነበር።
አሁን እየተደረገ በሚገኘው የቡዳፔሽቱ የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና እስካሁን ባለው በ1 ወርቅ፣ በ2 ብር፣ በ2 ነሐስ ከዓለም በሦስተኛ ደረጃ ላይ ትገኛለች።
@tikvahethsport @kidusyoftahe

3000ሜ መሰናክል ወንዶች ፍፃሜ ጀምሯል !
ኢትዮጵያውያን አትሌቶች የሚጠበቁበት የ 3000ሜ መሰናክል ወንዶች ፍፃሜ ውድድር መደረጉን ጀምሯል።
ሀገራችን ኢትዮጵያ በአትሌት ጌትነት ዋለ እና ለሜቻ ግርማ ተወክላለች
መልካም ዕድል ለአትሌቶቻችን 🇪🇹🇪🇹

#Budapest 🇪🇹 እንኳን ደስ አለን 🇪🇹
በ2023ቱ የአለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና የ 3000ሜ መሰናክል ወንዶች ፍፃሜ ውድድር ኢትዮጵያዊው አትሌት ለሜቻ ግርማ ለሀገራችን የብር ሜዳልያ ማስመዝገብ ችሏል።
ሀገራችን ኢትዮጵያ በአለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ውድድር ታሪክ በአትሌት ለሜቻ ግርማ አማካኝነት 101ኛ ሜዳልያዋን ማስመዝገብ ችላለች።
ውድድሩን ሞሯኳዊው አትሌት ኤል ባካሊ በአንደኝነት ሲያጠናቅቅ ኬንያዊው ሶስተኛ ደረጃን ይዟል።
ሀገራችን ኢትዮጵያ በዛሬው ዕለት ሁለት የብር ሜዳልያዎች ማስመዝገቧን ተከትሎ በውድድሩ ያላትን የሜዳልያ ቁጥር ወደ ስድስት ከፍ ማድረግ ችላለች።

#Photo 🇪🇹
ከደቂቃዎች በፊት ከተጠናቀቀው የ 1500ሜ ሴቶች እና 3000ሜ መሰናክል ወንዶች ፍፃሜ ሀገራችን በሁለቱም ርቀቶች የብር ሜዳሊያ ስታገኝ የተወሰዱ ምስሎች ይመልከቱ።

" ውጤቱ ከጠበቅኩት በላይ ነው " ድርቤ ወልተጂ
በ 1500ሜ ሴቶች ውድድር ሁለተኛ በመውጣት ለኢትዮጵያ በውድድሩ ታሪክ 100ኛ ሜዳልያ ማስመዝገብ የቻለችው አትሌት ድርቤ ወልተጂ በዚህ ደረጃ መወዳደር ለእሷ ትልቅ ክብር መሆኑን ገልፃለች።
" ውድድሩ በጣም አሪፍ ነበር ፈጣሪ የሰራሁትን ስለሰጠኝ አመሰግነዋለሁ ፣ በአለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ፍፃሜ ከታላላቅ አትሌቶች ጋር መፎካከር የተለየ ነው።
ወደ ቡዳፔሽት የመጣሁት በደንብ ተዘጋጅቼ ነው ያስመዘገብኩት ውጤት ከጠበቅኩት በላይ እና ወሳኝ ነው።"ስትል የብር ሜዳልያ አሸናፊዋ ድርቤ ትናገራለች።
ከሀያ አመት በታች የአለም ሻምፒዮና ውድድር ላይ ያስመዘገበችው ጥሩ ውጤት ወደፊት ከምርጥ አትሌቶች አንዷ የመሆን ተስፋ እንደሰጣት የምትናገረው ድርቤ " ይህንንም ማረጋገጥ ችያለሁ ነገር ግን ጠንክሬም ሰርቻለሁ።"ብላለች።