TIKVAH-SPORT
246K subscribers
46.9K photos
1.48K videos
5 files
2.98K links
Download Telegram
#PremierLeague 🇬🇧

የኒውካስል ዩናይትድ ግብ ጠባቂ ኒክ ፖፕ በዘንድሮው የውድድር ዓመት ጥሩ የሚባል ጊዜን እያሳለፈ ሲገኝ በአስራ ሶስት ጨዋታዎች ላይ ግብ ሳይቆጠርበት በመውጣት ከአምስቱ ታላላቅ የአውሮፓ ሊጎች ብቸኛው ግብ ጠባቂ መሆኑ ተገልጿል።

የ 30ዓመቱ እንግሊዛዊው ግብ ጠባቂ ኒክ ፖፕ በተጨማሪ በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ በዚህ የውድድር አመት በአስር ጨዋታዎች ላይ መረቡን ሳያስደፍር በመውጣት ቀደሚው ግብ ጠባቂ ነው።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
#PremierLeague 🇬🇧

የእንግሊዝ ፕርሚየር ሊግ የወርሀ ታህሳስ የወሩ ምርጥ አሰልጣኝ እና ተጫዋቾች ከደቂቃዎች በፊት ይፋ ተደርጓል ።

በዚህም መሰረት የመድፈኞቹ ዋና አሰልጣኝ ሚኬል አርቴታ በአመቱ ለሁለተኛ ጊዜ የወሩ ምርጥ አሰልጣኝ በመባል ተመርጠዋል።

የቡድኑ አምበል የሆነው ማርቲን ኦዴጋርድ በሌላ በኩል የወሩ ምርጥ ተጫዋችነት ሽልማት አሸናፊ መሆኑ ይፋ ተደርጓል።

@tikvahethsport @kidusyoftahe
#PremierLeague 🇬🇧

በዘንድሮው የውድድር ዓመት በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ብዙ ጨዋታዎች ላይ ግብ ሳይቆጠርበት በመውጣት የኒውካስል ዩናይትዱ ግብ ጠባቂ ኒክ ፖፕ ቀዳሚውን ደረጃ ይይዛል።

ኒክ ፖፕ በሊጉ አስራ አንድ ጨዋታዎች ላይ ግብ ሳይቆጠርበት መውጣት ሲችል አሮን ራምስዴል #በዘጠኝ እንዲሁም ዴቪድ ዴህያ #በስምንት ጨዋታዎች ላይ ግብ ባለማስተናገድ ተከታዩን ደረጃ ይይዛሉ።

@tikvahethsport @kidusyoftahe
#PremierLeague 🇬🇬

የእንግሊዝ ፕርሚየር ሊግ ተጨዋቾች በቀጣይ በሚደረጉ የሊጉ መርሐ ግብሮች ላይ አንድ ዓመት የሞላውን የዩክሬን እና የሩሲያ ጦርነት እንደሚያስቡ ተገልጿል።

በዚህ መሰረት በቀጣይ በሚደረጉ የእንግሊዝ ፕርሚየር ሊግ መርሐ ግብሮቹ ላይ ሁሉም ተጨዋቾች የዩክሬን ሰንደቅ ዓላማ ያለበት አርማ በእጃቸው ላይ አድርገው እንደሚገቡ ተነግሯል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
#PremierLeague 🇬🇬

የአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ የጥሎ ማለፍ የመጀመሪያ ዙር ጨዋታዎች ተደርገው ሲጠናቀቁ የፕርሚየር ሊግ ክለቦች ድል #ሳይቀናቸው ቀርቷል።

በሻምፒየንስ ሊጉ እየተሳተፉ የሚገኙት ቼልሲ ፣ ሊቨርፑል እና ቶተንሀም ሽንፈት ሲቀምሱ ማንችስተር ሲቲ ከሜዳቸው ውጪ አቻ በመውጣት የመልስ ጨዋታቸውን በመጠባበቅ ላይ ይገኛሉ።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
#PremierLeague 🇬🇬

ተወዳጁ የእንግሊዝ ፕርሚየር ሊግ በሳምንቱ መጨረሻ በተደረጉ ተጠባቂ ጨዋታዎች ተካሂደው ሲገባደዱ ያልተጠበቁ ውጤቶችን ተመዝገበው ተጠናቀዋል።

- ቼልሲ ከበርካታ ጨዋታዎች በኋላ በማሸነፍ ከ " TOP 4 " ደረጃ #በአስራ አንድ ነጥቦች ብቻ ርቀው አስረኛ ደረጃ ላይ መቀመጥ ችለዋል።

- አራተኛ ደረጃን ይዞ ለማጠናቀቅ #ቶተንሀም ፣ #ሊቨርፑል እና #ኒውካስል በቀጣይ የሊጉ መርሐ ግብር ብርቱ ፉክክር እንደሚያደርጉ ይጠበቃል።

- ላለመውረድ በሚደረገው ትንቅንቅ ከሀያ እስከ አስራ አምስተኛ ደረጃ ያሉ ክለቦች #በሶስት ነጥብ ብቻ ተራርቀው ይገኛሉ።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
#PremierLeague 🇬🇬

የተወዳጁ የእንግሊዝ ፕርሚየር ሊግ የ 2023/24 የውድድር ዘመን የመካሄጃ ጊዜያት አስመልክቶ አወዳዳሪው አካል ይፋ አድርጓል።

በዚህም መሰረት :-

ሰኔ 8/2015 :- የውድድር ዓመቱ መርሐ ግብር ይፋ ይደረጋል።

ነሐሴ 6/2015 :- የአዲሱ ውድድር ዓመት ይጀምራል።

ጥር 4-11/2016 :- የአዲሱ የውድድር ዓመት የመጀመሪያ ዙር እረፍት

ግንቦት 11/2016 :- የ 2023/24 የውድድር ዘመን በገባደጃ ቀን መሆኑ ታውቋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
#PremierLeague

የቀያይ ሴጣኖቹ የመሐል ሜዳ ተጫዋች ማርሴል ሳቢትዘር በሚያሟሙቅበት ወቅት ጉዳት ማስተናገዱን ተከትሎ ከጨዋታው ውጪ ሆኗል።

ማርሴል ሳቢትዘርን በመተካት ክሪስቲያን ኤሪክሰን ጨዋታውን እንደሚጀመር ተገልጿል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
#PremierLeague 🇬🇧

በሊጉ ጥሩ ጊዜን በማሳለፍ ላይ የሚገኘው ብራይተን ከ ዎልቭስ ጋር ያደረገውን ጨዋታ 6ለ0 በሆነ ሰፊ ውጤት ማሸነፍ ችሏል።

- የብራይተንን የማሸነፊያ ግቦች ዳኒ ዌልቤክ 2x ፣ ግሮስ 2x እና ኡንዳቭ 2x ከመረብ ማሳረፍ ችለዋል።

- የአሰልጣኝ ሮቤርቶ ዲ ዘርቢው ቡድን ብራይተን ማሸነፉን ተከትሎ ቀሪ ጨዋታዎች እያሉት በሀምሳ ሁለት ነጥቦች #ስምንተኛ ደረጃ ላይ መቀመጥ ችሏል።

- በተመሳሳይ ሰዓት በተደረገ ሌላ መርሐ ግብር ብሬንትፎርድ ከ ኖቲንግሀም ፎረስት ጋር ያደረጉትን ጨዋታ 2ለ1 በሆነ ውጤት ማሸነፍ ችለዋል።

- የብሬንትፎርዱ የፊት መስመር ተጨዋች ኢቫን ቶኒ በውድድር አመቱ ሀያኛ የሊግ ግቡን ከመረብ ማሳረፍ ችሏል።

- ብሬንትፎርድ ማሸነፉን ተከትሎ ነጥቡን ሀምሳ በማድረስ #ዘጠነኛ ደረጃ ላይ መቀመጥ ችሏል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
#PremierLeague

ኤርሊንግ ሀላንድ በውድድር ዓመቱ ያስቆጠራቸውን የግብ መጠን ወደ ሀምሳ አድርሷል።

ሀላንድ በፕርሚየር ሊጉ ሰላሳ አራተኛ ግቡንም በፉልሀም ላይ አስቆጥሯል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
#Premierleague

ሊቨርፑል ከማንችስተር ሲቲ ጋር የሚያደርገውን ተጠባቂ የእንግሊዝ ፕርሚየር ሊግ ጨዋታ ለመታደም በርካታ ደጋፊዎች ከአንፊልድ ውጪ ቡድኑን በመጠባበቅ ላይ ይገኛሉ።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
💥የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ጨዋታዎች ወደ ሜዳ ተመልሰዋል💥

አርሰናል የአሸናፊነት መንገዱን መቀጥል ይችል ይሆን?

👉 ዛሬውኑ ፓኬጅዎን ያሳድጉ። ጨዋታዎችን ከትንታኔ ፣ ከተጫዋች ብቃት እስከ ቡድን ወኔ በሱፐርስፖርት ይከታተሉ!

ለሚሰጡን አስተያየት በቅድሚያ እያመሰገንን፣ ስለ አገልግሎታችን ጥራት የሚደርስዎትን የፅሁፍ መልዕክት ሊንኩን በመጫን መጠይቁን እንዲሞሉ በትህትና እንጠይቃለን።

የዲኤስቲቪ አገልግሎቶችን ለማግኘት ከታች ያለውን ሊንክ ይጫኑ!
👇
https://mydstv.onelink.me/vGln/eth2

#PremierLeague #ሁሉምያለውእኛጋርነው #DStvSelfService #DStvEthiopia
#PremierLeague

በአሰልጣኝ ኤሪክ ቴን ሀግ የሚመራው የማንችስተር ዩናይትድ እግር ኳስ ክለብ በዘንድሮው የውድድር ዓመት " አስከፊ " የሚባል ጉዞን እያደረጉ ይገኛሉ።

ትላንት ምሽት ቡድኑ በክሪስታል ፓላስ መሸነፉን ተከትሎም :-

- ከ 87ዓመታት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ በአንድ የውድድር ዓመት 8⃣1⃣ ጎሎች ተቆጥሮባቸዋል።

- በአንድ የውድድር ዘመን 1⃣3⃣ ጨዋታ በሊጉ በመሸነፍ ሪከርድ ሆኖ ተመዝግቧል።

- በ 2024 የውድድር ዘመን በተጋጣሚ ቡድን ብዙ ሙከራዎች የተደረገባቸው ሲሆን 20ኛ ደረጃ ላይ ከሚገኘው ሼፍልድ ዩናይትድ #ያልተሻለ ነው።

- ባለፉት ስምንት ጨዋታዎች 2⃣1⃣ ጎሎች ተቆጥረውባቸዋል።

ቀያይ ሴጣኖቹ በ 3⃣ የግብ እዳ 5⃣4⃣ ነጥቦችን ሰብስበው #ስምንተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጠዋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
#PremierLeague

የአምስተኛ ሳምንት የ እንግሊዝ ፕርሚየር ሊግ መርሐ ግብሮች ሲገባደዱ ማንችስተር ሲቲ የሊጉን መሪነት ተረክበዋል።

በውድድር አመቱ አራት ቡድኖች በሊጉ ያልተሸነፉ ሲሆን :-

- ማንችስተር ሲቲ
- አርሰናል
- ብራይተን እና
- ኖቲንግሀም ፎረስት በሊጉ ያልተሸነፉ ብቸኞቹ ክለቦች ናቸው።

በተቃራኒው :-

- ሌስተር ሲቲ
- ክሪስታል ፓላስ
- ኢፕስዊች ታውን
- ሳውዝሀምፕተን
- ኤቨርተን እና
- ዎልቭስ በሊጉ የአምስት ሳምንታት ጎዞ ሶስት ነጥብ ማግኘት ያልቻሉ ክለቦች ሆነዋል።

በወራጅ ቀጠናው ሳውዝሀምፕተን ፣ ኤቨርተን እና ዎልቭስ ይገኛሉ።

በቀጣይ የስድስተኛ ሳምንት መርሐ ግብርም :-

- ኒውካስትል ዩናይትድ ከ ማንችስተር ሲቲ

- ቼልሲ ከ ብራይተን እና

- ማንችስተር ዩናይትድ ከ ቶተንሀም የሚያደርጉት ጨዋታ ከተጠባቂ መርሐ ግብሮች መካከል ይገኙበታል።

@tikvahethsport @kidusyoftahe