TIKVAH-SPORT
246K subscribers
46.9K photos
1.48K videos
5 files
2.98K links
Download Telegram
አርሰናል እና ቼልሲ ድል ቀንቷቸዋል !

በእንግሊዝ ፕርምየር ሊግ ሀያ ስድስተኛ ሳምንት መርሐ ግብር አርሰናል ከ በርንማውዝ ጋር ያደረገውን ጨዋታ 3ለ2 በሆነ ውጤት ሲያሸንፍ ቼልሲ በበኩሉ ሊድስን 1ለ0 በሆነ ውጤት አሸንፏል።

- የአርሰናልን የማሸነፊያ ግቦች ቶማስ ፓርቴ ፣ ኔልሰን እና ቤንጃሚን ዋይት ሲያስቆጥሩ ለበርንማውዝ ቢሊንግ እና ሰነሲ ከመረብ ማሳረፍ ችለዋል።

- የምዕራብ ለንደኑ ክለብ ቼልሲን ብቸኛ የማሸነፊያ ግብ ፎፋና ከመረብ ማሳረፍ ችሏል።

- አርሰናል በሊጉ ደረጃ ሰንጠረዥ ስልሳ ሶስት ነጥቦችን በመሰብሰብ #አንደኛ ደረጃ ላይ ሲቀመጥ በርንማውዝ በሀያ አንድ ነጥቦች በወራጅ ቀጠናው አስራ ስምንተኛ ደረጃን ይዟል።

- ቼልሲ በበኩላቸው በሰላሳ አራት ነጥቦች #አስረኛ ደረጃ ላይ መቀመጥ ሲችሉ ሊድስ ዩናይትድ በሀያ ሁለት ነጥብ አስራ ሰባተኛ ደረጃን ይዟል።

- በቀጣይ የሊጉ መርሐ ግብር አርሰናል ከ ፉልሀም እንዲሁም ቼልሲ ከሌስተር ሲቲ የሚገናኙ ይሆናል።

- በሌሎች የሊግ መርሐ ግብሮች ዎልቭስ ቶተንሀምን 1ለ0 ፣ ብራይተን ዌስትሀምን 4ለ0 እንዲሁም አስቶንቪላ ክሪስትያል ፓላስን 1ለ0 በሆነ ውጤት ማሸነፍ ችለዋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ብርቱካናማዎቹ ድል ቀንቷቸዋል !

በቤት ኪንግ የኢትዮጵያ ፕርሚየር ሊግ አስራ ስድስተኛ ሳምንት መርሐ ግብር ድሬዳዋ ከተማ ከ ሲዳማ ቡና ጋር ያደረጉትን ጨዋታ 2ለ0 በሆነ ውጤት ማሸነፍ ችለዋል።

የድሬዳዋን የማሸነፊያ ግቦች ያሬድ ታደሰ እና አቤል አሰበ ከመረብ ማሳረፍ ችለዋል።

ብርቱካናማዎቹ ከአራት ተከታታይ ሽንፈቶች በኋላ የመጀመሪያ ጨዋታቸውን ማሸነፍ ችለዋል።

ድሬዳዋ ከተማ ማሸነፉን ተከትሎ በሊጉ ደረጃ ሰንጠረዥ ሀያ አንድ ነጥቦችን በመሰብሰብ #አስረኛ ደረጃ ላይ መቀመጥ ችሏል።

ሲዳማ ቡና በበኩላቸው በሊጉ ደረጃ ሰንጠረዥ አስራ ዘጠኝ ነጥቦችን በመሰብሰብ አስራ አንደኛ ደረጃን ይዘዋል።

በቀጣይ የሊጉ መርሐ ግብር ድሬ ዳዋ ከተማ ከ ለገጣፎ ለገዳዲ እንዲሁም ሲዳማ ቡና ከ ሀድያ ሆሳዕና የሚጫወቱ ይሆናል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
አዳማ ከተማ ድል ቀንቷቸዋል !

በቤት ኪንግ የኢትዮጵያ ፕርሚየር ሊግ አስራ ስድስተኛ ሳምንት መርሐ ግብር አዳማ ከተማ ከ ፋሲል ከነማ ጋር ጨዋታውን አድርጎ 2ለ1 በሆነ ውጤት ማሸነፍ ችሏል።

የአዳማ ከተማን የማሸነፊያ ሁለት ግቦች ዮሴፍ ታረቀኝ ከመረብ ማሳረፍ ሲችል የፋሲል ከነማ ግብ ታፈሰ ሰለሞን ማስቆጠር ችሏል።

አፄዎቹ በተከታታይ ካደረጓቸው ያለፉት #ስምንት የሊግ ጨዋታዎች ማሸነፍ የቻሉት #አንዱን ብቻ ሲሆን በአራቱ ጨዋታዎች አቻ ተለያይተው በሶስቱ ተሸንፈዋል።

ፋሲል ከነማዎች በሊጉ ደረጃ ሰንጠረዥ ሀያ አንድ ነጥቦችን በመሰብሰብ #ስምንተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጠዋል።

አዳማ ከተማ ማሸነፉን ተከትሎ በሊጉ ደረጃ ሰንጠረዥ ሀያ አንድ ነጥቦችን በመሰብሰብ #አስረኛ ደረጃን ይዟል።

በቀጣይ የሊጉ መርሐ ግብር ፋሲል ከነማ ከ ወላይታ ድቻ እንዲሁም አዳማ ከተማ ከ መቻል የሚጫወቱ ይሆናል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ቼልሲ እና ቶተንሀም ድል ቀንቷቸዋል !

በእንግሊዝ ፕርሚየር ሊግ ሀያ ሰባተኛ ሳምንት መርሐ ግብር ቼልሲ ሌስተር ሲቲን 3ለ1 እንዲሁም ቶተንሀም ኖቲንግሃም ፎረስትን 3ለ1 በሆነ ውጤት ማሸነፍ ችለዋል።

የቼልሲን የማሸነፊያ ግቦች ቼልዌል ፣ ካይ ሀቨርትዝ እና ኮቫኪች ከመረብ ማሳረፍ ሲችሉ ለሌስተር ሲቲ ዳካ አስቆጥሯል።

የቶተንሀምን የማሸነፊያ ግቦች ሀሪ ኬን 2x እና ሰን ሁንግ ሚን ሲያስቆጥሩ የኖቲንግሀም ፎረስትን ብቸኛ ግብ ዎራል አስቆጥሯል።

የምዕራብ ለንደኑ ክለብ ቼልሲ በሊጉ ደረጃ ሰንጠረዥ ሰላሳ ሰባት ነጥቦችን በመሰብሰብ #አስረኛ ደረጃ ላይ ሲቀመጥ ሌስተር ሲቲ በሀያ አራት ነጥብ አስራ ስድስተኛ ደረጃ ላይ ይገኛል።

ቶተንሀም በበኩሉ ማሸነፋቸውን ተከትሎ ነጥባቸውን አርባ ስምንት በማድረስ #አራተኛ ደረጃ ላይ ሲቀመጥ ኖቲንግሀም ፎረስት በሀያ ስድስት ነጥብ አስራ አራተኛ ደረጃን ይዟል።

በቀጣይ የሊጉ መርሐ ግብር ቼልሲ ከ ኤቨርተን ፣ ሊስተር ሲቲ ከብሬንትፎርድ እንዲሁም ቶተንሀም ከ ሳውዛምፕተን የሚገናኙ ይሆናል።

በሌሎች የሊጉ መርሐ ግብሮች ሊድስ እና ብራይተን ጨዋታቸውን 2ለ2 ሲያጠናቅቁ ፣ ኤቨርተን ብሬንትፎርድን 1ለ0 በሆነ ውጤት ማሸነፍ ችሏል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ማንችስተር ሲቲ ቀጣዩን ዙር ተቀላቅሏል !

ማንችስተር ሲቲ በአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ የጥሎ ማለፍ የመልስ ጨዋታ ሌፕዚግን 7ለ0 በሆነ ሰፊ ውጤት በማሸነፍ ቀጣዩን ዙር ተቀላቅሏል።

የማንችስተር ሲቲን የማሸነፊያ ግቦች ኤርሊንግ ሀላንድ 5x ፣ ጉንዶጋን እና ኬቨን ዴብሩይን ከመረብ ማሳረፍ ችለዋል።

ማንችስተር ሲቲ ሌፕዚግን በድምር ውጤት 8ለ1 በሆነ ውጤት በማሸነፍ ሩብ ፍፃሜውን መቀላቀላቸውን አረጋግጠዋል።

ኤርሊንግ ሀላንድ በዘንድሮው የአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ ውድድር አመት #አስረኛ ግቡን በማስቆጠር የውድድሩ ከፍተኛ ግብ አስቆጣሪዎች ደረጃን መምራት ጀምሯል።

ኤርሊንግ ሀላንድ በአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ ውድድር ታሪክ በአንድ ጨዋታ #አምስት ግቦችን ማስቆጠር የቻለ ሶስተኛው ተጨዋች መሆን ችሏል።

በሌላ የአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ የጥሎ ማለፍ የመልስ ጨዋታ ኢንተር ሚላን ፖርቶን በድምር ውጤት 1ለ0 በማሸነፍ ሩብ ፍፃሜውን መቀላቀል ችለዋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
አፄዎቹ ድል ቀንቷቸዋል !

በቤት ኪንግ የኢትዮጵያ ፕርሚየር ሊግ አስራ ሰባተኛ ሳምንት መርሐ ግብር ፋሲል ከነማ ከ ወላይታ ድቻ ጋር ያደረገውን ጨዋታ 2ለ1 በሆነ ውጤት ማሸነፍ ችሏል።

የፋሲል ከነማን ሁለት የማሸነፊያ ግቦች ኦሴ ማውሊ ሲያስቆጥር የወላይታ ድቻን ግብ ቃልኪዳን ዘላለም ከመረብ ማሳረፍ ችሏል።

ፋሲል ከነማ ማሸነፉን ተከትሎ በሊጉ ደረጃ ሰንጠረዥ ሀያ አራት ነጥቦችን በመሰብሰብ #አምስተኛ ደረጃ ላይ መቀመጥ ችለዋል።

ሽንፈት ያስተናገዱት ወላይታ ድቻዎች በበኩላቸው በሊጉ ደረጃ ሰንጠረዥ ሀያ ሁለት ነጥቦችን በመሰብሰብ #አስረኛ ደረጃን ይዘዋል።

በቀጣይ የሊጉ መርሐ ግብር ፋሲል ከነማ ከ ባህርዳር ከተማ እንዲሁም ወላይታ ድቻ ከ ኢትዮ ኤሌክትሪክ የሚገናኙ ይሆናል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ወላይታ ድቻ እና ኢትዮ ኤሌክትሪክ አቻ ተለያይተዋል !

በቤት ኪንግ የኢትዮጵያ ፕርሚየር ሊግ አስራ ስምንተኛ ሳምንት መርሐ ግብር ወላይታ ድቻ ከ ኢትዮ ኤሌክትሪክ ጋር ያደረጉትን ጨዋታ 1ለ1 በሆነ አቻ ውጤት አጠናቀዋል።

የወላይታ ድቻን ግብ ቃልኪዳን ዘላለም ሲያስቆጥር ለኢትዮ ኤሌክትሪክ ልደቱ ለማ ከመረብ ማሳረፍ ችለዋል።

ወላይታ ድቻ በሊጉ ደረጃ ሰንጠረዥ ሀያ ሶስት ነጥቦችን በመሰብሰብ #አስረኛ ደረጃ ላይ ተቀምጠዋል።

ኢትዮ ኤሌክትሪኮች በበኩላቸው በሊጉ ደረጃ ሰንጠረዥ ዘጠኝ ነጥቦችን ይዘው በወራጅ ቀጠናው አስራ አምስተኛ ደረጃን ይዘዋል።

በቀጣይ የሊጉ መርሐግብር ኢትዮ ኤሌክትሪክ ከ ለገጣፎ ለገዳዲ እንዲሁም ወላይታ ድቻ ከ ኢትዮጵያ መድን የሚገናኙ ይሆናል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ባህር ዳር ከተማ ድል ቀንቶታል !

በቤት ኪንግ የኢትዮጵያ ፕርሚየር ሊግ አስራ ዘጠነኛ ሳምንት መርሐ ግብር ባህርዳር ከተማ ከ ድሬዳዋ ከተማ ጋር ያደረጉትን ጨዋታ 3ለ1 በሆነ ውጤት ማሸነፍ ችለዋል።

የባህርዳር ከተማን የማሸነፊያ ግቦች ሀብታሙ ታደሠ 2x እና ዱሬሳ ሹቢሳ ከመረብ ሲያሳርፉ ለድሬዳዋ ከተማ ቢኒያም ጌታቸው ማስቆጠር ችሏል።

የድሬዳዋ ከተማው የፊት መስመር ተጨዋች ቢኒያም ጌታቸው በውድድር አመቱ አስራ አንደኛ የሊግ ግቡን ከመረብ ማሳረፍ ችሏል።

የባህርዳር ከተማዎቹ ተጨዋቾች ዱሬሳ ሹቢሳ እና ሀብታሙ ታደሰ በውድድር አመቱ #ስድስተኛ የሊግ ግባቸውን ማስቆጠር ችለዋል።

ባህርዳር ከተማ ማሸነፉን ተከትሎ በሊጉ ደረጃ ሰንጠረዥ ሰላሳ ዘጠኝ ነጥቦችን በመሰብሰብ በቅዱስ ጊዮርጊስ በግብ ክፍያ ተበልጠው #ሁለተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጠዋል።

ድሬዳዋ ከተማዎች በበኩላቸው በሊጉ ደረጃ ሰንጠረዥ ሀያ አራት ነጥቦችን ይዘው #አስረኛ ደረጃ ላይ ተቀምጠዋል።

በቀጣይ የሊጉ መርሐ ግብር ባህርዳር ከተማ ከ ለገጣፎ ለገዳዲ እንዲሁም ድሬዳዋ ከተማ ከሀዋሳ ከተማ የሚገናኙ ይሆናል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ድሬዳዋ ከተማ ድል አድርጓል !

በቤት ኪንግ የኢትዮጵያ ፕርሚየር ሊግ ሀያኛ ሳምንት መርሐ ግብር ድሬዳዋ ከተማ ከ ሀዋሳ ከተማ ጋር ያደረገውን ጨዋታ 1ለ0 በሆነ ውጤት ማሸነፍ ችሏል።

-የድሬዳዋ ከተማን የማሸነፊያ ግብ አቤል ከበደ ከመረብ ማሳረፍ ችሏል።

- ድሬዳዋ ከተማ ማሸነፉን ተከትሎ ነጥቡን ሀያ ሰባት በማድረስ #አስረኛ ደረጃ ላይ መቀመጥ ችሏል።

- ሽንፈት ያስተናገዱት ሀዋሳ ከተማዎች በበኩላቸው በሰላሳ አንድ ነጥቦች #አራተኛ ደረጃ ላይ ይገኛሉ።

- በቀጣይ የሊጉ መርሐ ግብር ድሬዳዋ ከተማ ከ ኢትዮጵያ ቡና እንዲሁም ሀዋሳ ከተማ ከ ፋሲል ከነማ ጋር ይገናኛሉ።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ወላይታ ድቻ ድል አድርጓል !

በቤት ኪንግ የኢትዮጵያ ፕርሚየር ሊግ ሀያ አንደኛ ሳምንት መርሐ ግብር ወላይታ ድቻ ከ መቻል ጋር ያደረገውን ጨዋታ 1 ለ 0 በሆነ ውጤት ማሸነፍ ችሏል

- የወላይታ ድቻን የማሸነፊያ ግብ ስንታየሁ መንግስቱ ከመረብ ማሳረፍ ችሏል።

- ወላይታ ድቻ ማሸነፉን ተከትሎ ነጥቡን ሀያ ሰባት በማድረስ #አስረኛ ደረጃ ላይ ሲቀመጥ መቻል በ ሀያ ስድስ ነጥብ አስራ አንደኛ ደረጃ ላይ ይገኛል።

- በቀጣይ የሊጉ መርሐ ግብር ወላይታ ድቻ ከ ለገጣፎ ለገዳዲ እንዲሁም መቻል ከ ድሬዳዋ ከተማ ይገናኛሉ።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
#BKEthPL 🇪🇹

በቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕርሚየር ሊግ ሀያ አራተኛ ሳምንት መርሐ ግብር ወላይታ ድቻ ከ አርባምንጭ ከተማ ጋር ያደረጉትን ጨዋታ 0 ለ 0 በሆነ አቻ ውጤት አጠናቀዋል።

አርባምንጭ ከተማ በተከታታይ ያደረጓቸውን ስድስት ጨዋታዎች ማሸነፍ አልቻሉም።

በሊጉ ደረጃ ሰንጠረዥ ወላይታ ድቻ በሰላሳ ሁለት ነጥቦች #አስረኛ ደረጃ ላይ ሲቀመጥ አርባምንጭ ከተማ በሀያ አምስት ነጥብ አስራ አራተኛ ደረጃ ላይ ይገኛል።

በቀጣይ የሊጉ መርሐ ግብር ወላይታ ድቻ ከ ቅዱስ ጊዮርጊስ እንዲሁም አርባምንጭ ከተማ ከ አዳማ ከተማ ጋር የሚጫወቱ ይሆናል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
TIKVAH-SPORT
Photo
#BKEthPL 🇪🇹

በቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕርሚየር ሊግ ሀያ ስድስተኛ ሳምንት መርሐ ግብር ወላይታ ድቻ ከ ሲዳማ ቡና ጋር ያደረጉትን ጨዋታ 0 ለ 0 በሆነ አቻ ውጤት አጠናቀዋል።

ሲዳማ ቡና ከአራት ተከታታይ ድሎች በኋላ ነጥብ ተጋርቶ ወጥቷል።

በሊጉ ደረጃ ሰንጠረዥ ሲዳማ ቡና በሰላሳ አራት ነጥብ #አስረኛ ደረጃ ላይ ሲቀመጥ ወላይታ ድቻ በሰላሳ ሶስት ነጥቦች አስራ ሁለተኛ ደረጃ ላይ ይገኛል።

በቀጣይ የሊጉ መርሐ ግብር ሲዳማ ቡና ከ አርባምንጭ ከተማ እንዲሁም ወላይታ ድቻ ከ ሀዋሳ ከተማ ጋር የሚጫወቱ ይሆናል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
#BKEthPL 🇪🇹

በቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕርሚየር ሊግ ሀያ ሰባተኛ ሳምንት መርሐ ግብር ሲዳማ ቡና ከ አርባምንጭ ከተማ ጋር ያደረጉትን ጨዋታ 1 ለ 1 በሆነ አቻ ውጤት አጠናቀዋል።

ለአርባምንጭ ከተማ አህመድ ሁሴን ሲያስቆጥር የሲዳማ ቡናን የአቻነት ግብ አሸናፊ ፊዳ በራሱ ግብ ላይ ከመረብ አሳርፏል።

በሊጉ ደረጃ ሰንጠረዥ ሲዳማ ቡና በሰላሳ አምስት ነጥብ #አስረኛ ደረጃ ላይ ሲቀመጥ አርባምንጭ ከተማ በሰላሳ ነጥቦች አስራ አራተኛ ደረጃ ላይ ይገኛል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
የባርሴሎና ሴቶች ቡድን ሻምፒዮን ሆኗል !

የካታላኑ ክለብ ባርሴሎና ሴቶች ቡድን ከሪያል ሶሴዳድ ጋር ያደረገውን የስፔን ኮፓ ዴላሬና ፍፃሜ ጨዋታ 8ለ0 በሆነ ውጤት በማሸነፍ የዋንጫ አሸናፊ መሆናቸውን አረጋግጠዋል።

የባርሴሎና ሴቶች ቡድን #አስረኛ የስፔን ኮፓ ዴላሬና ዋንጫቸውን ማሳካት ችለዋል።

በዚህ አመት የሊጉን እና የስፔን ሱፐር ካፕ ዋንጫን ያሸነፈው የባርሴሎና ሴቶች ቡድን የሀገር ውስጥ የሶስትዮሽ ዋንጫ ስኬትን አስመዝግበዋል።

ባርሴሎና በተጨማሪም በአውሮፓ የሴቶች ሻምፒየንስ ሊግ ፍፃሜ ከፈረንሳዩ ክለብ ሊዮን ጋር የሚጫወቱ ይሆናል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
#TheFinalDay 🏴󠁧󠁢󠁥󠁮󠁧󠁿

የዋንጫ አሸናፊው ተለይቶ ያልታወቀበት የእንግሊዝ ፕርሚየር ሊግ የዘንድሮው የ2023/24 የውድድር አመት በዛሬው ዕለት በተመሳሳይ ሰዓት በሚደረጉ መርሐ-ግብሮች ፍፃሜውን ያገኛል።

- ሊጉን በሁለት ነጥብ ልዩነት እየመራ የሚገኘው ማንችስተር ሲቲ ለአራተኛ ተከታታይ አመታት ሊጉን በማሳካት አዲስ ታሪክ ሊፅፍ በሜዳው ዌስትሀም ዩናይትድን ያስተናግዳል።

- ጥሩ የሚባል የውድድር አመት በማሳለፍ ላይ የሚገኘው አርሰናል በበኩሉ ከሀያ አመታት በኋላ ዋንጫውን ወደ ኤምሬትስ ለመመለስ የሲቲን ነጥብ መጣል እየተጠባበቀ ከኤቨርተን ጋር ይጫወታል።

- የእንግሊዝ ፕርሚየር ሊግ በታሪኩ ለ #አስረኛ ጊዜ የዋንጫ አሸናፊውን ክለብ በመጨረሻ ቀን ውሎው የሚለይ ይሆናል።

- ከዚህ በፊት የፕርሚየር ሊጉ አሸናፊ ክለብ በመጨረሻ ሳምንት መርሐ ግብር በታወቀባቸው ዘጠኝ አጋጣሚዎች ሊጉን እየመሩ የነበሩ ክለቦች ሻምፒዮን ሆነዋል።

- በዘንድሮው የእንግሊዝ ፕርሚየር ሊግ ከወትሮው በተለየ መልኩ የዋንጫ አሸናፊነት እድል ባላቸው ማንችስተር ሲቲ እና አርሰናል ስታዲየሞች ሁለት የሊግ ዋንጫዎች እንደሚቀመጡ ተገልጿል።

- ቼልሲ እና ኒውካስል ዩናይትድ የአውሮፓ መድረክ ቦታን ለማግኘት ሲፋለሙ ማንችስተር ዩናይትድም በሊጉ በሒሳባዊ ስሌት በአውሮፓ መድረክ የመሳተፍ እድሉ አለው።

- የፕርሚየር ሊጉ ዋን ስራ አስፈፃሚ ሪቻርድ ማስተርስ በዛሬው ጨዋታ የአርሰናል እና ኤቨርተንን ጨዋታ ለመታደም ወደ ኤምሬትስ ያቀናሉ።

ሊጉን ማን ሊያሸንፍ ይችላል

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
#Paris2024            #TeamEthiopia 🇪🇹

በ 2024 ፓሪስ ኦሎምፒክ 1500ሜ ሴቶች ማጣሪያ ውድድር በአንደኛው ምድብ የተካፈለችው ኢትዮጵያዊት አትሌት ብርቄ ሀየሎም ለፍፃሜ ሳታልፍ ቀርታለች።

አትሌት ብርቄ ሀየሎም የግማሽ ፍፃሜ ውድድሩን #አስረኛ  ደረጃን በመያዝ ማጠናቀቅ ችላለች።

በመቀጠል በሁለተኛው ምድብ የሚገኙት ኢትዮጵያዊያን አትሌቶች ጉዳፍ ፀጋዬ እና ድርቤ ወልተጂ ውድድራቸውን የሚያደርጉ ይሆናል።

የ1500ሜ ሴቶች ፍፃሜ ውድድር ቅዳሜ ነሐሴ 4/2016 ዓ.ም ምሽት 3:25 የሚደረግ ይሆናል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe