TIKVAH-SPORT
246K subscribers
46.9K photos
1.48K videos
5 files
2.98K links
Download Telegram
#Paris2024

የውሀ ዋና ተጣበቂ ውድድሮች ምሽት ሲደረጉ አራት የወርቅ ሜዳሊያዎች ሲበረከቱ ተጠባቂዋ አሜሪካዊት ኬቲ ሌድኪ ዘጠነኛ የወርቅ ሜዳሊያዋን በኦሎምፒኩ ለማሸነፍ ትጠበቃለች።

ኬቲ ሌድኪ በ 800ሜትር የነፃ ዉሀ ዋና ምሽቱን ስትወዳደር ለማሸነፍ ቅድሚያ ግምቱን አግኝታለች።

ሌድኪ ምሽቱን የምታሸንፍ ከሆነ በኦሎምፒኩ ብዙ የወርቅ ሜዳሊያዎችን ማሸነፍ የቻለች ኦሎምፒያን ለመሆነ ትበቃለች።

ይህ ተጠባቂ ውድድር ከምሽቱ 4:20 ሲል መካሄዱን ይጀምራል።

@tikvahethsport @kidusyoftahe
#Paris2024

አሜሪካዊቷ ፈጣን የ 100ሜትር ሯጭ ሻ ካሪ ሪቻርድሰን ዛሬ ምሽት በሚደረገው የፍፃሜ ውድድር የማሸነፍ ትልቅ ግምትን አግኝታለች።

የኦሎምፒክ የመጀመሪያ ተሳትፎን እያደረገች የምትገኘው የአለም ሻምፒዮና ሻ ካሪ ማጣርያውን 10.94 በማግባት ማሸነፏ ይታወቃል።

የጃማይካ ተፎካካሪዋ ሼሪካ ጃክሰን በውድድሩ አለመኖር ሻ ካሪ በቀላሉ እንድታሸንፍ ከፍተኛ ግምትን አሰጥቷታል።

ሆኖም ግን ሻ ካሪ ከሶስት ጊዜ የ ኦሎምፒክ የወርቅ ሜዳሊያ አሸናፊዋ ሼሊ አን ፍሬዘር ፕራይስ ብርቱ ፉክክር ይጠብቃታል።

ሻ ካሪ ሪቻርድሰን በዘንድሮው የውድድር ዘመን በርቀቱ በተወዳደረችበት መድረክ አልተረታችም።

የ 100ሜትር ሴቶች ፍፃሜ ዛሬ ምሽት 4:15 ሲል ይጀምራል።

@tikvahethsport @kidusyoftahe
TIKVAH-SPORT
የኦሎምፒክ መክፈቻ ዝግጅት የእምነት ተቋማትን አስቆጣ ! ከቀናት በፊት አርብ ምሽት የተካሄደው የ2024 ፓሪስ ኦሎምፒክ ውድድር መክፈቻ ስነ ስርዓት ብዙ የእምነት ተቋማትን ማስቆጣቱ ተገልጿል። በመክፈቻ ዝግጅቱ ላይ የቀረበው ትዕይንት " የክርስትና እምነት ላይ ያፌዘ እና ክብረ ነክ ነው " በሚል የእምነቱን አባቶች ጨምሮ የሀገራት መሪዎችን አስቆጥቷል። በዝግጅቱ ላይ በክርስትና እምነት ተከታዮች…
#Paris2024

የ 2024 ፓሪስ ኦሎምፒክ መክፈቻ ዝግጅት ዳይሬክተር የነበሩት ቶማስ ጆሊ በማህበራዊ ሚዲያዎች የግድያ እና ማስፈራሪያ ዛቻ እንደደረሳቸው ተገልጿል።

የዝግጅቱ ዳይሬክተር ከመክፈቻው በኋላ ማስፈራሪያ እየደረሳቸው እንደሚገኝ ለፓሪስ መንግሥት ባለስልጣናት ማስታወቃቸው ተነግሯል።

የፓሪስ ከተማ ከንቲባ አኔ ሂዳልጎ በዚሁ ጉዳይ ላይ በሰጡት አስተያየት የሚመሩት ከተማ እንዲሁም በግላቸው የማስፈራሪያ ዛቻ ከደረሰባቸው የዝግጅቱ ዳይሬክተር ቶማስ ጆሊ ጎን መሆናቸውን ገልጸዋል።

በተጨማሪም በዳይሬክተሩ ላይ እየደረሱ የሚገኙ የጥላቻ ንግግሮች እና የግድያ እና የማስፈራሪያ ዛቻዎች ምርመራ እየተደረገባቸው እንደሚገኝ ተገልጿል።

በፓሪሱ ኦሎምፒክ መክፈቻ ስነ ስርዓት የተስተዋሉ ድርጊቶች የእምነት ተቋማትን ጨምሮ በርካቶችን ማስቆጣታቸው አይዘነጋም።

የዝግጅቱ ዳይሬክተር በስነ ስርዓቱ ላይ ስለተፈጠረው ድርጊት ባስረዱበት ወቅትም ማስተላለፍ የፈለጉትን መልዕክት በሚገባ ማስተላለፋቸውን ገልፀው ነበር።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
TIKVAH-SPORT
#Paris2024 አሜሪካዊቷ ፈጣን የ 100ሜትር ሯጭ ሻ ካሪ ሪቻርድሰን ዛሬ ምሽት በሚደረገው የፍፃሜ ውድድር የማሸነፍ ትልቅ ግምትን አግኝታለች። የኦሎምፒክ የመጀመሪያ ተሳትፎን እያደረገች የምትገኘው የአለም ሻምፒዮና ሻ ካሪ ማጣርያውን 10.94 በማግባት ማሸነፏ ይታወቃል። የጃማይካ ተፎካካሪዋ ሼሪካ ጃክሰን በውድድሩ አለመኖር ሻ ካሪ በቀላሉ እንድታሸንፍ ከፍተኛ ግምትን አሰጥቷታል። ሆኖም…
#Paris2024

ጃማይካዊቷ ታሪካዊ የ 100ሜትር ሯጭ ሼሊ አን ፍሬዘር ፕራይስ ከፓሪስ ኦሎምፒክ 100ሜትር ሩጫ ግማሽ ፍፃሜ ውድድር ውጪ ሆናለች።

አምስተኛ እና የመጨረሻ የኦሎምፒክ ተሳትፎዋን በማድረግ ላይ የምትገኘው ሼሊ አን ፍሬዘር ፕራይስ በአምስት ተከታታይ ኦሎምፒክ ሜዳልያ በማግኘት ባለታሪክ መሆን ትችል ነበር።

አትሌቷ በምን ምክንያት ከግማሽ ፍፃሜ ማጣሪያ ውድድር ውጪ እንደሆነች በይፋ የተገለፀ ነገር የለም።

የ 37ዓመቷ አትሌት ሼሊ አን ፍሬዘር ፕራይስ በ100ሜትር ሩጫ ሁለት የወርቅ ሜዳልያ ማሳካት ችላለች።

በተጨማሪም ሌላኛዋ ጃማይካዊት ሼሪካ ጃክሰን በፍፃሜ ውድድሩ የማትሳተፍ ይሆናል።

ይህንንም ተከትሎ አሜሪካዊቷ ሻ ካሪ ሪቻርድሰን ዛሬ ምሽት በሚደረገው የፍፃሜ ውድድር የማሸነፍ ትልቅ ግምትን አግኝታለች።

የ 100ሜትር ሴቶች ፍፃሜ ዛሬ ምሽት 4:15 ሲል ይጀምራል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
#Paris2024            #TeamEthiopia 🇪🇹

የ 2024 ፓሪስ ኦሎምፒክ ውድድር በዛሬው ዕለት ሲቀጥል ሀገራችን ኢትዮጵያ የምትሳተፍባቸው #የማጣሪያ አትሌቲክስ ውድድሮች ይጠበቃሉ።

በዛሬው ዕለት የሴቶች 800 እና 1,500 ወንዶች ግማሽ ፍፃሜ እንዲሁም የሴቶች 3000 መሰናክል ማጣሪያ ውድድሮች ይደረጋሉ።

ኢትዮጵያ በማን ትወከላለች ?

-
ቀን 5:05 :- 3000ሜ ሴቶች መሰናክል ማጣሪያ ( አትሌት ሎሚ ሙለታ እና ሲምቦ አለማየሁ )

- ምሽት 3:45 :- 800ሜ ሴቶች ግማሽ ፍፃሜ ( አትሌት ወርቅነሽ መሰለ  እና ፅጌ ድጉማ )

- ምሽት 4:10 :- 1,500ሜ ወንዶች ግማሽ ፍፃሜ ( አትሌት ሳሙኤል ተፈራ እና ኤርሚያስ ግርማ)

@tikvahethsport @kidusyoftahe
#Paris2024

የህንድ መንግሥት በፓሪስ ኦሎምፒክ እየተሳተፉ ለሚገኙ የሀገሪቱ አትሌቶች አርባ የአየር መቆጣጠሪያ " AC " ገዝቶ መላኩ ተገልጿል።

የፓሪስ ኦሎምፒክ አዘጋጆች በአትሌቶች መንደር ውስጥ ለሚገኙ አትሌቶች ባቀረቡት የማረፊያ ክፍል ውስጥ የአየር መቆጣጠሪያ ባለማቅረባቸው ቅሬታ ሲቀርብ እንደነበር ይታወሳል።

የህንድ ስፖርት ሚኒስቴር በበኩሉ ፈረንሳይ ከሚገኘው የሀገሪቱ ኤምባሲ እና ኦሎምፒክ ኮሚቴ ጋር በመነጋገር የአየር መቆጣጠሪያውን በራሱ ወጪ ገዝቶ መላኩ ተገልጿል።

የሀገሪቱ ስፖርት ሚኒስቴር ይሄንን ያደረገው አትሌቶቹ በፓሪስ በሚኖራቸው ቆይታ ጥሩ እረፍት እንዲያደርጉ እና ጥሩ ውጤት እንዲያስመዘግቡ እንዲያግዛቸው መሆኑ ተነግሯል።

በፓሪስ የሚገኙ አትሌቶች በአንድ ክፍል ውስጥ ተጋርተው እንደሚገኙ እንዲሁም ለሊቱን በሙቀት ምክንያት በር ከፍተው እንደሚተኙ ሲገለፁ እንደነበር አይዘነጋም።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
TIKVAH-SPORT
#Paris2024            #TeamEthiopia 🇪🇹 የ 2024 ፓሪስ ኦሎምፒክ ውድድር በዛሬው ዕለት ሲቀጥል ሀገራችን ኢትዮጵያ የምትሳተፍባቸው #የማጣሪያ አትሌቲክስ ውድድሮች ይጠበቃሉ። በዛሬው ዕለት የሴቶች 800 እና 1,500 ወንዶች ግማሽ ፍፃሜ እንዲሁም የሴቶች 3000 መሰናክል ማጣሪያ ውድድሮች ይደረጋሉ። ኢትዮጵያ በማን ትወከላለች ? - ቀን 5:05 :- 3000ሜ ሴቶች መሰናክል…
#Paris2024

የፓሪስ 2024 ኦሎምፒክ ውድድር ዘጠነኛ ቀኑ ላይ ሲገኝ ዛሬ ሀያ የወርቅ ሜዳልያዎችን ለአሸናፊዎች የሚያሰጡ የፍፃሜ ውድድሮች ይካሄዳሉ።

የኦሎምፒክ ሜዳልያ ሰንጠረዡን ቻይና በአስራ ስድስት የወርቅ ሜዳልያዎች በበላይነት እየመራች ትገኛለች።

አስራ አራት የወርቅ ሜዳልያ ያላት አሜሪካ በበኩሏ በአጠቃላይ ስልሳ አንድ ሜዳልያ ቀዳሚ መሆን ችላለች።

በኦሎምፒኩ በዛሬው ዕለት ከሚጠበቁ የፍፃሜ ውድድሮች መካከል የወንዶች ነጠላ ሜዳ ቴኒስ ፍፃሜ ውድድር ዋነኛው ነው።

ዛሬ ከቀኑ 7:00 ሰዓት በሮላንድ ጋሮስ በሚደረገው ተጠባቂ የቴኒስ ፍፃሜ ኖቫክ ጆኮቪች ከካርሎስ አልካራዝ ለወርቅ ሜዳልያ ይፋለማሉ።

በተጨማሪም በዛሬው ዕለት የሚካሄደው የ 100 ሜትር ወንዶች ፍፃሜ ሩጫ የዕለቱ ተጠባቂ ውድድር ነው።

ወቅታዊ የሜዳልያ ሰንጠረዡ ምን ይመስላል ?

1️⃣ ቻይና :- ( 16 ወርቅ ፣ 12 ብር እና 9 ነሐስ ሜዳልያ )

2️⃣ አሜሪካ :- ( 14 ወርቅ ፣ 24 ብር እና 23 ነሐስ ሜዳልያ )

3️⃣ ፈረንሳይ :- ( 12 ወርቅ ፣ 14 ብር እና 15 ነሐስ ሜዳልያ )

4️⃣ አውስትራሊያ :- ( 12 ወርቅ ፣ 8 ብር እና 7 ነሐስ ሜዳልያ )

5️⃣ ብሪታኒያ :- ( 10 ወርቅ ፣ 10 ብር እና 13 ነሐስ ሜዳልያ )

ኢትዮጵያ በኦሎምፒክ ሜዳልያ ሰንጠረዡ በአንድ የብር ሜዳልያ ከአለም አርባ ዘጠነኛ ደረጃ ላይ መቀመጥ ችላለች።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
#Paris2024            #TeamEthiopia 🇪🇹

በ 2024 ፓሪስ ኦሎምፒክ 3000ሜ ሴቶች መሰናክል ማጣሪያ ውድድር በመጀመሪያው ምድብ የተካፈለችው ኢትዮጵያዊቷ አትሌት ሎሚ ሙለታ ለፍፃሜ ማለፏን አረጋግጣለች።

አትሌት ሎሚ ሙለታ በማጣሪያ ውድድሩ 9:10.73 በሆነ ሰዓት በመግባት የግሏን ምርጥ ሰዓት በማስመዝገብ #አምስተኛ ደረጃን በመያዝ አጠናቃለች።

ሌላኛዋ ኢትዮጵያዊት አትሌት ሲምቦ አለማየሁ በሚቀጥለው ምድብ የማጣሪያ ውድድሯን በማድረግ ላይ ትገኛለች።

የ 3000ሜ ሴቶች መሰናክል ፍፃሜ ውድድር ማክሰኞ ሀምሌ 30/2016 ዓ.ም ምሽት 4:10 የሚደረግ ይሆናል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
#Paris2024            #TeamEthiopia 🇪🇹

በ 2024 ፓሪስ ኦሎምፒክ 3000ሜ ሴቶች መሰናክል ማጣሪያ ውድድር የተካፈሉት ሁለቱም ኢትዮጵያዊያን አትሌቶች ሲምቦ አለማየሁ እና ሎሚ ሙለታ ለፍፃሜ አልፈዋል።

በሁለተኛው ምድብ ማጣሪያ የተካፈለችው አትሌት ሲምቦ አለማየሁ 9:15.42 በሆነ ሰዓት ሁለተኛ ደረጃን በመያዝ ለፍፃሜ ማለፍ ችላለች።

በመጀመሪያው ምድብ የማጣሪያ ውድድሯን ያደረገችው ሎሚ ሙለታ አምስተኛ ደረጃን በመያዝ ለፍፃሜ መድረሷ ይታወቃል።

የ 3000ሜ ሴቶች መሰናክል ፍፃሜ ውድድር ማክሰኞ ሀምሌ 30/2016 ዓ.ም ምሽት 4:10 የሚደረግ ይሆናል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
#Paris2024

ጃማይካዊቷ የአጭር ርቀት ሯጭ ሼሪካ ጃክሰን በዛሬው ዕለት በተደረገው የ 200 ሜትር ሴቶች ሩጫ የማጣሪያ ውድድር ሳትሳተፍ ቀርታለች።

ሼሪካ ጃክሰን ትላንት በተመሳሳይ ከ 100 ሜትር ውድድር ውጪ እንደነበረች የሚታወስ ሲሆን የዛሬውን ውድድር በምን ምክንያት እንዳልተሳተፈች በግልጽ አልተነገረም።

ያለፉት ሁለት ውድድሮች የ 200ሜ የአለም ሻምፒዮኗ ሼሪካ ጃክሰን በፓሪስ ኦሎምፒክ የወርቅ ሜዳልያ ከፍተኛ ግምት አግኝታ ነበር።

የ 17ዓመቱ ፈረንሳዊ የነጠላ ጠረጴዛ ቴኒስ ኮከብ ፌሊክስ ሌብሩን ለነሐስ ሜዳልያ የተደረገውን ጨዋታ በማሸነፍ ለሀገሩ የነሐስ ሜዳልያ አስገኝቷል።

ፈረንሳይ በነጠላ ጠረጴዛ ቴኒስ ጨዋታ የምንግዜም ሶስተኛ የኦሎምፒክ ሜዳልያዋን ማግኘት ችላለች።

ፈረንሳይ ከሰላሳ ሰባት አመታት በኋላ በነጠላ ጠረጴዛ ቴኒስ ጨዋታ የመጀመሪያ ሜዳልያዋን ማግኘት ችላለች።

በነጠላ ጠረጴዛ ቴኒስ ጨዋታ ቻይናዊው ፋን ሼንዶንግ ስዊዲናዊውን ትሩልስ ሞሬጋርድን በመርታት የወርቅ ሜዳልያ አሳክቷል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe