TIKVAH-SPORT
246K subscribers
46.8K photos
1.48K videos
5 files
2.97K links
Download Telegram
#QatarWorldCup 🇶🇦

በ 2022 የኳታር የዓለም ዋንጫ የምድብ ጨዋታዎች ተደርገው ሲጠናቀቁ #ዘጠኝ አፍሪካዊያን ተጫዋቾች የጨዋታው ኮከብ ተሸላሚ መሆን ችለዋል።

በምድብ ጨዋታ #ሰባት_ድሎች በአፍሪካ ብሔራዊ ቡድኖች ሲመዘገቡ አዲስ ሪከርድ መሆኑም ተገልጿል።

በጥሎ ማለፉ የኳታር የዓለም ዋንጫ #ሞሮኮ እና #ሴኔጋል አፍሪካን በመወክል ብርቱ ፉክክር የሚያደርጉ ይሆናል።

@tikvahethsport @kidusyoftahe
#QatarWorldCup 🇶🇦

የኳታር የዓለም ዋንጫ የጥሎ ማለፍ ሁለተኛ ጨዋታ በመደረግ ላይ ሲገኝ አርጀንቲና በሊዮኔል ሜሲ ብቸኛ ግብ እየመራች ወደ መልበሻ ክፍል አቅንተዋል።

√ ሊዮኔል ሜሲ በዓለም ዋንጫ የጥሎ ማለፍ ጨዋታ ግብ ሲያስቆጥር በታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ ሆኗል።

√ ሊዮኔል ሜሲ በዓለም ዋንጫው ያስቆጠራቸውን የግብ መጠን በድምሩ #ዘጠኝ አድርሷል።

√ ሊዮኔል ሜሲ የአርጀንቲና ብሔራዊ ቡድንን #በአምበልነት እየመራ 100ኛ ጨዋታውን በማድረግ ላይ ይገኛል።

√ ሊዮኔል ሜሲ ለብሔራዊ ቡድኑ ያስቆጠራቸውን የግብ መጠን ወደ ዘጠና አራት ከፍ አድርጓል።

√ ሊዮኔል ሜሲ በእግር ኳስ ህይወቱ 1,000ኛ ጨዋታውን በማካሄድ ላይ ይገኛል።

@tikvahethsport @kidusyoftahe
ፈረንሳይ ቀጣዩን ዙር ተቀላቅላለች !

በታሪክ ለሶስተኛ ጊዜ የተገናኙት ፈረንሳይ እና ፖላንድ ባደረጉት ጨዋታ የዓለም ዋንጫ አሸናፊዎቹ ፈረንሳይ በድል አድራጊነታቸው ቀጥለዋው።

የዲድዬ ዴሻምፕ ስብስብ በኦሊቪዮ ጅሩድ እና ኪሊያን ምባፔ ጎሎች ፖላንድን 3ለ1 በማሸነፍ የሩብ ፍፃሜ ተፋላሚነታቸውን አረጋግጠዋል።

√ ኪሊያን ምባፔ ከሀያ አራት ዓመቱ በፊት በዓለም ዋንጫው በድምሩ #ዘጠኝ ጎሎችን በማስቆጠር በታሪክ #ቀዳሚው ተጫዋች ሆኗል።

√ ኦሊቪዬ ጅሩድ በዘንድሮ የዓለም ዋንጫ በሶስት ጨዋታዎች #ሶስተኛ ጎሉን ማስቆጠር ችሏል።

√ ኪሊያን ምባፔ በዓለም ዋንጫው #በሰባት ጎሎች ላይ ቀጥተኛ ተሳትፎን ሲያደርግ ቀዳሚው ተጫዋች ያደርገዋል።

√ ሮበርት ሊዋንዶውስኪ በእግር ኳስ ህይወት #ሁለተኛ የዓለም ዋንጫ ጎሉን አስቆጥሯል።

√ ኪሊያን ምባፔ #አምስት ጎሎችን ሲያስቆጥር ሁለት ለግብ የሚሆኑ ኳሶችን አመቻችቶ ማቀበል ችሏል።

√ ኪሊያን ምባፔ ለፈረንሳይ ብሔራዊ ቡድን ሰላሳ ሶስተኛ ጎሉን አስቆጥሯል።

የሩብ ፍፃሜ ጨዋታ መቼ ይደረጋል?

የኳታሩ ዓለም ዋንጫ የሩብ ፍፃሜ ጨዋታዎች ከቀጣይ ሳምንት #አርብ ጀምሮ ሲካሄድ ፈረንሳይ ከ #ሴኔጋል እና #እንግሊዝ አሸናፊ ጋር የምትጫወት ይሆናል።

ቅዳሜ :- ፈረንሳይ ከ እንግሊዝ / ሴኔጋል ( 4:00 ሰዓት )

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ኢንተር ሚላን ነጥብ ጥሏል !

በጣልያን ሴርያ ሀያ ሁለተኛ ሳምንት ኢንተር ሚላን ከ ሳምፕዶርያ ያደረገውን ጨዋታ 0ለ0 በሆነ አቻ ውጤት አጠናቋል።

ኢንተር ሚላን ከሜዳ ውጪ ያደረጋቸውን #ዘጠኝ ተከታታይ ጨዋታዎች አልተሸነፉም።

ሳምፕዶሪያ ከ አስራ አራት ጨዋታዎች በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ ግብ ሳይቆጠርባቸው መውጣት ችለዋል።

ኢንተር ሚላን በሊጉ ደረጃ ሰንጠረዥ ከሊጉ መሪ ናፖሊ በ አስራ አምስት ነጥብ ርቀው በአርባ አራት ነጥብ #ሁለተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጠዋል።

በቀጣይ የሊጉ መርሐ ግብር ኢንተር ሚላን ከ ዩድንዜ የሚገናኙ ሲሆን ሳምፕዶሪያ በበኩላቸው ከቦሎኛ ይጫወታሉ።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
TIKVAH-SPORT
ክርስቲያን አትሱ አሁንም እንዳልተገኘ ተገለፀ ! የቀድሞ የቼልሲ እና ኒውካስል ዩናይትድ ተጨዋች ክርስቲያን አትሱ ቱርክ ውስጥ በተከሰተው የመሬት መንቀጥቀጥ አደጋ ጠፍቶ ከፍርስራሽ ውስጥ በህይወት እንደተገኘ እና ሆስፒታል እንደገባ ተገልፆ ነበር። ነገር ግን ጋናዊው የፊት መስመር ተጨዋች ክርስቲያን አትሱ እስካሁን እንዳልተገኘ እና በፍርስራሽ ውስጥ እየተፈለገ እንደሚገኝ አሁን ላይ ይፋ የተደረጉ መረጃዎች…
ክርስቲያን አትሱ እንዳልተገኘ ተገለፀ !

የቀድሞ የቼልሲ እና ኒውካስል ዩናይትድ የፊት መስመር ተጨዋች ክርስቲያን አትሱ በሀገረ ቱርክ በተከሰተው የመሬት መንቀጥቀጥ አደጋ ምክንያት ሳይገኝ መቅረቱ ይታወቃል።

ጋናዊው የፊት መስመር ተጨዋች ክርስቲያን አትሱ በአደጋው ምክንያት ከጠፋ #ዘጠኝ ቀናቶች እንደተቆጠሩ እና እስካሁን #በፍለጋ ላይ እንደሚገኝ ወኪሉ ይፋ አድርጓል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ቼልሲ ሲሸነፍ ቤኔፊካ ድል ቀንቶታል !

በአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ የጥሎ ማለፍ ጨዋታ ዶርትመንድ በሜዳው ከቼልሲ ጋር ያደረገውን ጨዋታ 1ለ0 በሆነ ውጤት ማሸነፍ ችሏል።

በሌላ ጨዋታ ቤኔፊካ ከ ክለብ ብሩዥ ጋር ያደረገውን የጥሎ ማለፍ ጨዋታ 2ለ0 በሆነ ውጤት ማሸነፍ ችሏል።

የዶርትሙንድን ብቸኛ የማሸነፊያ ግብ ካሪም አዲዬምስ ከመረብ ማሳረፍ ችሏል።

የቤኔፊካን የማሸነፊያ ግብ ጇ ማርዮ እና ኔሬስ ከመረብ ማስቆጠር ችለዋል።

የምዕራብ ለንደኑ ክለብ ቼልሲ በሁሉም ውድድሮች ከሜዳው ውጪ ያደረጋቸውን ያለፉት #ዘጠኝ ጨዋታዎች ማሸነፍ አልቻለም።

ቦርሽያ ዶርትመንድ በሁሉም ውድድሮች ያደረጋቸውን ያለፉት ተከታታይ #ዘጠኝ ጨዋታዎች አልተሸነፉም።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ክቫራትሼሊያ ወደ ሪያል ማድሪድ ?

ሪያል ማድሪድ ጆርጂያዊውን የናፖሊ የፊት መስመር ተጨዋች ክቫራትሼሊያ ለማስፈረም ፍላጎት እንዳላቸው የተጨዋቹ ወኪል ይፋ አድርጓል።

የተጨዋቹ ወኪል በንግግሩ " አባቱ እና እኔ የባርሴሎና ደጋፊዎች ነን እሱ ግን ሪያል ማድሪድን ነው የሚወደው ፣ በባርሴሎና ብናየው ደስ ይለናል እሱ ግን ማድሪዳዊ ነው።"ሲል ተደምጧል።

የ 22ዓመቱ ጆርጂያዊ የፊት መስመር ተጨዋች ክቫራትሼሊያ በዘንድሮው የውድድር አመት ለናፖሊ በሊጉ ሀያ ጨዋታዎች ላይ ተሰልፎ መጫወት የቻለ ሲሆን #አስር ግቦችን አስቆጥሮ #ዘጠኝ አመቻችቶ ማቀበል ችሏል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ቱኒዚያ ለአፍሪካ ዋንጫው አልፋለች !

የቱኒዚያ ብሔራዊ ቡድን ከ ሊቢያ ብሔራዊ ቡድን ጋር ያደረገውን የአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ የምድብ አራተኛ ጨዋታ 1ለ0 በሆነ ውጤት ማሸነፍ ችሏል።

ቱኒዚያ ማሸነፏን ተከትሎ ነጥቧን #አስር በማድረስ ለኮትዲቯሩ የ2024 አፍሪካ ዋንጫ ማለፏን አረጋግጣለች።

በዚሁ ምድብ የምትገኘው ኢኳቶሪያል ጊኒ #ዘጠኝ ነጥቦችን በመሰብሰብ ሁለተኛ ደረጃ ላይ የተቀመጠች ሲሆን ቱኒዚያን በመከተል ለአፍሪካ ዋንጫው የማለፍ ዕድሏ የሰፋ ነው።

ቱኒዝያ ለኮትዲቯሩ የ2024 አፍሪካ ዋንጫ ማለፏን ያረጋገጠች ስድስተኛ ሀገር መሆን ችላለች።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ለገጣፎ ለገዳዲ ድል ቀንቶታል !

በቤት ኪንግ የኢትዮጵያ ፕርሚየር ሊግ አስራ ሰባተኛ ሳምንት መርሐ ግብር ለገጣፎ ለገዳዲ ከ ድሬዳዋ ከተማ ጋር ያደረገውን ጨዋታ 2ለ1 በሆነ ውጤት ማሸነፍ ችሏል።

ለገጣፎ ለገዳዲን አሸናፊ ያደረጉ ሁለት ግቦች ሱለይማን ትራኦሬ ከመረብ ማሳረፍ ሲችል የድሬዳዋ ከተማን ብቸኛ ግብ ቢኒያም ጌታቸው በመጨረሻዎቹ  ደቂቃዎች አስቆጥሯል ።

አዲስ አዳጊው ክለብ ለገጣፎ ለገዳዲ በውድድር አመቱ #ሁለተኛ ድላቸውን ማስመዝገብ ችለዋል።

በሊጉ ደካማ ጉዞ እያደረገ የሚገኘው ለገጣፎ ለገዳዲ በሊጉ ደረጃ ሰንጠረዥ #ዘጠኝ ነጥቦችን በመሰብሰብ አስራ አምስተኛ ደረጃ ላይ መቀመጥ ችሏል።

ሽንፈት ያስተናገዱት ድሬዳዋ ከተማዎች በበኩላቸው በሀያ አንድ ነጥቦች አስራ ሁለተኛ ደረጃን ይዘዋል።

በቀጣይ የሊጉ መርሐ ግብር ለገጣፎ ለገዳዲ ከ ኢትዮጵያ መድን እንዲሁም ድሬዳዋ ከተማ ከ ሀድያ ሆሳዕና ጋር የሚገናኙ ይሆናል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ባርሴሎና ነጥብ ጥሏል !

የስፔን ላሊጋ መሪው የካታላኑ ክለብ ባርሴሎና ካምፕ ኑ ላይ ከ ጅሮና ጋር ያደረገውን የሊግ መርሐ ግብር 0ለ0 በሆነ አቻ ውጤት አጠናቋል።

ባርሴሎና በዘንድሮው የውድድር አመት ሀያ አንድ የሊግ መርሐ ግብሮች ላይ ምንም ግብ አልተቆጠረበትም።

ባርሴሎና በዘንድሮው የውድድር አመት ባደረጓቸው ሀያ ስምንት የሊግ መርሐ ግብሮች ላይ የተቆጠሩበት #ዘጠኝ ግቦች ብቻ ናቸው።

ባርሴሎና በሊጉ ደረጃ ሰንጠረዥ ከተከታያቸው ሪያል ማድሪድ በአስራ ሶስት ነጥቦች ርቀው ሊጉን መምራታቸውን አጠናክረው ቀጥለዋል።

በቀጣይ የሊጉ መርሐ ግብር የአሰልጣኝ ዣቪ ሀርናንዴዙ ስብስብ ከጌታፌ ጋር የሚገናኝ ይሆናል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
#Budapest 🇪🇹

በ2023ቱ የአለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና የወንዶች ማራቶን ውድድር ኢትዮጵያዊው አትሌት ልዑል ገብረ ስላሴ ሶስተኛ ደረጃን ይዞ በማጠናቀቅ ለሀገራችን ሶስተኛውን የነሀስ ሜዳልያ ማስመዝገብ ችሏል።

ውድድሩን ዩጋንዳዊው አትሌት ኪፕላንጋት በበላይነት ሲያጠናቅቀው እስራኤላዊው ማሩ ተፈሪ ሁለተኛ ደረጃን በመያዝ ማጠናቀቅ ችሏል።

በውድድሩ የተሳተፉት ሌሎች ኢትዮጵያዊያን አትሌቶች ሚልኬሳ መንገሻ 6ኛ ፣ ፀጋዬ ጌታቸው 17ኛ ደረጃን ይዘው ማጠናቀቅ ችለዋል።

የባለፈው አመት የአለም ሻምፒዮን ኢትዮጵያዊ አትሌት ታምራት ቶላ ውድድሩን ለማቋረጥ ተገዷል።

ሀገራችን ኢትዮጵያ በዛሬው ዕለት አንድ ሜዳልያ ማስመዝገቧን ተከትሎ በውድድሩ ያላትን የሜዳልያ ቁጥር ወደ #ዘጠኝ ከፍ ማድረግ ችላለች።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
አል ናስር ድል አድርጓል !

በሳውዲ አረቢያ ሊግ ሰባተኛ ሳምንት መርሐ ግብር የክርስቲያኖ ሮናልዶው ክለብ አል ናስር ከአል አህሊ ጋር ያደረገውን ጨዋታ 4ለ3 በሆነ ውጤት ማሸነፍ ችሏል።

የአል ናስርን የማሸነፊያ ግቦች ክርስቲያኖ ሮናልዶ ( 2x ) እና ታሊስካ ( 2x ) ሲያስቆጥሩ ለአል አህሊ ፍራንክ ኬሲ ፣ ሪያድ ማህሬዝ እና አል ቡራይካን ከመረብ አሳርፈዋል።

- ፖርቹጋላዊው ኮከብ ክርስቲያኖ ሮናልዶ ሰባት መቶ ሰላሳኛ የክለብ ግቡን ከመረብ ማሳረፍ ችሏል።

- ክርስቲያኖ ሮናልዶ በ2023 አርባ አንድ ግቦች ላይ ቀጥተኛ ተሳትፎ ማድረግ ችሏል።

- አል ናስር በአስራ አምስት ግቦች አምስተኛ ደረጃ ላይ ሲቀመጥ አል አህሊ በበኩሉ በእኩል አስራ #አምስት ነጥብ በግብ ክፍያ ተበልጦ #ስድስተኛ ደረጃን ይዟል።

ሮናልዶ በዚህ አመት በሊጉ ያለዉ ቁጥር ምን ይመስላል ?

👉 በስድስት የሳውዲ አረቢያ ሮሸን ሊግ ጨዋታዎች #ዘጠኝ ግቦችን ከመረብ ማሳረፍ ችሏል።

👉 አጠቃላይ በሊጉ በዘንድሮው የውድድር አመት በአስራ ሶስት ግቦች ላይ ቀጥተኛ ተሳትፎ ማድረግ ሲችል ይህም በሊጉ ከፍተኛው ነው።

👉 በዘጠኝ ግቦች የሳውዲ አረቢያ ሮሸን ሊግ ከፍተኛ ግብ አስቆጣሪዎች ደረጃን በመምራት ላይ ይገኛል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ሀዋሳ ከተማ ድል አድርጓል !

በ2016 የኢትዮጵያ ፕርሚየር ሊግ የአምስተኛ ሳምንት መርሐ ግብር ሀዋሳ ከተማ ከሲዳማ ቡና ጋር ያደረጉትን ጨዋታ 1 ለ 0 በሆነ ውጤት ማሸነፍ ችለዋል።

የሀዋሳ ከተማን ብቸኛ የማሸነፊያ ግብ እዮብ አለማየሁ ከመረብ ማሳረፍ ችሏል።

ሀዋሳ ከተማ በውድድር አመቱ የሰበሰባቸውን ነጥቦች #ዘጠኝ በማድረስ ደረጃውን ማሻሻል ችለዋል።

ቀጣይ ጨዋታ ምን ይመስላል ?

- ሲዳማ ቡና ከ ሀድያ ሆሳዕና

- ሀዋሳ ከተማ ከ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
TIKVAH-SPORT
ሊቨርፑል ከፊኖርድ ጋር ይፋዊ ድርድር ጀመረ ! የመርሲሳይዱ ክለብ ሊቨርፑል ኔዘርላንዳዊውን አሰልጣኝ አርኔ ስሎት በሀላፊነት ለመሾም ከፊኖርድ ጋር ይፋዊ ድርድር መጀመራቸው ተገልጿል። አሰልጣኙ የውል ማፍረሻ ባይኖራቸውም ሊቨርፑል አሰልጣኙን ለመውሰድ ከፊኖርድ ጋር በካሳ ክፍያ ዙሪያ ንግግር ላይ መሆናቸው ተነግሯል። ሊቨርፑል አሁን ላይ ኔዘርላንዳዊውን አሰልጣኝ አርኔ ስሎት የየርገን ክሎፕ ተተኪ…
ሊቨርፑል ያቀረበው የመጀመሪያ ሒሳብ ውድቅ ሆነ !

የመርሲሳይዱ ክለብ ሊቨርፑል ኔዘርላንዳዊውን አሰልጣኝ አርኔ ስሎት ለመሾም ለፊኖርድ ያቀረቡት የመጀመሪያ የካሳ ክፍያ ውድቅ እንደሆነባቸው ተገልጿል።

ሊቨርፑል ለመጀመሪያ ጊዜ ያቀረበው የካሳ ክፍያ #ዘጠኝ ሚልዮን ዩሮ መሆኑ የተገለፀ ሲሆን ፊኖርድ ውድቅ በማድረግ ገንዘቡን ለማስጨመር ጠንካራ ድርድር ለማድረግ መምረጣቸው ተነግሯል።

ሊቨርፑሎች አሰልጣኝ አርኔ ስሎትን የአሰልጣኝ የርገን ክሎፕ ተተኪ ለማድረግ ንግግራቸውን መቀጠላቸው ተጠቁሟል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe