TIKVAH-SPORT
246K subscribers
46.8K photos
1.48K videos
5 files
2.97K links
Download Telegram
" አርሰናል ከጨዋታ ውጭ ያደርገናል"

የማንችስተር ሲቲ ዋና አሰልጣኝ ፔፕ ጋርዲዮላ ከሊጉ መሪ አርሰናል ጋር በሚኖራቸው ጨዋታ አሁን ላይ ባላቸው ወቅታዊ አቋም የሚቀርቡ ከሆነ ለማሸነፍ እንደሚከብዳቸው ተናግረዋል ።

አሰልጣኝ ፔፕ ጋርዲዮላ በአስተያየታቸው " አርሰናልን ማሸነፍ እንፈልጋለን ፣ በዚህ አጨዋወታችን የምንገጥማቸው ከሆነ ግን እነሱ ከጨዋታ ውጭ ያደርጉናል ።" ሲሉ ተደምጠዋል ።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
TIKVAH-SPORT
ዌስትሀም ተጨዋች ለማስፈረም ከጫፍ ደርሷል ! የአጥቂ ክፍላቸውን ለማጠናከር እየተንቀሳቀሱ የሚገኙት ዌስትሀም ዩናይትዶች የአስቶን ቪላውን የፊት መስመር ተጨዋች ዳኒ ኢንግስ ለማስፈረም መስማማታቸው ተዘግቧል። በዴቪድ ሞይስ የሚሰለጥኑት ዌስትሀሞች የ 30ዓመቱን የቀድሞ የሊቨርፑል ተጨዋች ዳኒ ኢንግስ ለማስፈረም 15 ሚልዮን ፓውንድ ወጪ እንደሚያደርጉ ተገልጿል። ዌስትሀም በዘንድሮው የውድድር አመት በሊጉ…
ዌስትሀም ተጫዋች አስፈርሟል !

የአጥቂ ክፍላቸውን ለማጠናከር እየተንቀሳቀሱ የሚገኙት ዌስትሀም ዩናይትዶች የአስቶንቪላውን የፊት መስመር ተጫዋች ዳኒ ኢንግስ ማስፈረማቸውን ይፋ አድርገዋል ።

ዌስትሀም ዩናይትድ የ 30ዓመቱን የቀድሞ የሊቨርፑል ተጫዋች ዳኒ ኢንግስ እስከ 2025 በሚደርስ የሁለት አመት ኮንትራት ውል ማስፈረማቸው ተገልጿል ።

ዌስትሀም ነገ በሊጉ መርሐ ግብር ከኤቨርተን ጋር በሚያደርገው ጨዋታ ዳኒ ኢንግስ ለጨዋታው ብቁ እንደሚሆን ክለቡ ይፋ አድርጓል ።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
አትሌቲኮ ማድሪድ ሜምፊስ ዴፓይን አስፈርሟል !

አትሌቲኮ ማድሪድ የባርሴሎናውን የፊት መስመር ተጫዋች ሜምፊስ ዴፓይ ማስፈረማቸውን ይፋ አድርገዋል ።

አትሌቲኮ ማድሪድ ሜምፊስ ዴፓይን ለማስፈረም 3.2 ሚልዮን ዶላር ወጪ ያደረገ ሲሆን ተጨዋቹ ለማድሪዱ ክለብ የሁለት አመት ኮንትራት መፈረሙ ይፋ ተደርጓል ።

ሜምፊስ ዴፓይ በዘንድሮው የውድድር ዓመት ለባርሴሎና አራት ጨዋታዎችን አድርጎ አንድ ግብ ብቻ አስቆጥሯል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ቼልሲ የተጫዋቾቹን ግልጋሎት አያገኙም!

የምዕራብ ለንደኑ ክለብ ቼልሲ ነገ ከሊቨርፑል ጋር በሚያደርገው ተጠባቂ ጨዋታ ላይ አሁንም የሁለት ተጨዋቾቹን ግልጋሎት እንደማያገኝ ተገልጿል።

የተከላካይ ስፍራ ተጨዋቹ ሪስ ጄምስ ከቡድኑ ጋር ልምምድ ማድረግ መጀመሩ ቢገለፅም ለነገው ተጠባቂ ጨዋታ እንደማይደርስ ተረጋግጧል።

ሰማያዊዎቹ በተጨማሪም በነገው ተጠባቂ ጨዋታ በጉዳት ላይ የሚገኘው የሌላኛውን የተከላካይ ስፍራ ተጨዋች ቤን ቺል ዌል ግልጋሎት እንደማያገኙ ተነግሯል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
" የነገው ጨዋታ ለእኛ የፍፃሜ ነው " መጂድ ቡጌራ

የቻን አፍሪካ ዋንጫ የምድብ የመጨረሻ ጨዋታዎች ከነገ ጀምሮ መካሄዳቸውን ሲጀምሩ አስቀድማ ማለፏን ያረጋገጠችው #አልጄርያ ከ ሞዛምቢክ ጋር የሚያደርጉት ጨዋታ ይጠበቃል።

የብሔራዊ ቡድኑ ዋና አሰልጣኝ መጂድ ቡጌራ በሰጠው አስተያየት " አስቀድመን ማለፋችንን ብናረጋግጥም ምድባችንን የበላይ ሆነን ማጠናቀቅ እንፈልጋለን ፣ የነገው ጨዋታ ለማድረግ ወደ ሜዳ ስንገባ ለእኛ የፍፃሜ ያህል ነው " በማለት ተናግሯል።

@tikvahethsport @kidusyoftahe
አርሰናል ተጨዋች አስፈርሟል !

የሰሜን ለንደኑ ክለብ አርሰናል የብራይተኑን ቤልጄማዊ የፊት መስመር ተጨዋች ሊያንድሮ ትሮሳርድ በቋሚ ውል ማስፈረማቸውን ይፋ አድርገዋል ።

መድፈኞቹ የ 28ዓመቱን አጥቂ ሊያንድሮ ትሮሳርድ የግላቸው ለማድረግ 27 ሚልዮን ፓውንድ ወጪ ያደረጉ ሲሆን ተጨዋቹ በአርሰናል ቤት የአምስት ዓመት ኮንትራት ውል መፈረሙ ተገልጿል ።

መድፈኞቹ እሁድ ከማንችስተር ዩናይትድ ጋር በሚያደርጉት ተጠባቂ ጨዋታ አዲሱ ፈራሚ ሊያንድሮ ትሮሳርድ ለጨዋታው ዝግጁ የመሆን እድል እንዳለው ተገልጿል ።

ሊያንድሮ ትሮሳርድ ለእንግሊዙ ክለብ ብራይተን በተሰለፈባቸው አንድ መቶ አስራ ስድስት ጨዋታዎች ሀያ አምስት ግቦች ከመረብ ማሳረፍ ችሏል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
" ለኢትዮጵያ ከዚህ የበለጠ መስራት አለብኝ " ጋቶች ፓኖም

በቻን አፍሪካ ዋንጫ እየተሳተፈ የሚገኘው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ወደ ቀጣዩ ዙር ለማለፍ ወሳኙን ጨዋታ ከሊቢያ ብሔራዊ ቡድን ጋር ነገ ምሽት 4:00 የሚያደርግ ይሆናል።

በዛሬው ዕለት ለጋዜጠኞች አስተያየታቸውን የሰጡት አሰልጣኙ " በምድቡ የመጨረሻ ጨዋታ የተቻለንን እናደርጋለን ቀላል ጨዋታ እንደማይሆን እናውቃለን " ሲሉ ተናግረዋል።

አያይዘውም " ለሁለታችንም የመጨረሻ የምድብ ጨዋታ ነው እኛ ካሸነፍን የሌሎቹን የምድብ ጨዋታ መጠበቅ ይኖርብናል ፣ በተቃራኒው ሊቢያ ነጥብ ይዘው ወደ ሀገራቸው ለመመለስ ብርቱ ፉክክር ያደርጋሉ።

በአናባ ያለው ቀዝቃዛ የአየር ንብረቱ ከአልጀርስ አንፃር ለውጥ መኖሩ ትንሽ ተፅዕኖ አለው ፣ ባለፉት ጨዋታዎች ብዙ ዕድሎችን አባክነናል ጎል ካላሰቆጠርክ ጨዋታዎችን ማሸነፍ አትችልም " ሲሉ አሰልጣኝ ውበቱ አባተ ተደምጠዋል።

በሞዛምቢክ ጨዋታ ኮከብ ሆኖ የተመረጠው ጋቶች ፓኖም በበኩሉ " የጨዋታው ኮከብ በመባሌ ደስተኛ ነኝ ፣ ሆኖም ግን #ለሀገሬ ከዚህ የበለጠ መስራት እንዳለበኝ ይሰማኛል።

ውድድሩ ትንሽ ፈታኝ ነው ሁሉም ተጫዋች በዚህ ውድድር ራሱን በማሳየት በትላልቅ ሊጎች ላይ የመጫወት ህልም አለው ፣ እኔም ጠንክሬ በመስራት ራሴን እያሳየሁ ነው።

የነገው ጨዋታ ከባድ እንደሚሆን እናውቃለን የማለፍ እድላችን በሌላ ቡድን ላይ ቢመሰረትም ወደ ቀጣዩ ዙር ለማለፍ የተቻለንን ሁሉ በሜዳ ላይ እናደርጋለን " ሲል ጋቶች ፓኖም ተናግሯል።

@tikvahethsport @kidusyoftahe
የፊርሚንሆ የሊቨርፑል ቆይታ ?

ብራዚላዊው የመርሲሳይዱ ክለብ ሊቨርፑል የፊት መስመር አጥቂ ሮቤርቶ ፊርሚንሆ በክለቡ እንዲቆይ የአጭር ጊዜ ኮንትራት እንደቀረበለት ተገልጿል።

ሊቨርፑሎች ከሮቤርቶ ፊርሚንሆ ጋር አሁንም በንግግር ላይ ሲገኙ በቀጣይ ጥቂት ቀናት ከስምምነት ይደርሳሉ ተብሎ ይጠበቃል።

@tikvahethsport @kidusyoftahe
ጁቬንቱስ ከባድ ቅጣት ተላለፈበት !

በአሰልጣኝ ማሲሚሊያኖ አሌግሪ የሚመራው የጁቬንቱስ እግር ኳስ ክለብ በሒሳብ ማጭበርበር የተለያዩ ቅጣቶች እንደተላለፉባቸው ይፋ ሆኗል።

ክለቡ ፈፅሟል በተባለው ጥፋት በሊጉ አስራ አምስት ነጥቦች እንዲቀነሱባቸው ውሳኔ ሲተላለፉ የክለቡ ሀላፊዎች ላይ እገዳ መተላለፉም ተገልጿል።

የክለቡ የቀድሞ ከፍተኛ አመራሮች ቅጣት ሲተላለፍባቸው ለሚቀጥሉት ዓመታት በስፖርታዊ ውድድሮች ላይ የማንመለከታቸው ይሆናል።

በዚህም መሰረት :-

- ፋቢዮ ፓራቲሲ :- ሁለት ዓመት ከስድስት ወር

- አንድሬያ አኜሊ :- ሁለት ዓመት

- ፌዴሪኮ ቼሩቢኒ :- አንድ ዓመት ከስድስት ወር

- ፓቬል ኔድቬድ :- ስምንት ወራቶችን መታገዳቸው ይፋ ሆኗል።

@tikvahethsport @kidusyoftahe
ባየርሙኒክ ነጥብ ተጋርቷል !

በጀርመን ቡንደስሊጋ አስራ ስድስተኛ ሳምንት መርሐ ግብር ባየርሙኒክ ከ ሌፕዚግ ጋር ያደረገውን ጨዋታ 1ለ1 በሆነ አቻ ውጤት ማጠናቀቅ ችሏል።

የባየር ሙኒክን ግብ ቹፖ ሞቲንግ ሲያስቆጥር የሌፕዚግን የአቻነት ግብ ደግሞ ሀልስተንበርግ ከመረብ ማሳረፍ ችሏል።

ባየርሙኒክ ከ ሌፕዚግ ጋር ያደረጋቸውን ያለፉት አስራ አንድ ጨዋታዎች አልተሸነፈም።

ባየርሙኒክ በሊጉ ደረጃ ሰንጠረዥ ሰላሳ አምስት ነጥብ በመሰብሰብ #አንደኛ ደረጃ ላይ ሲቀመጥ ሌፕዚግ በሀያ ዘጠኝ ነጥብ #ሶስተኛ ደረጃን ይዟል ።

በቀጣይ የሊጉ መርሐ ግብር ባየርሙኒክ ከ ኮለን የሚጫወቱ ሲሆን ሌፕዚግ በበኩላቸው ከ ሻልክ 04 የሚገናኙ ይሆናል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ቼልሲ ተጨዋች አስፈርሟል !

የምዕራብ ለንደኑ ክለብ ቼልሲ የፔኤስቪውን የፊት መስመር ተጨዋች ኖኒ ማዱኬ በቋሚነት ማስፈረማቸውን ይፋ አድርገዋል ።

ሰማያዊዎቹ የ 20ዓመቱን የፊት መስመር ተጨዋች ኖኒ ማዱኬ ለማስፈረም እስከ 35 ሚልዮን ዩሮ ወጪ እንዳደረጉ ተገልጿል ።

በግርሀም ፖተር የሚሰለጥኑት ቼልሲዎች በዚህ ወር አራት ተጨዋቾች በቋሚ እና አንድ ተጨዋች በውሰት ውል ያስፈረሙ ሲሆን ኖኒ ማዱኬ ስድስተኛ ፈራሚያቸው ሆኗል ።

እንግሊዛዊው ተጨዋች ኖኒ ማዱኬ ለኔዘርላንዱ ክለብ ፔኤስቪ ሀምሳ አንድ የሊግ ጨዋታዎች አድርጎ አስራ አንድ ግቦች ከመረብ ማሳረፍ ችሏል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ዋናው የዋናው አልባሳት የንግድ ምልክት ነው !

በጤና ቡድኖች እና በደጋፊዎች ተመራጭ እና ምቹ የሆኑትን ትጥቆች እንደተለመደው በተመጣጣኝ ዋጋ በመረጡት ዲዛይን እና የቀለም ምርጫ ሰርቶ ያቀርብልዎታል።

📞 ይደውሉ :- 📱0910 851 535   
                      📱0901138283

ቻናላችን :- https://t.iss.one/wanawsportwear

📌 አድራሻ ፦ ገርጂ መብራት ሃይል የካቲት ወረቀት ፊትለፊት

ማልያችን መለያችን ዋናው ወደ ፊት. . . . .
የዛሬ ተጠባቂ መርሐ ግብሮች !

4:00 ሊቢያ ከ ኢትዮጵያ

9:30 ሊቨርፑል ከ ቼልሲ

12:00 ሌስተር ሲቲ ከ ብራይተን

12:00 ዌስትሀም ከ ኤቨርተን

2:00 ሳሌሬንቲና ከ ናፖሊ

2:30 ክሪስታል ፓላስ ከ ኒውካስል ዪናይትድ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ኤርሊንግ ሀላንድ የወሩ ምርጥ ተጨዋች ተብሏል !

የማንችስተር ሲቲው ኖርዌያዊ የፊት መስመር ተጨዋች ኤርሊንግ ሀላንድ የእንግሊዝ ፕሮፌሽናል እግር ኳስ ተጨዋቾች ማህበር " PFA " የወሩ ምርጥ ተጨዋች በመሆን ተመርጧል።

በእጩነት የቀረቡት ተጨዋቾች ቡካዩ ሳካ ፣ ማርቲን ኦዴጋርድ፣ ማርከስ ራሽፎርድ ፣ ካሴሚሮ እና ኢቫን ቶኒ ሲሆኑ ኤርሊንግ ሀላንድ የወሩ ምርጥ ተጫዋች ተብሏል።

ኤርሊንግ ሀላንድ የእንግሊዝ ፕሮፌሽናል እግር ኳስ ተጨዋቾች ማህበር የወሩ ምርጥ ተጨዋች ሲባል ለተከታታይ ሶስተኛ ጊዜ ነው።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ከፍተኛ ገንዘብ አውጥቷል !

በጥር ወር የዝውውር መስኮት ከአምስቱ የአውሮፓ ታላላቅ ሊጎች በርካታ ገንዘብ ለተጨዋቾች ዝውውር በማውጣት ቀዳሚው ሊግ የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ መሆኑ ተዘግቧል።

የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ በዚህ የዝውውር መስኮት ለተጨዋቾች ዝውውር 387.5 ሚልዮን ዩሮ ወጪ እንዳደረገ ተገልጿል።

ሌሎች ሊጎች ምን ያህል ወጪ አደረጉ ?

- የእንግሊዝ ፕርሚየር ሊግ :- 387.5 ሚልዮን ዩሮ

- የጀርመን ቡንደስሊጋ :- 34 ሚልዮን ዩሮ

- የስፔን ላሊጋ :- 23.3 ሚልዮን ዩሮ

- የጣሊያን ሴሪያ :- 9.1 ሚልዮን ዩሮ

- የፈረንሳይ ሊግ :- 8.3 ሚልዮን ዩሮ ማውጣታቸው ተነግሯል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ለተሻለ ውርርድ betikaን ይጠቀሙ
አሁኑኑ ይወራረዱ!
BET NOW ON Betika.et
/on our Telegram Bot - @BetikaETBot
የካማቪንጋ የሪያል ማድሪድ ቆይታ ?

ፈረንሳያዊው የሪያል ማድሪድ የመሐል ሜዳ ተጨዋች ኤድዋርዶ ካማቪንጋ በማድሪዱ ክለብ ቤት ደስተኛ እንደሆነ እና ክለቡን የመልቀቅ ፍላጎት እንደሌለው ተነግሯል።

የ 20ዓመቱ ኤድዋርዶ ካማቪንጋ ስሙ ከእንግሊዞቹ ክለቦች አርሰናል እና ቼልሲ ጋር በስፋት ቢያያዝም በሪያል ማድሪድ ቤት ደስተኛ እንደሆነ ተገልጿል።

ኤድዋርዶ ካማቪንጋ የስፔኑን ክለብ ሪያል ማድሪድ እ.ኤ.አ በ 2021 ከተቀላቀለ በኋላ አርባ ሁለት ጨዋታዎች ማድረግ ሲችል ሁለት ግቦችን ማስቆጠር ችሏል።

@tikvahethsport @kidusyoftahe
የጨዋታ አሰላለፍ !

9:30 ሊቨርፑል ከ ቼልሲ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe