TIKVAH-SPORT
246K subscribers
46.8K photos
1.48K videos
5 files
2.97K links
Download Telegram
የጨዋታ አሰላለፍ !

5:00 ማንችስተር ሲቲ ከ ቶተንሀም

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
90 ' ፒኤስጂ 5- 4 የሪያድ ምርጦች

ሊዮኔል ሜሲ     ክርስቲያኖ ሮናልዶ
ማርኪኖስ              ሱን ያንግ
ራሞስ ታሊስካ
ምባፔ
ኢክቲኬ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ተጠናቀቀ | ፒኤስጂ 5- 4 የሪያድ ምርጦች

ሊዮኔል ሜሲ     ክርስቲያኖ ሮናልዶ
ማርኪኖስ              ሱን ያንግ
ራሞስ ታሊስካ
ምባፔ
ኢክቲኬ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
44' ማንችስተር ሲቲ 0-1 ቶተንሀም

ኩሉሴቭስኪ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
45' ማንችስተር ሲቲ 0-2 ቶተንሀም

ኩሉሴቭስኪ
ሮያል

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ባርሴሎና ወደ ቀጣዩ ዙር አልፏል !

በስፔን የኮፓ ዲላሪ ውድድር የካታላኑ ክለብ ባርሴሎና ከ ክዌታ ያደረገውን ጨዋታ 5ለ0 በሆነ ሰፊ የግብ ልዩነት በማሸነፍ ወደ ቀጣዩ ዙር አልፏል ።

የባርሴሎናን የማሸነፊያ ግቦች ራፊንሀ ፣ ሉዋንዶውስኪ 2x ፣ አንሱ ፋቲ እና ኬሴ ከመረብ ማሳረፍ ችለዋል ።

ባርሴሎና በተከታታይ ያደረጓቸውን ያለፉት አስር ጨዋታዎች አልተሸነፉም ።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
51' ማንችስተር ሲቲ 1-2 ቶተንሀም

     አልቫሬዝ       ኩሉሴቭስኪ
                            ሮያል

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
53' ማንችስተር ሲቲ 2-2 ቶተንሀም

     አልቫሬዝ       ኩሉሴቭስኪ
     ሀላንድ           ሮያል

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
63' ማንችስተር ሲቲ 3-2 ቶተንሀም

     አልቫሬዝ       ኩሉሴቭስኪ
     ሀላንድ           ሮያል
ማህሬዝ
@tikvahethsport     @kidusyoftahe
89' ማንችስተር ሲቲ 4-2 ቶተንሀም

     አልቫሬዝ       ኩሉሴቭስኪ
     ሀላንድ           ሮያል
    ማህሬዝ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ማንችስተር ሲቲ ወሳኝ ድል አስመዝግቧል !

በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ተስተካካይ መርሐ ግብር ማንችስተር ሲቲ ከቶተንሀም ጋር ያደረገውን ጨዋታ ከመመራት በመነሳት 4ለ2 በሆነ ውጤት ማሸነፍ ችሏል።

የማንችስተር ሲቲን የማሸነፊያ ግቦች ኤርሊንግ ሀላንድ ፣ ሪያድ ማህሬዝ 2x እና አልቫሬዝ ከመረብ ማሳረፍ ሲችሉ ለቶተንሀም ግቦችን ኩሉሴቭስኪ እና ሮያል አስቆጥረዋል ።

ኤርሊንግ ሀላንድ በውድድር አመቱ ሀያ ሁለተኛ ግቡን በማስቆጠር የውድድሩ ከፍተኛ ግብ አስቆጣሪዎች ደረጃን መምራቱን ቀጥሏል።

ማንችስተር ሲቲ ማሸነፉን ተከትሎ ከሊጉ መሪ አርሰናል ያለውን የነጥብ ልዩነት ወደ አምስት በማጥበብ በአርባ ሁለት ነጥብ #ሁለተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል ።

ቶተንሀም በሊጉ ደረጃ ሰንጠረዥ ሰላሳ ሶስት ነጥቦችን በመሰብሰብ #አምስተኛ ደረጃ ላይ መቀመጥ ችሏል።

በቀጣይ የሊጉ መርሐ ግብር ማንችስተር ሲቲ ከዎልቭስ እንዲሁም ቶተንሀም ከ ፉልሀም የሚገናኙ ይሆናል ።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ሪያል ማድሪድ ቀጣዩን ዙር ተቀላቅሏል !

በስፔን ኮፓ ዲላሪ ውድድር ሪያል ማድሪድ ከ ቪያሪያል ያደረገውን ጨዋታ ከመመራት ተነስት 3ለ2 በማሸነፍ ቀጣዩን ዙር መቀላቀሉን አረጋግጧል ።

የሪያል ማድሪድን የማሸነፊያ ግቦች ቪንሰስ ጁንየር ፣ ሚሊታዎ እና ሴባሎስ ሲያስቆጥሩ የቪያሪያልን ግብ ካፖ እና ቹኩዌዜ ከመረብ አሳርፈዋል።

ቪያሪያል ከስምንት ጨዋታዎች ያለመሸነፍ ጉዞ በኋላ ሽንፈት አስተናግደዋል ።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ጁቬንቱስ ወደ ቀጣዩ ዙር አልፏል !

በኮፓ ኢጣልያ ውድድር የማሲሚሊያኖ አሌግሪው ጁቬንቱስ ከሞንዛ ያደረገውን ጨዋታ 2ለ1 በሆነ ውጤት በማሸነፍ ቀጣዩን ዙር ተቀላቅሏል።

የጁቬንቱስን የማሸነፊያ ግቦች ሞይስ ኪን እና ቼሳ ሲያስቆጥሩ የሞንዛን ግብ ቫሎቲ ማስቆጠር ችሏል።

በሌላ የኮፓ ኢጣልያ ጨዋታ አታላንታ እና ላዚዮ ወደ ቀጣዩ ዙር ማለፋቸውን አረጋግጠዋል ።

ጁቬንቱስ በቀጣይ የኮፓ ኢጣልያ ዙር ከላዝዮ የሚገናኙ ይሆናል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ዋናው የዋናው አልባሳት የንግድ ምልክት ነው !

በጤና ቡድኖች እና በደጋፊዎች ተመራጭ እና ምቹ የሆኑትን ትጥቆች እንደተለመደው በተመጣጣኝ ዋጋ በመረጡት ዲዛይን እና የቀለም ምርጫ ሰርቶ ያቀርብልዎታል።

📞 ይደውሉ :- 📱0910 851 535   
                      📱0901138283

ቻናላችን :- https://t.iss.one/wanawsportwear

📌 አድራሻ ፦ ገርጂ መብራት ሃይል የካቲት ወረቀት ፊትለፊት

ማልያችን መለያችን ዋናው ወደ ፊት. . . . .
የፈረንሳይ የወሩ ምርጥ ተጨዋች ተብሏል !

ፈረንሳያዊው የፒኤስጂ የፊት መስመር ተጨዋች ኪሊያን ምባፔ የፈረንሳይ ሊግ የወርሀ ህዳር/ታህሳስ የወሩ ምርጥ ተጨዋች በመባል መመረጡ ይፋ ተደርጓል።

የ 24ዓመቱ ፈረንሳዊ ተጨዋች ኪሊያን ምባፔ የፈረንሳይ ሊግ የወሩ ምርጥ ተጨዋች ተብሎ ሲመረጥ ይህ #ለስምንተኛ ጊዜ መሆኑ ተገልጿል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
የቶተንሀም ደካማ ጉዞ ቀጥሏል !

የሰሜን ለንደኑ ክለብ ቶተንሀም ባደረጓቸው ያለፉት አስር የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ጨዋታዎች ላይ ጥሩ ውጤት ማስመዘገብ ሳይችሉ ቀርተዋል ።

በአንቶንዮ ኮንቴ የሚመሩት ቶተንሀሞች ለመጨረሻ ጊዜ ካደረጓቸው አስር የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ጨዋታዎች ማሸነፍ የቻሉት #ሶስቱን ብቻ እንደሆነ ተገልጿል ።

ቶተንሀም በሊጉ ደረጃ ሰንጠረዥ ሰላሳ ሶስት ነጥቦችን በመሰብሰብ ከሊጉ መሪ አርሰናል በአስራ አራት ነጥብ ርቀው #አምስተኛ ደረጃ ላይ ይገኛሉ ።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ሮበርት ሊዋንዶውስኪ በጥሩ ብቃቱ ቀጥሏል !

የካታላኑ ክለብ ባርሴሎና የፊት መስመር ተጨዋች ሮበርት ሉዋንዶውስኪ ለክለቡ በተሰለፈባቸው ሀያ ሶስት ጨዋታዎች ጥሩ የሚባል ጊዜን ማሳለፍ ችሏል።

ፖላንዳዊው አጥቂ ሮበርት ሉዋንዶውስኪ ለባርሴሎና ሀያ ሶስት ጨዋታዎች ላይ ተሰልፎ በመጫወት ሀያ አምስት ግቦችን ሲያስቆጥር አምስት ለግብ የሚሆኑ ኳሶችን አመቻችቶ አቀብሏል።

የ 34ዓመቱ አጥቂ ሮበርት ሉዋንዶውስኪ በካታላኑ ክለብ ባርሴሎና ቤት የመጀመሪያ ዋንጫውንም በዚሁ የውድድር ዓመት ማሳካት ችሏል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
ዋልያዎቹ ልምምዳቸውን ቀጥለዋል !

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን የምድብ የመጨረሻ ጨዋታውን በሚያደርግበት አናባ ከተማ ትላንት ምሽት የመጀመሪያ ልምምዱን አድርጓል።

በቀዝቃዛ የአየር ንብረት ልምምዳቸውን የሰሩት ዋልያዎቹ በነገው ዕለት ወሳኝ የምድብ ጨዋታቸውን ከሊቢያ ጋር የሚያደርጉ ይሆናል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ሊቨርፑል ተጫዋቹ ወደ ልምምድ ተመልሷል !

የመርሲሳይዱ ክለብ ሊቨርፑል የፊት መስመር ተጫዋች ዳርዊን ኑኔዝ ካጋጠመው ጉዳት በማገገም ወደ ልምምድ መመለሱ ተገልጿል ።

ዩራጋዊው የፊት መስመር ተጫዋች ዳርዊን ኑኔዝ በኤፌ ካፕ ውድድር ሊቨርፑል ከ ዎልቭስ ባደረገው ጨዋታ ላይ የጡንቻ ጉዳት ማስተናገዱ ይታወሳል ።

የ 23ዓመቱ የፊት መስመር አጥቂ ዳርዊን ኑኔዝ ነገ ሊቨርፑ ከቼልሲ በሚያደርጉት የሊግ ጨዋታ ወደ ሜዳ ሊመለስ እንደሚችል ተነግሯል ።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe