TIKVAH-SPORT
246K subscribers
46.8K photos
1.48K videos
5 files
2.97K links
Download Telegram
ሊቨርፑል እና ቼልሲ ነጥብ ተጋርተዋል !

በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ሀያ አንደኛ ሳምንት መርሐ ግብር ሊቨርፑል ከ ቼልሲ ያደረጉትን ተጠባቂ ጨዋታ 0ለ0 በሆነ አቻ ውጤት ማጠናቀቅ ችለዋል ።

ቼልሲ ከሜዳቸው ውጭ ያደረጓቸውን ያለፉት ሰባት ጨዋታዎች ማሸነፍ አልቻሉም ።

የሊቨርፑል ዋና አሰልጣኝ የርገን ክሎፕ በአሰልጣኝነት ታሪካቸው 1,000ኛ ጨዋታቸውን መምራት ችለዋል ።

የቼልሲ አዲሱ ፈራሚ ማይካይሎ ሙድሪክ ለሰማያዊዎቹ የመጀመሪያ ጨዋታውን ማድረግ ችሏል።

በሊጉ ደረጃ ሰንጠረዥ ሁለቱም ክለቦች ከ ሊጉ መሪ አርሰናል በአስራ ስምንት ነጥብ ርቀው በእኩል ሀያ ዘጠኝ ነጥብ ሊቨርፑል #ስምንተኛ ቼልሲ #አስረኛ ደረጃ ላይ ተቀምጠዋል ።

የመርሲሳይዱ ክለብ ሊቨርፑል በቀጣይ መርሐ ግብር ከ ዎልቭስ የሚገናኙ ሲሆን ቼልሲዎች በበኩላቸው ከ ፉልሀም የሚጫወቱ ይሆናል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
" ፈታኝ ጊዜ ላይ እንገኛለን "

የመርሲሳይዱ ክለብ ሊቨርፑል ተጫዋች ጄምስ ሚልነር ከቼልሲ ጋር ካደረጉት ጨዋታ መጠናቀቅ በኋላ በሰጠው አስተያየት ቡድኑ ከባድ ጊዜን እያሳለፈ እንደሚገኝ ተናግሯል።

እንደ ተጫዋቹ አስተያየትም " በዛሬው ጨዋታ ግብ ሳይቆጠርብን መውጣት መቻላችን ትልቅ ነገር ነው ፣ ፈታኝ ጊዜ እያሳለፍን ብንገኝም ከዚህ ፈተና ለመውጣት ጠንክርን መስራት ይኖርብናል " ሲል ጄምስ ሚልነር ተናግሯል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
አሰልጣኝ ግራም ፖተር ስለ ሙድሪክ ምን አሉ ?

የለንደኑ ክለብ ቼልሲ ዋና አሰልጣኝ ግራም ፖተር ስለ አዲሱ ፈራሚያቸው ማይካይሎ ሙድሪክ ከሊቨርፑል ጨዋታ መጠናቀቅ በኋላ አስተያየታቸውን ሰጥተዋል።

" ሙድሪክ ለረጅም ጊዜያት ከጨዋታ ርቆ በመቆየቱ የተወሰኑ ደቂቃዎችን ብቻ እንዲጫወት አድርገነዋል ፣ በሜዳ ላይ ያለውን ብቃት መመልከት ችላቹሀል የነበረው ሚና ጉልህ ነበር " በማለት ተናግረዋል።

@tikvahethsport @kidusyoftahe
ዶርትመንድ የወሳኝ ተጫዋቹን ውል አራዝሟል !

የጀርመኑ ክለብ ቦርስያ ዶርትመንድ የፊት መስመር ተጫዋቻቸውን ዩሱፋ ሙኮኮ ኮንትራት ውል ለተጨማሪ ዓመታት ማራዘማቸውን ይፋ አድርገዋል።

ጀርመናዊው የፊት መስመር ተጫዋች ዩሱፋ ሙኮኮ በዶርትመንድ ቤት እስከ 2026 የሚያቆየውን የሶስት አመት ኮንትራት ውል ማደሱ ተገልጿል።

ከዶርትመንድ የታዳጊዎች አካዳሚ የተገኘው የ 18ዓመቱ አጥቂ በ 2020 የዶርትመንድ ዋናው ቡድን ተቀላቅሎ ባለፉት ጊዜያት አርባ ስድስት ጨዋታዎች ላይ ተሰልፎ አስራ ሁለት ግቦችን አስቆጥሯል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
" በውጤቱ በጣም ደስተኛ ነኝ "

ጀርመናዊው የሊቨርፑል ዋና አሰልጣኝ የርገን ክሎፕ በአሰልጣኝነት ዘመናቸው 1000ኛ ጨዋታቸውን በመሩበት መርሐ ግብር አቻ መውጣታቸው እንዳስደሰታቸው ተናግረዋል።

የርገን ክሎፕ በሰጡት አስተያየት " አርሰን ቬንገር 1000ኛ ጨዋታቸውን በቼልሲ 6ለ0 ተሽንፈዋል ስለዚህ በዛሬው ውጤት በግሌ በጣም ደስተኛ ነኝ " ሲሉ ተናግረዋል።

@tikvahethsport @kidusyoftahe
#Bundesliga 🇩🇪

የጀርመን ቡንደስሊጋ አስራ ስድስተኛ ሳምንት መርሐግብር አምስት ጨዋታዎች በተመሳሳይ ሰዓት ተደርገዋል ።

በሊጉ ጥሩ የውድድር አመት በማሳለፍ ላይ የሚገኙት ፍራክፈርቶች ከሻልክ 04 ያደረጉትን ጨዋታ 3ለ0 በሆነ ውጤት ማሸነፍ ችለዋል።

ፍራንክፈርት ከሊጉ መሪ ባየርሙኒክ ያላቸውን ነጥብ ልዩነት ወደ አምስት በማጥበብ በሊጉ ደረጃ ሰንጠረዥ #ሁለተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጠዋል ።

በውድድር አመቱ በጥሩ ግስጋሴ ላይ የሚገኘው ሌላኛው ክለብ ፍሬቡርግ በዎልፍስበርግ 6ለ0 ተሸንፎ ከሊጉ መሪ ባየርሙኒክ ያለውን የነጥብ ልዩነት ወደ ሁለት ማጥበብ ሳይችል ቀርቷል ።

ፍሬቡርግ በሊጉ ደረጃ ሰንጠረዥ ሰላሳ ነጥቦችን ሰብስቦ #ሶስተኛ ደረጃ ላይ መቀመጥ ችሏል።

በወራጅ ቀጠናው የሚገኙት ሻልክ 04 እና ሄርታ በርሊን ዛሬ ባደረጉት ጨዋታ ላይም ሽንፈት አስተናግደዋል ።

የቡንደስሊጋው ቀሪ ጨዋታ ውጤቶች ከላይ በምስሉ ላይ ተያይዟል ።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
#PremiereLeague 🇬🇧

በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ የሀያ አንደኛ ሳምንት መርሐ ግብር በተደረጉ ጨዋታዎች ዌስትሀም ድል ሲቀናው ሌስተር ሲቲ እና ብራይተን ነጥብ ተጋርተዋል ።

ዋስትሀም በለንደን ስታዲየም ከመርሲሳይዱ ክለብ ኤቨርተን ጋር ያደረገውን ጨዋታ 2ለ0 በሆነ ውጤት ማሸነፍ ችሏል።

የዌስትሀምን የማሸነፊያ ግቦች ጃሮድ ቦውን ከመረብ ማሳረፍ ችሏል።

ሌስተር ሲቲ በኪንግ ፓወር ስታዲየም ከብራይተን ጋር ጨዋታውን አድርጎ በመጨረሻ ደቂቃ በተቆጠረበት ግብ ጨዋታውን 2ለ2 በሆነ አቻ ውጤት አጠናቋል ።

የሌስተርን ግቦች ኦልብራይተን እና ባርንስ ሲያስቆጥሩ የብራይተንን የአቻነት ግቦች ሚቶማ እና ፈርጉሰን ከመረብ አሳርፈዋል ።

በሌላ ጨዋታ አስቶንቪላ ሳውዛምፕተንን በዋትኪንስ ግብ 1ለ0 በሆነ ውጤት ማሸነፍ ችሏል።

የመርሲሳይዱ ክለብ ኤቨርተን እና ሳውዛምፕተን መሸነፋቸውን ተከትሎ በሊጉ ደረጃ ሰንጠረዥ በእኩል አስራ አምስት ነጥብ አስራ ዘጠነኛ እና ሀያኛ ደረጃ ላይ ተቀምጠዋል ።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ዋልያዎቹ ስታዲየም ደርሰዋል !

ከሰዓታት በኋላ የሊቢያ ብሔራዊ ቡድንን የሚገጥሙት ዋልያዎቹ ከጥቂት ደቂቃዎች በፊት በ " Stade 19-Mai-1956 " ስታዲየም ደርሰዋል።

ዋልያዎቹ ወደ ቀጣዩ ዙር ለማለፍ #ማሸነፍ እና በምድቡ ሌላኛ ጨዋታ የሞዛምቢክ ብሔራዊ ቡድንን #መሸነፍን ይጠብቃሉ።

@tikvahethsport @kidusyoftahe
የዋልያዎቹ አሰላለፍ ታውቋል !

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ከሊቢያ አቻው ጋር ለሚያደርገው የምድብ የመጨረሻ ጨዋታ በ 4-3-3 የጨዋታ አሰላለፍ ወደ ሜዳ ይገባሉ።

ፋሲል ገብረ ሚካኤል

ሱሌማን ሀሚድ
ሚልዮን ሰለሞን
ምኞት ደበበ
ረመዳን የሱፍ

ጋቶች ፓኖም
መስዑድ መሀመድ
ቢንያም በላይ

ቸርነት ጉግሳ
አማኑኤል ገብረ ሚካኤል
ከንአን ማርክነህ

@tikvahethsport @kidusyoftahe
ናፖሊ ወሳኝ ድል አስመዝግቧል !

በጣልያን ሴሪያ አስራ ዘጠነኛ ሳምንት መርሐ ግብር የሊጉ መሪ ናፖሊ ከ ሳለርኒታና ያደረገውን ጨዋታ 2ለ0 በሆነ ውጤት በማሸነፍ መሪነቱን አጠናክሯል ።

የናፖሊን የማሸነፊያ ግቦች ቪክቶር ኦስሜን እና ዲ ሎሬንዞ ከመረብ ማሳረፍ ችለዋል ።

ናፖሊ በውድድር አመቱ አስራ ስድስተኛ ድሉን ማስመዝገብ የቻለ ሲሆን ይህም ከአምስቱ ታላላቅ የአውሮፓ ሊጎች ብዙ ጨዋታ ያሸነፈ ብቸኛ ክለብ ያደርገዋል ።

ቪክቶር ኦስሜን የውድድር አመቱን አስራ ሶስተኛ ግብ በማስቆጠር የሊጉ ከፍተኛ ግብ አስቆጣሪ መሆን ችሏል።

ናፖሊ ማሸነፉን ተከትሎ ከተከታዮቹ ያለውን የነጥብ ልዩነት ወደ አስራ ሁለት በማስፋት በሃምሳ ነጥብ ሊጉን #በአንደኝነት መምራቱን ቀጥሏል።

ናፖሊ በቀጣይ የሊጉ መርሐ ግብር ከጆዜ ሞሪንሆው ሮማ ጋር የሚገናኙ ሲሆን ሳለርኒታና በበኩላቸው ከ ሊቼ የሚጫወቱ ይሆናል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ተጀመረ !

ኢትዮጵያ 0-0 ሊቢያ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
15' ኢትዮጵያ 0-0 ሊቢያ

15' አልጄሪያ 1-0 ሞዛምቢክ

ዴህሪ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ተጠናቀቀ | ክሪስትያል ፓላስ 0-0 ኒውካስል ዩናይትድ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe