TIKVAH-SPORT
246K subscribers
46.8K photos
1.48K videos
5 files
2.97K links
Download Telegram
ሊቨርፑል ሽንፈት አስተናግደዋል !

የመርሲሳይዱ ክለብ ሊቨርፑል በሊጉ መርሐ ግብር ከብራይተን ጋር ጨዋታውን አድርጎ 3ለ0 በሆነ ውጤት ተሸንፏል ።

የብራይተንን የማሸነፊያ ግቦች ማርች 2x እና ዳኒ ዌልቤክ ከመረብ ማሳረፍ ችለዋል ።

ሊቨርፑል በተከታታይ ባደረጋቸው ዘጠኝ ጨዋታዎች ላይ ግብ #ሳይቆጠርበት መውጣት አልቻለም ።

ብራይተን ማሸነፉን ተከትሎ በሊጉ ደረጃ ሰንጠረዥ ሊቨርፑልን በመብለጥ በሰላሳ ነጥብ #ሰባተኛ ደረጃ ላይ ሲቀመጥ ሊቨርፑል በሀያ ስምንት ነጥብ #ስምንተኛ ደረጃ ላይ ይገኛል ።

በቀጣይ የሊጉ መርሐ ግብር ሊቨርፑል ከ ቼልሲ የሚገናኙ ሲሆን ብራይተን በበኩላቸው ከሌስተር ሲቲ የሚገናኙ ይሆናል ።

በሌላ የሊግ ጨዋታ ሳውዛምፕተን ኤቨርተንን 2ለ1 ሲያሸንፍ ኖቲንግሀም ፎረስት ሌስተርን 2ለ0 አሸንፏል ።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe