TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.6K photos
1.43K videos
206 files
3.97K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#Attention😷

በዶ/ር ሠኢድ መሐመድ (የአጥንት ቀዶ ህክምና ስፔሻሊስት) ፦

የኮቪድ-19 ታማሚዎች እና የፅኑ ህሙማን መጠን የህዝቡን መዘናጋት በሚመጥን መልኩ በከፍተኛ ሁኔታ እየጨመረ በመምጣቱ ምክንያት ከአቅም በላይ የሆነ የኦክስጅን እጥረት ስለተከሰተ፣ ባሳለፍነው ሳምንት አዲስ አበባ ውስጥ ያሉ በርካታ ሆስፒታሎች ከክልል ከተሞች ኦክስጅን በአይሱዙ እያስጫኑ ለማምጣት ተገደዋል። አሁን ግን የክልል ከተሞችም ኦክስጅን እጥረት እያጋጠማቸው ነው።

ለምሳሌ ትላንት ሲዳማ ክልል ውስጥ ያሉ የመተንፈሻ ማሽኖች ሙሉ በሙሉ በኮቪድ ታማሚዎች በመያዛቸው ምክንያት ተጨማሪ ታማሚ ቢመጣ ምንም እርዳታ መስጠት እንደማይችሉ አሳውቀዋል። ሌሎች ክልሎች ውስጥ ተመሳሳይ ችግር እያጋጠመ እንደሆነ ተሰምቷል።

በዚህም ምክንያት ሠሞኑን የቀዶ ህክምና ስንሠራ ሠርጀሪው ተራዝሞ ኦክስጂን ያጥረን ይሆን? እያልን እየተሳቀቅን ነበር።

ከቀጣዩ ሳምንት ጀምሮ ደግሞ አዲስ አበባ ውስጥ ያሉ በርካታ ሆስፒታሎች ከድንገተኛ ህክምና ውጪ ያሉ የቀዶ ህክምናዎችን መስራት ያቆማሉ።

ኮቪድ-19 የመጨረሻ ማስጠንቀቂያ ሠጥቶን ሳንቀበለው በመቅረታችን የተፈራው መከሠት ጀምሯል።

አሁን ያለው የስርጭት ብዛት እና ከተለያዩ ሐገራት አንፃር ከፍተኛ የሚባለው በበሽታው የመያዝ ምጣኔ ትምህርት ቤቶችን ፣ አላስፈላጊ ስብሰባዎችን እና የዕምነት ተቋማትን በከፊል ወይም በሙሉ ለመዝጋት የሚያስገድድ ደረጃ ላይ የደረሰ ይመስለኛል። የጭፈራ ቤቶች ፣ ሲኒማ ቤቶች ፣ ጫት ማስቃሚያ ቤቶች ለህዝቡ ህልውና ሲባል በአፋጣኝ መዘጋት አለባቸው። ከዚህ በፊት የነበረው ጥንቃቄ የቱን ያህል በሽታውን ባለበት ለማስቆም ረድቶን እንደነበረ ማስታወስ ያስፈልጋል።

በተለይም በቀን አምስት ጊዜ በርካታ ህዝብ የሚሠባሰብባቸው መስጊዶች፣ ሠጋጆቻቸው ማስክ እንዲያደርጉ ፣ ተራርቀው እንዲቆሙ እና በተቻለ መጠን አየር በደምብ የሚገኝበት ስፍራ፣ ማለትም ግቢ ውስጥ ወይም ከበር ውጪ እንዲሠግዱ በማድረግ የጥንቃቄያቸውን መጠን እስከመጨረሻው ጥግ እንዲያሳድጉ ማሳሰብ ያስፈልጋል።

አብያተ ክርስቲያናትም የፀሎት ስነስርአቶቻቸውን ሲያከናውኑ የመጨረሻ (maximum) ጥንቃቄ ሊያደርጉ የሚገባበት ጊዜ አሁን ነው።

#No_Oxygen
#ኢትዮጵያ
#ኮቪድ19
#covid_is_real!

@tikvahethiopia