TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
56.9K photos
1.42K videos
205 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
በራይድ እና ዛይ ራይድ መካከል ውዝግብ ተነስቷል! በራይድ ትራንስፖርት አገልግሎት እና ዛይ ራይድ ሜትር ታክሲ መካከል ከንግድ ስም ባለቤትነት እና ከፈጠራ ባለቤትነት መብቶች ጋር በተያያዘ በተነሳው ውዝግብ ራይድ ባቀረበው አቤቱታ መሰረት በንግድ ውድድር እና ሸማቾች ጥበቃ ባለሥልጣን ምርመራ ተጀመረ። ከአራት ወራት በፊት ራይድ ትራንስፖርት አገልግሎት የስያሜው የባለቤትነት መብት ይገባኛል በሚል ለኢትዮጵያ…
#RIDE #ZayRide

ራይድ ትራንፖርት የቅርብ ተወዳዳሪው ዛይ ራይድ ታክሲ ላይ አቅርቦት የነበረው ከስያሜ እና ከንግድ ምልክት ባለቤትነት ጋር የተያያዘ አቤቱታ ለክስ የሚያበቃ ምክንያት የለውም በማለት የንግድ ውድድር እና ሸማቾች ጥበቃ ባለሥልጣን ውድቅ አደረገው።

ሁለቱ ተቋማት የትራንስፖርት አገልግሎትን በቴክኖሎጂ በመደገፍ ተጠቃሚዎችን እና ደንበኞችን በስልክ መተግበሪያዎች በማገናኘት የትራንስፖርት አገልግሎት ላይ የተሰማሩ ሲሆን ከንግድ ስያሜ እና ከባለቤትነት መብት ጋር በተያያዙ ጉዳዮች ወዝግብ ውስጥ ገብተው እንደነበር የሚታወስ ነው።

ምንጭ፦ አዲስ ማለዳ ጋዜጣ
@tsegabwolde @tikvahethiopia