TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
62.9K photos
1.61K videos
216 files
4.37K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

መረጃ እና መልዕክት ፦ 0919743630

ማርኬቲንግ ፦ 0979222111 ወይም
0979333111

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#WeyzeroLemlemBezabeh

ከድሬዳዋ አስተዳደር ጤና ቢሮ የተሰጠ ወቅታዊ መግለጫ ፦

- ከጅቡቲ ተመላሾችን ከድንበር ጀምሮ በተደራጀ መልኩ እንዲሰባሰቡና ወደለይቶ ማቆያ ማዕከላት ገብተው የጤንነታቸው ሁኔታ ተረጋግጦ ወደየአካባቢያቸው እንዲመለሱ ለመስቻል ስራዎች እየትሰሩ ነው።

- በአሁን ሰዓት ከ700 በላይ ከጅቡቲ ተመላሾች በለይቶ ማቆያ ማዕከላት ገብተው የጤና ክትትል እየተደረገላቸው ነው።

- ቀደም ሲል በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው የተገለፀውና በለይቶ ህክምና ተቋም ያሉ 6 ሰዎች በመልካም ጤንነት ላይ ይገኛሉ።

- መደበኛ የጤና አገልግሎቶች ፦ የእናቶችና ህፃናት ጤና፣ ክትባት፣ ተላላፊ ያልሆኑ በሽታዎች ቋሚ የጤና ክትትል የሚደልጉ እንደ ስኳር፣ ደምግፊት ፣ ኤች አይቪና የመሳሰሉት ለኮሮና ለይቶ ማቆያና ህክምና ከተመረጡ ተቋማት ውጭ በሌሎች ተቋማት በመደበኛነት የሚሰጡ በመሆኑ ህብረተሰቡ ይህንን ተገንዝቦ የአገልግሎቱ ተጠቃሚ እንዲሆን ተጠይቋል።

- የደም እጥረትን ለመቅረፍ የደም ልገሳ ተጠናክሮ እንዲቀጥል ተጠይቋል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia