TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.5K photos
1.43K videos
206 files
3.96K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#UNIVERSITY

በዘንድሮው ዓመት በመንግስት #ዩኒቨርሲቲዎች ቅበላ የሚያገኙ ተማሪዎች በተፈጥሮ ሳይንስ ወንድ 46 ሺህ 416፣ ሴት 32 ሺህ 865 በድምሩ 79 ሺህ 281 ሲሆኑ ፥ በማህበራዊ ሳይንስ ደግሞ ወንድ 34 ሺህ 838 ሴት 28 ሺህ 702 በድምሩ 63 ሺህ 540 መሆናቸው ተገልጿል።

በዚህ መሰረትም ወደ መንግስት ዩኒቨርሲቲዎች ከሚገቡ ተማሪዎች 55 ነጥብ 5 በመቶ የሚሆኑት የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች ሲሆኑ፥44 ነጥብ 5 በመቶዎቹ ደግሞ የማህበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች ናቸው።

የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር እንዳስታወቀው በዘንድሮው ዓመት በአጠቃላይ ወደ መንግስት ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት የሚገቡ ተማሪዎች ቁጥር 142 ሺህ 821 ነው። የመንግስት ዩኒቨርስቲዎች መግቢያ አራት መሰረታዊ የትምህርት አይነቶችን ውጤት መሠረት አድርጎ እንደሚወሰን መገለጹ ይታወሳል።

Via ኤፍ ቢ ሲ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#university

የኢትዮጵያ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ነባርና አዳዲስ ተማሪዎቻቸውን መቀበል ጀምረዋል፡፡ ዩኒቨርሲቲዎቹ ካለፉት ጊዜያት በተለዬ ተማሪዎቻቸውንና ወላጆቻቸውን ውል አስገብተው ነው እየተቀበሉ የሚገኙት፡፡ የወልዲያ ዩኒቨርሲቲ ዛሬ አዳዲስ ተማሪዎቹን መቀበል ጀምሯል፤ ሠላማዊ የመማር ማስተማር ሂደት እንዲኖር የሚያስችል የቅድመ ዝግጅት ሥራ አጠናቅቆ ተማሪዎችን መቀበል መጀመሩን ነው ዩኒቨርሲቲው ያስታወቀው፡፡

Via #AMMA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#FederalPolice #University #Ethiopia

በአማራና ኦሮሚያ ክልሎች በዩኒቨርሲቲዎች አጋጥመው ለነበሩ ግጭቶች እጃቸው አለበት የተባሉ የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች፣ መምህራንና የአስተዳደር ሰራተኞች እየተለዩ በፖሊስ ቁጥጥር ስር እየዋሉ ነው። የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ከዩኒቨርሲቲዎች ጋር በመተባበር ተጠርጣሪዎችን የመለየት ስራውን አሁንም እንደቀጠለ ነው ተብሏል። የኮሚሽኑ የኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ኃላፊ አቶ ጀይላን አብዲ በቁጥጥር ስር የዋሉትን ተጠርጣሪዎች ብዛት አሁን ላይ መናገር ባንችልም ከዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች፣ መምህራርንና የአስተዳደር ሰራተኞች ውስጥ ግጭት አነሳስተዋል የተባሉት ተለይተው እየታሰሩ ነው ብለዋል።

(ሸገር ኤፍ ኤም 102.1)
@tikvahethiopia @tikvahethiopia