TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.4K photos
1.51K videos
215 files
4.11K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#UnitedNations

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሰብአዊ እርዳታ ቢሮ ለረሃብ አደጋ ተጋላጭ ናቸው ላላቸው 7 የአፍሪካ እና የመካከለኛው ምስራቅ ሀገራት የ100 ሚሊዮን ዶላር ድጋፍ ማድረጉን (Al Ain News) ዘግቧል።

እንደ ቢሮው መግለጫ 80 ሚሊዮን ዶላር ለየመን፣ ለቡርኪና ፋሶ ፣ ለኮንጎ ፣ ለናይጀሪያ ፣ ለደቡብ ሱዳን እና አፍጋኒስታን ተሰራጭቷል።

ቀሪው 20 ሚሊዮን ዶላር ደግሞ ለኢትዮጵያ መመደቡን ከAl Ain News የተገኘው መረጃ ያሳያል።

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
#UnitedNations

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት (UN) በይፋዊ የትዊተር ገፁ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ ለሁለተኛ ጊዜ የድርጅቱ ዋና ፀሀፊ በመሆን ዳግም እንደተመረጡ አሳውቋል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Tigray , #Mekelle 📍 አሚና መሐመድ ትግራይ ክልልን ጎብኝተዋል። የተባበሩት መንግስታት ድርጅት (UN) ምክትል ዋና ፀሀፊ አሚና መሐመድ የተመራ ልዑክ ዛሬ በትግራይ ክልል መቐለ ጉብኝት አድርጓል። የልዑካን ቡድኑ በመቐለ ከተማ ዓይደር ሪፈራል ሆስፒታልን ተዘዋውሮ ጎብኝቷል ፤ የጤና ባለሞያዎችን አነጋግሯል። ከዚህ በተጨማሪም በመቐለ የሚገኙ በጦርነት የተፈናቀሉ ወገኖች የሚገኙባቸውን ካምፖች…
ስለ አሚና መሐመድ የአማራ እና የትግራይ ክልል ጉብኝት ምን ተባለ ?

የተባበሩት መንግሥታቱ ድርጅት ምክትል ዋና ፀሐፊ አሚና መሐመድ በጦርነቱ የተጎዱ የአማራና የትግራይ ክልል ከተሞችን ጎብኝተዋል። እንዲሁም ከክልል አመራሮች ጋር ተገናኝተዋል።

አሚና ባለፈው እሁድ በአማራ ክልል ኮምቦልቻን የጎበኙ ሲሆን ጦርነቱ በሕዝቡ በተለይ በሴቶችና በህፃናት ላይ ያደረሰውን አስከፊ ጉዳት ማየታቸውን ተመድ አስታውቋል።

በሆስፒታሎች፣ በሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች፣ በገበያ ስፍራዎች እና በሌሎች አካባቢዎች ላይ የደረሰውን ዘረፋና ውድመት የተመለከቱ ሲሆን የአማራ ክልል ምክትል ፕሬዚዳንትን ጨምሮ ሌሎችንም ባለሥልጣናትን አግኝተዋል።

ከኮምቦልቻ ጉብኝታቸው በኋላ ጦርነቱ ብዙ ያስከፈለ መሆኑን ገልጸው ሰላም ብቸኛ አማራጭ እንደሆነ ተናግረዋል "የኢትዮጵያን ሕዝብ ሰላም እንዲያገኝ መርዳት አለብን" ሲሉም ተናግረዋል።

ከኮምቦልቻ ቀጥለቅ ወደ ትግራይ ክልል፣ መቐለ ያቀኑት አሚና በጦርነቱ በሴቶችና በህፃናት ላይ ያደረሰውን አስከፊ ገፅታ ተመልክተዋል።

ግጭቱን በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት እና ለኢትዮጵያውን የሚያመጣውን እፎይታን በተመለከተ ከዶ/ር ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል ጋር መወያየታቸው ንተመድ ገልጿል።

አሚና በተመድ የሚደገፈውንና ከወሲባዊ ጥቃት የተረፉ ሴቶችን ጨምሮ ሁሉን አቀፍ ድጋፍ የሚያደርገውን የአይደር ሆስፒታልን ጎብኝተዋል።

" በግጭት ውስጥ አሸናፊዎች እንደሌሉ " በመጥቀስ ወሲባዊ ጥቃት የተረፉ ሴቶቹ ታሪኮች ሊነገሩ እንደሚገባ አፅንኦት ሰጥተዋል።

በሁለቱ ክልሎች ከሴቶች እንዲሁም ከተማሪዎች ጋር ባደረጉት ቆይታ የተመድ ወሲባዊ እንዲሁም ፆታን መሰረት ላደረጉ ጥቃቶችን እንደማይታገስ አፅንኦት በመስጠት ተናግረዋል።

አሚና ወሲባዊ ጥቃት ለደረሰባቸው ሴቶች አጋርነታቸውን ገልፀዋል።

በጦርነቱ ምክንያት በሴቶች ላይ የደረሰውን ግፍ እና በደል እንዲሁም አካላዊና ሥነ ልቦናዊ ጉዳት ለማቃለል ተመድ መፍትሄ በማፈላለግ ድጋፉን አጠናክሮ እንደሚቀጥል ተናግረዋል።

ሴቶች ካለባቸው ህመም እንዲፈወሱ በተሃድሶ እና በመልሶ ማቋቋም ሥራዎች ውስጥ እንዲካተቱም አመራሮቹን አሳስበዋል።

በተጨማሪ ተመድ በኢትዮጵያ ውስጥ የሚደረገውን የሰላም ጥረትም ይደግፋል ብለዋል።

#UnitedNations

@tikvahethiopia