TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.5K photos
1.43K videos
206 files
3.95K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#GERD 🇪🇹 #UNSC

ኢትዮጵያ ለተባበሩት መንግስታት ድርጅት የጸጥታው ምክር ቤት ደብዳቤ ፅፋለች።

ም/ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ለወቅቱ የምክር ቤቱ ፕሬዝዳንት በላኩት ደብዳቤ ኢትዮጵያ ፦

- በአፍሪካ ህብረት በሚመራው የሶስትዮሽ ድርድር ላይ ያላትን የፀና አቋም አስረግጣ ገልፃለች።

- ግብፅ እና ሱዳን በታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ሙሌትና አስተዳደርን በማስመልክት ወደሚደረገው የሶስትዮሽ ድርድር እንዲመለሱ፤ እንዲሁም በአፍሪካ ህብረት የሚመራውን የድርድር ሂደት እንዲያከብሩ ሊያስስቧቸው ይገባል ብላለች።

- በኢትዮጵያ በኩል ጥልቅ ፍላጎት ቢኖርም ፤ግብፅ እና ሱዳን ሁሉንም ሀገራት ተጠቃሚ ወደሚያደርገው መፍትሄ ለመምጣት በሚያስችል ቅን ልቦና እየተደራደሩ አይደለም ብላለች።

- ግብፅ እና ሱዳን ድርድሩን “በማኮላሸት” እና ጉዳዩን “ዓለም አቀፍ በማድረግ” በኢትዮጵያ ላይ ጫና ለማሳደርን መምረጣቸውን ገልፃለች።

- ሃገራቱ በአስገዳጅ ስምምነት ስም ኢ-ፍትሐዊ ሁኔታዎችን ለማስጠበቅ እና በግድቡ ውሃ እንዳትጠቀም ለማድረግ የሚያደርጉት ጥረት ተቀባይነት እንደሌለው ገልፃለች።

- የሶስቱ ሃገራት መሪዎች እ.ኤ.አ በ2015 በሱዳን ካርቱም ለፈረሙት የመርሆዎች ስምምነት ያላትን ቁርጠኝነትም ገልጻለች ግብጽ እና ሱዳን በስምምነቱ የገቡትን ቃል አለመጠበቃቸውን ጠቁማለች።

- ጫና ለማድረግ የሚደረጉ የትኛውም ዓይነት ሙከራዎች እና ድርድሩን ከህብረቱ ውጭ ለማድረግ የሚደረጉ ጥረቶች በሃገራቱ መካከል ያለውን መተማመን የበለጠ እንደሚጎዱ ገልፃለች። [Al AIN]

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBOT
#UNSC

የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የጸጥታው ምክር ቤት በኢትዮጵያ የትግራይ ክልል ሁኔታ ላይ እየመከረ ነው።

ይህ ስብሰባ ምክር ቤቱ በስምንት ወራት ውስጥ በኢትዮጵያ ጉዳይ #በግልጽ የመከረበት ነው።

ስብሰበውን #በቀጥታ በUN የYoutube ገፅ መከታተል ይቻላል።

@tikvahethiopia
#UNSC

ትላንት ምሽት በነበረው የፀጥታው ምክር ቤት ስብሰባ ላይ ሀገራት ምን አሉ ?

ሩሲያ ፦ በድጋሚ የኢትዮጵያ ጉዳይ የውስጥ ጉዳይ መሆኑን አፅንኦት ሰጥታ ገልፃለች፤ ነገር ግን ሰላም ለእርሻም ይሁን የተፈናቀሉ ዜጎችን ወደ ቦታቸውን ለመመለስ አስፈላጊ መሆኑን አስንታለች፤ ትግራይ ውስጥ ስላለው ሁኔታ ውስብስብ የሆነውን የወታደራዊ እና የፖለቲካ ሁኔታ ሂደት በቅርበት እንደምትከታተል ገልፃ፤ የኢትዮጵያ መንግስት ያወጀው የተናጠል ተኩስ አቁም ትክክለኛ እርምጃ ነው ብላለች።

ቻይና ፦ በድጋሚ ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ የኢትዮጵያን ሉዓላዊነት እና ባለቤትነት ሙሉ በሙሉ ማክበር እንዳለበት ገልፃለች፤ ትግራይ ውስጥ ሙሉ የተኩስ አቁም ስምምነት ይደረጋል ብላ ተስፋ እንደምታደርግ ገልፃ፤ በሁሉም ወገኖች በኩል ያለው ልዩነት በፖለቲካ ንግግር ሊፈታ ይገባል ብላለች።

ኬንያ በ #A3Plus1 ስም ፦ የእርዳታ ሰራተኞችን ጨምሮ ያልታጠቁ ሰዎችን ኢላማ ያደረጉ ጥቃቶችን አውግዘዋል፣ ወሲባዊ ጥቃት ስለደረሰባቸው ሴቶች እና ልጃገረዶች ሃዘናቸውን ገልፀዋል፣ ማንኛውም ኢትዮጵያዊ ያልሆነ ኃይል ከትግራይ እንዲወጣ ጠይቀዋል፤ መንግስት ያወጀውን የተናጠል የተኩስ አቁም ደግፈዋል፤ ለኢትዮጵያ የግዛት አንድነት እና ሉአላዊነት ያላቸውን ቁርጠኝነት አረጋግጠዋል፤ በዚህ ወሳኝ ወቅት ለሀገር ግንባታ፣ ለብልፅግና ፣ ለዘላቂ ሰላም ከኢትዮጵያ ጋር በአንድነት እንደሚቆሙ ገልፀዋል።

አሜሪካ ፦ የትግራይ ክልል ሰብዓዊ ሁኔታ እጅግ አስቸኳይ እና አሳሳቢ ነው ፤ ግጭቱ መቆም አለበት ፣ ያልተገደበ የሰብዓዊ ተደራሽነት ሊኖር ይገባል፣ ተጠናቂነትም መስፈን አለበት ብላለች።

ቀጣዩን ያንብቡ : telegra.ph/UN-Security-Council-07-03

@tikvahethiopia
#UNSC

ዛሬ የተመድ ፀጥታው ምክር ቤት በኢትዮጵያ ታላቁ የህዳሴ ግድብ ዙሪያ ይመክራል።

ስብሰባው ላይ ለመካፈል የኢትዮጵያ ዉኃ፣ መስኖ እና ኢነርጂ ሚንስትር ዶ/ር ኢ/ር ኢንጅነር ስለሺ በቀለ ወደ ኒውዮርክ ማቅናታቸውን አል አል ዐይን ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱን ዋቢ አድርጎ ዘግቧል።

ዶ/ር ኢ/ር ስለሺ የፀጥታው ምክር ቤት ኢትዮጵያ ፣ ግብፅ እና ሱዳን በገጠሙት የግድቡ ዉዝግብ ላይ ለመነጋገር በሚያደርገው ስብሰባ ላይ #ኢትዮጵያን ይወክላሉ፡፡

በስብሰባው ላይም የኢትዮጵያን አቋም ያንጸባርቃሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡

ኢትዮጵያን ከሚወክሉት ዶ/ር ኢ ር ስለሺ በቀለ በተጨማሪ በስብሰባዉ ላይ የግብፅና የሱዳን ዉጪ ጉዳይ ሚንስትሮች የሚገኙ ይሆናል፡፡

ከሶስቱ ሀገራት ሚንስትሮች በተጨማሪ ፦
- በአፍሪቃ ቀንድ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ልዩ መልዕክተኛ፣
- የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የአካባቢ ጥበቃ ኃላፊ
- የወቅቱ የአፍሪቃ ሕብረት ሊቀመንበር የኮንጎ ዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ዲፕሎማት ለተሰብሳቢዎች ማብራሪያ ይሰጣሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ አል ዓይን አስነብቧል።

@tikvahethiopia
#UNSC

የተመድ የጸጥታው ምክር ቤት የወርሃ መስከረም ሰብሳቢ አየርላንድ 🇮🇪 ሆና ተመረጠች፡፡

አየር ላንድ ሰብሳቢነቱን ከህንድ 🇮🇳 ነው የተረከበችው፡፡

የወርሃ ነሃሴ የምክር ቤቱ ሰብሳቢ የነበረችው ህንድ ም/ቤቱ በትግራይ ጉዳይ በተወያየበት ጊዜ በኢትዮጵያ የውስጥ ጉዳይ ጣልቃ ለመግባት የሚደረገውን በመቃወም ኢትዮጵያን መደገፏ የሚታወስ ነው፡፡

ወቅታዊ የኢትዮጵያን ሁኔታዎች በአሳሳቢነት ስትገልጽ የሰነበተችው አየርላንድ በበኩሏ ከአሁን ቀደም ምክር ቤቱ በኢትዮጵያ ጉዳይ ላይ አስቸኳይ ስብሰባን እንዲያደርግ ጥሪ ማቅረቧ የሚታወስ ነው፡፡

መረጃው የአል ዓይን ነው።

@tikvahethiopia
#UNSC

ዛሬ ተመድ ፥ "Peace and Security in Africa" በሚል የውይይት አጀንዳ ስር በኢትዮጵያ የትግራይ ክልል ውስጥ ስላለው ሁኔታ ለውይይት እንደሚቀመጥ ቢቢሲ ዘግቧል።

በዚህ ስብሰባ የኢትዮጵያ መንግሥት ተወካዮች ይገኛሉ ተብሎ ይጠበቃል። ክፍት ስብሰባም እንደሚሆን ተነግሯል።

ውይይቱ እንዲካሄድ የጠየቁት አሜሪካ፣ ዩኬ፣ ኖርዌይ፣ ኢስቶኒያ፣ ፈረንሳይ እና አየርላንድ ናቸው።

በዛሬው ስብሰባ የተመድ ዋና ጸሐፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ ንግግር ያደርጋሉ ተብሎ ይጠበቃል። ንግግራቸው 7ቱ የድርጅታቸው ሠራተኞች ከኢትዮጵያ መውጣታቸውን በተመለከተ እና በሰብአዊ ቀውስ ጉዳይ ነው ተብሎ የሚጠበቀው።

ተመድ የትግራይ ክልል ጦርነት ከጀመረ ጊዜ አንስቶ በኢትዮጵያ ጉዳይ ስብሰባ ሲቀመጥ ይኸኛው ለ10 ጊዜው ነው።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
የተመድ የፀጥታው ም/ቤት በኢትዮጵያ ጉዳይ ምን አለ ? የተመድ የፀጥታው ም/ቤት በኢትዮጵያ ጉዳይ ስብሰባ ሲቀመጥ ሁለት (2) ወር ባልሞላ ጊዜ ውስጥ ይኸኛው ለአራተኛ (4) ጊዜ (በዝግና በክፍት) ነው። ይኸኛው ስብሰባው ለምን ተጠራ ? - ኢትዮጵያ 7 የተመድ ሰራተኞችን ከሀገር በማስወጣቷ። - የሰሜን ኢትዮጵያ ሰብዓዊ ሁኔታ ላይ ለመወያየት። ስብሰባው እንዲካሄድ የጠየቁት፦ አሜሪካ ፣ ዩኬ (UK)፣…
#UNSC

ትላንት በተመድ የፀጥታው ምክር ቤት ኢትዮጵያ በተመድ ሰራተኞች ላይ ስለወሰደውች እርምጃ ማብራሪያ የሰጡት አምባሳደር ታዬ አጽቀስላሴ ፥ በዓለም አቀፍ ህግ ሀገራት መብቶቻቸውን መጠቀም ይችላሉ፤ የኢትዮጵያ መንግስት ለውሳኔውም ምንም አይነት ማብራሪያ የማቅረብ ግዴታ የለበትም ብለዋል።

ሀገራት የተለያዩ የተመድ ሰራተኞችን እና የሀገራት ዲፕሎማቶችን ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ከሀገራቸው ማስወጣታቸውን እናውቃለን፤ ሆኖም ግን ተመድ በእነሱ ላይ ስብሰባ አድርጎ ያውቅ ይሆን ? ሲሉ ጠይቀዋል።

የኢትዮጵያ መንግስት እርምጃውን ስለ መውሰዱ ለማንኛውም አካል ማብራሪያ የመስጠት ግዴታ የለበትም ሲሉ ተናግረዋል።

የተመድ ሰራተኞች የገለልተኝነት መርሆችን በጣሰ መልኩ ለህወሓት የሚወግኑ መሆናቸውን ገልፀዋል። 

የተመድ ሰራተኞች ያልሞቱ ሰዎችን በረሃብ ሞተዋል በሚል የሀሰት መረጃዎችን ማሰራጨት፤ የመገናኛ መሣሪያዎችን ለህወሓት ወገን ማድረስ፤ ህወሃት መቐለ ሲገባ ከቡድኑ ጋር ደስታቸውን መግለጽ ፤ ከሳዑዲ የትግራይ ተወላጆችን ወደ ሶስተኛ ሀገር በማምጣት ለቡድኑ እንዲዋጉ ስልጠና የሚያገኙበትን ሁኔታ ማመቻቸትና ህወሓትን የሚደግፉ ጹሑፎችን ማዘገጀት ላይ ተጠምደው ነበር ብለዋል።

ማን ይገባል፤ ማን ይወጣል ፣ ማን ይቆያል የሚለውን የሀገር መሰረታዊ ሉዓላዊ መብት ነው ብለዋል።

የመረጃ ግብአ አልዓይን ፣ ቪኦኤ፣ የUN ገፅ።

@tikvahethiopia
#UNSC : ደቡብ ሱዳን " ጎክማቻር " የሚባለው አካባቢ ከተመደበው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት (UN) የአብዬ ጊዜያዊ የፀጥታ ጥበቃ ኃይል ጋር በተያያዘ በከፍተኛ ደረጃ እያሽቆለቆለ ስላለው ሁኔታ ለተመድ የፀጥታው ምክር ቤት ገልፃ ተደርጓል።

ገለፃውን ያደረጉት በድርጅቱ የፖለቲካና የሰላም ግንባታ ክፍል የአፍሪካ ጉዳይ ምክትል ዋና ፃሃፊው ናቸው።

እኤአ መስከረም 14 ቀን የአንድ ኢትዮጵያዊ 🇪🇹 ሰላም አስከባሪ ህይወት የጠፋበትን ጨምሮ በ " ጎክማቻር " በቅርብ ጊዜያት በሰላም አስከባሪዎች ላይ የተደቀኑት አደጋዎች በጥልቅ የሚያሰጓቸው ሆነው እንዳገኟቸው የፀጥታ ምክር ቤቱ አባላት ተናግረዋል።

የደቡብ ሱዳን መንግስት የሰላም አስከባሪውን ኃይል የተልኮ ስልጣን ያለእንቅፋት እንዲያከናውን የማስቻል ኃላፊነቱን እንዲወጣ የሚሉ እና ሌሎች ተያያዥ ጥያቄዎችን የምክር ቤት አባላት ማቅረባቸውን ቪኦኤ ዘግቧል።

@tikvahethiopia
#UNSC : ትላንት ለሊት የተባበሩት መንግሥታት የፀጥታው ምክር ቤት በኢትዮጵያ ጉዳይ ስብሰባ ተቀምጦ ነበር።

በዚህ ስብሰባድ በሰሜን ኢትዮጵያ እየተካሄደ ያለው ጦርነት እየተባባሰ መሄዱ በጽኑ እንዳሳሰበውና በአስቸኳይ እንዲቆም ጥሪ አቀረበ።

ከስብሰባው በኋላ በ15ቱም አባላት #ተቀባይነት_አግኝቶ በወጣ መግለጫ ሁሉም በግጭቱ ተሳታፊ የሆኑ ወገኖች ጦርነቱን በማቆም "ዘላቂ ሰላም የሚያመጣ የተኩስ አቁም ለማድረግ" ውይይት እንዲጀምሩ ጥሪ አቀርቧል።

መግለጫው ለተፈጠረው ቀውስ መፍትሔ ለማግኘት እንዲቻል እና ሰላምና መረጋጋት ለማስፈን ሁሉን አቀፍ ብሔራዊ ውይይት ለማካሄድ አመቺ ሁኔታ እንዲፈጠር ጠይቋል።

የምክር ቤቱ አባላት ችግሩን ለመፍታት #የአፍሪካ_ሕብረትን በመሰሉ አካባቢያዊ ድርጅቶች በኩል የሚደረገውን ጥረት እንደሚደግፉና የሕብረቱ ልዩ መልዕክተኛ ኦሉሴጉን ኦባሳንጆ ተኩስ እንዲቆምና ጦርነቱ ሰለማዊ መቋጫ እንዲያገኝ የሚያደርጉትን ጥረት እንደሚደግፍ ገልጿል።

በተጨማሪ ሁሉም ወገኖች "ከአደገኛ ጥላቻ ከሚያስፋፉ፣ ግጭትንና መከፋፈልን ከሚያነሳሱ ንግግሮች" እንዲቆጠቡ አሳስቧል።

* ሙሉ መግለጫው ከላይ ተያይዟል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#AmbassadorTayeAtskeSelassie ትላንት በነበረው የተመድ ፀጥታው ምክር ቤት ስበስባ ላይ ኢትዮጵያን በመወከል አምባሳደር ታዬ አጽቀስላሴ ንግግር አድርገው ነበር። አምባሳደር ታዬ በህወሓት የተፈጸመው የክህደት ስራ በእጅጉ የሚያሳዝንና ኢትዮጵያ በዚህ ወንጀለኛ ቡድን ያሳለፈችውን ጊዜ ለመርሳት የአንድ ትውልድ ጊዜ የሚፈጅ እንደሆነ ተናግረዋል፡፡ ቡድኑ ያን ሁሉ ደም መፋሰስ እንዲፈጠር ባያደርግ…
#UNSC

በትላንትናው የፀጥታው ምክር ቤት ሰብሰባ ላይ የሀገራት ተወካዮች ምን አሉ ?

#ኢትዮጵያ

የኢትዮጵያ መንግስት ባለፈው አንድ (1) ዓመት ከህወሓት የተቃጣበትን ወታደራዊ አደጋ መመከቱን አምባሳደር ታዬ አጽቀስላሴ ተናግረዋል።

መንግሥት ምግብን ጨምሮ ሌሎች አስፈላጊ ቁሳቁሶችን በትግራይ ክልል የሰብአዊ እርዳታ ለሚፈልጉ ሰዎች ከUN ጋር በመተባበር ሲያቀርብ እንደነበር ተናግረዋል።

ለሰብአዊ ድጋፍ እንዲያመች በሚል የተናጠል የተኩስ አቁም ማድረጉን ተናግረዋል። ነገር ግን የተደረገው ጥረት ሁሉ በወንጀለኛው ቡድን ምክንያት ከንቱ ሆኖ ቀርቷል ብለዋል።

"በዚህ የወንጀል ቡድን ምክንያት የትግራይ ክልል ሕዝብ ያስፈልገው የነበረውን አስቸኳይ የሰብአዊ እርዳታ እያገኘ አይደለም" ሲሉ ለምክር ቤቱ አስረድተዋል።

በአማራ ክልል እና በአፋር ክልል በተለያዩ ከተሞች የሚኖሩ ሰዎችም በዚህ ቡድን በየበራቸው ላይ መገደላቸውን ገልጸዋል።

#ቻይና

ቻይናን የወከሉት ዣንግ ጁን ኢትዮጵያ ውስጥ እየተከሰተ ያለው ሁኔታ የፖለቲካ፣ የታሪክ፣ የብሔርና ሌሎች ምክንያቶች ጥምር ውጤት መሆኑን ጠቁመው መፍትሔ የሚገኘው በአገር ውስጥ ብቻ መሆኑን ተናግረዋል።

የአፍሪካን ችግሮች ለመፍታት አፍሪካዊ መፍትሄዎች ለማግኘት ለሚደረገው ጥረት በድጋሚ ድጋፍ እንሰጣለን ብለዋል።

በተለይ አሜሪካና የተለያዩ አገራት የሚያደርጉትን ማዕቀብ በተመለከተም አስተያየታቸውን የሰጡት ተወካዩ፣ በንግድ ላይ ገደብ ማድረግ እና እርዳታን ማቋረጥ በፖለቲካው መፍትሄ ላይ ጣልቃ መግባት እንደሆነ አስረድተዋል።

ለፀጥታው ምክር ቤት አባላት ምክራቸውን ያስተላለፉት የቻይናው ተወካይ አባል አገራቱ የአገሪቱን ሉዓላዊነትና አመራር በማክበር ኢትዮጵያ የሰብአዊ አቅሟን እንድታሻሽል እና የሚሰጠው እርዳታም ሊጨምር ይገባል ብሏል።

#አሜሪካ

አምባሳደር ሊንዳ ቶማስ ግሪንፊልድ 1 አመት ባስቆጠረው ግጭት ውስጥ ለተፈጠሩ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች ፥ "ሁሉም ኃሃይሎች ጥፋተኞች ናቸው፤ ጥፋት የለሌለበት የለም" ሲሉ ተናግረዋል።

አምባሳደር ሊንዳ የህወሓት ታጣቂዎች በአማራ ክልል እና አፋር ክልል እንዲወጡ እና ጥቃታቸውን ወደ አዲስ አበባ እንዳያሰፉ አሳስበዋል። የኢትዮጵያ መንግሥት ዓለም አቀፍ የጦርነት ሕጎችን እንዲሁም የሰብአዊ መብት ሕጎችን እንዲያከብር ጠይቀዋል።

ሰላምን ሊያመጡ የሚችሉት ኢትዮጵያዊያን ብቻ ናቸው ሲሉም አምባሳደሯ ተናግረዋል።

ያንብቡ : telegra.ph/UNSC-11-09
#UNSC

ከዚህ በፊት ስለኢትዮጵያ ጉዳይ ከአስር ጊዜ በላይ ስበስባ የተቀመጠው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የፀጥታው ምክር ቤት ዛሬ ሰኞ በኢትዮጵያ ጉዳይ ለመነጋገር ስብሰባ እንደሚቀመጥ ታውቋል።

ምክር ቤቱ ዛሬ በ “any other business” ስር በኢትዮጵያ ስላለው ሁኔታ የሚወያይ ሲሆን ስብሰባው እንዲካሄድ የጠየቁት ፦
🇪🇪 ኢስቶኒያ
🇫🇷 ፈረንሳይ
🇮🇪 አየርላንድ
🇳🇴 ኖርዌይ
🇬🇧 ዩናይትድ ኪንግደም
🇺🇸 አሜሪካ ናቸው።

የተመድ የሰብአዊ ጉዳዮች የአስቸኳይ ጊዜ ማስተባበሪያ ጽህፈት ቤት ኃላፊ ማርቲን ግሪፊትስ በኢትዮጵያ ያለውን የሰብአዊ እርዳታ ጉዳይን በተመለከተ ለፀጥታው ም/ ቤት አባላት አጭር ማብራሪያ ይሰጣሉ ተብሏል።

በትግራይ ክልል ውስጥ ጦርነት ከተቀሰቀሰ ጊዜ አንስቶ የተመድ ፀጥታው ምክር ቤት ስለኢትዮጵያ ጉዳይ ከአስር ጊዜ በላይ ስብሰባ የተቀመጠ ሲሆን የዛሬው ስብሰባ ባለፈው ሳምንት የተመድ የሰብአዊ መብቶች ም/ቤት ልዩ ስብሰባ አካሂዶ ከጦርነቱ ጋር በተያያዘ የተከሰቱ የመብት ጥሰቶችን የሚመረምር ዓለም አቀፍ የባለሙያዎች አካል እንዲቋቋም በድምጽ ብልጫ ከወሰነ በኋላ ነው።

https://www.securitycouncilreport.org/whatsinblue/2021/12/ethiopia-meeting-under-any-other-business.php

@tikvahethiopia
#UNSC

ዛሬ የተመድ የፀጥታው ምክር ቤት #በአፍጋኒስታን ጉዳይ በአሜሪካ የቀረበ የውሳኔ ሀሳብ በሙሉ ድምፅ አፀደቀ።

የተመድ የፀጥታው ምክር ቤት ዛሬ ረቡዕ ባካሄደው ስብሰባ ለአፍጋኒስታን ሰብአዊ ርዳታ የሚያመቻች በአሜሪካ የቀረበ የውሳኔ ሃሳብ በመሉ ድምፅ አጽድቋል።

የውሳኔ ሀሳቡ፥ "የገንዘብ ክፍያ፣ ሌሎች የፋይናንስ ሀብቶች ወይም የኢኮኖሚ ሀብቶች እና እንዲህ ዓይነቱን እርዳታ በወቅቱ ለማድረስ ወይም መሰል ተግባራትን ለመደገፍ አስፈላጊ የሆኑ እቃዎችና አገልግሎቶች አቅርቦት ይፈቀዳል " ነው የሚለው።

እንዲህ ያለው እርዳታ " አፍጋኒስታን ውስጥ ያሉ መሰረታዊ የሰው ልጆች ፍላጎቶችን " የሚደግፍ እንጂ ከታሊባን ጋር በተገናኙ አካላት ላይ የተጣለውን ማዕቀብ " መጣስ አይደለም " ሲልም ያክላል።

አፍጋኒስታን በከፋ የኢኮኖሚ ውድቀት አፋፍ ላይ ትገኛለች።

@tikvahethiopia
#UNSC #ETHIOPIA

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የፀጥታው ምክር ቤት ዛሬ በኢትዮጵያ ጉዳይ ዛሬ ስብሰባ ይቀመጣል።

ስብሰባው በኢትዮጵያ ስላለው የሰብዓዊ እርዳታ ሁኔታ ላይ ያተኮረ ነው ተብሏል።

ስብሰባው እንደደረግ የጠየቁት ዩናይትድ ኪንግደም (ዩኬ) ፣ አሜሪካ፣ አየርላንድ ፣ ፈረንሳይ እና አልቤኒያ ናቸው።

የፀጥታው ምክር ቤት በትግራይ ክልል ጦርነት ከተነሳ ጊዜ አንስቶ ከ12 ጊዜ በላይ ስብሰባ ተቀምጧል።

@tikvahethiopia
#UNSC

ትላንትና ሌሊት በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የፀጥታው ምክር ቤት ሩሲያ በዩክሬን ላይ " ወረራ " ፈፅማለች በሚል ለማውገዝ በምዕራባውያን የሚመራ የውሳኔ ሃሳብ ቢቀርብም ሩስያ ድምፅን በድምፅ የመሻር መብቷን [ veto power ] በመጠቀም #ውድቅ አድርጋዋለች።

ቻይናም በውሳኔ ሀሳቡ ላይ ድምፅ ከመስጠት ታቅባለች።

የቀረበውን የውሳኔ ሀሳብ እነማን ደገፉት ? ማን ተቃወመ ? እነማን ድምፃቸው አቀቡ ?

#የደገፉ_ሀገራት

🇺🇸 አሜሪካ
🇬🇧 ዩናይትድ ኪንግደም
🇫🇷 ፈረንሳይ
🇳🇴 ኖርዌይ
🇮🇪 አይርላድ
🇦🇱 አልባኒያ
🇬🇦 ጋቦን
🇲🇽 ሜክስኮ
🇧🇷 ብራዚል
🇬🇭 ጋና
🇰🇪 ኬንያ

#የተቃወሙ

🇷🇺 ሩስያ

#ድምፀ_ተአቅቦ_ያደረጉ

🇨🇳 ቻይና
🇮🇳 ሕንድ
🇦🇪 ዩናይትድ አረብ ኤምሬትስ (UAE)

@tikvahethiopia
#UNSC

አሜሪካ፣ ዩናይትድ ኪንግደም፣ ፈረንሳይ፣ አይርላንድ፣ ኖርዌይ እና አልባኒያ በኢትዮጵያ ጉዳይ የተመድ የፀጥታው ምክር ቤት ዛሬ ስብሰባ እንዲያካሂድ ጠይቀው የነበር ቢሆንም በም/ቤቱ ባለው አመግባባት ሳቢያ መካሄዱ እንደሚዘገይ ተሰምቷል።

ከዲፕሎማቶች ሰማሁኝ ብላ የአልጀዚራዋ ጋዜጠኛ አማንዳ ፕራይስ እንደገለፀችው ፤ የተመድ የፀጥታው ምክር ቤት በኢትዮጵያ ጉዳይ ለመነጋገር ተጠይቆ የነበረው ለዛሬ ሀሙስ ቢሆንም እስከሚቀጥለው ሳምንት ድረስ ሊዘገይ ይችላል።

ይህ የሆነውም ስብሰባው በዝግ ወይስ ክፍት ሆኖ በግልፅ ይካሄድ በሚለው ላይ በምክር ቤቱ አባላት ውስጥ ባለው አለመግባባት መሆኑ ተጠቁሟል።

በሌላ በኩል ፤ ተመድ ያቋቋመው የአለም አቀፍ የሰብአዊ መብቶች ኤክስፐርቶች ኮሚሽን በኢትዮጵያ መንግስት እና በህወሓት መካከል ዳግም ያገረሸው ግጭት እንደሚያሳስበው ባወጣው  መግለጫ ገልጿል።

ኮሚሽኑ የኤርትራ ወታደሮችም በጦርነት ውስጥ እየተሳተፉ ይገኛሉ ያለ ሲሆን ይህም ግጭቱ ወደ ሌሎች ሀገራት እንዳይዛመት ስጋት አለኝ ብሏል።

ኮሚሽኑ ሁሉም ወገኖች በአስቸኳይ ግጭት እንዲያቆሙና ወደ ውይይት ሂደቱ እንዲመለሱ በድጋሚ ጥሪዬን አቅርባለሁ ብሏል።

በቀጠናው ሰላምና ፀጥታ ላይ ካለው ስጋት አንፃርም የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የፀጥታው ምክር ቤት በአስቸኳይ የኢትዮጵያን ሁኔታ መመልከቱን ኮሚሽኑ እንደሚቀበለው በመግለጫው አሳውቋል።

ኮሚሽኑ ፤ ምክር ቤቱ የሲቪል ዜጎችን ደህንነት ለማረጋገጥ እና ቀጣናውን የበለጠ ሊያናጉ የሚችሉ ግጭቶችን ለመከላከል በወጣው ቻርተር መሰረት እርምጃ እንዲወስድ ጠይቋል።

የጉዳዩን አሳሳቢነት ከግምት ውስጥ በማስገባትም ምክር ቤቱ የኢትዮጵያ እና የአፍሪካ ቀንድ ሁኔታዎችን አጀንዳው አድርጎ እንዲቀጥልም ኮሚሽኑ አሳስቧል።

@tikvahethiopia
#UNSC

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የፀጥታው ምክር ቤት " የአፍሪካ ሰላምና ጸጥታ " በሚል ርዕስ በኢትዮጵያ ወቅታዊ ሁኔታ ላይ ትላንት መክሮ ነበር።

ስብሰባው እንዲካሄድ የጠየቁት A3 (ኬንያ፣ ጋቦንና ጋና) የነበሩ ሲሆን በዝግ ነው የተካሄደው።

የተመድ የፀጥታው ምክር ቤት ከስብሰባው በኃላ አንድ የጋራ መግለጫ ለማውጣት ሳይስማማ ቀርቷል።

ምክር ቤቱ በኢትዮጵያ ጉዳይ ላይ አንድ የጋራ መግለጫ ማውጣት ሳይችል የቀረው ቻይና እና ሩስያ ባለመደገፋቸው ምክንያት መሆኑ ተነግሯል።

@tikvahethiopia