TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#Update #TPLF
" ' ስልጣን ልቀቅ አልለቅም ' በሚሉ የሁለት ቡድን ፍላጎት የህዝባችን ስቃይ እንዲራዘም አንሻም " - የህወሓት ማእከላዊ የቁጥጥር ኮሚሽን አባላት
የህወሓት ማእከላዊ የቁጥጥር ኮሚሽን አባላት ዛሬ መግለጫ ሰጥተው ነበር።
የኮሚሽኑ አባላት በጋራ በሰጡት መግለጫ " ትናንት ህዝባችን ላይ ያደረስነው ጉዳት በመረዳት ዛሬ መፀፀትና ለደህንነቱ መትጋት ይገባናል " ብሏል።
" በኛ ጦስ ምክንያት በህዝባችን ላይ ሊከተል የሚችለው መከራ ከወዲሁ በመገንዘብ ሊካሄድ ከታሰበ ጉባኤ ራሳችንን አግልለናል " ሲሉ አሳውቀዋል።
" በህወሓት አቋም የሚባል ጠፍቶ ቦታውን ኔትወርክና መቦዳደን ተክቶታል " ሲሉም ገልጸዋል።
" ግልፅነት ፣ አሳታፊ አሰራር እና ዴሞክራሲ ጠፍቶ ስልጣንን አለአግባብ መጠቀም አይለዋል " ያሉት የኮሚሽን አባላቱ ፥ " 9 አባላት ያሉት የጉባኤ አዘጋጅ ኮሚቴ ለይስሙላ ቢቋቋምም ይህንን ወደ ጎን በመተው ስራውን የሚያከናውነው ሃይል የበላይነት አለኝ የሚል አካል ነው " በማለት ድርጊቱ አውግዘዋል።
" ' ስልጣን ልቀቅ አልለቅም ' በሚሉ የሁለት ቡድን ፍላጎት የህዝባችን ስቃይ እንዲራዘም አንሻም ፤ ከመተማመን መግባባትና ዴሞክራሲያዊ መንገድ ውጪ የሚካሄድ ህዝባዊ ጠቀሜታ ስለሌለው የዚሁ ተግባር አካልና ተባባሪ መሆን አንፈልግም " ብለዋል።
የኮሚሽኑ አባላት ፥ " አካሄዳችሁ አስተካክሉ ላለ አካልና ግለሰብ የሌለ ስም እየሰጡ ማጥላላት የትም አያደርስም " ያሉ ሲሆን " ከኔትወርክ እና መጠላለፍ ያልፀዳ ጉባኤ ማካሄድ ህዝብን ይጎዳል እኛም የዘህ ጉዳት ተባባሪ ላለመሆን ይካሄዳል ከሚባለው ጉባኤ ራሳችን አግልለናል " ሲሉ አሳውቀዋል።
#TikvahEthiopiaFamilyMK
@tikvahethiopia

🙏784❤173👏105🕊103😢38😡38🤔31🥰30😱30😭3
መቐለ እና የወንጀል የተግባር መስፋፋት !
" ፀጥታ እና ሰላም ከሌለ ሁሉም የለም " - የመቐለ ከንቲባ
በመቐለ ከተማ በያዝነው ዓመት ከአምናው በ1,841 በመቶኛ ሲሰላ 68 ፐርሰንት / የሚበልጥ የወንጀል ተግባር መፈፀሙ የከተማዋ የሰላምና የፀጥታ ዘርፍ አስታውቋል።
በ2015 ዓ/ም ላይ የተፈፀሙት የወንጀል ተግባራት 2,895 ሲሆኑ በያዝነው 2016 ዓ/ም 4,735 የወንጀል ተግባራት ተፈፅሟል።
ይህ ካለፈው ዓመት ጋር ሲነፃፀር ዘንድሮ የ1,841 የወንጀል ተግባራት መጨመር አሳይቷል።
" ፀጥታ እና ሰላም ከሌለ ሁሉም የለም " ያሉት የከተማዋ ከንቲባ ይትባረኽ ኣምሃ " ለፀጥታና ሰላም መጠበቅና የወንጀል ተግባር ለመቆጣጠር የሚያግዙ የድህንነት ካሜራዎች በተለያዩ የከተማ አከባቢዎች በመገጠም ላይ ናቸው " ብለዋል።
የትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር በህገ-ወጦች ላይ እርምጃ መውሰድ መጀመሩን አስመልክቶ ያወጣውን መግለጫ ተከትሎ " በከተማዋ የሚካሄደው ህግ የማስከበር ተግባር ተጠናክሮ ይቀጥላል " ያሉት ከንቲባው እስካሁን በምን የወንጀል ተግባር የተሳተፉ ፣ ምን ያህል ፣ እነማን ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር እንደዋሉ በይፋ አልገለፁም።
መቐለን ጨምሮ ሌሎችም ከተሞች ከደም አፋሳሹ ጦርነቱ በፊት በዚህ ልክ ወንጀል ተስፋፍቶባቸው አያውቅም።
በተለይም መቐለ ከተማ በደህንነት እና በጸጥታ ረገድ አንጻር ቀንም ማታም መንቀሳቀስ የሚቻልባት ነበረች። ወንጀልም በዚህ ልክ የተስፋፋባት ከተማ አልነበረችም።

😭318❤98😢43🕊43👏41😱26😡17🥰7🙏7
TIKVAH-ETHIOPIA
#Tigray #TPLF " እኔ ሳላውቀው ያለፈው ሰኔ 30 ቀን 2016 ዓ/ም ጉባኤ ለማካሄድ በድብቅ ሲሰራ ነበር። ይህ እንዲሆን ለምን አስፈለገ ? " - አቶ ጌታቸው ረዳ የትግራይ ክልል ጊዚያዊ አስተዳደር እና የህወሓት ምክትል ሊቀመንበር ጌታቸው ረዳ በወቅታዊ ጉዳዮች አስመልክተው ለድምፂ ወያነ ቴሌቪዥን ቃለመጠይቅ ሰጥተው ነበር። አቶ ጌታቸው ረዳ ምን አሉ ? - የፕሪቶሪያው የሰላም ስምምነት…
#Tigray : " ... ከጦርነቱ በኋላ የተቋቋመው መንግስት ስራውን ለመስራት አቅም ያጣበት ወቅት ላይ እንገኛለን " - አቶ ጌታቸው ረዳ
ሀምሌ 25 እና 26/2016 ዓ.ም " የትግራይ ፓለቲካዊ አስተዳደር " በሚል ርእሰ አንድ መድረክ መቐለ ውስጥ ተካሂዶ ነበር።
የክልሉ ፕሬዜዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ ተገኝተውም ንግግር አድርገው ነበር።
ምን አሉ ?
- በትግራይ የሃሳብ ጠቅላይነት ሊኖር አይችልም። ልዩነታችን በሰለጠነ መንገድ ከመፍታት ውጪ ሌላ አማራጭ የለም።
- የትግራይ ህዝብ ለዘመናት የቆዩ የዓለም ስልጣኔዎች ባለቤት የነበረ ቢሆንም እኛ ሳንሰራው በቀረ ወይንም ባለንበት አከባቢ አቀማመጥ ትውልዶች ወደ ጦርነት እየገቡ ለቀውስ እየተጋለጡ መጥቷል።
- እጅግ አሰቃቂ እና ደም አፋሳሽ በነበረው ጦርነት ጥያቄ ውስጥ የገባው የህዝቡ ህልውናውን በማረጋገጥ አንፃራዊ ሰላም ቢያገኝም ከጦርነቱ በኋላ የተቋቋመው መንግስት ስራውን ለመስራት አቅም ያጣበት ወቅት ላይ እንገኛለን።
- ፓለቲካዊ ልዩነታችን በሰለጠነ መንገድ በመፍታት በጦርነቱ ክፉኛ የተጎዳው ህዝባችን ሁሉንም አቅሞቻችን አሟጠን በመጠቀም መምራት ይጠበቅብናል።

❤393🕊70🤔27😡25😭23😱15😢12🙏12🥰9
የፅህፈት ቤት ኃላፊው ከግድያ ለጥቂት አመለጡ።
በትግራይ ማእከላዊ ዞን የአክሱም ከተማ አስተዳደር ፅህፈት ቤት ኃላፊ ከተቃጣባቸው የግድያ ሙከራ ለጥቂት ማማለጣቸው ተሰምቷል።
በኃላፊው ላይ የግድያ ሙከራ የተፈፀመው ሀምሌ 28/2016 ዓ.ም ከምሽቱ 2:00 ሰዓት ነው ተብሏል።
ኃላፊው ስራ ላይ አምሽተው ወደ ቤታቸው ሲገቡ ማንነታቸው ያልታወቁ ግለሰቦች ከተኮሱባቸው ሁለት ጥይቶች ያለ ጉዳት ተርፈዋል።
የአክሱም ከተማ ፓሊስ የግድያ ሙከራ ተግባሩን የፈፀሙ ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ለማዋል በጥረት ላይ እንደሚገኝ ገልፆ ህዝቡ የተለመደ ትብብሩ እንዲያደርግለት ጠይቋል።
የቱሪዝም መናገሻዋ የአክሱም ከተማ ከአስከፊውና ደም አፈሳሹ የትግራይ ጦርነት በኃላ በተጀመረው የአውሮፕላን በረራ አገልግሎት የአገር ውስጥና የውጭ ቱሪስቶች መቀበል ጀምራለች።
ስለሆነም ይህንን መሰል የፀጥታ ስጋቶች የቱሪስት ፍሰቱ ላይ አሉታዊ ተፅእኖ እንዳለው በመገንዘብ የፀጥታ መዋቅሩ የተቀናጀና የተናበበ ስራ መስራት እንዳለበት በርካታ የማህበራዊ የትስስር ገፅ ተጠቃሚዎች አስተያየት በመስጠት ላይ ይገኛሉ።

😱170❤87🙏85😭31🕊29😢9😡7🤔6
#ትግራይ
" በሰው ህይወት ላይ የደረሰ ጉዳት የለም " - ፅ/ቤቱ
በትግራይ ማእከላዊ ዞን ዓድዋ ወረዳ የመሬት መደርመስ አደጋ ተከስቷል።
የመሬት መደርመስ አደጋው በሰው ህይወት ያደረሰው ጉዳት ባይኖርም የእህል አዝርእት ሙሉ በሙሉ አውድሟል።
የመሬት የመደርመስ አደጋ ያጋጠመው ሀምሌ 29/2016 ዓ.ም በዓድዋ ወረዳ በታሪካዊትዋ የይሓ ቀበሌ ገበሬ ማህበር ነው።
የወረዳው የቁጠባ ዘርፍ ፅ/ ቤት ፤ " በአደጋው የ21 አርሶ አደሮች የተዘራ እህል ሙሉ በሙ ወድሟል " ብሏል።
' ደምባፍሮም ' በተባለች መንደር የተዘራው ስንዴ ሙሉ በሙሉ መውደሙ ተመላክቷል።
" ከአሁን በፊት በትግራይ ያልተለመደ የመሬት የመደርመስ አደጋ አሁን አሁን መታየት ጀምሯል " ያለው ፅ/ቤቱ " አርሶ አደሩ የክረምቱን ሀያልነት ከግምት ያስገባ ሁሉን አቀፍ ጥንቃቄ እንዲያደርግ " ሲል አሳስቧል።
ዘንድሮ በትግራይ ክልል ያለው ኃይለኛ ክረምት በንብረትና በእንስሳት አደጋ በማደረስ ላይ ይገኛል።
ባለፈው ሳምንት በክልሉ የራያ ጨርጨር ወረዳ ዝናብ ያስከተለው ኃይለኛ ጎርፍ በ106 የቤት እንስሳትና በ11 ሄክታር የእርሻ መሬት ከፍተኛ ጉዳት አድርሷል።
በጎርፉ 91 እንስሳት ሲወሰዱ ፣ 15 ቱ የአካል ጉዳት ደርሷቸዋል። በ11 ሄክታር የተዘራ እህል ከጥቅም ውጭ ሆኗል።

😢731🙏140❤122😭94🕊42😱20👏17😡16🥰11🤔6
" በተሰማራሁበት የዘመናዊ እርሻ ፣ የላሞች እርባታ የወተትና የወተት ተዋፅኦ ስራ ለ1,100 ወገኖች ጊዚያዊና ቀዋሚ የስራ እድል ፈጥሪያለሁ " - ባለሃብቱ
እያንዳንዳቸው በቀን ከ40 -60 ሊትር ወተት የመስጠት አቅም ያላቸው 165 የሆላንድና የዴንማርክ ላሞች በኢትዮጵያ አየር መንገድ ካርጎ ተጭነው ትግራይ ክልል መቐለ ከተማ ገብተዋል።
ራያ ዓዘቦ አካባቢ በሆቴልና በእርሻ እንቨስትመንት የተሰማሩት ባለሃብቱ ሃለቃ ሞጎስ ንጉሰ ፤ 600 ላሞች ገዝተው በዙሮች ወደ አገር ውስጥ እያስገቡ መሆኑ ገልጸዋል።
" ላሞቹ ብዙ ሊትር ወተት የመስጠት የተሻለ ዝርያ ያላቸው ናቸው " ያሉ ሲሆን " በቀጣዮቹ የግንቦትና የሰኔ ወራት 435 ተጨማሪ የወተት ላሞች ይገባሉ " ብለዋል።
ባለሃብቱ 600ዎቹ ላሞች ተጠቃልለው ወደ አገር ሲገቡ በቀን ከ24 - 30 ሺህ ሊትር ወተት የመስጠት አቅም እንዳላቸው ገልጸዋል።
ባለሃብቱ በተሰማሩበት የዘመናዊ እርሻ ፣ የላሞች እርባታ የወተትና የወተት ተዋፅኦ ስራ ለ1,100 ወገኖች ጊዚያዊና ቀዋሚ የስራ እድል መፍጠራቸው ጠቅሰዋል።
አሁን ላይ የጀመሩት የፋብሪካ የማስፋፍያ ስራ ሲጠናቀቅ ተጨማሪ 500 ወገኖች ተጠቃሚ ይሆናሉ ብለዋል።
በተሰማሩበት ዘርፍ ኢንቨስት ለማድረግ ካቀዱት 7 ቢሊዮን ብር 5 ቢሊዮኑ ስራ ላይ በማዋል ተግባራዊ እንቅስቃሴ በማድረግ ላይ እንደሚገኙ ከክልሉ የኢንቨስትመንት ኮሚሽን የተገኘው መረጃ ያሳያል።
ባለሃብቱ ከአውዳሚው ጦርነት በፊት ከሆላንድ የገዙዋቸው የተሻለ ወተት መለገስ የሚችሉ 495 ላሞች ሙሉ በሙሉ የወደሙ ሲሆን በአሁኑ ወውት 500 ሄክታር ዘመናዊ የእርሻ መሬት በማልማት ላይ ይገኛሉ ተብሏል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
መቐለ

❤771👏390🙏37🤔28😭23🕊14😡10🥰8😢3
🕊#Peace
" ለችግሮቻችን መፍትሄ ከጠመንጃ ይልቅ የጠረጴዛ ውይይት እናስቀድም " - የሰላም ሚኒስቴር ሚንስትር
➡️ " በአሁኑ ሰዓት ትልቅ የህልውና አደጋ ለተጋረጠበት የትግራይ ህዝብ ስለ ዴሞክራሲና ልማት ማውራት ቅንጦት ነው " - የጠቅላይ ሚንስትሩ የምስራቅ አፍሪካ ጉዳዮች አማካሪ ሚንስትር
በአዲስ አበባ ከተማ " ሰላም ፣ ዲሞክራሲ እና ልማት በትግራይ እድሎችና ፈተናዎች " በሚል ርእስ የውይይት መድረክ ተካሂዶ ነበር።
የውይይት መድረኩ CENTRE FOR RESPONSIBLE AND PEACEFUL POLITICS (CRPP) የተባለ ተቋም ከአዲስ አበባ ዪኒሸርስቲ በመተባበር ነው ያዘጋጁት።
የውይይት መድረኩ ላይ ተገኝተው መልእክት ያስተላለፉት የሰላም ሚንስቴር ሚንስትር አቶ መሐመድ እድሪስ " ከመነጋገር እናተርፋለን " ብለዋል።
" ሃሳብ ነው ሃገርን የሚገነባው ስለሆነም ለሃሳብ ክብርና ልዕልና እንስጥ ፤ ጠመንጃንና ጦርነትን እንጠየፍ የትግራይ የፓለቲካ ምህዳር ለወጣቶች እድልና ቅድሚያ ይስጥ " ሲሉ ተናግረዋል።
" ' አንዋጋም ይበቃል ' ማለት ታላቅ ድፍረት ይጠይቃል ከተቻለ ግን ውጤቱ እጅግ አመርቂና ፍሬውም ጣፋጭ ነው። ስለሆነም እርስ በርስ መዋጋት ይብቃ ፤ ሳንገዳደል አሸናፊ የምንሆንበት ሰላማዊ መንገድ እናስቀድም የመገዳደል የመተላለቅ ታሪክ ልንዘጋው ይገባል " ሲሉ ተደምጠዋል።
የጠቅላይ ሚንስትሩ የምስራቅ አፍሪካ ጉዳዮች አማካሪ ሚንስትር አቶ ጌታቸው ረዳ፥ " የትግራይ ህዝብ አሁንም ከህልውና አደጋ አልወጣም " ብለዋል።
" ችግሮቻችን በውጭ ምክንያቶች እያሳሰበን ከመኖር ውስጣችን በደምብ በመፈተሽ የተወሳሰቡ ችግሮቻችን መፍታት እንችላለን " ሲሉ ገልጸዋል።
" ትግራይ ጥቂት አመራሮች ማረምና ማንሳት አቅተዋት በከባድ ፈተና ተዘፍቃ ትገኛለች ፤ ይህንን ከባድ ፈተና ለመወጣትና ለማለፍ ወጣቶችን ወደ መሪነት ማምጣት ይጠበቅበታል " ብለዋል።
" በአሁኑ ሰዓት ትልቅ የህልው አደጋ ለተጋረጠበት የትግራይ ህዝብ ስለ ዴሞክራሲና ልማት ማውራት ቅንጦት ነው " በማለት አክለዋል።
ለአንድ ቀን በተካሄደው የውይይት መድረክ " ሰላምና ደህንነት ፣ ዲሞክራሲ ግንባታ ፈተና እና እድል " የሚሉና ሌሎች የመወያያ ፅሁፎች ቀርበዋል።
በመድረኩ ከትግራይ የተለያዩ ዩኒቨርስቲዎች ፣ ተፎካካሪ ፓርቲዎች ፣ ስቪክ ማህበራት እንዲሁም በአዲስ አበባ የሚኖሩ ታዋቂ ሙሁራንን ፓለቲከኞች ተገኝተው ነበር።

❤610😡104🕊50🙏18🤔13😱9😭9🥰7👏7😢2