TIKVAH-ETHIOPIA
#BenishangulGumuz በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ፤ አሶሳ ከተማ የኤሌክትሪክ ኃይል ከተቋረጠ 2 ሳምንት አልፏል። የአሶሳ አጠቃላይ ሆስፒታል ሁኔታው በዚህ ከቀጠለ አገልግሎት ሊቆም እንደሚችል አሳውቋል። ሆስፒታሉ በየቀኑ ከ400 እስከ 500 ከዞን ፣ ከወረዳ፣ ከአጎራባቹ ኦሮሚያ ክልል ታካሚዎችን ያስተናግዳል። ሆስፒታሉ ከሚሰጠው አገልግሎት አንጻር 24 ሰዓት ሙሉ የማይቋረጥ ኃይል ማግኘት ያለበር ቢሆንም…
" ይኸው በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል፤ በዋናው ከተማ አሶሳ እና በተለያዩ ወረዳዎች መብራት ከጠፋ ወደ 1 ወር እየተጠጋ ነው። መቼ ነው ችግሩ የሚፈታው ? ማነው የሚነግረን ? ምንም የሰማነው ነገር የለም። ለበርካታ ቀናት ጨለማ ውስጥ ቁጭ ብለናል። ከዛሬ ነገ መፍትሄ ይሰጠናል ብለን እየጠበቅን ነው። ተሰቃየን የሚመለከታችሁ አካላት ስለፈጠራችሁ መፍትሄ ስጡን !! ህዝቡ ጨለማ ውስጥ ነው መደረግ ያለበት ነገር በፍጥነት ይደረግና ችግሩን ፍቱልን። " - ነዋሪዎች
#TikvahEthiopiaFamilyBG
@tikvahethiopia
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
😭850❤95🙏64😢36🥰34😱32😡27👏22🤔21🕊19