TIKVAH-ETHIOPIA
#ጽዮንማርያም የ2017 ዓ/ም የአክሱም ህዳር ፅዮን ሃይማኖታዊ በዓል ከነገ በስቲያ ህዳር 21 ይከበራል። የትግራይ ባህልና ቱሪዝምና ቢሮ ፤ " በቅድስት የአክሱም ከተማ እና በሌሎችም የክልሉ አከባቢዎች የህዳር ፅዮን በዓል የሚያከበሩ ገዳማት ቱሪዝምን በማነቃቃት የበኩላቸው አስተዋፅኦ አላቸው " ብሏል። ቢሮው ፤ ህዳር 21 የአክሱም ፅዮን በዓልን ለሚያከብሩ ሁሉ መልካም ምኞቱን ገልጿል። ህዝቡ በዓሉ…
የአክሱም ፅዮን በዓል !
" አክሱም ፍፁም ሰላም ናት ፤ ለአገር ውስጥና የውጭ ቱሪስቶች የሚያውክ የፀጥታ ስጋት የለም " - የአክሱም ከተማ ከንቲባ አበበ ብርሃነ
ዓመታዊው የአክሱም ህዳር ፅዮን 2017 ዓ.ም በዓል በልዩ ድምቀት መከበሩን አክሱም የሚገኘው የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባል አሳውቆናል።
በዓሉ ለመታደም ከቅርብ እና ከሩቅ የመጡ በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ምእመናን ምእመናትና ጉብኚዎች ተገኝተው ነበር።
በዓሉ በሰላም ተከብሮ መጠናቀቁም ታውቋል።
አክሱም ከተማ እጅግ ደምቃለች።
ከበዓሉ ጋር በተያያዘ ግን ወደ አክሱም የሚደረግ የአውሮፕላን ትኬት ዋጋ ልክ በዓሉ ሲቃረብ መጨመሩ በርካቶችን እንዳስከፋ ከበዓሉ ታዳሚዎች ለመረዳት ችለናል።
የዋጋ ጭማሪው ከተጓዦች ባለፈ የጊዜያዊ አስተዳደሩ ካቢኔዎች መነጋገሪያ የሆነ ሲሆን በጉዳዩ ላይ እንደሚነጋገሩበት ለመረዳት ተችሏል።
በሌላ በኩል ፤ ካለፉት የአከባበራ ዓመታት በተለየ መልኩ ዘንድሮ በበዓሉ የክልሉ ጊዚያዊ አስተዳደር ፕሬዜዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ ጨምሮ የተገኘ ከፍተኛ የመንግስትም ሆነ የፓለቲካ ፓርቲ አመራር የለም።
በአክሱም የሚገኘው የቲክቫህ ኢትዮጵያ የመቐለ ቤተሰብ አባል ከበዓሉ አዘጋጆች ጠይቆ ባገኘው መረጃ ፤ ለሁለት የተከፈሉት የህወሓት አመራሮች በበዓሉ መልእክት እንዳያስተላልፉ መከልከላቸውን አረጋግጠዋል።
ይህ በእንዲህ እንዳለ የጊዚያዊ አስተዳደሩ ፕሬዜዳንት ጌታቸው ረዳ በ X ገፃቸው ፤ የህወሓት ሊቀ-መንበር ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል (ዶ/ር) በፌስኩክ ገፃቸው " የእንኳን አደረሳችሁ !! " መልእክት አስተላልፈዋል።
ዛሬ በተከናወነው ደማው የበዓል ስነስርዓት የአክሱም ከተማ ከንቲባ አበበ ብርሃነ ተገኝተው መልዕክት አስተላልፈዋል።
" ስጋት ያንዣበበባቸው የአክሱም ሀውልቶች የመጠገን ስራ ተጀምረዋል " ያሉ ሲሆን ጅምሩ ከጫፍ እንዲደርስ የፌደራል መንግስትና የዓለም አቀፍ የቅርሶች ተቆርቋሪ ተቋማት ድጋፋቸው እንዲቸሩ ጠይቋል።
" አክሱም ፍፁም ሰላም ናት፣ ለአገር ውስጥ እና የውጭ ቱሪስቶች የሚያውክ የፀጥታ ስጋት የለም " ያሉት ከንቲባው " በትግራይ የፀጥታ ሃይሎች ላይ የሚደረገው ስም የማጥፋት ዘመቻ በመከላከል ህዝቡ የበኩሉ እንዲወጣ " ሲሉ አደራ ብለዋል።
በዋዜማ እና በዋናው የበዓሉ ዕለት በ14 ቤተ መቅደሶች በአበው ጳጳሳት የተመሩ የቅዳሴ ፣ የስብከት እና የመዝሙር ስነ-ሰርዓቶች ተከናውነዋል።
ከታሪካዊቷ ዓድዋ በ25 ኪ/ሜ ፣ ከእንዳስላሰ-ሽረ ከተማ በ60 ኪ/ሜ ርቀት የምትገኘው ቅድስት እና ታሪካዊትዋ የአክሱም ከተማ በውስጥዋ እና በዙሪያዋ በቱሪስት መስህቦች የበለፀገች ናት።
- የታቦተ ፅዮን ማድሪያ
- የበርካታ ሀውልቶች መገኛ
- የማህሌታይ ያሬድ የሙዚቃ ኖታ እና የፈላስፋ ዘርዓያዕቆብ ማህደር
- የኢትዮጵያ ፊደላት ፣ ቁጥር ፣ የግእዝ ቋንቋና የዘመን አቆጣጠር ያበቀለች
- የኢትዮጵያ የኪነ-ህንፃና ስነ-ፅሁፍ መፍለቂያ
- የነገስታት መቃብር
- የተለያዩ የእጅ ጥበብ ውጤቶች
- ጥንታዊ ሙዝየሞችና ሌሎች መገኛ ናት አክሱም።
እንዲሁም በአርኪሎጂስቶች ግኝት መሰረት ከአክሱም ከተማ ቀድሞ መመስረቱ የሚነገርለት በእንዳስላሰ-ሽረ ከተማ አጠገብ የማይ አድራሻ ጥንታዊ ከተማ ፤ ነጮች የተሸነፉበት የዓድዋ እና የተምቤን ወርቃኣምባ ታሪካዊ ተራራዎች ከአክሱም ከተማ በቅርብ ርቀት ይገኛሉ።
#TikvahEthiopiaFamilyAxum
ፎቶ፦ ትግራይ ቴሌቪዥን
@tikvahethiopia