TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
62.7K photos
1.6K videos
216 files
4.36K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

መረጃ እና መልዕክት ፦ 0919743630

ማርኬቲንግ ፦ 0979222111 ወይም
0979333111

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች መልካም የልደት በዓል እንዲሆንላችሁ እንመኛለን።

" ዛሬ በዳዊት ከተማ መድኃኒት እርሱም ክርስቶስ ጌታ የሆነ ተወልዶላችኋል። " (ሉቃ. 2÷11)

መልካም የልደት በዓል !
Ayyaana Qillee Gaarii!
ርሑስ በዓል ልደት!

#TikvahEthiopiaFamily

@tikvahethiopia
987🙏159😡36🕊34🥰18😭9🤔6😢6😱1
TIKVAH-ETHIOPIA
#Kenya ትላንት ምሽት በኢትዮጵያ ደቡብ እና ደቡብ ምዕራብ ክፍሎች በሰማይ ላይ እየተቀጣጠሉ በከፍተኛ ፍጥነት ሲንቀሳቀሱ የነበሩ ብርሃን ያላቸው የቁስ አካላት ስብስብ በኬንያ ሰሜናዊ ምስራቅ ክፍልም ታይተዋል። እነዚህ ቁስ አካላት በኬንያ ቱርካና፣ ማርሳቢት፣ ሞያሌ አካባቢ መታየታቸውን የኬንያ የማህበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚዎች ገልጸዋል። ምንም እንኳን ቁስ አካላቱ " የጠፈር ፍርስራሾች ናቸው በገጠሪቱ…
" የቁስ አካላቱ ሞያሌ ላይ አልወደቁም " - ነዋሪዎች

በሰማይ ላይ እየተቀጣጠሉ በከፍተኛ ፍጥነት ሲንቀሳቀሱ የነበሩ የቁስ አካላት ስብስብ  ነገር ሞያሌ ላይ አለመዉደቁን ነዋሪዎች ገለጹ።

ትላንት ምሽት በደቡባዊ የሀገራችን ክፍሎች ሰማይ ላይ ከተለመዱት ተወርዋሪ ኮከቦች በተለየ መልኩ በመጠን የገዘፈና በዘገምተኛ አኳሃን ሲጓዝ እንደነበር የተገለጸው ብርሃናማ የተቀጣጠሉ ቁስ አካላት " ሞያሌ አከባቢ ወድቋል " እየተባለ በማህበራዊ ሚዲያ ምንጫቸው ያልተረጋገጠ መረጃዎች ሲሰራጩ ነበር።

ዛሬ ማለዳ ጀምሮ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ከሞያሌ ኢትዮጵያ እና ጋምቦ አካባቢዎች ባደረገው ማጣራት ብርሃናማዉ አካል በተመሳሳይ መልኩ በሞያሌ ሰማይ ላይ ወደ ሶማሊያና ምስራቃዊ ኬንያ አቅጣጫ ማለፉንና በአከባቢው አለመዉደቁን ለማወቅ ችሏል።

በሞያሌ ጋምቦ የሚገኘው የመረጃ ምንጫችን ስለጉዳዩ በሰጠው ቃል " በሰሞኑ የመሬት መንቀጥቀጥ አፋር አከባቢ መደጋገሙን ስንሰማ ስለነበር በዚህም ክስተት ሰዉ ሁሉ ደንግጦ ነበር፤ ነገሩ በሞያሌ ሰማይ ላይ ሲያልፍ አይቻለሁ " ብሏል።

አክሎ " ሪችት ይመስላል-ሞያሌ ወደቀ የሚል ነገር ሰምቼ እስከ ማርሳቤትና ናይሮቢ ድረስ ደዋዉዬ አጣራሁ ያሉኝ ነገሩ ናይሮቢ አልደረሰም፤ ነገር ግን የማርሳቤት ሰዎች ሰማይ ላይ አይተነዉ ኡጂሩ በተባለች የኬንያ ድንበር አድርጎ ወደ ሶማሊያ መሄዱን ነግረዉኛል " ሲል ገልጿል።

አንዳንድ ጉዳዩ ላይ አስተያየታቸውን የሰጡ የስነ ከዋክብትና ስፔስ ሳይንስ አጥኝዎች ይኸው ተቀጣጣይ ነገር " የጠፈር ፍስራሾሽ " ሊሆኑ ይችላሉ ብለዋል።

በኢትዮጵያም ይሁን በኬንያ ተቋማት በኩል ቁርጥ ያለ ነገር ባይነገርም በኢትዮጵያ ስፔስ ሳይንስ ሶሳይቲ በኩል ጉዳይን በዝርዝር ለማሳወቅና ለማብራራት ስራዎች እየተሰሩ ነው።

ባሳለፍነው የፈረንጆች ዓመት ማገባደጃ በኬኒያ ሙኩኩ በተባለ ገጠራማ መንደር 500 ኪ.ግ የሚመዝን ቀለበታማ የጋለ ብረት  መውደቁ የተነገረ  ሲሆን የሀገሪቱ ስፔስ ኤጀንሲ ብረቱ በስፔስ ላይ ከሚገኙ ሮኬቶች ተገንጥሎ የወደቀ ሊሆን እንደሚችል ማስታወቁ አይዘነጋም።

#TikvahEthiopiaFamily #Moyalle #Gambo

@tikvahethiopia
🙏15672😭40🤔34🕊15😢12🥰9😱2😡2
#ጥምቀት

እንኳን ለብርሃነ ጥምቀቱ አደረሳችሁ ! በዓሉ በደስትና በረከት የተሞላ እንዲሆን ከልብ እንመኛለን።

መልካም የጥምቀት በዓል !

#TikvahEthiopiaFamily

@tikvahethiopia
862🙏124🕊27🥰24😢18😡15🤔5😭4
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
" ፈጣሪ ይጠብቀን እንጂ የዛሬውስ እጅግ ያስፈራ ነበር " - ነዋሪዎች

ለሊት ከ8:46-8:48 ባለው ጊዜ ከወትሮ የተለየ በርካታ ሰዎችን ከተኙበት ጥንልቅ እንቅልፍ ሁሉ ሳይቀር የቀሰቀሰ የመሬት መንቀጥቀጥ ተከስቷል።

እስካሁን ባለው መጠኑን  የዓለም አቀፍ ተቋማት ከ5.0 - 5.3 በሬክተር ስኬል መዝግበውታል።

የጀርመን ጂኦ ሳይንስ ጥናትና ምርምር ማዕከል መንቀጥቀጡ ከጭሮ ሰሜን ምዕራብ 60 ኪሎሜትር ላይ የተከሰተ ነው ብሏል።

የአሜሪካው ጂኦሎጂካል ሰርቬይ ደግሞ ቦታውን በተመሳሳይ ገልጾ መጠኑ በሬክተር ስኬል 5.3 ነው ሲል አመልክቷል።

በርካታ አፋርና አካባቢው የሚገኙ ነዋሪዎች መልዕክታቸውን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ልከዋል።

" አላህ ይጠብቀን ምን አይነት አስፈሪ መንቀጥቀጥ እንደነበር በቦታው ያለ ሰው ብቻ ያውቀዋል " ሲል አንድ የቤተሰባችን አባል ክስተቱን ገልጿል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ ከአዲስ አበባ ከሌሎች በርካታ ከተሞችም ከቤተሰቦቹ መልዕክቶችን እየተቀበለ ይገኛል።

ንዝረት ከነበረባቸው ከተሞች መካከል አዲስ አበባ እና አካባቢዋ ዋነኞቹ ናቸው።

የሽሮ ሜዳ፣ ጎሮ፣ ፊሊዶሮ፣ ፓስተር ፓውሎስ ሆስፒታል፣ አባዶ፣ አያት ፣ ጀሞ፣ ሰፈራ፣ ጋርመንት ፣ ፈንሳይ፣ ሰሚት ፣ ባልደራስ ፣ ገርጂ፣ ኮዬ ፈጬ፣ ላፍቶ፣ ሰሜን ማዘጋጃ ፣ ቱሉ ዲምቱ፣ ኮዬ ፈጬ ... ሌሎችም አብዛኛው የአዲስ አበባ እና አካባቢዋ ሰፈሮች የሚኖሩ ነዋሪዎች ንዝረቱ ከፍ ብሎ ተሰምቷቸዋል።

አንድ የቤተሰባችን አባል 5ኛ ፎቅ ላይ እንደምትኖር ገልጻ " እጅግ ያስፈራ ነበር የዛሬው ከሁሉም ነው የተለየብኝ ህንፃው ተደረመሰ እያልኩ ነው ያለፈው " ብላለች።

ሌላኛው ፤ " ፈጣሪ ይጠብቀን እንጂ የዛሬው ያስፈራ ነበር። እኔ አልጋው እየተነቃነቀ መስሎኝም ነበር ከዚህ በፊት እንዲህ ተሰምቶኝ አያውቅም በድንገት መሆኑ ደሞ ሁላችንንም አስፈርቶ ነበር " ብሏል።

ሌላ አንድ የቤተሰባችን አባል ደሞ ፥ " እኔን ጨምሮ ሁሉም ቤት ውስጥ ያለነው ተነስተን ቁጭ ለማለት ተገደናል ፤ እንዲህ ተሰምቶን ስለማያውቅ ተደናግጠናል በተለይ የህንፃው ከፍተኛው ወለል ላይ ስሜቱ ያስታውቅ ነበር " ብሏል።

ምንም እንኳን የዓለም አቀፍ ተቋማት መጠኑን ከ5. 0 እስከ 5.3 በሬክተር ስኬል ቢመዘግቡትም ስሜቱ ግን ከወትሮ የተለየና ጠንካራ ነበር።

#TikvahEthiopiaFamily

@tikvahethiopia
😭1.07K🙏403259🕊101😱58😢45👏33🤔29😡25🥰23😁1
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
መልካም የዐቢይ ጾም !

ቲክቫህ ኢትዮጵያ ለውድ ቤተሰቦቹና ለመላ ምዕመናን መልካም የዐቢይ ጾም እንዲሆን ይመኛል።

ጾሙ የፈጣሪን በረከት ፣ ዕርቅ ፣ ምህረት ፤ ለመላው ሀገራችን ፍጹም ሰላምና ዘላቂ መረጋጋትን የሚያመጣ እንዲሆን ከልብ ይመኛል።

ከብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ  ሊቀ ጳጳስ ዘአኵስም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት የጾመ ኢያሱስ ሱባዔ (ዐቢይ ጾም) መልዕክት የተወሰደ ፦

" ከጌታችን ጾም የምንወስደው ብዙ ትምህርት አለ ፤ ከሁሉ በፊት ሰው በሕይወት መኖር የሚችለው በእንጀራ ብቻ ኣይደለም ብሎናል።

ይህ ኣባባል በሕይወት ለመኖር እንጀራ አያስፈልግም ማለት ኣይደለም፤ ሕይወትን ማኖር የሚቻለው በእንጀራ ብቻ እንደ ሆነ አድርገን እንዳናስብ ግን ቃሉ ያስተምራል ፤ ይህም በዓለማችን በየዕለቱ የምናውቀው ሓቅ ነው፤ ብዙ ሰዎች እንጀራን ሳያጡ በየዕለቱ ሕይወትን ያጣሉ፤ ምክንያቱም በሕይወት ለመኖር የእግዚአብሔር ቃልም እንጂ እንጀራ ብቻው በቂ አይደለምና ነው።

ዓለማት ሁሉ በእግዚአብሔር ቃል ሁኑ ተብለው በቃሉ እንደተፈጠሩ፤ በቃሉም ጸንተው እንደሚኖሩ ኋላም በቃሉ እንደሚያልፉ ሁሉ የሰው ሕይወትም በዚህ ቃል ይወሰናል።

እንጀራ ኖረም አልኖረ ቃሉ በቃ ካለ ያበቃል ፤ ኑር ካለ ደግሞ እንጀራ ባይኖርም ይኖራል፤ ስለዚህ በሕይወታችን ወሳኝ ሥልጣን ያለው የእግዚአብሔር ቃል እንጂ፣ እንጀራ ብቻ ኣለመሆኑ ጌታችን በዚህ ኣስተምሮናል።

ጾመ ኢየሱስ እያልን በየዓመቱ የምንጾመው የታላቁ ጾማችን ዓላማ ዲያብሎስን ለማሸነፍ ነው፤ የዲያብሎስ ማሸነፊያ ስልት የመልካም ኅሊና ልዕልና ነው። "

መልካም የዐቢይ ጾም !

#TikvahEthiopiaFamily

@tikvahethiopia
53.56K🙏740🕊97🥰84😡39👏32😭21🤔18😱18😢14
TIKVAH-ETHIOPIA
🔈#የኢትዮጵያውያንድምጽ “ ወደ 29 ኢትዮጵያውያን ይበልጥ የከፋ ቦታ ተወስደዋል። ” - ኢትዮጵያዊያን በማይናማር ካሉበት ችግር እንዲያወጣቸው መንግስትን በተደጋጋሚ የተማጸኑ ፣ ማይናማር “ ታይሻንግ ካምፕ ” ታግተው የነበሩ 29 ኢትዮጵያውያን እስከዛሬ ሲደርስባቸው ከነበረው የከፋ ስቃይ ወዳለበት ስፍራ ተገደው መወሰዳቸውን ጓደኞቻቸው ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናገሩ። የተወሰዱት “ ዋልዋይ ” የተሰኘ ማይናማር…
🔈 #የኢትዮጵያውያንድምጽ

" እዚህ ያለነው ወደ 70 ኢትዮጵያውያን ነን ፤ ያለንበት ሁኔታ አስከፊ ነው ፤ ያናገረን አንድም አካል የለም " - ማይናማር የሚገኙ ኢትዮጵያውያን

በማይናማር / ማይዋዲ KK2 የሚባለው ስፍራ የሚገኙ በቁጥር 70 የሚሆኑ ወጣቶች ከቦታው የሚያስወጣቸውን አጥተው ጭንቀት ላይ እንደሆኑ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል።

ያሉበት ቦታ በማይናማር ወታደራዊ ሰዎች እየተጠበቀ እንዳለ ጠቁመዋል።

ኢትዮጵያውያኑ " እኛ በጣም አስከፊ ሁኔታ ላይ ነን። 70 እንሆናለን። ማንም መጥቶ የጠየቀን የለም። መቼ እንደምንወጣም አናውቅም። ሁሉ ነገር ጨልሞብናል " ብለዋል።

" የሚሰጠን ምግብ የማይበላ ነው። ማደሪያ የለንም እንጨት ላይ ነው የምንተኛው ምን አይነት ሁኔታ ውስጥ እንዳለን ለመናገር ይከብዳል ስቃይ ላይ ነን " ሲሉ ገልጸዋል።

" ባለፈው አንድ ወንድማችን በጣም ታሞ በስንት መከራ ነው ህይወት የዘራው " ሲሉ አክለዋል።

" ያሉትን የMilitary ሰዎች ጠይቀናቸው ነበር አብረውን ካሉት ውስጥ ' የህንድ መንግሥት ዜጎቹን ለመውሰድ accept ስላደረገ እነሱ ይወጣሉ በእናተ በኩል ምንም ምላሽ የለም ' ብለውናል " ሲሉ ገልጸዋል።

" ቢያንስ ትወጣላችሁ የሚለን የለ ወይ ስለኛ የሚናገር የለም እባካችሁ ስቃያችንን ስሙን " ሲሉ ተማፅነዋል።

" ህንዶቹ ነገ እና ከነገ ወዲያ ይወጣሉ ዛሬ እየተዘጋጁ ነው ከኛ ሀገር በኩል ያናገረን የለም በጣም ተጨንቀናል " ብለዋል።

እኚህ ወጣቶች ህይወትን ለማሸነፍ ሲሉ ታይላንድ ተብለው ወደ ማይናማር በግዳጅ የተወሰዱና በዛም በማፊያዎች ስንትና ስንት ስቃይ ያዩ ሲሆን ከዛ ስፍራው እንዲወጡ ከተደረጉ በኃላ አሁን ደሞ ሌላ ስቃይ እያዩ እንደሆነ አመልክተዋል።

#TikvahEthiopiaFamily

@tikvahethiopia
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
😭1.3K🙏118114😡62🕊31😢22🥰18😁18👏3😱3
TIKVAH-ETHIOPIA
🔈 #የጤናባለሙያዎችድምጽ 🔴 " በየጊዜው ቃል ከመግባት የዘለለ ምንም መፍትሄ የሰጠን አካል የለም !! " - የጤና ባለሙያዎች ➡️ " ከ8 ወራት በላይ የትርፍ ሰዓት ክፍያ ስላልተከፈለን ለ2ኛ ጊዜ ስራ ለማቆም እየተገደድን ነዉ !! " በማዕከላዊ ሲዳማ ዞን ሎካ-አባያ ወረዳ ሀንጣጤ ሆስፒታል የሚሰሩ የጤና ባለሙያዎች በበዓላት፣ በማታና የእረፍት ቀናት የሰሩበት ከ6 እስከ 9 ወራት የትርፍ ሰዓት…
#Update

" ተመላላሽ የሕክምና ቀጠሮ ቢኖረንም ሆስፒታሉ ዝግ ስለሆነ አገልግልት ማግኘት አልቻልንም " - ተገልጋዮች

➡️ " ከ6 እስከ 9 ወራት ታግሰን የትርፍ ሰዓት ክፍያ ባለመከፈሉ ከአቅማችን በላይ ሆኖ ስራ አቁመናል" - የጤና ባለሙያዎች

🔴 " የትርፍ ሰዓት ክፍያ አልተከፈለንም ብለዉ መደበኛ ስራቸዉን በሚያቆሙ ላይ ሕጋዊ እርምጃ እንወስዳለን " - የዞን አስተዳዳሪ

በሲዳማ ክልል ማዕከላዊ ሲዳማ ዞን ሎካ አባያ ወረዳ በሀንጣጤ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል የሚገኙ የጤና ባለሙያዎች ከ6 እስከ 8 ወራት የሰሩበት የትርፍ ሰዓት ክፍያ ባለመክፈሉ ስራ ለማቆም እንደሚገደዱ በመግለፅ በቲክቫህ ኢትዮጵያ በኩል ቅሬታቸዉን አሰምተዉ ነበር።

በወቅቱ የዞኑ አስተዳዳሪ ቅሬታዉ ተገቢ መሆኑን በመግለፅ " ከክልል ብድር ጠይቀናል በጥቂት ቀናት ስለሚፈፀም የ5 ወራት ክፍያ በአንድ ላይ በመፈፀምና ቀሪዉን በየወሩ እንዲከፈላቸዉ ይደረጋል " ሲሉ ምላሽ ሰጥተዉ ነበር።

ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ቅሬታቸዉን ዳግም ያደረሱት የሆስፒታሉ ጤና ባለሙያዎች " ከቅሬታዉ ምላሽ በኋላ ተጨማሪ አንድ ወር ታግሰን ለሙያ ቃል ኪዳናችንና ሕብረተሰቡን ማገልገል ስላለብን በችግሮች ዉስጥ አልፈን እየሰራን ብንቆይም አሁን ላይ ከአቅማችን በላይ በመሆኑ ስራ አቁመናል " ሲሉ ገልፀዋል።

" ከ6 እስከ 9 ወራት የትርፍ ሰዓት ክፍያ ካለመፈፀሙም ባሻገር አመራሮች ነገሮች እንዲመቻቹላችሁ ' የብልፅግና ፓርቲ ሕንፃ ግንባታ መዋጮ የአንድ ወር ደመወዝ አዋጡ ' ብለዉን ሁሉም ባልተስማማበት ከመደበኛ ደመወዝ እየቆረጡ ነዉ ፤ በዚህም ለዘርፈ ብዙ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ቀዉሶች ተዳርገናል " ሲሉ ተናግረዋል።

" ዶክተር ሆነህ ' ቸገረኝ አበድረኝ ' ማለት ያሳቅቃል ይህ በሞራልም እየጎዳን ነዉ " ሲሉ ስሜታቸዉን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ያጋሩ ዶክተሮች ተናግረዋል።

እንዲሁ ሌላ የጤና ባለሙያ " ለህክምና የመጣች አንዲት ታካሚ ዱቤ ልትጠይቀኝ መስሎኝ ተደብቅያለሁ " ሲል እያሳለፉ ስላለው ህይወት ተናግረዋል።

ተገልጋዮች ምን አሉ ?

" በሀንጣጤ ሆስፒታል የሕክምና ክትትል ስለነበረን ግን ወደ ሆስፒታሉ  ቅዳሜ ጠዋት ስንሄድ ግቢዉ ዝግ ነበር፤ ጥበቃዉ የጤና ባለሙያዎች አለመግባታቸውን ነገረን " ሲሉ አንድ የሆስፒታሉ ተገልጋይ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል።

እኚሁ ተገልጋይ አማራጭ አጥተዉ በስልክ ከሕክምና ባለሙያዎች ባገኙት ምክር ከግል የጤና ተቋማት መድሐኒት ለመግዛት መገደዳቸውን ገልጸዋል።

ሳምንቱን በስራ ላይ አሳልፈዉ ለልጃቸዉ ሕክምና ቅዳሜ ወደ ሆስፒታሉ ቢመጡም ሐኪሞች ባለመኖራቸው ለሰዓታት ጠብቀዉ መዉጣታቸውን የገለፁት ሌላኛዉ የሀንጣጤ ከተማ ነዋሪ ከእሳቸዉም ዉጪ ሌሎችም አገልግሎት ለማግኘት መጥተዉ ሲያማርሩ ማየታቸዉንና ችግሩ ከጤና ባለሙያዎች የትርፍ ሰዓት ክፍያ ጋር የተያያዘ መሆኑን መስማታቸውን ተናግረዋል።

ሆስፒታሉ ለአከባቢዉ ሕብረተሰብ ከሚሰጠዉ አገልግሎት አንፃር የሚመለከታቸዉ አካላት ፈጣን መፍትሔ እንዲሰጡ ጠይቀዋል።

የዞን አስተዳዳሪ ምን አሉ ?

ቲክቫህ ኢትዮጵያም የማዕከላዊ ሲዳማ ዞን ዋና አስተዳዳሪ የሆስፒታሉ የቦርድ ሰብሳቢ አቶ መንግስቱ ማቴዎስን ለምን በተገባላቸዉ ቃል መሰረት ክፍያው አልተፈፀመላቸዉ ሲል ጠይቋል ? አቶ መንግስቱ በምላሻቸው " አሁን ጥረት እያደረግን ነዉ፤ ከላይ በጀት ሲገኝ ነዉ ችግሩ የሚፈታዉ " ያሉ ሲሆን " ልጆቹም ስራ ለመስራትም ፈቃደኛ አይደሉም፣ መስራት የሚፈልግ ይቀጥላል ያልተመቸዉ ሊለቅ ይችላል " ብለዋል።

" ኖሪማሊ ጉዳዩ እኔን የሚመለከተኝ አይደለም፤ ወረዳዉ ነዉ ባለቤቱ " የሚሉት የዞኑ አስተዳዳሪ " ሠራተኞቹ እየሄዱበት ያለው አካሄድ ተገቢ አይደለም፤ የትርፍ ሰዓት ክፍያ አልተከፈለንም ብለዉ መደበኛ ስራቸዉን በሚያቆሙ ላይ ሕጋዊ እርምጃ እንወስዳለን " ሲሉ አስጠንቅቀዋል።

የሆስፒታሉ ሰራተኞች የትርፍ ሰዓት ስራ ብቻ ማቆማቸዉንና በተደጋጋሚ ቃል እየተገባ ስለማይፈፀምላቸዉ ስራ ማቆማቸዉን ገልፀዉልናል ይህን ማድረጋቸው ያስጠይቃቸዋል ወይ ? ሲል ቲክቫህ ኢትዮጵያ ላነሳላቸዉ ጥያቄ  " መደበኛ ስራ ነዉ እያቆሙ ያሉት፣ ከደሞዝ መቁረጥ እስከ ማሰናበት እርምጃ ይወሰድባቸዋል " ብለዋል።

" በአንፃሩ የትርፍ ሰዓት ስራ ማቆም መብታቸዉ ነዉ ሲሉም " ተደምጠዋል።

ሰራተኞች ስራ ከማቆማቸዉ በፊት በጽሑፍ ለወረዳ ፣ ለዞኑና ለክልሉም ጤና ቢሮ ጭምር ቅሬታቸዉን ማቅረባቸውን ገልፀዉልናል ፤ በሆስፒታሉ የጤና ክትትል የበራቸዉና ለሕክምናም መጥተዉ በዕረፍት ቀናት አገልግሎት ባለማግኘታቸዉ የተቸገሩ ተገልጋዮችም ቅሬታቸዉን አሰምተዉናል ሲል ቲክቫህ ኢትዮጵያ ላነሳላቸዉ ጥያቄ አቶ መንግስቱ " በአካል ካልመጣችሁ ከዚህ የበለጠ መረጃ ልሰጣችሁ አልችልም ! " በማለት አቋርጠዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያም ከሲዳማ ክልል ጤና ቢሮ በጉዳዩ ላይ ተጨማሪ ማብራሪያ ለማግኘት ያደረገዉ ሙከራ በድጋሚ አልተሳካም፤ ተጨማሪ መረጃዎችን ማግኘት ስንችል የምናካትት ይሆናል።

#TikvahEthiopiaFamily

@tikvahethiopia
😭450131😡101👏51🙏22😢17🥰14🕊12😱10🤔8💔8
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
ሰሙነ ሕማማት !

ከሆሳዕና በዓል (እሁድ) ስድስት ሰዓት እስከ አርብ (ስቅለት) ማታ ድረስ ያሉት ቀናት ሰሙነ ሕማማት ናቸው።

ሳምንቱ " ዘመነ ፍዳ " የሚታሰብበት ጊዜ ነው።

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ሰሙነ ሕማማት ወቅት " የፈጣሪን ህመም " ታሳቢ ያደረግ ልዩ ህግና ስርዓት አለ።

ቤተክርስቲያን ወትሮ የምታከናውናቸው ስርዓቶች በሕማማት ቀናት አይከናወኑም።

ህዝበ ክርስቲያኑ በሰሙነ ሕማማት የፈጣሪውን መከራ በማሰብ በተለየ ስርዓት ነው ቀናቱን የሚያሳልፈው።

በሰሞነ ሕማማት የትኞቹ የቤተ ክርስቲያን ስርዓቶች አይተገበሩም ?

በሰሙነ ሕማማት በቤተ ክርስቲያን " ግብረ ህማማት " የሚባል መጽሀፍ ይነበባል ፤ ለሳምንቱ የተዘጋጀ ልዩ ጸሎት ይደረጋል።

የሌሎች ስርዓቶች ክዋኔ ይገታል።

በሰሙነ ሕማማት ፦
- ቅዳሴ አይቀደስም (ከጸሎተ ሀሙስ ውጭ)
- ማህሌት አይቆምም
- ጸሎተ ፍትሀት አይደረግም
- መስቀል አይሳለምም
- ክርስትና አይነሳም
- ኑዛዜ አይሰጥም አይቀበልም

እነዚህ ስርዓቶች በሆሳዕና ዕለት አስቀድመው የሚከናዎኑ ናቸው።

ምዕመናን ሰሙነ ሕማማትን በምን ስርዓት ይከውናሉ ?

በቤተ-ክርስቲያኗ " የመከራ ዘመን " የሚባለውን 5500 ዓመትን በመወከል አምስት ቀናት ተኩል የሆነው ሰሙነ ሕማማት በምመናን ዘንድ በተለያዩ ድርጊቶች ይታሰባል።

የሚተገበሩት ድርጊቶች ሀዘንን ለመግለጽ እንዲሁም ከአስተምሮ ጋር መልዕክ ያላቸው ናቸው።

ምእመናን በሰሙነ ሕማማት ፦
- ከመጨባበጥና መሳሳም በመራው
- በባዶ እግር በመቆም
- በስግደት
- በጸሎት
- ራስን ዝቅ ማድረግ ያስባሉ።

አባቶች በሕማማት ሳምንት ምዕመኑ ፦
° ወደ ራሱ ጠልቆ በመግባት መጸለይ እንዳለበት
° ሰው ስለ ኃጢያቱ ማሰብ እንዳለበት
° ስለ ሀገሩ ማዘን እንዳለበት
° ለሰላም መጸለይ እንዳለበት
° የሰው ልጅ ሰላም እንዲያገኝ ሰላም ያጣው ህዝብ ሰላም እንዲያገኝ መጸለይ እንዳለበት
° ፈጣሪ የተቀበለውን መከራ በማሰብ ለሀገር ሰላም እንዲሰጥ ህይወታችንን ያስተካክል ዘንድ መለመን እንዳለበት
- ከኃጢያታችን ይቅር እንዲለን መጸለይ እንዳለበት ያስገነዝባሉ።

(መላከ ገነት ክብሩ ገ/ጻድቅ - ከዚህ ቀደም ለአል አይን ከሰጡት ቃል)

#TikvahEthiopiaFamily
@tikvahethiopia
333.49K🙏438😡97😭85🤔57🕊37💔29👏28🥰24😱15😢1
#ትንሣኤ

ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለብርሃነ ትንሣኤው አደረሳችሁ !

" በዚህ የለም ፤ እርሱ እንደተናገረው ተነሥቷል "  


በማቴዎስ ወንጌል ፥ " እነሆ ታላቅ የምድር መናወጥ ሆነ፤ የእግዚአብሔር መልአክ ከሰማይ ወርዶአልና ፤ ቀርቦም በመቃብሩ አፍ ላይ ድንጋይዋን አንከባሎ በላይዋ ተቀመጠ፡፡

መልኩም እንደ መብረቅ ፤ ልብሱም እንደ በረዶ ነጭ ነበር፡፡

እርሱንም ከመፍራት የተነሣ መቃብሩን የሚጠብቁ ታወኩ ፤ እንደ በድንም ሆኑ፡፡

መልአኩ መልሶ ሴቶቹን እንዲህ አላቸው፥ ' እናንተስ አትፍሩ ፤ የተሰቀለውን ኢየሱስን እንደምትሹ አውቃለሁና፡፡ በዚህ የለም ፤ እርሱ እንደ ተናገረው ተነሥቶአል ' " ተብሎ እንደተጻፈው መድኃኒዓለም ብርሃንን ተጎናጽፎ በታላቅ ኃይልና ሥልጣን በክብር ተነሥቶአል፡፡

መልካም የትንሣኤ በዓል !
በዓሉ የሰላምና የፍቅር ይሆን ዘንድ እንመኛለን !


ቲክቫህ ኢትዮጵያ
#TikvahEthiopiaFamily

@tikvahethiopia
1273.63K🙏389🕊117😡78🥰76🤔45😭36👏35😢22😱16💔4
የሳቀ ሁሉ ደስተኛ አይደለም !!

(ዶክተር ኃይለልዑል መኮንን)

ሁሌም ስታገኙት ደስተኛና ሳቂታ የነበረ ሰው በድንገት ራሱን አጥፍቶ ሞተ ሲባል ሰምታችሁ ታዉቃላቹ ?

ብዙ ሰዉ የድብርት ህመም ደስተኛ አለመሆን ፣ የሀዘን ስሜት ፣ ተስፋ መቁረጥ እና የመሳሰሉት ብቻ ይመስለዋል። አንዳዴ እየሳቁ እና እየተጫወቱ በከባድ የድብርት ህመም የሚሰቃዩ ሰዎች አሉ። በህክምናዉ (atypical depression) ይባላል።

- አብዛኛዉን ጊዜ ደስ የሚያሰኝ ነገር ሲያገኙ ለተወሰነ ጊዜ መደሰት ከዛም መልሶ የሀዘን እና የባዶነት ስሜት ዉስጥ መግባት፣
- ምግብ ፍላጎት እና ክብደት መጨመር፣
- ከሳምንታት በላይ ቀኑን ሙሉ መድከም እና እንቅልፍ ማብዛት፣
- በትንንሽ አስተያየቶች እና ትችቶች መሰበር፣
- የዘወትር ተግባራትን ለመከወን መቸገር የድብርት በሽታ ሌላኛዉ መልክ ሊሆን ይችላል።

ስለዚህ የሳቀ ሁሉ ደስተኛ አይደለም፤ ምናልባት ከሳቁ ጀርባ የተደበቀ የባዶነት እና የሀዘን ስሜት ይኖራልና እርስ በእርስ እንጠያየቅ።

(ይህ የግንቦት ወር በዓለም አቀፍ ደረጃ የአዕምሮ ጤና ግንዛቤ ወር ነው)

#የአዕምሮ_ጤና_ግንዛቤ_ወር
#ዶክተር_ኃይለልዑል_መኮንን
#MentalHealthAwarenessMonth

#TikvahEthiopiaFamily

@tikvahethiopia
😢1.92K680🙏495👏162😭89💔74🕊62🤔47😱44🥰29😡23
ከት/ቤት የራቁ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ተማሪዎች፣ ምን ዓይነት ችግሮችን ያስተናግዳሉ ?

" ሚዲያዎቹ በችግሩ ላይ መወያየት በሀገሪቱ ውስጥ ያለውን አለመረጋጋት ማስታወስ ስለሚሆንባቸው፣ ጉዳዩን አይዘግቡትም !! "    

በኢትዮጵያ በተለያዩ አካባቢዎች ባሉት ግጭቶችና የተፈጥሮ አደጋዎቸ ምክንያት በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ሕፃናት እና ወጣቶች ከትምህርት ገበታ ውጭ መሆናቸውን የትምህርት ሚኒስቴር ከሳምንታት በፊት አስታውቆ ነበር።

በዚህ ዓመት ብቻ ከ7 ነጥብ 8 ሚሊዮን በላይ ሕፃናት ከትምህርት ገበታ ውጭ መኾናቸውን ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ይፋ አድርጎ ነበር።

በአማራ ክልል ብቻ፣ በ2017 የትምህርት ዘመን፣ 7 ሚሊዮን ተማሪዎችን ለመመዝገብ ታቅዶ የተመዘገቡት ግን 2 ነጥብ 8 ሚሊዮን ተማሪዎች ብቻ መሆናቸውን ክልሉ አመልክቷል፡፡

የተባበሩት መንግስታት የህፃናት ፈንድ ወይም ዩኒሴፍ ደግሞ በዚህ ዓመት ታህሳስ ወር ባወጣው ሪፖርቱ፣ በኢትዮጵያ በግጭት፣ በተፈጥሮ አደጋዎችና በመፈናቀል ምክንያት 9 ሚሊዮን ልጆች ከትምህርት ገበታ ውጭ መሆናቸውን፣ 10 ሺህ ት/ቤቶችም መጎዳታቸውን አመልክቷል፡፡

ቲክቫህ ኢትዮጵያ ይህን መነሻ በማድረግ፣ ከት/ቤት ውጭ የሆኑት ህፃናትና ልጆች ምን ዓይነት ጉዳት እንደሚደርስባቸው፣ አንድ የዘርፉ ባለሙያን አስተያየት ጠይቋል።

ባለሙያው በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ፣ የትምህርት ዘርፍ መምህርና ተመራማሪ ናቸው፡፡ በተለያዩ ምከንያቶች፣ ከትምህርት ገበታ ውጭ በሚሆኑ ህፃናት ዙሪያም በርካታ ምርምሮችን ማድረጋቸውን ጠቅሰዋል፡፡   

ባለሙያው ስለዚህ ጉዳይ ምን አሉ ?

" በኢትዮጵያ የመማር ማስተማር ሒደቱ እንዳይከናወን መሰረታዊ ምክንያት የሆነው የሰላምና የፀጥታው ጉዳይ ነው፡፡

ሰላምና ፀጥታ የሌለባቸው አካባቢዎች፣ ትምህርት የለም፡፡ ለምን ብትል፣ በተዋጊ ሀይሎች ስጋት ስለሚያድርባቸው ነው፡፡ ወላጅ ልጁን ት/ቤት ለመላክ ስጋት ይኖርበታል፣ ት/ቤቶች ለተለያዩ ጥቃቶች ተጋላጭ ይሆናሉ፡፡

ሁለተኛው ምክንያት እንደ ድርቅና ጎርፍ ያሉ የተፈጥሮ አደጋዎች ናቸው፡፡

አንደኛው ችግር ከደህንነታቸው ጋር የተያያዘ ነው፡፡ ልጆች ት/ቤት በሚውሉበት ጊዜ የሚያገኙት አንዱና ትልቁ ጥቅም፣ አንፃራዊ የሆነ ጥበቃ ነው፡፡ ከት/ቤት ውጪ ሲሆኑ፣ ለተለያዩ አካላዊና ስነልቦናዊ ጥቃቶች ይዳረጋሉ፡፡ ልጆቹ ወደ ተለያዩ ስራዎች ይሰማራሉ፣ የቤት ውስጥ አገልጋይ ይሆናሉ፣ ለህፃናት ጉልበት ብዝበዛ ይጋለጣሉ፣ ሴቶቹ ደግሞ ያለእድሜ ጋብቻ ይጋለጣሉ፡፡

ልጆች ከ 2 እስከ 3 አመት ከት/ቤት ውጪ ከሆኑ፣ ወደ ት/ቤት የመመለስ ዕድላቸው ከአስር በመቶ ያነሰ መሆኑን ጥናቶች ያሳያሉ፡፡ የመመለስ እድል አይኖራቸውም አብዛኞቹ፡፡

ሁለተኛው ችግር እነዚህ ተማሪዎች የወደፊት አምራች ዜጋ የመሆን እድላቸው አናሳ ነው፡፡ በሀገር ኢኮኖሚ ተፅዕኖ ያስከትላል፡፡ ያልተማረ፣ ያላነበበ ልጅ ሌላ ተጨማሪ ክህሎት የማዳበር ዕድሉ አነስተኛ ነው፡፡ በሒደት ኋላቀርነት ነው የሚስፋፋው፡፡ ነገ ኮምፒዩተር ልማር፣ መንጃ ፈቃድ ላውጣ፣ ሙያ ልሰልጥን ቢል የሚሆን ነገር አይደለም፣ ለምን አልተማረም፡፡ ወደፊት ምርታማነቱ ያነሰ ህብረተሰብ ነው የሚፈጠረው፡፡

ሶስተኛው ችግር፣ የልጆቹ ስነልቦና ስለሚጎዳ፣ ላላስፈላጊ ድርጊቶች የመጋለጥ ዕድል ያጋጥማቸዋ፡፡ አዕምሮዋዊ እድገታቸው ይገታል፣ ለከፍተኛ ጭንቀት ይጋለጣሉ፡፡ በማህበረሰቡ ዘንድ ያለን ቦታ አናሳ ነው ብለው ያምናሉ፡፡ በህብረተሰቡ ዘንድ ተቀባይነት የሌላቸው ባህሪያትን ያዳብራሉ፡፡ ከዛም ማህበራዊ ቀውስ ይከተላል፡፡ "

በመንግስት በኩል እነዚህ ችግሮች ትኩረት አላገኙም፡፡ የእነዚህ ተማሪዎች ጉዳይ ምን ያህል በመንግስት ሚዲያዎች አጀንዳ ሆኖ ይቀርባል፣ መፍትሔ ለማምጣት፣ ችግሩን ለመቅረፍ ምም ያል በትኩረት ይዘገባል ካልን ብዙም አይደለም፡፡

በችግሩ ላይ መወያየት በሀገሪቱ ውስጥ ያለውን አለመረጋጋት ማስታወስ ስለሚሆንባቸው፣ ጉዳዩን አይዘግቡትም፡፡

አንዳንድ ጊዜ አለፍ አለፍ ብለህ ከምትሰማው ዜና በስተቀር፣ እንደ አጀንዳ ተይዞ በጉዳዩ ላይ ውይይት ሲደረግ አታይም፡፡ የእነዚህን ልጆች ጉዳይ፣ ስራዬ ብሎ ወስዶ እንዴት ልፍታው የሚለው ላይ በተገቢው መንገድ እየተሰራ ነው ብዬ አላምንም፡፡ "

መፍትሔው ምድነው ?

" በትምህርት ጉዳይ ላይ በማህበረሰቡና በግጭቱ ተሳታፊዎች መካከል መግባባት መፈጠር አለበት፡፡

ግጭት ባሉባቸው የተለያዩ ሀገራት ዘንድ ትምህርት እንዲቀጥል የሚያስችሉ መግባባቶች ላይ ሲደረስ እናያለን፡፡ እንደ ቀይመስቀል እና ዩኒሴፍ የመሰሉ ሶስተኛ አካላት ሐላፊነት ወስደው፣ የመማር ማስተማር ሒደት እንዲቀጥል የሚደረግባቸው ሁኔታዎች አሉ፡፡ እኛም ጋ ይህን ይቻላል፡፡ ይህን ለመፈፀም ግን በተዋጊዎቹ ዘንድ ልባዊ ቅንነትና ዝግጁነት ያስፈልጋል፡፡

በተፋላሚ ሀይሎች ትምህርት የፖለቲካ አጀንዳ ማስፈፀሚያ መሆን የለበትም፡፡

እነ ቀይመስቀልን እነ ዩኒሴፍን በመጠቀም፣ ትምህርት እንዲቀጥል ማድረግ ይቻላል፡፡እነዚህ ተቋማት ከቦታ ቦታ የመንቀሳቀስ ዕድል ስላላቸው፣ በተዋጊ ሀይሎች ዘንድ ቅንነት ካለ፣ ይህን ማድረግ ቀላል ነው፡፡

በግጭት ቦታዎች የመማር ማስተማር ስራ እንዴት ይቀጥል የሚለው መታየት አለበት፡፡ ብዙ መንገዶች አሉ፡፡

አንዳንድ ሀገራት እንዲህ አይነት ችግር ሲገጥማቸው፣ የመማር ማስተማር ሒደቱን በሞባይል ስልኮችና በሬድዮ በማስቀጠል፣ ከመደበኛው አሰራር ውጭ የሖነ አማራጭ መንገድን ይጠቀማሉ፡፡ ይህ አካሔድ ልጆች ከትምህርት እንዳይርቁ ያደርጋል፡፡ እንዲህ ዓይነት አማራጮች፣ በእኛም ሀገር ሁኔታ ተግባራዊ መሆን ይችላሉ፡፡ "

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ
#TikvahEthiopiaFamily

@tikvahethiopia
😢26054😡21👏13🕊12😭12🥰7🤔6🙏6😱2
TIKVAH-ETHIOPIA
የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና የሚሰጥበት ቀን ይፋ ተደረገ። የ2017 ትምህርት ዘመን ኢትዮጵያ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ማጠናቀቂያ / የ12ኛ ክፍል ፈተና የሚሰጥበት መርሃ ግብር ይፋ ተደርጓል። የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ይፋ ባደረገው መርሃ ግብር ፈተናው ከሰኔ 23/2017 ዓ/ም ጀምሮ እስከ ሐምሌ 8/2017 ዓ/ም የሚሰጥ ይሆናል። በወረቀት የሚፈተኑ የተፈጥሮ ሳይንስ ተፈታኞች ሰኔ 21…
የ12ኛ ክፍል አገር አቀፍ ፈተና የሚሰጥበት ቀን ይፋ ሆኗል።

የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች ፈተና መቼ ይሰጣል ?


➡️ በወረቀት ፈተናቸውን የሚወስዱ ተፈታኞች ፦ ሰኔ 23 ፣ ሰኔ 24 እና ሰኔ 25/2017 ዓ/ም

➡️ በበየነ መረብ (ኦንላይን) /ፈተናቸውን የሚወስዱ የ1ኛ ዙር ተፈታኞች ፦ ሰኔ 23 ፣ ሰኔ 24 እና ሰኔ 25/2017 ዓ/ም

➡️ በበየነ መረብ (ኦንላይን) /ፈተናቸውን የሚወስዱ የ2ኛ ዙር ተፈታኞች ፦ ሰኔ 26 ፣ ሰኔ 27 እና ሰኔ 30/2017 ዓ/ም

የማህበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች ፈተና መቼ ይሰጣል ?

➡️ በወረቀት ፈተናቸውን የሚወስዱ ተፈታኞች ፦ ሐምሌ 1 ፣ ሐምሌ 2 እና ሐምሌ 3/2017 ዓ/ም

➡️ በበየነ መረብ (ኦንላይን) /ፈተናቸውን የሚወስዱ የ1ኛ ዙር ተፈታኞች ፦ ሐምሌ 1 ፣ ሐምሌ 2 እና ሐምሌ 3/2017 ዓ/ም

➡️ በበየነ መረብ (ኦንላይን) /ፈተናቸውን የሚወስዱ የ2ኛ ዙር ተፈታኞች ፦ ሐምሌ 4 ፣ ሐምሌ 7 እና ሐምሌ 8/2017 ዓ/ም

#Ethiopia #NationalExam #Grade12

#TikvahEthiopiaFamily

@tikvahethiopia
😭829321🙏165👏81🥰58🕊46💔37😡34🤔33😱25😢16
" ጎቶሌ" በቡርጂ ብሔረሰብ የሴቶች የደቦ ሥራ !

" አንዲት እማወራ በወር የማትጨርሰዉን አረም በ'ጎቶሌ' በአንድ ቀን እንጨርሳለን " - የቡርጂ ብሔረሰብ ሴቶች

(ቲክቫህ ኢትዮጵያ በቡርጂ)

" ጎቶሌ " በቡርጂ ብሔረሰብ ዘንድ ትልቅ ትርጉም የሚሰጠዉ ሰዎች በጋራ በመሆን የአንድን ግለሰብ የስራ ጫና ያለምን ክፍያ በነፃ የሚጋሩበት ባህላዊ የመረዳዳት ስርአት ነዉ።

በብሔረሰቡ የሴቶች " ጎቶሌ " ደግሞ ሴቶች በቡድን በመሆን በተለይም ለአርሶ አደሩ እጅግ ፈታኝ የሆነዉን የአረም ስራ በልዩ ልዩ ባህላዊ ዜማዎች እና መሞጋገሶች የሚከዉኑበት ድንቅ የስራ እሴት ነዉ።

የጎቶሌዉ አባላት እነማናቸዉ ?

የሴቶች ጎቶሌ አባላት በተቀራራቢ የዕድሜ ክልል ዉስጥ ያሉ የአንድ መንደር ሴቶች ናቸው። እኚህ ሴቶችም አንዳች መስፈርት አዝመራ በአረም መወረር ሲጀምር በመሰባሰብ ይመካከራሉ።

ከ6 እስከ 15 ሴቶች በአንድ ቡድን የሚካተቱ ሲሆን በተፈጥሯዊ ሁኔታም ሆነ በሌሎች ምክንያቶች የአቅም ውሱንነት ያላቸዉ ከብርቱዎቹ ጋር እየተሰባጠሩ በየዓመቱ የሚቀያየር የቡድን መጠሪያ ስያሜ ያወጣሉ።

በማስከተልም የቡድን መሪ (ላላዶ) እና ቃል አቀባይ (ሀወይሴ) በመምረጥ አስቀድመዉ እንደ ማሟሟቂያ የአቅመደካማ አዛዉንቶችና የመበለቶችን ማሳ ያለምንም ክፍያ በነፃ ያርማሉ።

ቀጥሎም የቡድኑ " ጎቶሌ"ዉ አባላት ቤተሰቦችን ማሳ በፍላጎት አልያም በዕጣ ቅደም ተከተል የማረም ስራ ይሰራሉ።

የቡድን መሪዋ እና ቃል አቀባይዋ ተግባር ምንድነው ?

የቡድን መሪዋ " ላላዶዋ " ከቡድኑ አባላት ቀልጣፋና ተናጋሪ ስትሆን ልክ እንደ ቃሉ ትርጉም (ላላዶ-አነፍናፊ) በማነፍነፍ የስራ ጥራት፣ ቅደም ተከተልና አጠቃላይ ሂደቱን የመምራት ስራ ትሰራለች። ባለማሳዉ ወገን ምግብና መጠጥ በሰዓቱ እንዲያቀርቡም ታስደርጋለች።

" ሀወይሴ " ወይንም ቃል አቀባይዋ ደግሞ አባላቱን ገና በማለዳ በልዩ የኮድ ጥሪ ለስራ የማሰባሰብ እና የሰዓት ቁጥጥሩን እንዲሁም ቡድኑን የማጫወት የማሳሳቅ ስራን ታከናዉናለች። ልዩ ልዩ አነቃቂ ዜማዎችንም በመጫወት ጠንካሮችን የመሞጋገስና ደከም ያሉትን በመዉቀስ እንዲበረቱ የሚያደርጉ ባለሙያዎችን የመጋበዝ ስራም ትሰራለች።

የቡድኑ አባላት የሚገኛኙት እንዴት ነዉ ?

ገና በማለዳ ሀወይሴዋ ማዕከል በሆነ ቦታ ላይ በመሆን የቡድኑ አባላት ብቻ በሚያቁት ኮድ ድምጿን ከፍ አድርጋ ትጣራለች። አባላቱም ወዲያዉ ይሰባሰቡና በዓመቱ በወጣላቸዉ መጠሪያ ስያሜ እያዜሙ ወደ ማሳ ያቀናሉ።

ስያሜዉ ለምን በየዓመቱ ይቀያየራል ?

የቡድኑ ስያሜ በአከባቢው በዓመቱ ከተስተዋሉ በጎ በጎ ክስተቶች፣ የብሔረሰቡ የስራ ወቅት ስያሜዎችና አንዳንዴም በመሪዋ ስም ሊሰየም የሚችል ሲሆን በየዓመቱ የሚቀያየረዉም ሁኔቶች ስለሚቀያየሩ ነዉ።

የቡድኑ ቆይታ እስከ መቼ ነዉ?

ቡድኑ የአረም ወቅት እስኪጠናቀቅ የሚቀጥል ሲሆን በዚያዉ መጠሪያ ዳግም በአጨዳና ምርት የመሰብሰብ ወቅት ይገናኛል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ በአከባቢዉ ተገኝቶ ይህን መረጃ ባዘጋጀበት ወቅት " ላቴ " እና " ጦልንዴ " የተሰኙ ሁለት የሴቶች ጎቶሌ ቡድኖችን የተመለከተ ሲሆን ትርጉማቸዉም " ልማት " እና " ኮከብ " የሚል እንደሆነ ከአባላቱ ተረድቷል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ ይህን ጠንካራ የመረዳዳት እሴት በተመለከተበት ወቅት ያነጋገራቸው የቡድኑ አባላትም ፥ አንዲት እማ ወራ ብቻዋን ብትሆን በወራት ልትጨርሰዉ የማትችለዉን አረም በአንድ ቀን እንደሚጨርሱና " ሴት በዛ ጎመን ጠነዛ " የሚባለው አባባል ፍፁም ስህተት እንደሆነ በአደባባይ የሚታይበት እንደሆነ ተናግረዋል።

ፎቶ ፦ መ/ር ደጀኔ ፈጠነ

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
#TikvahEthiopiaFamily

@tikvahethiopia
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
507👏144🥰13🕊13🙏11🤔8😡8😢7😭4😱3
TIKVAH-ETHIOPIA
“ እናቴን በሕይወት ባጣም ሌሎች ኢትዮጵያዊያን እናቶቼ ያላችሁን በማገዝ ከሞት ታደጉኝ ” - የ16 ዓመቷ የልብ ታማሚ በጸጥታ ችግር ከወለጋ ተፈናቅላ በደብረ ብርሃን ቻይና መጠለያ ካምፕ ከገባች አራት አመት እንዳስቆጠረች የገለጸችው የ16 ዓመት ታዳጊ ለቀዶ ህክምና ከፍተኛ ገንዘብ በመጠየቋ እርዳታ እንዲረግላት ተማጸነች። በቶሎ ካልታከመች ሕይወቷ ከባድ አደጋ ላይ መሆኑን እንደተነገራት ለቲክቫህ ኢትዮጵያ…
ምስጋና 🙏

" ህይወቴን ስለታደጋቹልኝ በፈጣሪ ስም አመሰግናለሁ ፤ እኔም ነገ ለሀገሬ ምችለውን ሁሉ አደርጋለሁ " - ሀያት በላይ

ከዚህ ቀደም በደብረብርሃን ቻይና ካምፕ የተፈናቃዮች መጠለያ የነበረች እና እናቷን በሞት የተነጠቀች የ16 ዓመት ታዳጊ ሀያት በላይ ከልብ ጋር በተያያዘ ላለባት የቆየ ህመም ቀዶ ህክምና ለማድረግ ድጋፍ እንዲደረግላት ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ ጥሪ አቅርባ ነበር።

በዚህም ጥሪ መሰረት ከፍተኛ የሆነ ድጋፍ አግኝታ ህክምናዋ በተሳካ ሁኔታ ተካሂዷል።

" ለአመታት ስሰቃይበት ከነበርው የልብ ህመሜ እንድድን ስለረዳቹን በፈጣሪ ስም ከልብ አመሰግናለሁ " ስትል ለመላው የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት ምስጋናዋን ልካለች።

" ባጋጠመኝ ከፍተኛ የሆነ የልብ ህመም ስታመም ከርሜ ቀዶ ህክምና እንደሚስፈልገኝ የልብ ሀኪሞች ተረጋጦ ነበር። ለህክምናው የተጠየኩት ብር ከቤተሰቦቼ አቅም በላይ ስለነበር በቀን 6/6/2017 ወደ ውዱ የኢትዮጵያ ህዝብ የእርዳታ ጥሪ አቅርቤ ፣ ለችግር ፈጥኖ ደራሽ የሆነው ወገኔም ችግሬን ተረድቶ  ህይወቴን ታድጎኛል " ብላለች ታዳጊዋ።

" ደስ ብሎኛል ደስ ይበላቹ ፤ በአዲሱ ልቤ በድጋሚ ከልብ እያመሰገንኩኝ ለውዱ የኢትዮጵያ ህዝብ በተለይም ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ ሁሌም ጤና፣ ፍቅር እና ሰላም እመኛለሁ ፤ እኔም ነገ ለሀገሬ ምችለውን ሁሉ አደርጋለሁ " ስትል ገልጻለች።

በዚህ አጋጣሚ በማስረጃ ተደግፎ እገዛ ለሚፈልጉ ወንድም ፣ እህቶች እና ወገኖች ሁሉ የእገዛ ጥሪ ሲቀርብላችሁ ካላችሁ ላይ ቀንሳችሁ ለምታካፍሉ የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት ረጅም እድሜን ከጤና ጋር ይስጣችሁ።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
#TikvahEthiopiaFamily❤️

@tikvahethiopia
32.83K🙏363👏90🥰73🕊40😢10💔6😭6😱1
#ExitExam

የቅድመ-ምረቃ መርሐግብር ተማሪዎች የመውጫ ፈተና ከነገ ሰኔ 2 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ እስከ ሰኔ 10 ቀን 2017 ዓ/ም ድረስ ይሰጣል።

ከ190 ሺህ በላይ ተፈታኞች የመውጫ ፈተናውን በ51 ዩኒቨርሲቲዎች በተዘጋጁ 87 የፈተና ማዕከላት ይወስዳሉ፡፡ ከእነዚህ ውስጥ 88 ሺህ የሚሆኑት ዳግም የመውጫ ፈተናውን የሚወስዱ ናቸው።

የመውጫ ፈተናው በ238 የትምህርት መርሐግብሮች በበይነ መረብ ነው የሚሰጠው።

የተከለከሉ ነገሮች ምንድናቸው ?

➡️ የማይፈቀዱ የሂሳብ ማሽኖች (በአንዳንድ ፕሮግራሞች #ካልኩሌተር ማምጣት ይፈቀዳል፡፡ ሆኖም ግን ስልክ፣ ስማርት ዋች፤ ታብሌትና ተመሳሳይ ቁሶችን እንደ ካልኩሌተር መጠቀም ፈፅሞ አይፈቀደም። ሥራ ላይ የሚውሉ ካልኩሌተሮች የተራቀቁ እንዲሁም ፕሮግራመብል እንዳይሆኑ ተገቢውን ጥንቃቄ ማድረግ ይገባል)፣
➡️ ተንቀሳቃሽ ስልክ፣
➡️ ሜሞሪ ያለው የእጅ ሰዓት፣
➡️ የተጭበረበሩ ሰነዶች፣
➡️ የራስ ያልሆነ መታወቂያ፣
➡️ አጫጭር ማስታወሻዎች፣
➡️ ማንኛውንም ዓይነት የጦር መሣሪያ ይዞ መገኘት ክልክል ነው።

በተጨማሪም ፦
⚠️ አደንዛዥ ዕጽ ተጠቅሞ መምጣት፣
⚠️ ከፈተና አስፈጻሚዎች ጋር አሉታዊ ተጽእኖ ያላቸው ውዝግቦችን መፍጠር፣
⚠️ያለመታወቂያ ካርድ ወደ ፈተና ማእከል መሄድ፣
⚠️ ያለፈቃድ ፈተና ማዕከል መገኘት፣
⚠️ ለሌላ ሰው መፈተን ፍጹም የተከለከሉ የዲሲፒሊን ጥሰቶች ናቸው።

ተፈታኝ ተማሪዎች ፈተናው ከመጀመሩ ከ30 ደቂቃ ቀድመው በተመደቡበት የፈተና ክፍል መገኘት የሚኖርባቸው ሲሆን ፤ ከተመደቡበት ክፍል ውጪ መፈተን ውጤት ያሰርዛል።

ተፈታኞች የፋይዳ መታወቂያ መያዝ ይኖርባቸዋል።

መያዝ የሚፈቀደው የፋይዳ መታወቂያ ፦
- በኢትዮ ቴሌኮም ወይም የኢትዮጵያ ፖስታ አገልግሎት አማካኝነት የታተመ የፋይዳ መታወቂያ፣
- ከ "Fayda ID" ሞባይል መተግበሪያ ፣ ከቴሌብር ሱፐር አፕ፣ እንዲሁም ሲቢኢ ብር ሞባይል መተግበሪያ ላይ #QR_ኮድ በማውረድ እና በወረቀት በማሳተም መያዝ ይቻላል።

📵 ዲጂታል የፋይዳ መታወቂያ ኮፒ በስልክ ይዞ መገኘት አይቻልም።

በሌላ ሰው ስም፣ User Name እና Pasword መፈተን አይቻልም፡፡

ከላይ የተዘረዘሩ የፈተና ስርአቶችን የጣሰ ተፈታኝ ውጤቱ ተሰርዞ በዲሲፒሊን ጥሰት የሚጠየቅ መሆኑ ተገልጿል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ ለመላው ተፈታኞች መልካም እና በውጤቱም የምትደሰቱበት የልፋታችሁን ፍሬ የምታዩበት የተሳካ ፈተና እንዲሆን ይመኛል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
#TikvahEthiopiaFamily

@tikvahethiopia
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
1.29K🙏153😭64🕊39🥰20😱17😡14🤔12👏9😢3
" የጸጥታ ችግር አለባቸው የሚባሉ የአማራ ፣የኦሮሚያ እና የትግራይ ክልል አካባቢዎች ላይ ከችግሩ በፊት የተተከሉ የኔትወርክ ማማዎች ላይ አንዲት እቃ አልተነካብንም "- ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ

ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ የአገልግሎት ፍቃዱን በተረከበ በአራት ዓመታት ጊዜ ውስጥ በአገሪቱ ዙሪያ ያሉት የ90 ቀናት ንቁ ደንበኞቹ ቁጥር 10 ሚሊዮን መድረሱን ይፋ አድርጓል።

የግል የቴሌኮም አቅራቡ ድርጅት የሆነው ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ በአሁኑ ሰአት የአራተኛ ትውልድ ኔትወርክ ከኢትዮጵያ ሕዝብ ውስጥ ከግማሽ በላይ ለሚሆነው ተደራሽ ማድረጉን የገለጸ ሲሆን ለዚህም ከመቶ ሃምሳ በላይ በሆኑ ከተሞች 3,141 የኔትወርከ ማማዎችን መገንባቱን ገልጿል።

የሳፋሪኮም ኢትዮጵያ ቺፍ ኤክስተርናል አፌርስ ኦፊሰር አቶ አንዷለም አድማስ "ሳፋሪኮም የመጠንከር የመወዳደር እና ቀና ብሎ የመጓዝ ሂደት ላይ" ነው ሲሉ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አስረድተዋል።

አቶ አንዷለም አድማስ በዝርዝር በሰጡት ሃሳብም ምን አሉ ?

" 10 ሚሊየን ንቁ(Active) ደንበኞች ማለት ባለፉት ዘጠና ቀናት ውስጥ የደወለ ወይም መልእክት የተቀበለ ማለት ነው።

ባለፉት 90 ቀናት ካልደወለ ወይም ካርድ ካልሞላ ከእኛ ዳታ ቤዝ ውስጥ ይወጣል ከደወለ ወይም ካርድ ከሞላ ወደ ዳታ ቤዛችን ይገባል ስለዚህ 10 ሚሊየን ንቁ ደንበኛ ስንል ገንዘብ የምናገኝበት ትክክለኛ ደንበኛችን ማለት ነው።

3141 ታወሮች በጣራ ላይ እና ግሪን ፊልድ ላይ አሉን የተወሰኑ ሳይቶችን ከኢትዮ ቴሌኮም ጋር በጋራ ነው የምንጠቀመው ለዚህም ኢትዮ ቴሌኮም ጥሩ ገቢ ያገኛል።

ዋና ዋና የሚባሉ ከተሞች አዳርሰናል ከዚህ በኋላ ወደ ሌሎች ከተሞችም እንዳረሳለን ለዚህም ከ 1.5 ቢሊየን ዶላር በላይ ተጨማሪ ኢንቨስት እናደርጋለን።

በአሁኑ ሰአት ከኮሪደር ልማት ጋር በተገናኘ የ Fiber መቆረጥ አለ እሱ መፍትሄ በሚሰጥ መልኩ እየተሰራ ነው።

በመላ ሃጋሪቱ ነው የምንንቀሳቀሰው እቃዎች ተጭነው ነው የሚሄዱት በአንዳንድ አካባቢዎች ላይ እንደማንኛውም ሰው እክል ሊገጥመን ይችላል ነገር ግን የተጋነነ ነገር አለ ብዬ አላስብም።

የጸጥታ ችግር አለባቸው የሚባሉ የአማራ ፣የኦሮሚያ እና የትግራይ ክልል አካባቢዎች ላይ ከችግሩ በፊት የተተከሉ የኔትወርክ ማማዎች ላይ አንዲት እቃ አልተነካብንም " ብለዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ
#TikvahEthiopiaFamily

@tikvahethiopia
1.4K👏208😡41🙏32🥰19🕊15🤔11😱11😭11😢9💔3
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#Update

ሲዳማ ቡና ስፖርት ክለብ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴን ውሳኔ " ተገቢና ህግን ያልተከተለ ውሳኔ " ሲል ተቃወመ።

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፈዴሬሽን የሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ የኢትዮጵያ ዋንጫ ከሲዳማ ቡና ተነጥቆ ለወላይታ ዲቻ እንዲመለስ ሲል ውሳኔ አሳልፏል።

ይህ ተከትሎ የሲዳማ ቡና እግር ኳስ ክለብ ቦርድ ውሳኔውን " ተገቢነት የለሌው ውሳኔ ነው። ውሳኔው እጅግ አሳዝኖናል " ብሏል።

" ብርቅዬ የክለባችን ተጫዋቾች በጨዋታ ሜዳ የገጠሙትን ሁሉንም ከጨዋታ ብልጫ ጋር በማሸነፍ የ2017 ዓ.ም የኢትዮጵያ ዋንጫ ማሸነፉ የአደባባይ ምስጥር ነዉ " ሲል ገልጿል።

" ይሁን እንጂ ' የሊግ ካምፓኒ ያወጣውን የፋይናንስ ደንብ አላከበራችሁም ' በሚል በክለቡና በተጫዋቾች ላይ ቅጣት ተጥሎባቸዋል ቢባልም ክለቡ  ያነሳዉ ዋንጫ የኢትዮጵያ ጥሎ ማለፍ በ48 ክለቦች መካከል የተደረገው መሆኑ ዕሙን ነው " ብሏል።

" የሲዳማ ቡና ስፖርት ክለብ የታገዱ ተጫዋቾችን አሰልፎ ከሆነ በጥሎ ማለፉ ያሸነፋቸው ክለቦች በሙሉ ፎርፌ አግኝተው ጉዳያቸው እንደገና መታየት አለበት እንደ ማለትም ይሆናል " ብሏል።

" እርስ በርስ የሚጣረሱ ሀሳቦችን በማገናኘት ውጤቱን ለመቀማት መሞከር  ተገቢና ህግን የተከተለ ውሳኔ ነው ብለን አናምንም " ሲል ቦርዱ አሳውቋል።

" ፌዴሬሽኑ ዉሳኔውን ከህግጋቱ ጋር በማገናዘብ እንደገና እንዲያጠነዉ ቅሬታችንን እናሰማለን " ብሏል።

" ህዝባችን በፌደሬሽኑ ውሳኔ የተከፋ ቢሆንም የአፊኒ ባህል ያለው ታላቅ ህዝብ ስለሆነ ክስተቶችን በመረጋጋት መርምሮ በተገቢው እንዲያጠነውና  ሂደቱን  በትዕግሥት እንዲጠባበቅ በአክብሮት እየጠይቃል " ሲል ገልጿል።

" የተነፈግነው ፍትህ እስኪረጋገጥ ድረስ ጉዳዩን እስከ ፊፋ ገላጋይ ፍርድ ቤት ድረስ በይግባኝ ወስደን ለጉዳዩ  ተገቢው እልባት እስኪሰጥ ድረስ የክለቡ ቦርድ ቁርጠኛ መሆኑን እናረጋግጣለን " ሲል አሳውቋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
#TikvahEthiopiaFamily

@tikvahethiopia
1.11K🤔144👏77😭48😡47🙏31🕊23😢10😱8💔7🥰1
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
" በእስራኤል እና በኢራን መካከል የተካሄደውን የተኩስ አቁም ስምምነት ተከትሎ ወደ ሶስቱም ከተሞች ያቋረጥናቸውን በረራዎች በድጋሚ አስጀምረናል " - የኢትዮጵያ አየር መንገድ

በዛሬው ምሽት የኢትዮጵያ አየር መንገድ ፖርቶ ወደ ተሰኘች የፖርቹጋል ከተማ አዲስ በረራ ይጀምራል።

አየር መንገዱ የፖርቹጋል ሁለተኛ ትልቋ ከተማ ወደ ሆነችው ፖርቶ የሚያደርገው በረራ የኢትዮጵያ አየር መንገድ በአውሮፓ ያሉትን የበረራ መዳረሻዎች ቁጥር 22 እንደሚያደርሰው ይፋ በማድረጊያ ስነስርዓቱ ላይ ተገልጿል።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ አውሮፓ ከሚያደርጋቸው ጉዞዎች በሀገር ደረጃ ፖርቹጋል 17 ተኛዋ ሃገር ስትሆን ይህ በረራ ወደ ፖርቹጋል የተደረገ የመጀመሪያው በረራ መሆኑን ተነግሯል።

የአየር መንገድ ግሩፕ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ መስፍን ጣሰው " የኢትዮጵያ አየር መንገድ በመጪው አንድ ወር ጊዜ ወደ ወደ ዱባይ እና ቬትናም  ተጨማሪ ሁለት መዳረሻዎችን ይፋ የሚያደርግ ይሆናል " ብለዋል።

በእስራኤል እና በኢራን መካከል ተቀስቅሶ የቆየውን ግጭት ተከትሎ አየር መንገዱ ወደ ቀጠናው የሚያደርገው ጉዞ ማቋረጡ ይታወሳል።

ተቋርጠው የቆዩት በረራዎች በድጋሚ መጀመራቸውን አቶ መስፍን ጣሰው አስታውቀዋል።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ዋና ስራ አስፈጻሚ በዝርዝር ምን አሉ ?

" መካከለኛው ምስራቅ እና ገልፍ አካባቢ ያሉ ሃገሮች ላይ ግጭት መኖሩን ተከትሎ የተወሰኑ ከተሞች በረራ አቋርጠን ነበር።

እስራኤል ውስጥ ወደ ቴልአቪቭ፣ ሊባኖስ ውስጥ ወደ ቤሩት እንዲሁም ዮርዳኖስ ውስጥ ወደ ኦማን ከተሞች ስናደርግ የነበረውን በረራዎች በጊዜያዊነት አቋርጠን ቆይተናል።

በእስራኤል እና በኢራን መካከል የተካሄደውን የተኩስ አቁም ስምምነት ተከትሎ ወደ ሶስቱም ከተሞች ያቋረጥናቸውን በረራዎች በድጋሚ አስጀምረናል።

ተቋርጦ በቆየበት ወቅት መንገደኞች ወደዛ አካባቢ መጓጓዝ ያቆማሉ ስለዚህ መጠነኛ የተጓዦች መቀነስ ይታያል በረራ ላይ ሲታይ ግን ትልቅ ለውጥ የነበረው አይደለም " ብለዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ
#TikvahEthiopiaFamily

@tikvahethiopia
840👏84🕊58🤔19😡19😭12🙏11😢10🥰8😱5
" 10 ሰዎች ተገድለዋል፤ ከ10 በላይ ሰዎች ቆስለዋል " - የቤሩ ወረዳ አስተዳዳሪ

በጋምቤላ እና ደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል አዋሳኝ ዲማ እና ቤሩ አከባቢዎች በተነሳ ግጭት የሰዎች ህይወት ማለፉን የአካባቢው ባለስልጣናት ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገለፁ።

በጋምቤላ ክልል የአኙዋሃ ብሔረሰብ ዞን ዲማ ወረዳ እና በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የምዕራብ ኦሞ ዞን ቤሩ ወረዳ አዋሳኝ አከባቢዎች በወርቅ ቁፋሮ ቦታ ምክንያት በተነሳ ግጭት ከ10 ሰዎች በላይ መሞታቸውን ባለስልጣናት ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አረጋግጠዋል።

የጋምቤላ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ኦጉላ ኡጁሉ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ እንደተናገሩት በዲማ ወረዳ የወርቅ ማምረት ስራ ላይ ፈቃድ ወስደዉ የተሰማሩ ባለሃብቶችንና በሳይት ጥበቃ ላይ የነበሩ ሚሊሻዎችን የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል ምዕራብ ኦሞ ዞን በኩል አስረዉ መወሰዳቸውን ተከትሎ ግጭቱ መከሰቱን አስታውቀዋል።

" በግጭቱ ምክንያት ሁለቱም በኩል የሰዉ ሕይወት ጠፍቷል " ሲሉ ገልፀዋል።

" የሟቾችን ቁጥር እስካሁን አልለየንም " ያሉት ኮሚሽነሩ መረጃዉ ተጣርቶ ሲደርስ እንደሚያሳዉቁም ገልፀዋል።

በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል ምዕራብ ኦሞ ዞን የቤሩ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ገመዳ ከይዳዴ በበኩላቸው " ድንበር አልፈዉ የወርቅ ቁፋሮ ሲያካሂዱ የነበሩ 11 ግለሰቦችንና 1 የጦር መሳሪያ በቁጥጥር ስር አዉለን ተገቢውን ማጣራት እያደረግን ባለንበት ወቅት ከጋምቤላ ክልል በኩል ተኩስ ተከፍቶ 2 የአድማ ብተና አባላት፣ 1 መደበኛ ፖሊስ እና ሴቶች ጨምሮ 7 በወርቅ ቁፋሮ ስራ ላይ የነበሩ ንፁሃን ዜጎች በድምሩ 10 ሰዎች ተገድለዋል፤ ከ10 በላይ ሰዎች ቆስለዋል " ሲሉ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል።

በግጭቱ ምክንያት ከ20 ሺህ ነዋሪዎች ተፈናቅለዉ እንደነበር የገለፁት ዋና አስተዳዳሪዉ ከማምሻ ጀምሮ የፌዴራል ፖሊስ እና የሀገር መከላከያ ሠራዊት አከባቢውን በመቆጣጠሩ ተፈናቃዮችን ወደ ቦታቸዉ የመመለስ ስራ እየተከናወነ መሆኑን ተናግረዋል።

በአሁኑ ሰዓት በአካባቢው ግጭት መቆሙንና የሀገር መከላከያ ሰራዊት፣ የፌዴራል ፖሊስና የሁለቱም ክልል ባለስልጣናት ሕዝቡን የማረጋጋት ስራ እየሰሩ ስለመሆኑ ከሁለቱም ክልሎች በኩል ቲክቫህ ኢትዮጵያ ማረጋገጥ ችሏል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
#TikvahEthiopiaFamily

@tikvahethiopia
474😭119💔47🕊30🥰6🙏5😢4🤔3😱3😡3