TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
62.7K photos
1.6K videos
216 files
4.36K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

መረጃ እና መልዕክት ፦ 0919743630

ማርኬቲንግ ፦ 0979222111 ወይም
0979333111

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
#ETHIOPIA🇪🇹 ሀገራችን ኢትዮጵያ በሳዑዲ አረቢያ በማቆያ ጣቢያ የሚገኙ ዜጎቿን ከነገ ጀምሮ በተቀናጀ መንገድ የመመለስ ሥራ እንደምትጀምር የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቋል። በሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ብርቱካን አያኖ የተመራ የመንግሥት ልዑክ በሳዑዲ አረቢያ ሪያድ የኢትዮጵያ ኢምባሲ እና የጂዳ ቆንስላ ጀነራል ሰራተኞች እና የኮሙኒቲ አስተባባሪዎች ጋር በመወያየት በተመላሾች መለየት እና መመለስ ላይ…
#Update

“ ከሳዑዲ ተመላሾች በመደበኛው የሥራ ዕድል ፈጠራ ተጠቃሚ እንዲሆኑ ተካተዋል ” - ሴቶች እና ማኀበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር

ኢትዮጵያ ከሳዑዲ አረቢያ ዜጎቿ እየመለሰች እንደምትገኝ የሴቶችና ህፃናት ጉዳይ ሚኒስቴር ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገለጿል።

በሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የሕገ ወጥ ሰዎች ዝውውር መካላከልና የተመላሽ ዜጎች ድጋፍና ክትትል ሂደት መሪ ስራ አስፈጻሚ አቶ ደረጀ ተግይበሉ በሰጡት ቃል ፣ " በሳዑዲ አረቢያ የሚገኙ ዜጎችን የመመለሱ ስራ እየተሰራ ነው " ብለዋል።

ዛሬ እና ትላንት ብቻ 1913 ሰዎች ተመልሰዋል።

ምን ያህል ወገኖችን ለመመለስ ታስቧል ? ሲል ከቲክቫህ ኢትዮጵያ ያቀረበላቸው አቶ ደረጃ “ በአጠቃላይ ለመመለስ የታቀደው ወደ 70 ሺሕ የሚሆኑ ኢትዮጵያውያንን ነው። በሚቀጥሉት 3 እና 4 ወራት ውስጥ በስምንት 3 ወይም 4 ቀናት በሚደረግ በረራ የማስመለስ ዕቅድ ተይዟል ” ሲሉ መልሰዋል።

70 ሺሕ ወገኖችን ከመመለስ ባሻገር ኢትዮጵያ ውስጥ በቋሚነት ለማቋቋም ምን ታቅዷል ? በሚል ላነሳነው ጥያቄ ፥ “ በተለይ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ትኩረት ሰጥቶ የሳዑዲ ተመላሾች በመደበኛው የሥራ ዕድል ፈጠራ ተጠቃሚ እንዲሆኑ ተካተዋል ” ብለዋል።
 
በዚህ ወቅት በመደበኛው ሆነ በኢመደበኛው የሄዱ በአጠቃላይ በሳዑዲ አረቢያ ምን ያህል ኢትዮጵያውያን ስደተኞች አሉ ? ለሚለው ጥያቄ፣ “ አብዛኛዎቹ መደበኛ ባልሆነ ስርዓት ስለሆነ የሚሄዱት ይህን ይህል ናቸው ተብለው በመንግሥት አይታወቅም ” ብለዋል።

በሳዑዲ በጣም በርካታ ኢትዮጵያውያን ዜጎች እንዳሉ፣ ነገር ግን ሁሉም መደበኛ ባልሆነ ፍልሰት የሄዱ ናቸው ተብሎ ስለማይጠበቅ ከሳዑዲ መንግሥት ጋር በተደረገ ድርድር እየተመለሱ ያሉት በኢመደበኛ ፍልሰት የሄዱትንና በአስቸጋሪ ሁኔታ ሚገኙትን እንደሆነ አስረድተዋል።

በኢመደበኛ መንገድ የሚሄዱ ዜጎች፦
- የሞት አደጋ፣
- ሴቶች ለፆታዊ ጥቃት፣
- በደላላ ገንዘባቸውን የመበዝዘብ ችግር እንደሚደርስባቸው የገለጹት አቶ ደረጀ፣ “ መደበኛውን የፍልሰት ስርዓት ተከትለው የሚሄዱባቸውን ሁኔታዎች ከመንግሥት አካላት መረጃ ወስደው እንዲጠቀሙ አደራ እንላለን
” ሲሉ አስገንዝበዋል።

#ThikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
299👏56🕊34🙏33😭26😡26🤔16😱15🥰13😢3
TIKVAH-ETHIOPIA
" ... ሠራተኞቹ የአገር ልማት ሥራ ላይ ሲደክሙ ነው ይሄ ችግር የደረሰባቸው። ግለሰቦቹን በማገት የሚመጣ ለውጥ የለም " - የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል መስረከም 19/2016 ዓ/ም ለስራ በወጡበት በታጣቂዎች ከታገቱ 6 የኤሌክትሪክ ኃይል ሰራተኞች ሁሉም እንዲለቀቁ 2.8 ሚሊዮን ብር ቢከፈልም 3ቱ ተለቀው የቀሩት 3ቱ እስካሁን ያልተለቀቁ ሲሆን ያሉበት ሁኔታም አይታወቅም። የታጋች ቤተሰቦች ዛሬም በሀዘን…
#Update

“ ከታገቱ ሚያዚያ 19/2016 ዓ/ም ሰባት ወራት ይሆናቸዋል። እንደቀላል ነገር በወጡበት ቀሩ ” - የታጋች ባለቤት

ከ6 ወራት በፊት ወደ ባቱ (ዝዋይ) ለስራ ጉዳይ እየተጓዙ በታጣቂዎች ታገቱ ከተባሉ 6 የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ሠራተኞች መካከል 3ቱ ቢለቀቁም 3ቱ ግን እንዳልተለቀቁ ቤተሰቦቻቸው ለቲክቫህ ኢትዮጵያ መግለጻቸው ይታወሳል።

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይልም የሚችለውን ሁሉ እንደሞከረ ከ2 ሳምንታት በፊት ገልጾልን ነበር።

በወቅቱ #እንባ እየተናነቃቸው ቃላቸውን የሰጡን የአንዱ ታጋች እህት ፣ “ በስልክ እንኳን ‘አለሁ በሕይወት’ እንዲለን ድምጹን ያሰሙን። 2.8 ሚሊዮን ብር ተከፍሎ 3ቱ ሠራተኞች ግን ከእገታ አልተለቀቁም ” ማለታቸው ይታወሳል።

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጠው ቃል፣ “ ሠራተኞቹ የአገር ልማት ሥራ ላይ ሲደክሙ ነው ይሄ ችግር የደረሰባቸው። ግለሰቦቹን በማገት የሚመጣ ለውጥ የለም። በሰላም እንዲለቋቸው የሚል ጥሪ ማስተላለፍ እፈልጋለሁ ” ነበር ያለው።

አሁንስ ምን አዲስ ነገር አለ ?

ከ3ቱ ታጋቾች መካከል የሁለት ልጆቻቸው አባት የታገተባቸው ወ/ሮ ቤተልሄም ገዛኸኝ ፥ ታጋቾቹ አሁንም እንዳልተለቀቁ ገልጸዋል።

ከባለቤታቸው በተጨማሪ አንድ የሁለት ልጃቸው እናት የሞቱባቸው አባትና አንድ ሁለት ቤተሰቦቹን የሚያስተምር ሠራተኞች እንደሚገኙበትና ከታገቱ ከ6 ወራት በላይ ቢያስቆጥሩም ፣ አሁንም ያሉበት እንደማይታወቅ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጸዋል።

በንግግራቸው መሀል #የሚያለቅሱት ወይዘሮ ቤተልሄም በሰጡት ቃል ፣ “ በሕይወቱ ስለመኖሩም እየተጠራጠርኩ ነው። ሁለቱ ልጆቹ በትምህርታቸው ከፍተኛ አሉታዊ ተፅዕኖ ደርሶባቸዋል። አንዷ ተመራቂ፣ አንዱ ማትሪክ ተፈታኝ ናቸው። እኔም የስኳርና የደም ግፊት ሕመምተኛ ነኝ ” ብለዋል።

ለመንግሥት ጭምር ባስተላለፉት መልዕክትም፣ “ ሞቷልም፣ አለም ቢባል እኮ አንድ ነገር ነው። እንዲህ አድርጉ የሚሉን ነገር ካለም ቢጠቁሙን መፍትሄ ነው” ብለው፣ “እንደ ቀላል ነገር በሀገራቸው ላይ ታግተው በወጡበት ቅርት ሲሉ ዝም ማለት በጣም ይከብዳልና ሁሉም ርብርብ ያድርጉልን ” ሲሉ ጠይቀዋል።

“ ከታገቱ ሚያዚያ 19 ቀን 2016 ዓ/ም 7 ወራት ይሆናቸዋል። እንደቀላል ነገር በወጡበት ቀሩ። እቃ እንኳን ሲጠፋ ዝም አይባልም እንኳን ሰው። እንደ ሰው ትኩረት ይሰጣቸው ” ሲሉም አክለው አሳስበዋል።

“ እንዲያው በእግዚአብሔር፣ በሁሉም ልጆች ባሏቸው አባቶች፣ እህት፣ ወንድም ባላቸው ሰዎች ሁሉ ስም ሁሉም ሰዎች እንደራሳቸው አይተው የሚችሉትን ነገር ሁሉ ይተባበሩን። ያጣሩ። ከእግዚአብሔር በታች ሰዎችን ነው የምለምነው ” ነው ያሉት።

#ThikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
😢1.11K😭378173😡60🙏54😱22🤔21🕊18👏17🥰15
#TikTok

" ግለሰቦቹ ለሕግ ቀርበው ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡ ተመጣጣኝ ቅጣት ይቀጡ፤ መላው መስማት የተሳናቸው ማህበረሰብን በሕግ ፊት ይቅርታ ይጠይቁ " - መስማት የተሳናቸው ማሕበረሰቦች

መስማት የተሳናቸው ማሕበረሰብ እና ምልክት ቋንቋ ላይ " በማሾፍ " ቪዲዮዎችን በ
#ቲክቶክ ላይ ያጋሩ፣ ከድርጊታቸው እንዲታቀቡ ቢጠየቁም ፈቃደኞች ባለመሆናቸው በሕግ ተገቢውን ቅጣት እንዲያገኙና ለሌሎች ማስተማሪያ እንዲሆኑ ያሰባሰቡትን ፊርማ ለአዲስ አበባ ፓሊስ ጠቅላይ መምሪያ አስገብተው ምርመራ እንዳስጀመሩ ስሞታ አቅራቢዎቹ  ገለጹ።

ወጣቶቹ መስማት የተሳናቸው ማህበረሰቦችንና የሚግባቡበትን ምልክት ቋንቋ ክብር የሚነኩ፣ በሕግ የሚያስጠይቁ ተግባራትን በመፈጸም ቪዲዮ ያሰራጩ መሆናቸውን ከሳሾቹ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል።

የክሱ ሂደት አስተባባሪ መስማት የተሳናነው ጋዜጠኛና መምህር ናትናኤል ሽፈራው፣ " ድርጊቱ መስማት ለተሳነን፣ ለቤተሰቦቻችን፣ ለሀገራችን እንደማንጠቅም አድርጎ የሚያስገነዝብ ነው " ሲሉ ወቅሰዋል።

" በማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴ የነቃ ተሳትፎ እንዳናደርግ የተሳሳተ ግንዛቤ የሚፈጥር፣ 'መስማት የተሳናቸው አይችሉም' የሚለው የቆየ እሳቤ በዚህ ዘመን እንዲንጸባረቅ በር የሚከፍት አደገኛ ድርጊት በመሆኑ በርካቶቻችን አስቆጥቷል " ነው ያሉት።

" ድርጊቱ የግንዛቤ ማነስ ይሆናል ብለን ያጋሩትን እንዲያጠፉ ብንጠይቅም ንቀው በማለፋቸው መብታችን ለማስከበር ጠንከር ያለ ዘመቻ ስንገባ ጥቂቶቹ  ይቅርታ ቢጠይቁም ሌሎቹ ግን ልንቆጣጠረው በማንችለው ሁኔታ እያስፋፉት በመሆኑ ሕጉ በሚያዘው መሰረት ተገቢውን ቅጣት እንዲያገኙ ለሌሎች ማስተማሪያ እንዲሆኑ የሚመለከተው አካል የድርሻውን ይወጣልን " ሲሉ አሳስበዋል።

"ግለሰቦቹ ለሕግ ቀርበው ድርጊታቸው እንዲቆጠቡ ተመጣጣኝ ቅጣት ይቀጡ፤ መላው መስማት የተሳናቸው ማህበረሰብን በሕግ ፊት ይቅርታ ይጠይቁ " ሲሉም ገልጸዋል።

ጉዳዩን ለአዲስ አበባ ፓሊስ ጠቅላይ መምሪያ በደቤዳቤና ባሰባሰቡት ፊርማ ማሳወቃቸውን ገልጸው፣ አስነዋሪ ድርጊቶች እንዳይስፋፉ ሚዲያዎች ትኩረት ሰጥተው እንዲዘግቡ በአንክሮ ጠይቀዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ
#ThikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
1.46K👏360😭66🙏52🤔38😡28🕊27💔24🥰15😱13😢3