TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
62.7K photos
1.6K videos
216 files
4.35K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

መረጃ እና መልዕክት ፦ 0919743630

ማርኬቲንግ ፦ 0979222111 ወይም
0979333111

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
የኮቪድ-19 ክትባት!

የኦክስፎርድ ዩኒቨርስቲ የኮሮና ቫይረስ ክትባት ወደ 2ተኛው ደረጃ ተሸጋገረ። በቀጣይ ክትባቱን በ10,260 ሰዎች ላይ (ከ70 ዓመት በላይ እና ከ5-12 ዓመት የእድሜ ክልል) በሙከራ ደረጃ ለመስጠት ታቅዷል።

እስካሁን ክትባቱ ጥሩ ውጤት እያሳየ ነው የተባለ ሲሆን ሳይንቲስቶች አሁን ያለው ሂደት በዚህ ከቀጠለ በጥቂት ወራቶች ውስጥ ክትባቱን በስፋት ለማዘጋጀትና ለማድረስ እንደሚሰራ ተናገርዋል።

የUK መንግስት በተደጋጋሚ በዚህ ጉዳይ ላይ ምንም አይነት ዋስትና እንደሌለ ተናግሯል ፤ የኮቪድ-19 ክትባትን ለመዘጋጀት ጊዜ ሊውስድ እንደሚችልም ጠቁሟል።

በርካታ ባለሞያዎች ለዚህ ወረርሽኝ ፍቱን ክትባት አግኝቶ እና አምርቶ ለሰዎች ለማዳረስ ከ12-18 ወራት ሊወስድ እንደሚችል እየተናገሩ ነው።

በአሁን ወቅት በዓለም አቀፍ ደረጃ ከ100 በላይ ኮቪድ-19 #ይከላከላሉ የተባሉ ክትባቶች ሙከራ እየተደረገባቸው ይገኛል።

#TheHill #BBC #nbc
@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot