የቲክቫህ ወጣቶች ጥያቄ፦
ስራ...ስራ...ስራ...ስራ...ስራ...ስራ!
ዩኒቨርሲቲ ጨርሻለሁ ፤ አሁን ድረስ በተማርኩት ትምህርት የስራ እድሎችን ማግኘት አልቻልኩም። አሁን ሀገራችን ላይ ስራ የሚባለውን ነገር እየሞተ ነው። በተለይ በዚህ ዓመት ደግሞ ብሶበታል።
የፖለቲካው ጉዳይ በሚመስል መልኩ የስራ ቅጥር በክልል ከተሞች ላይ አስቸጋሪ እየሆነ መጥቷል። የግል ድርጅቶች እራሱ ሰራተኛ ከመቅጠር ወደመቀነስ እየሄዱ እንዳለ እያየን ነው። የሀገራችን ያለመረጋጋት ሁኔታ፣ የሰላም መደፍረስ፣ የፖለቲካው አለመረጋጋት ትልቅ ተፅእኖ እያሳደረ ነው።
ፖለቲከኞች ለስራ አጥነት፣ለወጣቶች ተጠቃሚነት ሳይሆን ለራሳቸው ጥቅም ብቻ ነው እየሰሩ ያሉት። ፖለቲካው ሙሉ በሙሉ የወጣቱን ጉዳይ፣ የህይወት ማሻሻል ረስቶት በተለያየ ነገር ተጠምዷል። ጭራሽ ስለዚህ ጉዳይ አያነሱም!
ቢያንስ ፖለቲከኞች ይህን ኃላፊነታቸውን ቢወጡ ሰላም እንዲሰፍን ፣ የወጣቶችን ችግር የሚፈታ የስራ ሃሳብ ቢያቀርቡ አሁን ያለው ሁኔታ ይቃለላል። እኛ ስራ መስራት ባለመቻላችን እናዝናለን። ፖለቲከኞች ይህን ጉዳይ የማስተካከል ስራን ቢሰሩ ጥሩ ነው። ሁሉም የሚጮኸው ለራሱ ነው።
ፖለቲከኞች ለወጣቶች የስራ እድል በስፋት እንዲፈጠር የመገፋፋት፣ ወጣቶች እንዲሰሩ፣ የስራ ሃሳቦች በማቅረብ ላይ ቢረባረቡ፣ አሁን ያለውን ነገር ለመቀየር ቢሰሩ መልካም ነው። አሁን ኢትዮጵያ ውስጥ ተዘዋውረን ለመስራት እንኳን ይከብዳል፣ የስራ እድሎችን የተለያዩ ቦታዎች ላይ እንዳንሞክር አስቸጋሪ ነው፤ ከአንዱ ክልል ወደ ሌላው ክልል በነፃነት ለመንቀሳቀስ አስቸጋሪ ነው፤ ከየት ነው የመጣኸው የሚል አካልም ብዙ ነው ይህ ነገር ቢስተካከል ጥሩ ነው።
#TM
መልዕክት መቀበያ : @tikvahethiopiaBot
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia