TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
62.7K photos
1.6K videos
216 files
4.36K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

መረጃ እና መልዕክት ፦ 0919743630

ማርኬቲንግ ፦ 0979222111 ወይም
0979333111

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#Ramaḍān

የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዝዳንት ተቀዳሚ ሙፍቲ ሀጅ ዑመር ኢድሪስ በዚህ ሳምንት የሚጀመረውን የረመዳን ጾም አስመልክተው ጦር ኃይሎች በሚገኘው ቢሯቸው መግለጫ ሰጥተዋል።

ተቀዳሚ ሙፍቲ ሐጅ ኡመር ኢድሪስ በመግለጫቸው መስጅዶች በኮሮና ወረርሽኝ ምክንያት ለምዕመናኑ ዝግ ቢሆኑም ህዝበ ሙስሊሙ ወሩን በተለያዩ የአምልኮ ተግበራት በቤቱ ሆኖ ወደ ፈጣሪው የሚቃረብበት ጊዜ እንዲሆን ጥሪ አቅርበዋል።

በወሩ ውስጥ መልካም ስራዎችን ማብዛትና የተለመደው መደጋገፍ ለኮሮና ቫይረስ በማያጋልጥ መልኩ መፈፀሙ ወቅቱ የሚጠይቀው መንፈሳዊ ተግባር መሆኑንም አስምረውበታል። የረመዳን ጾም ራስን ከመጣው ወረርሽኝ በመጠበቅ የመጣው ፈተና እንዲነሳ ህዝበ ሙስሊሙ አበክሮ እንድጸልይም ጠይቀዋል።

በዚህ የረመዳን ወር ከቤት ውጭ የተለመደው ዓይነት የህብረት ሶላትም ሆነ መሰል የአምልኮ ተግበራት እንደማይኖሩም አመልክተዋል። የዘንድሮው የረመዳን ጾም ጨረቃ ረቡዕ ምሽት ከታየች ሀሙስ እንደሚጀመርና፣ ይህ ካልሆነ ደግሞ አርብ ዕለት እንደሚጀምር ተቀዳሚ ሙፍቲ ሐጂ ዑመር ኢድሪስ አስታውቀዋል።

(EBC)
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia