#Qatar2022
" ለኳታሩ 2022 የዓለም ዋንጫ በዳኝነት እንዳጫውት በፊፋ መመረጤን አላውቅም " - ባምላክ ተሰማ (ለቢቢሲ)
ዓለም አቀፍ ዳኛ ባምላክ ተሰማ "ለኳታሩ 2022 የዓለም ዋንጫ በዳኝነት እንዳጫውት በፊፋ መመረጤን አላውቅም" ሲል ተናግሯል።
ኢንተርናሽናል ዳኛ ባምላክ ለቢቢሲ በሰጠው ቃል ፥ " ምንም ነገር አላውቅም። በይፋ የደረሰኝ ነገር የለም " ብሏል።
ባምላክ ተሰማ በኳታሩ የዓለም ዋንጫ እንዲዳኙ በFIFI ከተመረጡ 8 አፍሪካውያን ዳኞች መካከል አንዱ መሆኑን የምዕራብ አፍሪካ ድረ-ገጾች እና በሀገራችን የተለያዩ ሚዲያዎች ሲዘግቡ ነበር።
" እንደዚህ ዓይነት መረጃ ከየት እንደሚመጣ አላውቅም" ያለው ኢንተርናሽናል አልቢትር ባምላክ ተሰማ ለኳታሩ የዓለም ዋንጫ በፊፋ ስለመመረጡ የወጡ ዘገባዎችን መመልከቱን ግን ተናግሯል።
የተለያዩ ሚዲያዎች ባምላክ ለኳታሩ የዓለም ዋንጫ መመረጡን የዘገቡት ፊፋን ዋቢ አድርገው ሲሆን በፊፋ ይፋዊ ድረ-ገጽ ላይ የተባለ ነገር የለም።
ባምላክ ፊፋ የዓለም ዋንጫን የሚመሩ ዳኞችን ማንነት ይፋ ለማድረግ ጊዜው የፈጠነ ነው ብሎ እንደሚያስብም ለቢቢሲ በሰጠው ቃል ገልጿል።
@tikvahethiopia

በዓለም ዋንጫ ላይ አፍሪካን ወክለው የሚሳተፉ ዳኞች ይፋ ሆኑ።
በኳታር አዘጋጅነት በ 2022 ለሚካሄደው የአለም ዋንጫ ፊፋ 36 ዋና ዳኞችን 69 ረዳት ዳኞችን እና 24 የቫር ዳኞችን ውድድሩን እንዲመሩ መሾሙን አስታውቋል ።
ኢትዮጵያዊው ኢንተርናሽናል ዋና ዳኛ ባምላክ ተሰማ ፊፋ የአለም ዋንጫን እንዲመሩ ከሾማቸው ዳኞች ስም መካከል #አለመካትቱ ታውቋል ።
ፊፋ ለመጀመሪያ ጊዜ በኳታር አዘጋጅነት በሚካሄደው የአለም ዋንጫን ላይ ሶስት ዋና ሴት ዳኞችን እና ሶስት ረዳት ሴት ዳኞችን ውድድሩን እንዲመሩ መምረጡ ተገልጿል ።
የአለም ዋንጫን ለመጀመሪያ ጊዜ እንዲመሩ ከተመረጡ ሶስት ሴት ዳኞች መካከል አንዷ ሩዋንዷዊቷ ሳሊማ ሙካንሳንጋ መሆኗ ተዘግቧል ።
አፍሪካን ወክለው የአለም ዋንጫን እንዲመሩ የተመረጡ ስድስት ዋና ዳኞች ሳሊማ ሙካንሳንጋ ፣ ጃኒ ሲካዝዌ ፣ ባካሪ ጋሳማ ፣ ቪክቶር ጎሜዝ ፣ ማጉዬቴ ኒዳዬ እና ሙስጣፋ ጎርባል መሆናቸው ተነግሯል ።
More : @tikvahethsport