TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.4K photos
1.51K videos
215 files
4.12K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
ፕሮፌሰር መስፍን ወልደማርያም (1922 -2013) - ከዛሬ 91 ዓመት በፊት አዲስ አበባ ከተማ ተወለዱ፣ - የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርታቸውን ተፈሪ መኮንን ትምህርት ቤት ሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን እትጌ መነን ተምረዋል፣ - ከ1955 ዓ.ም ጀምሮ በለንደንና በተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች ከፍተኛ ትምህርት ተከታትለዋል፣ - በአዲስ አበባ ዩንቨርስቲ ውስጥ በጂኦግራፊ ዲፓርትመንት በመምህርነት ና በትምህርት…
#ProfMesfinWoldemariam

መምህር፣ ተመራማሪ፣ የሰብአዊ መብት ተሟጋች እንዲሁም ደራሲ ፕሮፌሰር መስፍን ወልደማርያም በህይወት ዘመን ላበረከቱት አስተዋጽኦ እንዲሁም ራእያቸውን ለማስቀጠል በስማቸው ፋውንዴሽን ተመስርቶላቸዋል።

የፋውንዴሽኑ ዋና የቦርድ ሰብሳቢ ዶክተር በድሉ ዋቅጅራ ፤ ፕሮፌሰር መስፍን የሰብዓዊ መብት ትግል ማዕተም የሆነው ስማቸው እንዳይደበዝዝ በማሰብ ፋውንዴሽኑ ሊቋቋም እንደቻለ አሳውቀወል።

ዶ/ር በድሉ ፥ " ... ይህ የሰብዓዊ መብት መከበር ትግል እንዳይደበዝዝ ፣ እንዳይገፈፍ ለማድረግ ነው። ለወጣቶች እንዲደርስ ፣ በጎልማሶች እንዳይዘነጋ፣ ለእውነት የቆሙ ለጭቆና ያልገበሩ ፣ ግላዊነት ያለጎማቸው ፤ ለምን ? ብለው የሚጠይቁ ሰዎች እስካለን ድረስ መስፍን ወልደማርያም የሰብዓዊ መብት መከበር ፣ የፀረ ጭቆና ግፍ ማህተም ሆኖ ይኖራል" ብለዋል።

የፕሮፌሰር መስፍን ልጅ ዶ/ር መቅደስ መስፍን ፥ ፋውንዴሽኑ እንዲመሰረት፣ የፕሮፌሰር መስፍን ስራ በከንቱ እንዳይቀር ላደረጉ አካላት ምስጋና አቅርበዋል፤ የተመሰረተውን ፋውንዴሽን ወደትልቅ ደረጃ ለማድረስ በመተጋጋገዝ እንደሚሰራም ገልፀዋል።

ፕሮፌሰር መስፍን ወልደማርያም ፋውንዴሽን ከመንግስት ፣ ከማንኛውም ሃይማኖት፣ ከጎሳ እንዲሁም ከማንኛውም አይነት የፖለቲካ አመለካከት ገለልተኛ ሆኖ መቋቋሙን በፋውንዴሽኑ ምስረታ ማብሰሪያ መርሃ ግብር ላይ ተገልጿል።

በሌላ በኩል የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን በአ/አ ዋና መስሪያ ቤት የሚገኘው መሰብሰቢያ አዳራሹን በፕሮፌሰር መስፍን ወልደማርያም ስም እንደሚሰየም የኢሰመኮ ዋና ኮሚሽነር ዶ/ር ዳንኤል በቀለ አሳውቀዋል።

በፕሮፌሰር መስፍን ስም የተሰየመው መሰብሰቢያ አዳራሽ የምርቃት ስነ ስርዓት ወደፊት ይካሄዳል።

Photo Credit : AMN

@tikvahethiopia
#ProfMesfinWoldemariam

የፕሮፌሰር መስፍን ወልደ ማርያም መታሰቢያ እና ዓመታዊ ኮንፈረንስ መስከረም 22 ቀን 2015 ዓ/ም ሊካሄድ ነው።

የፕሮፌሰር መስፍን ወልደ ማርያም ፋውንዴሽን በላከልን መልዕክት ፤ መስከረም 22 ቀን 205፣ ከ7፡30 አንስቶ ለግማሽ ቀን በአዲስ አበባ ዩንቨርስቲ ቢዝነስና ኢኮኖሚክስ ፋካልቲ " እሸቱ ጮሌ አዳራሽ " በርካታ እንግዶች በተገኙበት ታላቅ ጉባዔ ይካሄዳል ብሏል።

" የተመራማሪ፣ መምህር፣ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች፣ ደራሲ፣ የሰላማዊ ትግል አቀንቃኝ እና የፍትሕ ተቆርቋሪ በሆኑት ፕሮፌሰር መስፍን ወልደ ማርያም ስም የተመሰረተው ፋውንዴሽን በሲቪል ማሕበረሰብ ድርጅቶች ባለሥልጣን ተመዝግቦ በሕጋዊ መንገድ እየተንቀሳቀሰ ይገኛል " ሲል ፋውንዴሽኑ አስታውሷል።

የድርጅቱ ዋና ዓላማ ከችግርና ድህነት የተላቀቀች፣ ሰላም የሰፈነባት፣ ሰብዓዊ መብትና የሕግ የበላይነት የሰፈነባት ኢትዮጵያን እውን ማድረግ ነው ብሏል።

ፋውንዴሽኑ ዓላማውን ለማሳካት ከሚያከናውናቸው ተግባራት መካከል አንዱ በሰብዓዊ መብትና ማሕበራዊ ፍትሕ፣ አገራችን ከድህነትና ችጋር ልትላቀቅ ስለምትችልበት መንገዶች፣ ቅራኔን በሰላማዊ መንገድ ስለመፍታት፣ በመስኩ ሰፊ የሆነን ልምድ እና እውቀት ባካባቱ ሰዎች ጥናታዊ ወረቀት በማቅረብ ሰፋ ያለን ውይይት በዓመታዊው ጉባኤ ማካሄድ ዋነኛው ነው ሲል ገልጿል።

@tikvahethiopia