TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.5K photos
1.43K videos
206 files
3.95K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#LemmaMegersa #PP

"...አይሆንም ያልኩበት ምክንያት አንደኛ እኛ የኦሮሞ አመራር አባላት የኦሮሞ ህዝብ አምኖን ያቀረበልን ትላልቅ ጥያቄዎች አሉ፤ እነዚህ ጥያቄዎችን እንመልስላችኃለን ብለን ቃል ገብተናል። ህዝባችን ይህን ጥያቄ ያቀረበልን የትላንቱን #ኦህዴድ ስም ለውጠንለት #ኦዴፓ ካልን በኃላ ነው። ስለዚህ ህዝቡ ጥያቄውን አንድ፣ ሁለት፣ ሶስት ብሎ የሰጠው ለሀገራዊ ፓርቲ ሳይሆን ለኦዴፓ ነው። ስለዚህ የህዝቡን ጥያቄ ሳንመልስ ይህን ማድረግ ትክክል አይደለም፤ እምነት ማጉደል ይሆናል እናም ጥያቄዎቹን ቆጥሮ እንደሰጠን መመለስ አለብን የሚል እምነት አለኝ።" አቶ ለማ መገርሳ

.
.
"...የመደመር ፍልስፍና የምንለው ለውጡ የሚመራበት ፍኖተ ካርታ፤ እይታ ነው። በበፊቱ አግባብ መሄድ አንችልም። ጠንካራ ጎኖችን ከድሮ እናስቀጥላለን። ደካማ ጎኖችን ማረም አለብን። ይሄ ለውጡ በምን አይነት ፍኖተ ካርታ ይመራ የሚል የህዝብም የሊሂቃንም ጥያቄ ነበር። በምንድነው የምንመራው ? ፍኖተ ካርታ የለም የሚል አንድ አመት፣ አንድ አመት ተኩል ይሆናል ለውጡ ከተጀመረ በኃላ፤ የመደመር ዋነኛው አስፈላጊነት ለውጡ በምን ጎዳና ይመራል? ከዴሞክራሲ አኳያ እንዴት ነው የምንመራው? ከሰላም አኳያ እንዴት ነው የምንመራው? ከኢኮኖሚ አኳያ እንዴት ነው የምንመራው? ከፖለቲካ አኳያ ቀጣይ እይታችን፣ ቀጣይ ሃሳባችን ፍኖተ ካርታው ባጠቃላይ ሚመራበት ምንድነው የሚለውን ሚመልስ ነው።" አቶ ፍቃዱ ተሰማ (የብልፅግና ፓርቲ ኦሮሚያ ፅ/ቤት ኃላፊ)

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot
#PP

ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ የሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ስብሰባ መጀመሩን ገለፁ።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ሚዲያ ገፃቸው፥ "አያሌ ወሳኝ ጉዳዮች ላይ አተኩሮ የሚከናወነው የሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴያችን ስብሰባ ዛሬ ተጀምሯል" ብለዋል።

@tikvahethiopia
#PP

የገዢው ብልፅግና ፓርቲ የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ በአሁን ሰዓት ስብሰባውን እያካሄደ ነው።

ስብሰባው በዐበይት ሀገራዊ ጉዳዮችና በልዩ ልዩ የፓርቲ አጀንዳዎች ላይ እንደሚወያይ የፓርቲው ፕሬዝዳንት እና የኢትዮጵያ ጠ/ሚር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ላይ ገልፀዋል።

@tikvahethiopia
" ከሶማሊያ ጋር የመዋጋት ፣ የመጣላት ፍፁም ፍላጎት የለንም " - ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ

ኢትዮጵያ ከሶማሊያ ጋር #የመዋጋትም ሆነ የመጣላት ፍላጎት እንደሌላት የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር እና የብልፅግና ፓርቲ ፕሬዝዳንት ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ተናገሩ።

ዶ/ር ዐቢይ ይህን ያሉት ለፓርቲያቸው ማዕከላዊ ኮሚቴ ባቀረቡት ገለፃ ነው።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ፤ " የምንከተለው የዲፕሎማሲ ጉዟችን ክብርንና ጥቅምን ማስከበር ላይ ያተኮረ ነው። " ብለዋል።

" ሶማሊያ ከማንም በላይ የኢትዮጵያ ወንድም ዘመድ ጎረቤት ናት፤ ባለፉት 10 ዓመታት በሺሕ የሚቆጠሩ ኢትዮጵያዊያን በሶማሊያ ውስጥ የሶማሊያ ሰላም ለማስከበር የህይወት ዋጋ ከፍለዋል። " ሲሉ ገልጸዋል።

" ማንም ሀገር በዓለም ላይ ኢትዮጵያ የከፈለችውን ያህል የከፈለ የለም " ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ፤ " አግዛለው ብሎ መፎከርና ሄዶ መሞት ይለያያል " ብለዋል።

" ኢትዮጵያ ከሶማሊያ ህዝብና መንግስት ጋር ለመጣላት ለመዋጋት ፍጹም ፍላጎት የላትም " ሲሉም ተደምጠዋል።

" አሁን በኢትዮጵያ ያለው መንግስት በሶማሊያ አንድነት የሚታማ መንግስት አይደለም " ያሉት ዶ/ር ዐቢይ ፤ " ለመጀመሪያ ጊዜ በኢትዮጵያ ታሪክ ሶማሊያዊያን አንድ እንዲሆኑ በንግግር ሳይሆን በተግባር የሰራ መንግስት ነው " ብለዋል።

" ከልባችን አንድ እንዲሆኑ ስለምንፈልግ የቀድሞው ፕሬዜዳንት ፈርማጆ ስልጣን ላይ እያሉ ከሱማሌላንድ ፕሬዜዳንት ቢሂ ጋር ኢትዮጵያ፣ ጅቡቲ ለማገናኘት በተደረገ መኩራ እንዲገናኙ አድርገን ውይይት ተደርጓል ፤ ሶማሊያ እና ኬንያ በድንበር ጉዳይ ሲጣሉ አለም ሲንጫጫ ፕሬዜዳንት ፈርማጆን ኬንያ ወስደን ከወንድማቸው ከፕሬዜዳንት ኡሁሩ ጋር እንዲነጋገሩ ጥረት አድርገናል፤ ለምን ? የነሱ ሰላም የኛ ስለሆነ " ሲሉ አስረድተዋል።

" ሶማሊያ እንደ ግጭት ሰፈር አድርጎ የመጠቀም ፍላጎት ከብዙ ኃይሎች ይነሳል፤ እኛ ለዓለም ህዝብ የቀይ ባሕር 'አክሰስ' ጥያቄያችን ህጋዊ መሆኑን አሳይተናል። ዓለም በሙሉ ይገባቸዋልኮ ግን፣ ግን ነው የሚለው ፤ የኛ ፍላጎት ባሕርን አክሰስ ማድረግ ብቻ ነው " ሲሉ ገልጸዋል።

" ከኢትዮጵያ መውሰድ ሲሆን ችግር የለውም፤ ለኢትዮጵያ መስጠት ነው ነውሩ ፤ ዲፕሎማሲያችን እንደዚያ ነው፤ አሁን መልኩን እየቀየረ ነው " ብለዋል።

" በእኛ እና ሶማሊያ መካከል ችግር ይፈጠራል ብዬ ባላስብም " ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ፤ " በሕዝቦች መካከል ጥላቻ እንዳይፈጠር ቁርሾ እንዳይፈጠር በተረጋጋና በሰከነ መንገድ ውጫዊ አክተር በሚያሰክን መንገድ መምራት ይጠይቃል " ሲሉ ተናግረዋል። #PP

@tikvahethiopia