#DrAbiyAhmed
የጀርመኗ መራሒተ መንግሥት አንጌላ ሜርክል ዛሬ ከሰዓቱን በጠሩት የጂ-20 ኮምፓክት ዊዝ አፍሪካ የተሰኘ ጉባዔ ላይ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በበይነ መረብ በመታገዝ ተሳትፈዋል።
“ለንግድ እና ለኢንቨስትመንት ማሕቀፋዊ ሁኔታዎች” በሚል ርዕስ የሚካሄደው ጉባዔ የስምምነቱ ፈራሚ የሆኑ ሀገራት ተጨማሪ የንግድ እና የኢንቨስትመንት ዕድሎችን እንዲያገኙ በሚያስችል ሁኔታ ማሕቀፋዊ ሁኔታዎችን ወደ ቀጣይ ርምጃዎች ለመውሰድ የታለመ ነው።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ባደረጉት ንግግር፣ ለሙዐለ ነዋይ ፍሰት ምቹ ነባራዊ ሁኔታ እንዲኖር ለማስቻል በኢትዮጵያ የሀገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያ አማካኝነት ማክሮ ኢኮኖሚያ፣ መዋቅር እና የዘርፍ ማሻሻያዎች መደረጋቸውን ገልጸዋል።
#PMofficeEthiopia
@tikvahethiopia

#Senegal
የኢትዮጵያ ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ለአንድ ቀን የስራ ጉብኝት ሴኔጋል፤ ዳካር ገቡ።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በሴኔጋል ቆይታቸው ከሴኔጋል ፕሬዚዳንት ማኪ ሳል ጋር የሁለትዮሽ ጉዳዮችና አህጉራዊ ጉዳዮች ላይ ምክክር ያደርጋሉ ተብሎ ይጠበቃል።

ሹመት !
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር) ለከፍተኛ የመንግስት ሃላፊነት ቦታዎች ሹመቶች ሠጡ::
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር) በዛሬው እለት አቶ ተፈሪ ፍቅሬን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት ሃላፊ እና የካቢኔ ጉዳዮች ሚኒስትር አድርገው በድጋሚ የሾሙ ሲሆን ለ4 ከፍተኛ የሃላፊነት መደቦችም በሚኒስቴር ማእረግ የሚከተሉትን ሹመቶች ሰጥተዋል፡-
1. አቶ አደም ፋራህ - በሚኒስትር ማዕረግ የዲሞክራሲ ስርዓት ግንባታ ማስተባበሪያ ማዕከል ዋና አስተባባሪ
2. አቶ ተስፋዬ ቤልጅጌ - በሚኒስትር ማዕረግ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የመንግስት ተጠሪ
3. ዶ/ር ስለሺ በቀለ - በሚኒስትር ማዕረግ የድንበር ተሻጋሪ ወንዞችና የህዳሴ ግድብ ዋና ተደራዳሪና አማካሪ
4. ዶ/ር ለገሰ ቱሉ - በሚኒስትር ማዕረግ የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ኃላፊ
በተጨማሪም ፦
- ዶ/ር ምህረት ደበበ - የአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ ፕሬዚዳንት፤
- አቶ ፍሰሃ ይታገሱ - የኢትዮጵያ ብሮድካስት ኮርፖሬሽን ዋና ሥራ አስፈፃሚ፤
- እንዲሁም አቶ አብዱራህማን ሩቤ - የኢትዮጵያ ብሮድካስት ኮርፖሬሽን ምክትል ዋና ሥራ አስፈፃሚ ሆነው ተሹመዋል፡፡
#PMOfficeEthiopia

👍2❤1🙏1
#Update
በኢትዮጵያ የመጀመሪያ የሆነው የፊልድ ማርሻል ወታደራዊ ማዕረግ ለጀነራል ብርሃኑ ጁላ ተሰጠ።
በተጨማሪ ፦
• 4 ሌትናል ጀነራሎች ወደ ሙሉ ጀነራልነት፣
• 14 ሜጀር ጀነራሎች ወደ ሌትናል ጀነራልነት፣
• 24 ብርጋዴር ጀነራሎች ወደ ሜጀር ጀነራልነት፣
• 58 ኮሎኔሎች ወደ ብርጋዴር ጀነራልነት በአጠቃላይ 100 ከፍተኛ የጦር አመራሮች እድገት ተሰጥቷል።
ሹመቱ በጦር ሀይሎች ጠቅላይ አዛዥ ዶክተር ዐቢይ አህመድ አቅራቢነት በኢፌዴሪ ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ በኩል ነው የተሰጠው።
የማዕረግ እድገት ያገኙ ከፍተኛ መኮንኖች ሙሉ ዝርዝር : https://telegra.ph/Tikvah-01-08

👎2.28K👍2.13K❤241😁134🔥62🎉62🤩50😱40😢39
#ETHIOPIA🇪🇹 #UAE🇦🇪
ዛሬ የኢትዮጵያ አየር ኃይል እና የተባበሩት አረብ ኤሜሬትስ (UAE) አየር ኃይል አባላት በጋራ ሆነው " ጥቁር አንበሳ " የተሰኘ የአየር ላይ ወታደራዊ ትርዒት አቀረቡ።
ትርዒቱን ያቀረቡት የኢትዮጵያ አየር ኃይል 88ኛ ዓመት የምስረታ በዓልን ምክንያት በማድረግ በቢሾፍቱ ከተማ በተካሄደ ስነስርዓት ላይ ነው።
በስነሥርዓቱ ላይ የተገኙት የኢፌዴሪ ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ፤ " በኢትዮጵያና በተባበሩት ዓረብ ኤምሬቶች አየር ኃይሎች በጋራ የቀረበው ወታደራዊ የአየር ላይ ትርዒት በትብብር ከሠራን የምንደርስበትን ደረጃ ያሳየ ነው " ብለዋል።
የኢትዮጵያ አየር ኃይል ዋና አዛዥ ሌተናል ጄኔራል ይልማ መርዳሳ በበኩላቸው የአየር ትርዒቱ ኢትዮጵያና የተባበሩት አረብ ኢማራት በፖለቲካው እና በውትድርናው መስክ ያላቸውን መልካም ግንኙነት፣ ወዳጅነትና ትብብር ያሳየ ነው ሲሉ ገልጸዋል።
የኢትዮጵያ አየር ኃይል ከተመሰረተ 88ኛ አመቱን የያዘ ሲሆን ካለፈው ህዳር 20 ጀምሮ የምስረታ በዓሉ እየተከበረ ነው።
Photo Credit - #PMOfficeEthiopia

😡1.28K❤546👏131😭62🙏44🕊30😱29🥰14😢13
TIKVAH-ETHIOPIA
" የባህር በር ጥያቄን ማንሳት ነውርነቱ አቁሟል " - ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ኢትዮጵያ ለቀይ ባህር ስትል ኤርትራን የመውረር ፍላጎት እንደሌላት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለጹ፡፡ " የኢትዮጵያ ፍላጎት እንነጋገር፣ ሰጥቶ በመቀበል መርህ፣ ህዝቦች በሚጠቀሙበት መርህ እንወያይ የሚል ነው " ብለዋል። " የኤርትራ ህዝብ የሚያስፈልገው ልማት ነው፣ ተባብረን መልማትና መስራት እንጂ…
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ስለ ፕሪቶሪያ ስምምነት ምን አሉ ?
" ስራዎች ተገምግመው የግለሰቦች መቀያየር ሊኖር ይችላል " - ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ፦
" የፕሪቶሪያው ስምምነት መሰረተ ልማቶችን በመመለስ የትግራይ ህዝብ አገልግሎት እንዲያገኝ አድርጓል ፤ ያም ሆኖ አሁንም በበቂ ሁኔታ ያልተፈጸሙ ጉዳዮች አሉ።
ከዚህም አንደኛው የታጣቂዎች ተሃድሶ (ዲዲአር) ስራ ነው። ይህ በዋናነት የሚጎዳው የትግራይ ህዝብን ነው። ወጣቶች በታጣቂ ስም ከመቀመጥ ወደ ልማት መሰማራት አለባቸው። በየወሩ ለልማት መዋል የነበረበት በቢሊዮን የሚቆጠር ገንዘብ ለዚህ ስራ ይወጣል።
ተፈናቃዮችን ወደ ቀያቸው በመመለስ ረገድም በራያና ጸለምት ጥሩ ስራ ተከናውኗል። በሌሎች አከባቢዎች ግን በተፈለገው ልክ አልሆነም። ይህ የሆነውም ሰብዓዊ ስራ እና ፖለቲካ የሚቀላቅሉ ኃይሎች በመኖራቸው ነው።
ነገር ግን የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ባለፉት ሁለት ዓመታት ተጨማሪ ጦርነትን በማስቀረት ረገድ ከፍተኛ ስራ አከናውነዋል። ጊዜያዊ አስተዳደሩ የተሰጠው የሁለት ዓመት ጊዜ በማለቁ የህግ ማሻሻያ የሚፈልግ ጉዳይ አለ። ህግ ሲሻሻል ደግሞ የነበሩ አፈጻጸሞች መገምገም አለባቸው።
በዚህም የፕሪቶሪያውን ስምምነት ባከበረ መልኩ መጠነኛ ለውጥ ከተካሄደ በኋላ ጊዜያዊ አስተዳደሩ ስራውን እያከናወነ ህዝቡን ለምርጫ የሚያዘጋጅ ይሆናል።
ይህን በተመለከተም ከጊዜያዊ አስተዳደሩ አመራሮችና ሌሎች ባለድርሻ አካላት ጋር ውይይቶች እየተደረጉ ነው። በዚህ ሂደት ስራዎች ተገምግመው የግለሰቦች መቀያየር ሊኖር ይችላል። "

❤620😡265🕊103🤔40😭38💔15👏14🙏11🥰9😱9😢3