TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.3K photos
1.51K videos
211 files
4.1K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
" የማህበራዊ ሚዲያው ከዚህ በፊት ታይቶ በማይታወቅ ሁኔታ ተደራሽነትን እና ፍጥነትን በመስጠት ለጥላቻ ንግግር ምቹ ሜዳ ሆኗል " - ቮልከር ተርክ ነገ እሁድ ሰኔ 11 / June 18 የዓለም አቀፍ የጸረ-ጥላቻ ንግግር መከላከል ቀን ይከበራል። ቀኑን አስመልክቶ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት (UN) የጥላቻ ንግግርና አደገኛ መልዕክቶችን " ሰፊ ስርጭት " መከላከልን ጨምሮ ለመቆጣጠር የተቀናጀ ዓለም…
#NoToHate

ዛሬ እሁድ ሰኔ 11 / June 18 በዓለም አቀፍ ደረጃ  የጸረ-ጥላቻ ንግግር መከላከል ቀን እየተከበረ ይገኛል።

በተለይም በሀገራችን የማህበራዊ ሚዲያዎች በፖለቲከኞች ፣ በታዋቂ ግለሰቦች፣ በጋዜጠኞች፣ በሌሎችም የማህበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚዎች የሚነገሩ የጥላቻ ንግግሮች ግጭቶች እንዲባባሱ  ፣ ሰዎች በማንነታቸው እንዲጠቁ፣ እንዲፈናቀሉ፣ እንዲሰደዱ አስተዋጽኦ አድርጓል።

ከምንም በላይ የጥላቻ ንግግሮች በሌሎች በግለሰቦች ላይ ጥላቻ እንዲሰርፅ፣ ቂም እና በቀል እንዲያድር  እንዲሁም የማህበራዊ ህይወት ላይ መሸርሸር እንዲመጣ አድርጓል።

እንደ አንደ ሀገር ዜጋ በማንኛውም ጉዳይ ሀሳባችንን ስንገልፅ ከጥላቻ ቃላት በራቀ፣ በፍቅር፣ ለመግባባት፣ ለመተማመን በሚያግዙ ቃላት ሊሆን ይገባል።

ሁሉም ሰው የእኛን አይነት አመለካከት እንደሌለው በመገንዘብ አንድን ሀሳብ ስንቃወም ወይም በጉዳዩ ላይ ሀሳብ ስንጠት ከጥላቻ በራቀ ሁኔታ መሆን አለበት። ይህን ስናደርግ አንድነት ይጠነክራል፣ የጋራ ችግሮች መፍትሄ ያገኛሉ፣ ሀገራዊ ፍቅር ይዳብራል፣ የማንግባባቸው ጉዳዮችን እየቀነሱ ይመጣሉ።

እያንዳንዳችን የጥላቻ ንግግሮችን ለመከላከል እንችላለን ፦

💗 የመቻቻል መልዕክቶችን በማካፈል የጥላቻ ንግግሮችን እንዋጋ።

💗በጥላቻ ንግግር የተጎዱ ሰዎችን እንደግፍ።

💗 በማህበራዊ ሚዲያ ላይ የጥላቻ ንግግር ስንመለከት ሪፖርት እናድርግ።

ውድ ቤተሰቦቻችን ከጥላቻ ንግግር ጋር በተያያዘ እናተ ላይ ወይም ቤተሰቦቻችሁ ላይ የደረሰባችሁ ነገር ካለ ፤ ወይም በማህበራዊ ሚዲያ የምትታዘቡትን በ @tikvah_eth_BOT ላይ አጋሩን

የጥላቻ ንግግር ፦ ማለት የግhሰቦች ወይም የቡድኖች ሀይማኖት ፣ ብሔር ፣ ዘር ወይም አካላዊ ሁኔታ ላይ ያነጣጠረ የጥቃት ንግግር ወይም የሚዲያ ውጤት ነው ፤ ይህም በሁለት ግለሰቦች መካከል ካለ የቃላት ልውውጥ ጀምሮ በትልልቅ መገናኛ ብዙሃ እስከሚሰራጭ ይዘት ሊዘልቅ ይችላል።

የጥላቻ ንግግር ይገድላል ፤ ከጥላቻ ንግግር እንቆጠብ !
@tikvahethiopia