#AddisAbaba
የግብረ-ስጋ ግንኙነት እንዲፈፅሙ ጠይቋት ፈቃደኛ ባለመሆኗ ሟችን በቢላዋ ወግቶ የገደለው ተከሳሽ በ23 ዓመት ፅኑ እስራት ተቀጣ።
ዳንኤል በርሄ ስዩም የተባለ ተከሳሽ ሀምሌ 15 ቀን 2014 ዓ.ም ከጠዋቱ በግምት 3፡30 ሲሆን በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ወረዳ 06 ሳሪስ አደይ አበባ መኪና መሻገሪያ ድልድይ አካባቢ በሚገኘው ፍሬሕይወት ህንፃ ውስጥ ሟችን የሽንት ቤት ቁልፍ ክፈችልኝ ብሏት ስትከፍትለት የግብረ-ስጋ ግንኙነት እንዲፈፅሙ ጠይቋት ፈቃደኛ ባለመሆንዋ አንገትዋን በቢላ በመውጋት ሕይወትዋ እንዲያልፍ አድርጓል፡፡
በዚህም ምክንያት በአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ምርመራ ተጣርቶ በሴቶችና ህጻናት ላይ የሚፈፀሙ ወንጀሎች ዐቃቤ ሕግ ዳይሬክቶሬት በወ/ሕ/አ 539/1/ሀ መሰረት በፌዴራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ልደታ ምድብ 1ኛ የሰው ግድያና ከባድ ውንብድና ወንጀል ችሎት ክስ ቀርቦበት ክርክር ሲደረግ ቆይቷል፡፡
በክርክሩ ሂደትም የዐቃቤ ሕግ ማስረጃ ከተሰማ በኋላ ተከሳሽ እንዲከላከል ብይን ተሰጥቶ ተከሳሽ የመከላከያ ምስክሮች በማስረጃነት አቅርቦ ያሰማ ቢሆንም በዐቃቤ ሕግ የቀረበበትን ክስ መከላከል ባለመቻሉ ምክንያት ፍርድ ቤቱ በተከሳሽ ላይ የጥፋተኛነት ፍርድ በመስጠት ተከሳሽ በ23 ዓመት ፅኑ እስራት እንዲቀጣ ሲል ወስኗል፡፡
#MinistryofJustice
@tikvahethiopia

😭636😡193❤66🙏35😢24😱15🕊14🥰9
TIKVAH-ETHIOPIA
#ኢትዮጵያ በወንጀል የተገኘ ንብረት ሕጋዊ ማስመሰል እና ሽብርተኝነትን በገንዘብ መርዳትን የሚመረምር ሰው፤ በምርመራ ወቅት ከአቅሙ በላይ በሆነ ምክንያት ከ #ግድያ ውጪ የትኛውንም ዓይነት ወንጀል ቢፈጽም ተጠያቂ የማያደርግ አዋጅ ጸደቀ፡፡ በወንጀል የተገኘ ንብረት ሕጋዊ ማስመሰል እና ሽብርተኝነትን በገንዘብ መርዳት ወንጀልን ለመከላከልና ለመቆጣጠር የወጣው አዋጅ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጸድቋል፡፡…
አዋጅ ቁጥር 1387/2017
በወንጀል ድርጊት የተገኘ ንብረት ወይም ገንዘብ ሕጋዊ አስመስሎ ማቅረብንና ሽብርተኝነትን በገንዘብ መርዳትን ለመቆጣጠርና ለመከላከል የወጣው አዋጅ ቁጥር 780/2005 ‘ን ለማሻሻል የወጣው ሰሞኑም የፀደቀውን አዋጅ ቁጥር 1387/2017ን በተመለከተ የፋይናንስ ደህንነት አገልግሎት ምን አለ ?
" ኢትዮጵያ በወንጀል ድርጊት የተገኘ ንብረትን ህጋዊ አስመስሎ ማቅረብ እና ሽብርተኝነትን በገንዘብ የመርዳት ወንጀልን ለመቆጣጠር ተቋም ያቋቋመችው በ2002 ዓ.ም ነው።
በዚህም የፋይናንስ ደህንነት አገልግሎት ተቋቁሟል፤ ተልዕኮው ደግሞ ሀገራችን የአለም አቀፍ የፋይናንስ ድርጊት ግብረሃይል የሚባለው ምከረሃሳብን መተግበር ከሚጠበቅባቸው ከ200 በላይ ሀገራት አንዷ በመሆኗ ነው።
የፋይናንስ ድርጊት ግብረሃይል 40 ቀጥታ አባል አገራት አሉት፡፡ እንዲሁም ደግሞ ዘጠኝ ቀጠናዊ አባል ሀገሮች አሉ።
ከአፍሪካም ሶስት የምስራቅ እና ደቡቡን የሚያካትተው 21 አባል ሀገሮችን የያዘው የምስራቅ እና ደቡብ አፍሪካን የያዘው ኢስተርን ኤንድ ሶውዘርን አፍሪካ አንቲ ላውንድሪ ግሩፕ (eastern and southern africa anti money laundry group) ይባላል፡፡
ኢትዮጵያም ከ21 አባል ሀገራት አንዷ ናት።
እነዚህ አባል ሀገራት የፋይናንስ ድርጊት ግብረሃይል ሽብርተኝነትን በገንዘብ የመርዳት ወንጀልን ለመከላከል የሚያስችሉ 40 ምክረ ሃሳቦችን ይተገብራሉ፤ በየአምስት ዓመቱም የእርስ በእርስ ግምገማ ያካሂዳሉ ያሉት ሶስተኛውም ገምገማ በመጪው ዓመት ይካሄዳል።
እነዚህን ምከረ ሃሳቦች ተግበባራዊ ከምናደርግባቸው ህጎች አንዱ ባለፈው የተሸሻለው በወንጀል የተገኘ ንብረት ሕጋዊ ማስመሰል እና ሽብርተኝነትን በገንዘብ መርዳት ወንጀልን ለመከላከልና ለመቆጣጠር የወጣው አዋጅ ነው።
የተሸሻለው አዋጅ ኢትዮጵያ ለ12 ዓመታት ስተገለገልበት ቆይታለች። የተሸሻለበት ምክንያት ደግሞ አለም አቀፉ የፋይናንስ ድርጊት ግብረሃይል ምክረሃ ሃሰቦቹን እያሻሻለ በመሄዱ ነው።
በዚህም የተሸሻሉ ምከረ ሃሳቦች ስላሉ እነሱን ሊመልስ የሚችል ህግ በማስፈለጉ እና ግብረ ሃይሉም ወንጀሎች እየተለዋወጡ ስለመጡ ሀገራት እነሱን ለመከላከል የሚመጥን የህግ ማዕቀፍ እንዲኖራቸው ስለሚያዝ ነዉ።
የቀድሞው አዋጅ አመንጪ ወንጀሎችን በዝርዝር አያስቀምጥም ይህም አንዱ የአዋጁ ችግር ነበር " ብሏል።
#MinistryofJustice #FinancialIntelligenceService #ShegerFM

❤519😡126🤔13😭11🙏9🕊8👏6😱5😢4💔4🥰2
TIKVAH-ETHIOPIA
አዋጅ ቁጥር 1387/2017 በወንጀል ድርጊት የተገኘ ንብረት ወይም ገንዘብ ሕጋዊ አስመስሎ ማቅረብንና ሽብርተኝነትን በገንዘብ መርዳትን ለመቆጣጠርና ለመከላከል የወጣው አዋጅ ቁጥር 780/2005 ‘ን ለማሻሻል የወጣው ሰሞኑም የፀደቀውን አዋጅ ቁጥር 1387/2017ን በተመለከተ የፋይናንስ ደህንነት አገልግሎት ምን አለ ? " ኢትዮጵያ በወንጀል ድርጊት የተገኘ ንብረትን ህጋዊ አስመስሎ ማቅረብ እና ሽብርተኝነትን…
#UndercoverInvestigation
" ከፍርድ ቤት ፍቃድ ውጪ የሚደረግ ምርመራን አዋጁ አይፈቅድም " - የፍትሕ ሚኒስቴር
የፍትሕ ሚኒስቴር ፤ በወንጀል የተገኘ ንብረት ህጋዊ ማስመሰል እና ሽብርተኝነትን በገንዘብ መርዳት ወንጀልን ለመከላከልና ለመቆጣጠር የወጣው አዋጅ ከፍርድ ቤት ፍቃድ ውጪ የሚደረግ ምርመራን እንደማይፈቅድ አሳውቋል።
ሚኒስቴሩ ሰሞኑን በፓላማው የፀደቀውን የተሻሻለ አዋጅ በተመለከተ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥቶ ነበር።
በዚህም " አዋጁን አንዳንዶች የተረዱበት መንገድ ልክ አይደለም " ብሏል፡፡
የፍትሕ ሚኒስቴር ምን አለ ?
" አዲሱ አዋጅ ከመደበኛ የወንጀል መርመራ ሂደት የወጣ መንገድን የሚከተል እንደሆነ ሰው ሊረዳው ይገባል።
አዲሱ አዋጅ ልክ በመደበኛው የምርመራ ሂደት እንደሚደረገው ተጠርጣሪዎችን በፍርድ ቤት መያዣ መያዝ ፣ ሰነዶችን ማሰባሰብ፣ ምስከሮችን መስማት እና መሰል ሂደቶችን አይከተልም።
አዋጁ ወስብስብ የሆኑ ወንጀሎችን ከመሰረቱ ለመለየት የሚስችል የምርመራ ሂደትን የሚከተል ነው።
ለምሳሌም፦ መርማሪው አካል ወንጀለኞችን መስሎ ተቀላቅሎ ወይንም አብሮ በመስራት፣ ተባባሪ መስሎ አብሮ ውሎ በማደር፣ ሲሸጡ ገዢ መስሎ ፣ ሲገዙ ሻጭ መስሎ ሊሆን ይችላል።
ምርመራውን የሚየካሂደው አካል ምረመራ ማድረግ የሚችለው የፍርድ ቤት ተዕዛዝ ካገኘ ብቻ ነው።
ፍርድ ቤት በሽፋን ስር የሚደረግ ምርመራ ተግባራዊ እንዲደረግ በአሳማኝ ምክንያት ሲፈቅድ ምርመራው የሚፈጸምበትን ዘዴ ፣ የአተገባበር ሁኔታ ፣ የሚከናወንበትን ጊዜ በትዕዛዙ ላይ በግልጽ ማስቀመጥ እንዳለበት አዋጁ ደንግጓል።
እንደሚባለው አዋጁ ተጠርጣሪን አስሮ እያሰቃዩ አይመረምርም ይህም ፍጹም ስህተት ነው። በማስገደድ ማስረጃ የሚሰበሰብበትም አይደለም።
መርማሪው ፍርድ ቤት አሳማኝ ምክንያት ሲፈቅድለት በሽፋን ስር የሚደረግ ልዩ የምርመራ ዘዴን ይተገብራል ሲባል በተጠርጣሪዎች ወይም በሌላ ሦስተኛ ወገኖች ላይ ወንጀል ሊፈጽምባቸው ይችላል፤ ወንጀሉን ከፈጸመባቸው በኋላ በወንጀል አይጠየቅም የሚል አይደለም።
ከተጠርጣሪዎች ጋር የወንጀል ተካፋይ ወይም ግብረ-አበር በመሆን በራሱ ፈቃድ አስቦና ፈቅዶ ሳይሆን ፦
- ያለፈቃዱ፣
- ተገዶ፣
- በተጽእኖ፣
- በተጠርጣሪዎች ሕገ ወጥ ትዕዛዝ ወይም ከአቅሙ በላይ በሆነ ማንኛውንም ምክንያት ሌላ ከባድ ጉዳትን ለማስቀረት ወይም የተሰጠውን ሕጋዊ ተልእኮ ለማሳካት ሲል ወንጀል የሚፈጽምበት ሁኔታ ሲኖር ከወንጀል ክስ #ነጻ የሚደረግበትን ሁኔታ ለማመላከት የተደነገገ ድንጋጌ መሆኑን መገንዘብ ያስፈልጋል። " ብሏል።
በወንጀል የተገኘ ንብረት ሕጋዊ ማስመሰል እና ሽብርተኝነትን በገንዘብ መርዳትን የሚመረምር ሰው፤ በምርመራ ወቅት ከአቅሙ በላይ በሆነ ምክንያት ከግድያ ውጪ የትኛውንም ዓይነት ወንጀል ቢፈጽም ተጠያቂ የማያደርግ አዋጅ ከሰሞኑ መፅደቁ ይታወሳል፡፡
ይህም መርማሪዎችን ወንጀል እንዲፈፅሙ በር ይከፍታል በሚል ከምክር ቤት ትችት ሲቀርብበት ነበር።

❤1.16K😡270🙏62🤔51😭31😢20🕊20💔19👏17😱4🥰2