TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
205 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#MinistryOfHealthEthiopia

ጤና ባለሙያዎች ከምረቃ በኋላ የሙያ ፍቃድ ከማግኘታቸው አስቀድሞ የሙያ ብቃት ማረጋገጫ ፈተና እንዲፈተኑ የሚያስችል ስራ እየተሰራ ነው ተብሏል።

ይህ የተባለው የኢፌዴሪ ጤና ሚኒስቴር በአገሪቱ ውስጥ ካሉ የጤና ሙያ ማህበራት ጋር ባካሄደው ምክክር ላይ ነው።

በመድረኩ ላይ ከሙያ እድሳት ጋር በተያያዘ ከዚህ ቀደም ማንኛውም የጤና ባለሙያ በሙያው ሲያገለግል ቆይቶ ጊዜው ሲደርስ እድሳቱን እንደሚከውን ተጠቁሟል፡፡

አሁን ላይ አንድ ባለሙያ እድሳት ለመፈጸም የተለያዩ የሙያ ማጎልበቻ ስልጠናዎችን ለመውሰድ እንደሚገደድና በቂ ስልጠና ጊዜን ማሳለፉም መረጋገጥ እንዳለበት ተገልጿል፡፡

ሚኒስቴሩ በአሁኑ ግዜ ተመርቀው ስራ እያጡ ያሉ የጤና ባለሙያዎች ቁጥር እየጨመረ መምጣቱንና በዚህም ላይ ከጤና ሙያ ማህበራቱ ጋር መፍትሄ ለማምጣት እየተሰራ መሆኑን ጨምሮ አመልክቷል፡፡

ምንጭ፦ ኢቢኤስ ቴሌቪዥን
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia