TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
62.9K photos
1.61K videos
216 files
4.37K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

መረጃ እና መልዕክት ፦ 0919743630

ማርኬቲንግ ፦ 0979222111 ወይም
0979333111

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#LteAdvanced

ኢትዮ ቴሌኮም የLte advance 4G አገልግሎት በአዲስ አበባ በይፋ መጀመሩን አስታውቋል። የ4G ኔትወርክ አገልግሎት ማብሰሪያ ፕሮግራም በአዲስ አበባ በመካሄድ ላይ ነው። የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ስራ አስፈፃሚ ወ/ት ፍሬህይወት በማስጀመሪያ ፕሮግራሙ ላይ እንዳሉት በጣም ፈጣን የኢንተርኔት አገልግሎት ልታገኙ ስለሆነ እንኳን ደስ ያላችሁ ብለዋል።

የዚህ ኔትወርክ ማስፋፊያ ግንባታ የቻይናው ሁዋዌ ኩባንያ የተከናወነ ሲሆን ይህ ግንባታ 170 ሚሊዮን ብር እንደፈጀ ተገልጿል። ወይዘሪት ፍሬህይወት እንደገለጹት የደንበኞች እየጨመረ ያለ ፍላጎት ለዚህ እንዳበቃቸው ገልጸው በቀጣይ ከፍተኛ የኢንተርኔት ፍላጎት ያላቸውን የኢትዮጵያ ከተሞች በጥናት እየለየን Lte Advance 4G ተግባራዊ እናደርጋለን ብለዋል።

ይሄ የኔትወርክ ማስፋፊያ ያለምንም ዕዳ በመንግስት ወጪ የተገነባ ሲሆን አገልግሎቱ ከዛሬ በመላ አዲስ አበባ አገልግሎት ይጀምራል። ይህ የ4G Lte አገልግሎት በ 50 የተመረጡ የመዲናዋ ቦታዎች ላይ የሙከራ አገልግሎት ሲሰጥ የቆየ ሲሆን ከዚህ በኋላ አገልግሎት የሚሰጠውም የኢንተርኔት ፍላጎት ከፍተኛ በሆኑባቸው አካባቢዎች ብቻ ነው ተብሏል። አዲሱ አገልግሎት በአንዳንድ አፕሊኬሽኖች ላይ፣ advanced Lte ከ4G አራት ዕጥፍ ከ 3G ደግሞ 14 ዕጥፍ እንደሚፈጥን ወይዘሪት ፍሬህይወት ተናግረዋል።

[ETHIO FM 107.8]
@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot