TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
62.7K photos
1.6K videos
216 files
4.36K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

መረጃ እና መልዕክት ፦ 0919743630

ማርኬቲንግ ፦ 0979222111 ወይም
0979333111

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#KulubiGabriel

የም/ሐረርጌ ዞን ፖሊስ ሰኞ በሚከበረው የቁልቢ ገብርኤል ንግሥ በዓል ላይ የሚገኙ ምእመናንን ደህንነት ለመጠበቅ እና በዓሉ በሰላም እንዲጠናቀቅ ለማድረግ ዝግጅት መደረጉን አስታውቋል።

በበዓሉ የሚታደሙ ምእመናን የአፍ እና የአፍንጫ መሸፈኛ ጭንብል (ማስክ) ማድረግ እንደሚጠበቅባቸው ማሳሰቢያ ተሰጥቷል።

ከድሬዳዋ አስተዳደር ፣ ከሐረሪ ክልል ፣ ከፌዴራል ፖሊስ እና ከመከላከያ ሠራዊት እንዲሁም ከሚሊሺያ እና የመረጃ ደህንነት ኃላፊዎች ጋር ውይይት ተደርጎ የሰላም ማስከበሩን ሥራ በቅንጅት ለመሥራት ዝግጅት መደረጉም ተነግሯል።

በሜታ ወረዳ ሰላማ ቀበሌ ፖሊስ ዘረፋ እና ሌሎች የወንጀል ድርጊቶች እንዳይፈጸሙ ዝግጅት መደረጉን ፖሊስ አሳውቋል።

የፀጥታ አካላት ከወዲሁ ወደ ስፍራው ተልከዋል።

በዘንድሮ በዓል የጥበቃ ሥራው ከምሥራቅ ሸዋ ሞጆ ከተማ ፣ ጅግጅጋ እና ድሬዳዋ ጀምሮ እንደሆነ የተገለፀ ሲሆን በዓሉ በሚከበርበት ስፍራ ጊዜያዊ ፖሊስ ጣቢያዎች ፣ ዐቃቤ ሕግ እና ጊዜያዊ ፍርድ ቤት ተቋቁሟል። (ENA)

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia