#Amhara , #Kobo 📍
በአዲስ ጥቃት ምክንያት ቆቦ ላይ ተፈናቃዮች መስፈራቸውን ተሰምቷል።
ቆቦ ከተማ የሰፈሩት ከዋጃ ፣ ጥሙጋና አላማጣ አካባቢዎች የተፈናቀሉ ናቸው።
ከተፈናቃዮቹ መካከል ከበርካታ ወራት በኃላ ወደ መኖሪያ ቄያቸው ሀገር ሰላም ነው ብለው የተመለሱ ይገኙበታል።
አንድ ከዋጃ የተፈናቀሉ ግለሰብ ለቪኦኤ ሬድዮ ጣቢያ በሰጡት ቃል ፥ አካባቢው ነፃ ወጣ ከተባለ በኃላ የመንግስት ሚዲያዎችም ገብተው ዘግበው እንደነበር ነገር ግን በታህሳስ 29 የህወሓት ታጣቂዎች ተመልሰው እንደገቡ ከዛ በኃላ ህፃናት ፣ሴቶች፣ እናቶች ተፈናቅለው ወደ ቆቦ መምጣታቸውን ገልጿል። ህዝቡ ስቃይ ላይ ነው የሚዲያ ሽፋንም እያገኘ አይደለም ሲሉ ሁኔታውን አስረድተዋል።
ተፈናቃዮቹ በአሁን ሰዓት ከባድ የሚባል የምግብ እንዲሁም የአልባሳት እጥረት እንዳለባቸው ተነግሯል።
የዋጃ ጥሙጋ ቀበሌ ዋና አስተዳደሪ ያሬድ አድማሱ ለሬድዮ ጣቢያው በሰጡት ቃል ፤ የህወሓት ኃይሎች ከታህሳስ መጨረሻ ጀምሮ ወደ አካባቢው መግባታቸውን ተከትሎ እና እንደአዲስ በከፈተው ጥቃት ከ12 ሺህ በላይ ሰዎች መፈናቀላቸውን አሳውቀዋል።
ተፈናቃዮች በቆቦ ከተማ በሁለት ካምፕ ውስጥ ይገኛሉ።
በሌላ በኩል ፤ ህወሓት በአፋር ክልል በኩል በትግራይ አዋሣኝ ቦታዎች አብአላ፣ በርሃሌ ኤሬብቲና መጋሌ በከፈተው አዲስ ጥቃት ከ200 ሺህ በላይ ሰዎች መፈናቀላቸውን በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የኢትዮጵያ ሙሉ መልዕክተኛ አምባሳደር ታዬ አፅቀስላሴ አሳውቀዋል።
@tikvahethiopia

TIKVAH-ETHIOPIA
" የሰላም ንግግር አሁንም ይቻላል " - አምባሳደር ዘነበ ከበደ በጄኔቫ የኢትዮጵያ ቋሚ መልዕክተኛና ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር ዘነበ ከበደ በኢትዮጵያ መንግስት እና በህወሓት መካከል የሰላም ንግግር አሁንም ይቻላል ብለዋል። ነገር ግን ፤ ይህ የሚወሰነው የሰላም ንግግርን ውድቅ አድርጎ ወደ ጦርነት ባመራው ህወሓት /TPLF/ አቋም ነው ሲሉ ገልፀዋል። የኢትዮጵያ መንግስት ለሰላም ያለውን አቋም በዓለም…
#KOBO
የኢትዮጵያ መከላከያ " ቆቦ " ን ለቆ መውጣቱን መንግስት ገለፀ።
የኢፌዴሪ መንግስት ኮሚኒኬሽን ማምሻውን ባወጣው መግለጫ ፥ " አሻባሪው ህወሓት የሰው ኃይል ማዕበልን በመጠቀም የቆቦ ከተማን ከውጭ በብዙ አቅጣጫ እያጠቃ ነው " ብሏል።
በሌላ በኩል ደግሞ በከተማ ውስጥ ሠርጎ ገቦችን በማሥረግ የሕዝቡን ደኅንነት አደጋ ውስጥ በሚያስገባ መልኩ የከተማ ውስጥ ውጊያ ለማድረግ የሚያስችል ሁኔታ እየፈጠረ ይገኛል ብሏል።
በዚህም ፤ " የሕዝብን ከፍተኛ ፍጅት ለማስወገድ የመከላከያ ኃይል የቆቦ ከተማን በመልቀቅ እና ወደ ኋላ መጥቶ ለመከላከል የሚስችለውን ወታደራዊ ይዞታዎችን ለመያዝ ተገዷል " ሲል አሳውቋል።
የኢፌዴሪ መንግስት ኮሚኒኬሽን ፥ " አሸባሪው ኃይል የትግራይን ወጣት እየማገደ በሕዝብ ማዕበል ማጥቃቱን ካላቆመ መከላከያ ሕጋዊ ፣ ሞራላዊና ታሪካዊ ግዴታውን ለመወጣት የሚገደድ ይሆናል " ብሏል።
ምንም እንኳን ከተለያየ አቅጣጫ ሰላም እንዲሰፍን እና መሳሪያ ወርዶ ንግግር እንዲጀመር ጥሪዎች ቢቀርቡም በሰሜን ኢትዮጵያ ዳግም ያገረሸው ግጭት ከዕለት ወደ ዕለት እየተባባሰ መጥቷል።