TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
206 files
3.91K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#Irreecha2013

በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ሰዎች በተገኙበት ሲከበር የነበረው የኢሬቻ በዓል ዘንድሮ የኮቪድ -19 ወረርሽኝን ከግምት ባስገባ መልኩ እንደሚከበር አባገዳዎች ዛሬ በሰጡት መግለጫ አስታውቀዋል።

የሆረ ፊንፊኔ የኢሬቻ በዓል መስከረም 23 ቀን 2013 ዓ.ም የሚከበር መሆኑንና የሆረ አርሰዲ ኢሬቻ በዓል ደግሞ መስከረም 24 ቀን 2013 ዓ.ም እንደሚከበር አባገዳዎቹ ገልጸዋል፡፡

በበዓሉ ላይ የሚሳተፉ ሰዎች ቁጥር በሽታውን (ኮሮና ቫይረስ) ለመከላከል በሚያመች መልኩና የጤና ባለሙያዎች በሚሰጡት ምክር መሰረት የሚወሰን መሆኑ ተገልጿል፡፡

የገዳ ስርዓት ባለቤት የሆነው የኦሮሞ ህዝብ የአባ ገዳዎችን ጥሪና የጤና ባለሙያዎቸን ምክር ተከትሎ በዓሉን እንዲያከብር አባገዳዎቹ ጥሪ አቅርበዋል።

ምንጭ፦ የኦሮሚያ ኮሚኒኬሽን ቢሮ፣ ኢቲቪ
@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
#Irreecha2013

በዛሬው ዕለት የኦሮሚያ ጤና ቢሮ ኃላፊ ዶክተር መንግስቱ በቀለ በኢሬቻ በዓል ወቅት መደረግ ስለባቸው ጥንቃቄዎች መግለጫ ሰጥተዋል።

ዶ/ር መንግስቱ በመግለጫቸው ተከታዩን ብለዋል ፦

- የኮቪድ 19- ወረርሽኝ ከዚህ ቀደም ከነበረው ጊዜ በላይ እየተስፋፋ በመሆኑ የሆረ ፊንፊኔም ሆነ የሆረ አርሰዲ የኢሬቻ በዓል ላይ የሚሳተፉ ሰዎች በጥንቃቄ በዓሉን ሊያከብሩ ይገባል።

- በኢሬቻ በዓል የሚሳተፉ ሰዎች አካላዊ ርቀትን ሊጠብቁ እንዲሁም የአፍ እና አፍንጫ መሸፈኛ ጭምብል ሊያደርጉ ይገባቸዋል።

- በበዓሉ ወቅት ሊያጋጥሙ የሚችሉ የጤና ችግሮች ለመከላከል ቢሮው 7 ኮሚቴዎችን አዋቅሮ አስፈላጊውን ዝግጅት አጠናቋል።

- በበዓሉ ወቅት ከጤና ጋር ተያይዞ ለሚከሰት ችግር እርዳታ ማግኘት የፈለገ ሰው በነፃ 6955 ላይ ደውሎ መረጃ ማግኘት ይችላል። (etv)

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
#Irreecha2013

የኦሮሚያ ክልል ኮሚኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ አቶ ጌታቸው ባልቻ በሆራ ፊንፊኔ እና በሆራ አርሰዲ የኢሬቻ በዓል ላይ የሚገኙ ሰዎች መለየታቸውን ለሸገር ኤፍ ኤም 102.1 ተናግረዋል።

በእያንዳንዱ ቀን በሚከበረው በዓል ላይ የሚታደመው የሰው ቁጥር ከ5,000 እስከ 6,000 ይደርሳል ተብሏል።

አቶ ጌታቸው የኢሬቻ በዓል ለኮሮና ቫይረስ በማያጋልጥ መልኩ እንደሚከበርም ለሬድዮ ጣቢያው ገልፀዋል።

የፀጥታ ጥበቃውን አስተማማኝ ለማድረግ የክልሉ የፀጥታ አካላት ከአዲስ አበባ እና ከፌዴራል ፖሊስ ጋር በመሆን እየሰሩ ይገኛሉ፤ የክልሉ ፀጥታ ጥበቃ በሁሉም ዞኖች እና ከተሞች እየተካሄደ መሆኑን አቶ ጌታቸው አስታውቀዋል።

የኢሬቻ በዓል አከባበርን ወደ ፖለቲካ አጀንዳ ለመቀየር እና በኦሮሚያ ክልል አለመረጋጋት ለመፍጠር የሚያስቡ ወገኖች አሉ ያሉት አቶ ጌታቸው የፀጥታ አካላት በተቀናጀ መንገድ እየሰሩ ስለሆነ የሚያሰጋ ነገር አይኖርም ሲሉ ለሬድዮ ጣቢያው ገልፀዋል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#ATTENTION

የሆራ ፊንፊኔ ኢሬቻ በዓል በሚከበርበት ዙሪያ እና አካባቢው ዛሬ ከቀኑ 8 ሰዓት 30 ጀምሮ ፕሮግራሙ እስኪጠናቀቀ ድረስ በግራ እና በቀኝ ለረጅምም ሆነ ለአጭር ጊዜ ተሽከርካሪ አቁሞ መሄድ በፍጹም የተከለከለ መሆኑን አዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አስታውቋል።

#Irreecha2013
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#Irreecha2013

2ኛው ኢሬቻ ፎረም አባገዳዎች፣ የኦሮሚያ ክልል ፕሬዘዳንት አቶ ሽመልስ አብዲሳ፣ የሶማሌ ክልል ፕሬዘዳንት አቶ ሙስጠፌ ሙሀመድ ፣ የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ ፣ የባህልና ቱሪዝም ሚኒስትር ዶክተር ሂሩት ካሳውና ሌሎችም የፌዴራል እና የክልል ከፍተኛ ባለስልጣናት በተገኙበት በአዲስ አበባ እየተካሄደ ይገኛል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
Baga ittiin isin gahe, nu gahe !
እንኳን አደረሳችሁ፤ አደረሰን !

Ayyaana Gaarii !
መልካም በዓል !
#Irreecha2013

(Tikvah Itoophiyaa)

[3 MB]
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#Irreecha2013

የሆረ ፊንፊኔ የኢሬቻ በዓል በአዲስ አበባ በውስን ተሳታፊዎች ብቻ እየተከበረ ይገኛል። በበአሉ አባገዳዎች ፣ ሀደ ሲንቄዎች፣ የኃይማኖት አባቶች እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።

PHOTO : EBC
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#Irreecha2013

ዛሬ በውስን ተሳታፊዎች የተከበረው የ "ሆራ ፊንፊኔ" የኢሬቻ በዓል አንዳች የጸጥታ ችግር ሳያጋጥም በሰላም መጠናቀቁን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አስታውቋል።

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
#Irreecha2013

የቢሾፍቱ ሆራ አርሰዴ ኢሬቻ በዓል በሠላም ተከበረ።

የኦሮሞ ገዳ ሥርዓት አካል የሆነው የኢሬቻ በዓል ከንጋቱ ጀምሮ በሆራ አርሰዴ በተከናወነ ስነስርዓት ተከብሯል።

የበዓሉ ስነ ስርዓት በገዳ ሥርዓት መሰረት በአባገዳዎች ምርቃት ነው የተጀመረው፡፡

በበዓሉ ላይ ለመታደም ከተለያዩ አካባቢዎች ወደ ሆራ አርሰዴ በማቅናት በባህሉ መሰረት ለፈጣሪያቸው ምስጋናቸውን አቅርበዋል፡፡

በሌላ በኩል የሆረ አርሰዲ የእሬቻ በዓል አባገዳዎች ባስቀመጡት አቅጣጫ መከበሩን አባገዳ ጎበና ሆላ ገልጸዋል፡፡

አባገዳ ጎበና ሆላ መጪው ዓመት የኮቪድ -19 ወርርሽኝ አልፎ እንደተለመደው ህዝቡ በዓሉን በጋራ እንዲያከብረው ያላቸውን ተስፋ መግለፃቸውን ኢቲቪ ዘግቧል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia