TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
62.7K photos
1.6K videos
216 files
4.36K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

መረጃ እና መልዕክት ፦ 0919743630

ማርኬቲንግ ፦ 0979222111 ወይም
0979333111

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#እንድታውቁት

ሱስ ምንድን ነው ?

- ቀጣይነት ያለው፣ ሊመላለስ የሚችል፣ ተጓዳኝ ችግሮች እንዳሉት እየታወቀ እንኳን ከፍትኛ የሆነ ንጥረ-ነገር የመጠቀም ፍላጎት ነው፡፡

- እንደ የአዕምሮ እክል የሚቆጠር ሲሆን፣ አእምሮን የተለመደ ስራውን እንዳይሰራ በእጅጉ ይገድበዋል ፡፡

- መከላከል እንዲሁም መታከም የሚችል ነው፡፡

- ብዙ ጊዜ ከደካማነት የተነሳ ሰዎች
እንደሚያደርጉት እየታሰበ ቢቆይም፤ በአሁን ጊዜ በዚህ በሽታ የተጠቁ ሰዎች ለመጠቀም ዋነኛ ምክንያታቸው ከአካላዊ እና ከስሜታዊ ህመሞቻቸው ለመሸሽ እንደሆነ እየታመነ ነው፡፡

- ሱስ ከንጥረ-ነገር ጋር የተያያዘ (ሲጋራ፣አልኮል) ወይም ያልተያያዘ (እንደ ቁማር) ሊሆን ይችላል፡፡

አጋላጭ ሁኔታዎች፦
* ከቤተሰብ የሱስ ችግር ከነበረ
* የአቻ ግፊት
* ስነ-ልቦናዊ ችግሮች የመሳሰሉት ናቸው።

- ሱስ እጅግ አደገኛና በአንድም በሌላ መንገድ የብዙ ሰዎችን ህይወት የሚቀጥፍ ነው፡፡

- ከሱስ መላቀቅ ይቻላል፡፡ አብዛኛውን ጊዜ ሰዎች በራሳቸው ጊዜ ሲያቆሙ በህክምና እርዳታም መቆም ይችላል፡፡

- ይህ ችግር ተመላላሽ ስለሆነ ለማቆም ብዙ ሙከራዎች ያስፈልጉታል፡፡በተለይም የሲጋራ ሱስ ለማቆም ረጅም ጊዜ ሊወስድ ይችላል፡፡

- በአሁን ጊዜ ግን በሰለጠነው ዓለም የተለያዩ ሳይንሳዊ ግኝቶች ይህን ችግር የበለጠ ለመረዳት እያገለገሉ ይገኛሉ፡፡
(ምሳ. Brain Imaging Technologies)-አዕምሮአችን ለተለያዩ ሁኔታዎች (ለንጥረ-ነገር ጋር የተያያዙ ወይም ያልተያያዙ ሱሶች) ተመሳሳይ ምላሽ እንደሚሰጥ አሳይተዋል፡፡

መፍትሄ ፦
ለማቆም ተነሳሽነትን ማዳበር
አካባቢያችንን፣ ውሎአችንን ማስተካከል
የስነ-ልቦና ምክር
በሽታ መሆኑን በመገንዘብ ወደ ህክምና አልያም ማገገሚያ ቦታዎች መሄድ ያስፈልጋል።

#HarvardHealthPublishing

@tikvahethiopia 
214🙏40😢11🕊7😱6😭4🥰2😡2